………….አራግፈው
✍🏻 በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጠፍቶበት ፍለጋ ላይ እያለ በመጨረሻ አህያውን መውጣት በማይችልበት ጥልቅ በሆነ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ያገኘዋል።
አህያውን ለማውጣት ብዙ ከሞከረ በኋላ ገበሬው ተስፋ በመቁረጥ ማውጣት ካልቻልኩ ምን አደርጋለው በማለትና አፈር ለማልበስ ይወስን እና አፈር ማልበስ ይጀምራል፤ ታዲያ በዚህ ጊዜ አንድ አስደናቂ ነገር አህያው ያደርጋል ወደ እርሱ በተደጋጋሚ የሚመጣውን አፈር ከላዩ ላይ ለማራገፍ በሚያደርገው ጥረት አፈሩ ከስር እየገባ እርሱን ደግሞ ከፍ እያደረገው ይመጣ ጀመር።
በዚህም ምክንያት አህያው ለሞቷ የተወረወረው አፈር እያራገፈ ከላዩ ላይ በመቆም መውጫ ሲሆነው ፤ ለገበሬውም አህያውን ማትረፍ ሆነለት።
🔥
SHAKE IT OFF AND STEP UP!!!
👉🏻 በሕይወት ላይ የሚደርሱብን የትኛውም ፈተና እና ችግር ተስማምተን እና ተቀብለነው ከተቀመጥን ሊገለን እና ሊያጠፋን እንደሚችል ተረድተን የሚወረወረውን ዱላ ሁሉ ማገዶ እያደረግን መቀጠል ይኖርብናል።
ጳውሎስ በአንድ ወቅት የደረሰበትን መከራ ተቀብሎ ቢቀመጥ ኖሮ የሞት ድግስ ይጠብቀው ነበር። ነገር ግን ስላራገፈው የእግዚአብሔርን ተአምራት እጅ እርሱ ብቻ ሳይሆን አብረውት ያሉት ሁሉ አዩ።
ሐዋርያት ሥራ 28፡3፣5-6
3 ጳውሎስም ጭራሮ ሰብስቦ ወደ እሳቱ ሲጨምር፣ ከሙቀቱ የተነሣ እፉኝት ወጥታ እጁ ላይ ተጣበቀች።
5 ጳውሎስ ግን እባቢቱን ወደ እሳቱ አራገፋት፤ አንዳችም ጒዳት አልደረሰበትም።
6 ሰዎቹ ከአሁን አሁን ሰውነቱ ያብጣል ወይም ድንገት ሞቶ ይወድቃል ብለው ይጠባበቁ ነበር፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ጠብቀው ምንም የተለየ ነገር እንዳልደረሰበት ባዩ ጊዜ፣ ሐሳባቸውን ለውጠው፣ “ይህስ አምላክ ነው” አሉ።
#በእባብ_ተነደፍን_ማለት_እንሞታለህ_ማለት_አይደለም_መርዝ_ሊመርዘው_የማይችል_የእግዚአብሔር_ሕይወት_እኛ_ውስጥ_አለ!!!
👉🏻 በመጨረሻም ከእኛ ጋር መቀጠል የሌለበት የትኛውም ነገር ልናራግፈው በእርሱ ላይ ተረማምደን ጉዞአችንን ልንቀጥል ይገባል።
መልካም ቀን!
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድShow more ...