#የተሸነፈው\_አያድክማችሁ
ጠላታችን ዲያቢሎስ የዛሬ 2000 ዓመት በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በአብ ቀኝ መቀመጥ የተሸነፈ ነው። ካላስቆምካችሁ የሚለው ዲያቢሎስ የተሸነፈ ነው ፤ ስለዚህ በክርስቶስ ያለንን ማንነት በመረዳት የተሸነፈው እንዳያደክመን መስራት አለብን።
የተሸነፈው ዲያቢሎስ በ3 ነገር ክርስቲያኖችን በምድር ላይ ሊጥላቸው ፣ ሊያደክማቸው ፣ ሊያስቆማቸው ወደ ሕይወታቸው ይመጣል።
1) በፈተና
“ፈታኝም ቀርቦ፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው።”
— ማቴዎስ 4፥3
2)በስደት
“በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥12
3) በክስ
“.....ቀንና ሌሊት በአምላካችን ፊት ሲከሳቸው የነበረው፣ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።”
— ራእይ 12፥10 (አዲሱ መ.ት)
እነዚህን አውቀን በመጽናት መዋጋት እና ማሸነፍ አለብን።
መልካም ቀን
ሬቨ. ተዘራ ያሬድ
Join us :-
@GospelTvEthiopiaShow more ...