cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በእግዚአብሔር ቃል📖እውቀት ማደግ🥀

“በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥...በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን።” ቆላስይስ 1፥10-12 የዚህ Channel ዋናው 🎯ዓላማ የእግዚአብሔርን ቃል በመማር በእግዚአብሔር ቃል እውቀት መደግ ነው። 🙋ጥያቄና አስተያየት ካለ👉 @beigziabiher_kal_iwuket_madeg1 Owner 👉 @cherumk68

Show more
Advertising posts
535Subscribers
No data24 hours
-17 days
-730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ክፍል-2 ኢየሱስን በማየት አብን ማየት ከቻለን ኢየሱስን በማሳየት አብን ማሳየት እንችላለን። አሁንማ ቀና ብለን በመንፈስ ካየን ኢየሱስን በአብ ቀኝ ያ የነበረውን፤ አልፋውን፤ ፊተኛውን፤ መጀመርያውን በክብር እናያለን። ይህንን ኢየሱስን ነውኮ ሐዋርያው ዮሐንስ በራዕ 1፥ 10-18 ላይ በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፥ እንዲሁም፦ የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊልድልፍያም ወደ ሎዶቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ። የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየሁ፥ በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር። ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥ ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ። በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ። ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ። እንደዚህ ያለው። ይህንን ኢየሱስን ያለውንና የነበረውን ካየን ያለንበትን እንረሳለን፤ የከበበን ነገሮችንም እንረሳለን። ክብሩን በማየት በፍርሃት ከወደቀንም ያነሳናል። አይዞአችሁ ክብሩን በማየት ለመዉደቅ አትፈሩ ይህንን ኢየሱስን ማየት ይሁንላችሁ። ይህ ዮሐንስ ኢየሱስ ሲገረፍ፣ ሲሰቀል፣ ሲተፉበት፣ ሲያንገላቱ፣ እርቃኑን ሲያስቀሩ.....ወ.ዘ.ተ ሲያደርጉ ቆሞ ያየ ነበር ግና በክብሩና በግርማው ሲያየው ወደቀ። ስለዚህ እኛም ኢየሱስን በእኛ ሁኔታ ሳይሆን በአምላክነቱ ማየት ይሁንልን። እርሱም ይህን ካየ በኋላ መልእክቱን እንደዚህ መጻፍ ጀመረ። “... ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦” ራእይ 2፥8 “፦ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦” ራእይ 3፥14 ይህ ነው ኢየሱስ ከአብ ጋር የነበረ፤ ለዮሐንስም በራዕይ 1፥8 ላይ “ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።” ብሎ እራሱን የገለጠ። ወገኖቼ ይህን ኢየሱስን እንደ መጥመቁ ዮሐንስ "እነሆ....." እያለን ማሳየት እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን።
Show all...
