cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Bemnet Library

ሁሉም ዓይነት መፅሀፍ ለእርስዎ ቀርቧል #ማጋራት መተሳሰብ ነው ! ከ 2014 ጀምሮ! እንደ እርስዎ ላሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ቁጥር 1 ምርጫዎች ነበርን 💬 @Bemni_Alex

Show more
Advertising posts
46 196Subscribers
+24024 hours
+5277 days
+1 43230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🗣 በአጭር ጊዜ ውስጥ እንግሊዝኛ ቋንቋ አቀላጥፎ ለመናገር የሚረዳቹ ምርጥ ሀገርኛ የቴሌግራም ቻናል። ከ 135ሺ በላይ ተከታይ ያለው። 🗣, The best national Telegram channel where you can learn to speak English fluently in a short period of time. ቻነላችንን ለመቀላቀል 👇 @English_Ethiopian @English_Ethiopian
Show all...
👍 1
🌐 J O I N 🌐
45,000 followers on #Telegram አመሰግናለሁ! Galatoomaa! የቐንየለይ! Paid Promotion @Bemni_Alex
Show all...
👍 59 8🙏 4👏 3
ፀሃይ vs አምፖል ፀሃይ እሷ ወደ ፈለገችበት የሰውን ጥላ ታንቀሳቅሳለች ሰውየው ቆመም ሄደም። አምፖል ግን ሰውየው የራሱን ጥላ እንደፈለገው ተንቀሳቅሶ መቀየር ይችላል። አንተም እንደ ፀሃይ ሁን በዙሪያህ ያሉትን ሰዎች አንተ በምትፈልገው አይነት ባህሪ ቅረፃቸው። ✍️:- alfewz @Bemnet_Library
Show all...
👍 48🔥 8 2🙏 1
ስድስት ኪሎ ላይብረሪው አካባቢ ካለው መናፈሻ መሳይ ቦታ ላይ ቁጭ ብዬ ወጪ ወራጁን ቃኛለው።  ድንገት ገሊላ መፅሀፍ ይዛ ወደኔ አቅጣጫ እየፈነደቀች ከሩጫ ትንሽ ዝቅ ባለ ዱቡዱብ በፈገግታ ታጅባ መጣች።  "ካሊድዬ የፈለከውን ጥያቄ ጠይቀኝ ስሩ የተባልነውን ሁሉ ጥያቄ ከማኪ ጋር ሆነን ዶርም ውስጥ ሰርተናል አለችኝ"  በመሮጥዋ በተፈጠረው ያተነፋፈስ ልዩነት ለመረጋጋት እየሞከረች። እሺ ብዬ መፅሀፉን ተቀብዬ የተለያዩ ገፆች ላይ ያሉ ወደ አስር የሚጠጉ ጥያቄዎች ጠየኳት  ሁለቴ ማሰብ ሳይጠበቅባት ነው ከአፌ መንትፋ መልሶቹን የምትነግረኝ። "እውነትም አልተቻልሽም!" አልኳት ደስታዋ ተጋብቶብኝ አብርያት ፈገግ እያልኩ ። ግን ከዚህ መፅሀፍ ውጪ ጥያቄ አለኝ አልኳት መልስ በሚፈልግ ድምፀት "እእ አስተማሪው ከተናገረው ነው የምትጠይቀኝ ? " "አይደለም ልቤ ከተናገረችው ነው" በስሱ ፈገግ ብላ " ይሁና እስኪ ልጠየቀዋ " አለች ድምፅዋን ቀንሳ የልቤን ገፆች በለሆሳስ ገልጬ አንድ ጥያቄ ሆና ሺህ መልስ የምታስከትል ጥያቄ አሻገርኩ ። " የወሰድሽውን ልቤን  መልሺልኝ " የማፍቀር ጉም በሸፈነው ድምፀት ። የዚህን መፅሀፍ ጥያቄዎች ለመመለስ ኬኔዲ ላይብረሪ ሳነብ እንደነበርኩ አንተንም በህይወት ላይብሪሪ ካንተነትህ ባሻገር ልወቅህ መፈለግ ውስጥ ነው ያለው ማግኘት ፍቅር ከማየት ባሻገር ማጤን ይጠይቃል ገረፍታ አንብቢህ ልብህን ልመልስልህ ማለት የሞኝ ጥናት ነው ለመጠየቅ ብሎ ማጥናት እና ለማወቅ ብሎ ማጥናት መንገዱም ማብቂያውም ይለያያል እና..... ብላ እጄን ጎትታ ከተቀመጥኩበት አስነሳቺኝና ወደ ካፌው አቅጣጫ ጉዞ ጀመርን ...... ✍️ ካሊድ አቅሉ 📚 @Bemnet_Library
Show all...
