cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

#///////# በዚህ ቻናል ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህሮቶችና ታሪካዊ ዳህራዎች ይቀርቡበታል / ይቀላቀሉ https://t.me/EOC_21 https://t.me/EOC_21 https://t.me/EOC_21 ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ተቀብሎ መልስ ይሰጣል። ሁሉም የእምነት ተከታዮች ጥያቄ ማቅረብ እና መወያየት ይችላሉ።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
498Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን # ሼር አድርጉት 33ቱ የእመቤታችን በዓላት ሠላሳ ሦስቱ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት እነዚህ ናቸው፡- + ነሐሴ 7- እመቤታችን የተፀነሰችበት ዕለት፡፡ + ነሐሴ 16- ሥጋዋ የፈለሰበት/በልጇ ኃይል ከሞት ተለይታ የተነሣችበትና ወደ ሰማይ ያረገችበት ዕለት፡፡ + ከነሐሴ 17 እስከ ነሐሴ 21 ድረስ ለ5 ቀናት ትንሣኤዋ እንደልጇ ትንሣኤ ይከበራል፡፡ የጌታ ትንሣኤ አንድ እሑድ ቀን መኾኗ የታወቀ ቢሆንም የትንሳኤው መታሰቢያ እስከ 50 ቀናት ማክበራችንን እናስታውስ የእመቤታችንም እንደዚሁ ነው፡፡ + መስከረም 10- ሥጋን የለበሰች የምትመስለውና ብዙ ተአምራት ታደርግ የነበረችው የእመቤታችን ሥዕል ፄዴንያ ወደተባለ አገር ገብታ የተቀመጠችበትን ዕለት፡፡ + መስከረም 21 ትከብራለች፡፡ አርዮስን ለማውገዝ በ326 ዓ.ም በኒቅያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን ከሚያዝያ እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ በመሆኑ የመስከረም ማርያም (ብዙኃን ማርያም) ተብሎ በዓሏ ይከበራል፡፡ እንዲሁም ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የክርስቶስን ቅዱስ መስቀል ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም በመስከረም 21 ቀን ስላስገቡ ምእመናን በዓሉን በግሸን ማርያም ያከብሩታል፡፡ + ጥቅምት 21- ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡ + ኅዳር 6- ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል ሀገር ገብታ ያረፈችበት ዕለት፡፡ + ኅዳር 21- ጽላተ ሙሴ አክሱም ቤተ መቅደስ ተሠርቶላት በክብር ያረፈችበት ዕለት፡፡ ዳግመኛም ካህኑ ዘካርያስ የእመቤታችን ምሳሌ የሆነውን የመቅረዝ ፋና ሲበራ ያየበት ዕለት ነው፡፡ + ታኅሣሥ 3-በሦስት ዓመቷ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት፡፡ + ታኅሣሥ 21 ትከብራለች፡፡ የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡ + ታኅሣሥ 22- ብሥራተ ገብርኤል (ቅዱስ ደቅስዮስ እመቤታችን ጌታን የፀነሰችበትን የመጋቢት 29 ቀንን በዓል በዚህ ዕለት አከበረ)፡፡ + ታኅሣሥ 28- በዓለ ገና ነው።ይሀውም የልደት ዋዜማ(ገሃድ) ይባላል።ፍትሐነገሥት አንቀጽ15። + ታኅሣሥ 29- ጌታችንን በድንግልና የወለደችበት የመታሰቢያ በዓል፡፡ + ጥር 21- እመቤታችን በ64 ዓመቷ ያረፈችበት ዕለት፡፡ + የካቲት 16- ከልጇ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበለችበት ዕለት፡፡ + የካቲት 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡ + መጋቢት 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡ + መጋቢት 29 ትከብራለች/ጌታችንን የፀነሰበት ጥንተ በዓል፡፡ + ሚያዝያ 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡ + ግንቦት 1- እመቤታችን የተወለደችበት ዕለት፡፡ + ግንቦት 21- በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር ያደረገችበት፡፡ + ግንቦት 22- በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡ + ግንቦት 23- በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡ +ግንቦት 24- እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ አገር የገባችበት ዕለት፡፡ + ግንቦት 25- ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት፡፡ + ሰኔ 8- ተወዳጅ ልጇ ከደረቅ ዓለት ላይ ውኃ ያፈለቀበት፡፡ + ሰኔ 21- ጌታችን ሰኔ 20 ተገልጦ ሐዋርያቱን ተሰብስቦ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ከሠራላት በኋላ በቀጣዩ ቀን ቅዳሴ ቤቷን ያከበረበት ዕለት ነው፡፡ ++ ሐምሌ 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!!! Join https://t.me/EOC_21 https://t.me/EOC_21 https://t.me/EOC_21
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