👍 2
ያለውና የነበረው ክፍል-1 "ያለውና የነበረው" በሚለው ንዑስ ርዕስ እንዴት ብዬ እንደምፅፍ እያሰብኩ ብቆይም በዮሐ 1፥1-10 ያለውን ክፍል አንድ በአንድ ስለ ኢየሱስ ምን እንደምል ለመጻፍ ልቤ አዘነበለ። ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ መጻፍ ገና ሲጀምር ከለሎች ወንጌላት ጸሃፊዎች፥ ከማቴዎስ፣ ከማርቆስ እና ከሉቃስ ለየት ባለ መልኩ ፍፃሜ በለሌው አጀማመር ይጀምራል። ወደ መጽሐፉ እንመለስ፡- 👉ዮሐ 1፥1-2 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ዮሐንስ "በመጀመርያ" ሲል ኢየሱስ በማርያም ከመፀነሱ በፊት ያለውን ጊዜ ለመናገር አይደለም። እግዚአብሔር ነገሮችን ሁሉ የፈጠረበት መጀመርያም አይደለም። ዮሐንስ የተናገረው ከዘላለም በፊት ስለነበረው ጊዜ ነው። ይህ ቃል በመጀመርያው ነበረ እንጅ ለዚህ ቃል መጀመርያ የለውም። ደግሞም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። አሁን በዚህ ቦታ ልብ በሉ ቃልና "በእግዚአብሔር ዘንድ" የተባለው እግዚአብሔር ወልድንና አብን እንደሚያመላከት አስቡበት። ደግም ከሱ ቀጥሎ "ወልድ(ቃል) እግዚአብሔር አይደለም ወይ? እንዴት?" ብለን እንዳንወዛገብ " ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ።" በማለት ግልፅ ያደርግልናል። ቀጥሎም ደግሞ ቃልም እግዚአብሔር ከሆነ አብ ወልድ ነው ብለን እንዳንደመደም በቁጡር 2 ላይ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ በማለት አብ እና ወልድ ልዩ አካል እንዳላቸው ያስረዳል። ይህ ኢየሱስ ያለውና የነበረው ነው። የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን። ዮሐንስንም እግዚአብሔር ይባርከው፤ እናንተም ይባርካችሁ። 👉ዮሐ 1፥3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በዘፍ 1፥1 “በመጀመሪያ እግዚአብሔር(ኤሎሂም) ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።" በሚለው ዐ.ነገር ውስጥ "እግዚአብሔር " የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ኤሎሂም" ማለት ነው። ይህም ብዙ ቁጥር አመልካች ሲሆን ግን ዐ.ነገሩ በመጨረሻ የታሰረው በነጠላ ግስ ነው። ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጥረቱ አፈጣጠር በመጀመርያ በሥላሴ ውስጥ ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንደነበረ ሦስት አካልም አንድ አምላክ እንደነበረ የሚያሳይ ነው። ይህ አምላክ ሁሉን ፈጠረ እንጂ ለራሱ አልተፈጠረም። የፍጥረታት ሁሉ ጅማሬ የተፈጠረበት ቀን ነበር ግን የፈጣሪው መጀመሪያ ከመታወቅ ያለፈ ነው እርሱ ከዘላለምም በፊት የነበረ ነው አሁንም ያለው ዘላለማዊ ነው። ሃለሉያ። "አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።” ሮሜ 9፥5 ".......፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።" የሚለውጋ ስንመጣ አብ እግዚአብሔር በልጁ ሰማይንና ምድርን ፍጥረታትን ሁሉ እንደፈጠረ በአድስ ክዳን የተለያዩ ጻፍዎች በመንፈስ ቅዱስ በመመራት እውነታውን አስቀምጠዋሉ። “እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤” ቆላስይስ 1፥15-16 “ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤”“እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤” ዕብ 1፥1-3 እንዲሁም የዕብራዊያን ጸሐፍ እግዚአብሔር በልጁ ዓለምን መፍጠሩን ብቻ ሳይሆን እራሱን እንደገለጠ ያስቀምጣል። ሙሴ ማየት ያልቻለውን ፍቱን እግዚአብሔርም ሙሴን "አትችልም" በማለት የከለከለበትን ፍቱን በልጁ በኩል እንድናይ ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኮልናል። ኢሳያስም ቢሆን ክብሩን አየ እንጂ ፊቱን አላየም፥ ማንኛውም የጥንት አባቶች በተለያዩ መንገድ፥ ታአምር ሲሠራ፣ ከእንጨት የተሠራ ታቦት ሆኖ በመሐላቸው ሲቀመጥ፣ በምድረ በዳ የተሰቀል የናስ እባብ ሆኖ ሲያድናቸው...... በተለያዩ መንገዶች አዩ እንጂ የእግዚአብሔርን ፊት አላዩም ነበር። መልአክን አይተን ለምንፈራ ለእኛ፤ አብን ያየ አብን ሊያሳይ የባርያን መልክ ይዞ ዝቅ በማለት የመጣ ፤ እንዳንፈራ በግርግም የተወለደ እነሆ እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም እንዲህ ነው፡- የፀሐይ ብርሃን ከራሱዋ ከፀሃይ ሊለይ እንደማይችል ሁሉ፤ የእርሱ ነፀብራቅ እንዲሁ ከመለኮቱ ሊለይ አይችልም። ምክንያቱም እርሱ ራሱ አምላክ ከሥላሴ አካላት አንዱ ነው። እርሱም የባሕሩ ትክክለኛ ምሳሌ ነው ደምቆ የሚታይ ባህሪ አለው እንጅ የደበዘዘ ባህሪ የለውም። ለዚህም ነው ዮሐንስ በዮሐ 1፥18 ላይ “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።” ያለዉ። በዮሐ 14፥9 ኢየሱስም ለፊልጶስ ሰመለስ፡- “......፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ አብን አሳየን ትላለህ?” 📝ይቀጥላል።
Show all...