👍 42 21
" ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች ”የለውጥ ኩርባ” አለችው። አስተሳሰቡ ወይ ስሜቱ አሊያም ድርጊቱ የሚቀየርባት ። ወደ ዐዲስ ምዕራፍ የሚታጠፍበት ወይም ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርበት ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት። ለውጥ ወደ ተሻለ ማደግ ብቻ አይደለምና ኩርባውን ሲታጠፍ ውድቀትም ሊሆን ይችላል። ያች የለውጥ ኩርባ አንድ የሆነች ኢምንት ክስተት ልትሆን ትችላለች ወይም ዐረፍተ ነገር ወይም አንዲት ቃል ምናልባት አንዲት መሳም ወይም የአንድት ደቂቃ መታቀፍ ወይም.... " - ከ'ጠበኛ እውነቶች ' መጽሐፍ ገፅ 116 ደራሲ :- ሜሪ ፈለቀ 📚 @Bemnet_Library
Show all...
👍 12🔥 1
ሞካሪና አስሞካሪ (ሜሪ ፈለቀ) "ከንፈር መሞከር ፈልጋለሁ።" አልኩት "እስከዛሬ ተስመሽ አታውቂም።?" "እስከዛሬ ፈልጌ አላውቅም።" ከንፈሩን አቀበለኝ። ወራት ነጎዱ…… "ድንግል መሆን አልፈልግም።" አልኩት "ገናኮ 18 ዓመትሽ ነው ማሬ። ለምን ትንሽ አንቆይም? " "አሁን ነው የምፈልገው።"…… አክሱሙን አቀበለኝ። ወራት ነጎዱ……… "ጫት ለጥናት ጥሩ ነው ሲሉ ጊቢ ሰማሁ። መሞከር ፈልጋለሁ።" "አይ አይ አይ…… ጥሩ አይደለም ማሬ ስሞትልሽ አትሞክሪ።" አለኝ እያንገፈገፈው "ልንገርህ ብዬ እንጂ መሞከሬ አይቀርም። እነቤቲ ዛሬ እንቅማለን ብለዋል…… " ሳልጨርስ ቀድሞ "እሺ በቃ ፍቅሬ እሺ…… መሞከር ከፈለግሽ  እኔም አብሬሽ እሞክራለሁ። ከኔጋ ቃሚ…… " ጫቱንም ፍራሹንም ሰጠኝ።…… መቃም በፈለግኩ ቁጥር ከስራ እየቀረ አብሮኝ ቃመ። ወራት ነጎዱ……… "ልመረቅ ስለሆነ ስክር ማለት እፈልጋለሁ ክለብ ውሰደኝ" አልኩት…… "እሺ እንደፈለግሽ ሁኚ እጠብቅሻለሁ።" አለኝ…… መጠጡን ቀዳልኝ… እንደፈለግኩ ሆንኩ…… ሰዓታት ነጎዱ…… "ማጨስ እፈልጋለሁ።" "እማ ስካሩ አይበቃም? ፕሊስ ጭሱ ይቅር? "ለአፉ አለኝ እንጂ የፈለግኩትን ሳልሞክር ማቆሚያ እንደሌለኝ ያውቃል። "እሺ ገዝቼልሽ ልምጣ? " "አልፈልግም የተጨሰ ግማሽ የደረሰ ሲጋራ ነው ማጨስ የምፈልገው።