#///////# በዚህ ቻናል ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህሮቶችና ታሪካዊ ዳህራዎች ይቀርቡበታል / ይቀላቀሉ

https://t.me/EOC_21

https://t.me/EOC_21

https://t.me/EOC_21

ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ተቀብሎ መልስ ይሰጣል። ሁሉም የእምነት ተከታዮች ጥያቄ ማቅረብ እና መወያየት ይችላሉ።

🍀 ህንጸተ ቤተክርስቲያን 21 🍀 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗየተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ። ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል።  ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተመቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር። ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።  እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።  ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
Show all...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝ ኦርቶዶክሳውያን እንኳን ለጾመ ሐዋርያት አደረሳችሁ 🌹🌹🌹🌹 ሰኔ 13 ቀን ጾመ ሐዋርያት ይጀምራል ​​ፆመ ሐዋርያት፦ አንዳንዶች የሰኔ ፆም የቄስ ፆም ነው በሚል ከመፆም ወደኋላ ሲሉ ይታያሉ ነገር ግን ቅድስት ቤተክርስቲያን በአዋጅ ከምትፆማቸው ሰባት አፅዋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢፆመው እጅግ በርካታ በረከቶችን ያገኝበታል ከነዚህም ጥቂቶችን እነሆ 1.በረከተ ሐዋርያት ይገኝበታል ይህን ፆም መጀመርያ ፆመው እንድንፆመው ሰርዐት የሰሩልን ሐዋርያት ናቸዉ ስለዚህም ፆሙ መታሰቢያነቱ የሐዋርያት ነው የጻድቅ መታሰቢያ ደግሞ ለበረከት ነው ። ምሳ.10፥7 እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም የሐዋርያቱን በረከት እናገኛለን ሐዋ.13፥1-3 ሐዋ.14፥23 2. በስራችንና በአገልግሎታችን በረከት እናገኛለን ሐዋርያት ይህን ፆም የፆሙት አገልግሎታቸው እንዲከናወንላቸው እንዲባረክላቸው ነው ነብዩ ነህምያም እየሩሳሌምን የመስራት ተግባሩ እንዲባረክለት በፆመው ፆም ስራው ሁሉ ተባርኮለታል። ነህም.1፥4። እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም በዕለት ተዕለት ተግባራችን በረከት እናገኛለን። 3. ዝናብ ምህረትን ጠለ በረከትን እናገኛለን የሰኔ ፆም በአገራችን የክረምቱ መግቢያ ላይ የሚፆም ፆም ነው ይህም መጪው የክረምቱ ወራት የተስተካከለ የምህረት ዝናም እንዲኖረው ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል ዘመን ዝናብ ጠፍቶ ዛፎቹ ሳይቀር በደረቁ ጊዜ በፆም በፀሎት ወደ እግዚአብሔር በተማፀኑ ሰዓት ዝናመ በረከትን አግኝተዋል። ኢዩ.1፥13-14 4. በረከተ ምርትን እናገኛለን የሰኔ ፆም በሃገራችን ገበሬው ዘር መዝራት በሚጀምርበት ጊዜ የሚፆም ፆም ነው ሰለዚህም በዚህ ሰዓት የሚፆመው ፆም ዘርን እንዲባረክ በረከት እንዲበዛ ያደርጋል ይህም አገር ወገን ከረሃብ ከችግር ነፃ እንዲወጣ ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል እንደተገለጸው በፆም የዕህል የመጠጥ በረከት ይገኛል ። ኢዩ.2፥12-14 5. የነፋስ በረከትን እናገኛለን ፆም በመንፈስ የደከመች የዛለች ነፍስን ያበረታል የነፍስን ቁስል ይፈውሳል ስጋዊ ኃይልን ያደክማል የሥጋን ፈቃድ ለነፍስ ያስገዛል መዝ.108፥24 ፤ ገላ.5፥24 የዓለምን ሃሳብ ያስወግዳል ከእግዚአብሔር ያስታርቃል ማቴ. 17፥21 ሚስጥር ይገልጣል ዘስ.34፥27-28 ፤ ዳን. 10፥1-3 "በአምላካችን ፊት እራሳችንን እናዋርድ ዘንድ ከርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ ...... ፆምን አውጃለሁ " መጽሐፈ ዕዝራ.8፥21 ከመዋዕለ ፆሙ ረድኤት በረከት ያሳትፈን ! ፆሙን የኃጢአት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን አሜንንንን !!! ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ይደርስ ዘንድ # ሼር 💚
Show all...
ድርሳን ዘቅዱስ ሚካኤል ዘውርሃ ሰኔ🍃 ለአባታችን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን💠⛪️🕯⛪️ በዕድሜ በፀጋ ይጠብቅልን🌺🌾 እናዳምጥ በረከት ነው መልካም ቆይታ💠👂🕊👆
Show all...
#ኦ_ሚካኤል ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል/2/ ስንጠራህ ድረስልን ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል ዘንዶው ጠላታችን ከፊታችን ቆሟል ከባህር ሊጥለን አድፍጦ ያደባል የመላዕክት አለቃ እርዳን በፀሎትህ ጥበቃህ አይራቀን በቀን በሌሊት/2/ ክርስትና ኑሮ እጅጉን ከብዶናል የጌታን ውለታ ፍቅሩን ዘንግተናል አፅናኙ መልዐክ ከፊታችን ቅደም በመንገድህ ምራን እንድንሆን ሰላም/2/ የጌታ ባለሟል የህዝብ እረኛ ባህሩን አሻግረን ቅረበን ወደ እኛ ከጌታህ አማልደን መልዐከ ራማ የልጆችህን ቃል ድምፃችንን ስማ በሚያስፈራው ዘመን ሰላም በሌለበት ባስጨናቂው ጊዜ ፍቅር በጠፋበት የፍቅርን ወንጌል ቃሉንም ስበከን ሚካኤል ተራዳን ድረስም አፅናናን ዘ/ዲ ሱራፌል ስዩም 💚
Show all...
#ይበራል በክንፋ ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው (2) #አዝ ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ ዛሬ ላለሁበት ብሩቱ ጉልበት ሆነኝ ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ #አዝ በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ አለሁ እስከዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ የህይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከርሱ ጋራ ተፅፏል በልቤ የሚካኤል ስራ #አዝ በዙሪያዬ ተክሎ የእሳት ምሰሶውን ፅድቅ እየመገበ ኣሳደገኝ ልጁን የአምላኬን ምስጋና ዘውትር እያስጠናኝ እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ #አዝ ፊት ለፊት ተተክሎ ከታናሿ መንደር ይስማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር ይወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ ታላቁት በረከት በውስጤ አፈሰሰ #አዝ ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ መራኝ ወደ ህይወት መዳኔን ወደደ የሞአብን ቋንቋ ከአፌ ላይ አጥፍቶ በፀጋው ቃል ቃኘኝ በበረከት ሞልቶ
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!