cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✟ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የንጽጽር ቻናል

ይህ የተከፈተው ገጽ በአንድ ሀጢያተኛ ባርያ ሲሆን ባለችን አጭር ጊዜ እንኳን ሰው ወደ እግዚአብሔር በንስሀ እንዲመለስ ለማድረግ ነው።በዚህ ገጽ የሚቀርቡት➤ ➤የኢ/አ/ብርሀን መልእክቶች ። ➤>>>>>>>>>ቤተሰብ ምስክርነት ። ➤>>>>>>>>>ትምህርቶች ። ➤አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች መልእክቶች ናቸው።

Show more
Advertising posts
433Subscribers
-124 hours
+47 days
+4730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

◦●◦●◦ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፨ ◦●◦●◦ ~❴ ሚያዝያ ፲፰/18 ❵~ በዚህች ቀን፦ ● የቅዱስ ሱስንዮስ አገልጋይ #ቅዱስ_አውሳብዮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ ● የአባ ብሶይ ወንድም #አባ_ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ◦◦●●◦◦
Show all...
.    •❀• [ ስንክሳር ዘሚያዝያ ፲፰ ] •❀•                              •• ቅዱስ አውሳብዮስ ••                         ๏-❀-๏ ሚያዝያ ዐሥራ ስምንት በዚህች ቀን የቅዱስ ሱስንዮስ አገልጋይ ቅዱስ አውሳብዮስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም ቅዱስ ሱስንዮስን በሚያሠቃየው ጊዜ ንጉሥ ሆይ አውሳብዮስ የሚባል አገልጋይ አለው፣ እርሱም በፍጹም ልቡ እንደ ጌታው ክርስቶስን ያመልከዋል፡፡ የአንተን አማልክት አያመልክም አሉት፡፡ አምጡት አለ፡፡ ወደ እርሱ በቀረበ ጊዜ ስለ ሃይማኖቱ ጠየቀው፡፡ እርሱም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ፡፡ ንጉሡም ብዙ አባበለው አማልክቶቹን ማምለክ በመተው ገሰጸው፡፡ ቅዱሱም የዕውነተኛ አምላክ የአግዚአብሔርን አምልኮ በመተው ንጉሡን መልሶ ገሰጸው፡፡ ስለዚህም ንጉሡ ቁጣን ጨመረ ሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ፡፡ ይህም ቅዱስ ከጌታ ከሱስንዮስ ቀድሞ የሰማዕትነትን አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ፡፡ ◦🌿◦🌿◦🌿◦
Show all...
የሰሞነ ሕማማት ጸሎትና ስግደት የያዘ መጽሐፍ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚     🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪       ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧       ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
Show all...
#ሰላም_ዕብል_ሐዋርያ_ፍንወ፥ አኅወ ወንጌላዊ #ዮሐንስ እንተ ይሄሉ ሕያወ፥ አህጒራተ ይስብክ ጊዜ አንሶሰወ፥ ድምፀ አራዊት ወዘአዕዋፍ ንቃወ፥ በመንፈስ #ቅዱስ_ያዕቆብ ለበወ። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ የሚያዝያ 17)
Show all...
ኬንያና ሶማሊያ የጎርፍ አደጋ ማስጠንቀቂያ አወጡ‼️ በምሥራቅ አፍሪቃ አካባቢ ከፍተኛ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ የጎርፍ አደጋ ማስጠንቀቂያ ለማውጣት ተገደዋል። የኬንያው ቀይ መስቀል ማኅበር እንደሚለው ከበድ ባለው ዝናብ ምክያት ባለፈው ሳምንት ስድስት ሰዎች ሲሞቱ፣ ከ11ሺሕ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ተፈናቅለዋል።ሶማሊያም በወንዞች ዳርቻ የሚኖሩ ዜጎቿ ከፍ ወዳለ ቦታ እንዲዛወሩ ጠይቃለች። ትናንት በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከ30 በላይ ሰዎች ሞተዋል። የኬኒያ የመረጃ ምንጮች በጎርፉ ምክንያት 40 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል ያሉ ቢሆንም ተመድ ግን 130ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል ብሏል።
Show all...
ኬንያም ይኸው በጎርፍ ተጠቅልቃለች። ምክንያቱም ዘመኑ የፍርድ እና የጠረጋ ነውና።
Show all...
ዱባይ  በጎርፍ ከተጥለቀለች በኃላ ያላት ገጽታ ‼️ በዚህ ቀን እንዲህ ይሆናል የሚለውን ለእግዚአብሔር  እንተወውና በሰሞኑ የወረደው መቅሰፍት ምን ይመስላል? የሚለውን እና የእግዚአብሔር ፍርድ ሲመጣ በሰከንድ ሁሉን እንዳልነበር እንደሚያደርገው ጥቂት ማሳያ መሆኑን እንረዳ። ስለ ሁሉም ነገር ግን እግዚአብሔር ይመስገን  ።
Show all...