… እንደውም ያን ሰውዬ ስጠኝ እለዋለሁ።" "እሺ እሺ በቃ የተጨሰ አይደል ማጨስ የምትፈልጊው? በቃ እኔ አጭሼ ሰጥሻለሁ።…… ከሌላ ሰው ከንፈር ተውሰሽ አታጨሺም! " አጭሶ ሰጠኝ። አጨስኩ።… እስክመረቅ በጨፈርኩ ቁጥር የተጨሰ ሲጋራ አቀበለኝ። ዓመታት ነጎዱ…… ብዙ ዓመታት…… እንደተመረቅኩ ከሃገር ወጣሁ።…… ተራራቅን…… ከጊዜ በኋላ መገናኘት አቆምን።… አገባሁ…… ወለድኩ…… ለበዓል ወደሃገር ቤት ተመልሼ ሳለሁ መንገድ ላይ አየሁት።…… ደነዘዝኩ። ያ ሊነኩት የሚያሳሳ ቆዳው ከስሎ…… የሚያንጠራራ መለሎ ቁመናው ጎብጦ… የሚያኮራ ደልዳላ አካሉ ኮስምኖ… አይሆንም እሱ አይሆንም! "አቁምልኝ! አቁምልኝ! "ጮህኩኝ ባሌ ላይ… ዘልዬ ወረድኩ እና እጁን ይዤ አስቆምኩት። "እማ አንቺ ነሽ ስካሬ እያስቃዠኝ ነው? " አለኝ ከቃላቶቹ እኩል የርካሽ መጠጥ ጠረን እየተፋ "አባ አንተ ነህ? ምን ሆነሃል? በየሱስም ምን አገኘህ? ታመህ ነበር? በየሱስ ስም…… ደህና ነህ? ቆይ ምንድነው የተፈጠረው?" "አንቺ እማ! አንቺ ነሽ የተከሰትሽው! ሌላ ማን አለ አንቺ "… የሆነ የአዳም ረታ መፅሃፍ ውስጥ ያለሁ ገፀ ባህሪ የሆንኩ መሰለኝ። እንጂማ እኔ በእውነታው ይህችን ሴት ልሆን አልችልም። በሱስ ምክንያት በተደጋጋሚ አማኑኤል ሆስፒታል እንደነበረ ነገረኝ። በዛ ምክንያትም ስልክ ኖሮት ስለማያውቅ ላገኘሁ እንዳልቻልኩ አብራራልኝ…… "እማ አንቺ ማለት የምትበር ቢራቢሮ ነበርሽ…… ነፃ የሆንሽ… ነፃነትሽን የምትወጂ… ካልሞከርሽ የማታረጋግጪ…… ሁሉን ሞከርሽ እኔን ጨምሮ ሁሉን ተውሽ! ሁሉን አስሞከርኩሽ ከሁሉ ተጋባሁኝና ቀረሁ። " አለኝ። አይ አይሆንም የአዳም አንዷ ገፀባህሪማ ሆኛለሁ።…… ነፃነት? ሌላውን የገደለ ነፃነት? በሌላው ባርነት ላይ የቆመ ነፃነት? የአባን ገፅ ያከሰለ ነፃነት? ……… አይሆንም ውሸት ነው። እኔማ እውን አይደለሁም… 📚 @Bemnet_Library
Show all...
🔥 45👍 40😢 29💔 18 8
ወጥመድ መላኩ በማግስቱ ወደ ዱባይ ሊሄድ ዝግጅቱን ጨርሷል። ኮንፈረንሱ የሚጀመረው ሰኞ ሲሆን እሱ ለመብረር ያሰበው እሁድ ነው። ሣራም ትንሹን ልጇን ጉንፋን አሞት ስለነበር ላለፉት ሦሥት ቀናት ከቤት አልወጣችም። ዛሬ ግን ሻል ብሎት እሷም አረፍ ብላለች። ሌሎቹ ሁለቱ ልጆቿ ከአባታቸውና ከአያቶቻቸው ወደ ደብረማርቆስና ባህርዳር ለአንድ ሳምንት ቆይታ ከሁለት ቀን በፊት ስለሄዱ በአንድ በኩል ትንሽ እፎይ ብላ ነው የሰነበተችው። ቅዳሜ ከሰአት ጀምሮ ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ ከመላኩ ጋር ሸራተን ነበር የቆዩት። ለአንድ ሰዓት ከዋኙ በኋላ ሳዉና ባዝ ወስዳ፣ ማሳጅ አድርጋ ስለነበር ትንሽ ድካም ቢሰማትም፣ ለእራት ሲወጡ የረጋ ሰውነቷ ሁሉ ተከፋፍቷል። ልጇም ያለወትሮው ተኝቶ ስለነበር አላስቸገረም። ቢያንስ እስካሁን አልተደወለላትም። ምናልባት ሌሊት እንቅልፍ ሊኖራት እንደማይችል በማሰብ ፈርታለች። ከዚህ አይነቱ ጥሩ ቀን በኋላ ግን የማትችለው ነገር አይኖረም። ሣራና መላኩ አሜሪካ ከመሄዱ በፊት ስለነበራቸው መልካም ትዝታ እያወሩ ሁለቱም ርቧቸው ስለነበር ወደ አንድ ፒዛ ቤት ሄዱ። 📚 ርዕስ፦ ዝጓራ ✍️ ደራሲ፦ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ማጋራት መተሳሰብ ነው! @Bemnet_Library
Show all...
🗣 በአጭር ጊዜ ውስጥ እንግሊዝኛ ቋንቋ አቀላጥፎ ለመናገር የሚረዳቹ ምርጥ ሀገርኛ የቴሌግራም ቻናል። ከ 135ሺ በላይ ተከታይ ያለው። 🗣, The best national Telegram channel where you can learn to speak English fluently in a short period of time. ቻነላችንን ለመቀላቀል 👇 @English_Ethiopian @English_Ethiopian
Show all...
👍 3
🌐 J O I N 🌐
በአስማት ወደ ውሻነት ተለውጫለሁ። ማንም ይህን እውነት ለማመን ቢቸገር ተቸገረ አይባልም። ይህንን ለመቀበል እንኳ ለሌላው ለእኔም ከብዶኛል። የማንም እምነት እኔን ከውሻነቴ አይመልሰኝም። ይህ እውነት ቢሆን ባይሆን የሚቸግረው ላይኖር ይችላል። አይኑር። የእውነቱን የማይኖር፣ የእውነቱን የማይስቅ፣ የእውነቱን የማያለቅስ ትውልድ ይህንን አስቸጋሪ ሀቅ እንዲያምን አይገደድም። ሀቁ ግን ይኸው ነው። በአርአያ ሥላሴ የተፈጠርኩ ሰውዬ በአርአያ ቡቼ ከች ብያለሁ። ሰው ነበርኩ። እነሆ አሁን ግን ውሻ ነኝ። እንደ ምጣድ ቂጥ የበሰልሁ ውሻ። ይኸው ወደ አንዲት ጥርት ያለችና ከፈሳሽ የተሰራች መስታወት ወደመሰለች ምንጭ ዳር ደርሼ መልኬን ውሃ ውስጥ እየተመለከትኩ ነው። ሰአት እላፊ የመሰልሁ፣ ጥቁር ውሻ። ማጋራት መተሳሰብ ነው! 📚 @Bemnet_Library
Show all...
👍 65 4
ሁሉም ሰው ሊያነባቸው የሚገቡ 5 ምርጥ መጽሃፍት 📚 @Bemnet_Library
Show all...
👍 23 5🙏 4