ቦይንግ ኩባንያ በሦስት ወራት ውስጥ የ4 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ደረሰበት ድርጅቱ ከ737 ማክስ አውሮፕላን ጋር በተያያዘ የደህንነት ችግር አጋጥሞታል
Show all...
📌 እኛ ከእንግዲህ ድርሻችንን ተወጥተናል። እግዚአብሔር ያዘዘንን ገልጸናል። አድርሰናል። ግዳጃችንን ተወጥተናል። እንግዲህ ወገኖቼ እዳ የለብንም። የፍቅር እዳ የለብንም። የታዘዝንበትም እዳ የለብንም። ሁሉንም ነገር በጊዜውና በሰአቱ በዚህ ክፉ ሰአት ውስጥ ሁሉ ሊደርስ ወደ ሚገባው ሁሉ አድርሰናል ማለት ነው። ከእንግዲህ በየበዓታችን ሆነን መጪውን የእግዚአብሔርን እርምጃ ማየት ብቻነው። ኖህ በመርከቡ አይደል! የተካተተው? አዎ እኛም በእምነት መርከባችን ተካተን  ውጤቱን መከታተል ብቻ ነው። መቼም ለምታስተውሉ አለም ወዴት እየሄደች እንደሆነ ግልጽ እያየን ስለሆነ ምንም ድብቅም ስለሌለ። ከእንግዲህ ለአዳም ዘር አስተዋሽ አያስፈልገውም ።ፍርዱ ሁሉ ከደጁ ነው። የቁጣው እሳት ሲያጠልመው ሲለበልበው ሲያቀልጠው ያኔ የእግዚአብሔር ፍርድ ነውና ይገበዋል።በ ፍርዱም ይካተታል። እኛ ደግሞ እግዚአብሔርንን እያመሰገንን በየበዓታችን መቀመጥ ነው። ⚡️ለአለም መንግሥታት እና ሕዝብ ይደርሱ ዘንድ በቀን 7/5/2016 ዓ,ም ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንሥት ከተጻፉት ደብዳቤች መካከል በንባብ  ከተላለፈው ክፍል 1 መግቢያ እና ማብራሪያ ላይ የተወሰደ።
Show all...
.    •❀• [ ስንክሳር ዘሚያዝያ ፲፯ ] •❀•                     •• ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ ••                         ๏-❀-๏     ሚያዝያ ዐሥራ ሰባት በዚህች ቀን የዘብዴዎስ ልጅ የወንጌላዊ ዮሐንስ ወንድም ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም በእስያ ውስጥ ከአስተማረ በኋላ ዕርቅ በተገኘባት በእውነተኛ አምላክ በጌታችን ወንጌል ሊያስተምራቸው ወደ ተበተኑ ወደ ዐሥራ ሁለቱ ነገድ ወጣ። እነርሱም አንድ አምላክን የሚአመልኩ አልነበሩም እየራሳቸው የመረጡትን የሚአስቷቸው ጣዖታትን ያመልኩ ነበረ እንጂ። ከቄሣር ሥልጣን በታች የተሾመ ኄሮድስም ሹመቱ በሚዳብር መንግሥቱ በሚያጸና ገንዘብ ብዙ ግብር እንዲገብሩ እጅ መንሻም እንዲአስገቡ አዘዘ። ያዕቆብ ግን ወደእርሳቸው በደረሰ ጊዜ በአገራቸው ቋንቋ ሰበከላቸው። የፍጥረትን ሁሉ ቋንቋ ማወቅን እግዚአብሔር ሰጥቶት ነበርና የሚያውቀው የሰው ቋንቋ ብቻ አልነበረም። የእንስሳና የአራዊት የሰማይ ወፎችንም ቋንቋ ነበረ እንጂ። በውስጣቸው በሰበከም ጊዜ የከፋ ሥራቸውን ትተው በሕያው እግዚአብሔር በአንድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት በሆነ መንፈስ ቅዱስ ነፍሶቻቸው በእጁ ውስጥ በተያዙ በአንድ አምላክ እንዲያምኑ አዘዛቸው። እርሱም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ የሚመጣ ነው። ዳግመኛም በማይጠፋና በማይበላሽ በሰማያት ድልብ ይሆናቸው ዘንድ ከገንዘባቸው ለችግረኞችና ለድኆች እንዲመጸውቱ አዘዛቸው። ትምህርቱንም በሰሙ ጊዜ ከክፋ ሥራቸው ተመልሰው በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብም ትምህርቱን ፈጥነው ስለተቀበሉት እጅግ ወደዳቸው። በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው በየአገራቸው ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው። ዳግመኛም ከእንስሶቻቸው ከሚዘሩአቸው እህሎችና ወይን አትክልቶች ፍሬዎች ለካህናትና ለድኆች ምግብ ሊሆን ለቤተ ክርሰቲያን የመጀመርያውን መባ እንዲሰጡ አዘዛቸው። ሕዝቡም በአንድ ቃል ያዘዝከንን ሁሉ እኛ እናደርጋለን አሉት። ከዚህ በኋላ ከእንስሳት መጀመሪያ የተወለደውን ከእህሉም ቀዳምያቱንና ዓሥራትን ለቤተ ክርስቲያን አመጡ። ኄሮድስም ቅዱስ ያዕቆብ ለቤተ ክርስቲያን መባ ይሰጡ ዘንድ እንዲሚያዝ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ጭፍራ ልኮ ወደርሱ አስመጣውና "ሕዝቡ ገንዘባቸውን ሁሉ ለድኆች ምጽዋትና ለቤተ ክርስቲያን መባ እንዲሰጡ የምታዝ አንተ ነህን" አለው። "አዎን እኔ ነኝ" አለው። ያን ጊዜ ኄሮድስ ተቆጥቶ ራሱ በሰይፍ አንገቱን መትቶ ቆረጠው። በኢየሩሳሌምም ሁከትና ሽብር ሆነ። ደግሞ ከፋሲካ በዓል በኋላ ሊገድለው አስቦ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ ወስዶ አሠረው። የእግዚአብሔር መልአክም ኄሮድስን ቀሠፈው። ተልቶ ተበላሽቶ ሞተ። ልዑል አምላክን አላከበረውምና። የቅዱስ ያዕቆብን ሥጋ ግን ምዕመናን ወሰዱት፤ ገንዘው በቤተ መቅደስ ውስጥ ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የሐዋርያው የቅዱስ ያዕቆብ በረከት ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ◦🌿◦🌿◦🌿◦
Show all...
🙏 1