👍 2
እጸልያለሁ - ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ** ሌሊቱ ሲነጋ ጐህ ሲቀድ አእዋፍ ሲንጫጩ በአንድነት በዜማ ፈጣሪን ለማምለክ ሲወጡ ሁሉም ከያሉበት እኔ ግን መኝታዬ ሞቀኝ ዝምብለሽ ተኚ ተኚ ቢለኝ መኝታዬን ወዲያ ገፍፌ ለጸሎት ነቃሁኝ ከእንቅልፌ ለጸሎት መንፈሴ ሲነቃ ሥጋዬ ባይደሰት ቢከፋ ሳይወድ በግዱ ያብርና መጸለዬ ይቀጥላል ገና ስሙን ስጠራው የጌታዬን ያድሰዋል ደካማው ጐኔን ቅባቱ መፍሰስ ይጀምራል ለጸሎት ጉልበቴን ያድሳል እጸልያለሁ (፫x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ መች አፍሬ አውቃለሁ እጸልያለሁ (፫x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ ድልን አግኝቻለሁ እጸልያለሁ (፫x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ መልስን አግኝቻለሁ እጸልያለሁ (፫x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ እንደሚሰማ አምናለሁ አንዳንዴ ውስጤ ጸልይ ሲለኝ ስጋዬ ግን ሲያታልለኝ ቆይ ትጸልያለህ በኋላ እያለ ጊዜዬን ሊበላ ግን ዳንኤልን ጉድጓድ ያስጣለው አትጸልይ የሚል ህግ ነው ቢያስመርጡት ከምንም ነገር ጸሎት ነው ለእርሱ ትልቅ ነገር ይህንን ሳስታውስ እነቃለሁ ስጋዬን ተወኝ እለዋለሁ ስታዘዝ ለነቃው መንፈሴ ለጸሎት ተጋልኝ ጉልበቴ ጸሎት ትልቅ መሳሪያዬ ነው ሰይጣንም ይሄ ስለገባው እንዳልጸልይ ቢታገለኝም ምክኒያትን ለሥጋዬ አልሰጥም አዝ፦ እጸልያለሁ (፫x) ግራ ሲገባኝ በሕይወቴ መምበርከክ ሲያቅተው ጉልበቴ ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ስሞላ መፍትሄ መልስን ሳጣ መላ ከመጸለይ ይልቅ በፊቱ ሳወራ ላገኘሁት ሁሉ ይባባስብኛል ችግሬ ያጐብጠኛል ያ ጠብቆ ቀምበሬ ግን በሬን ዘግቼ ስገባ የውስጤን ሁሉ ወደ ሚረዳ በጸሎት ዙፋኑ ስር ስወድቅ ይታደሳል ውስጤ በድንገት ያልወጣሁት ችግር ጸልዬ ፍፁም የለምና በሕይወቴ ባልጸልይ እራሴን እጐዳለሁ ይህንን በተግባር አውቃለሁ አዝ፦ እጸልያለሁ (፫x)  * ጦር ሜዳ:-https://t.me/btlfld
Show all...
"ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች፡፡ በአስራ ስምንተኛዉ ወር ዉሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት “እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርጉዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡ ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነዉ ልጅ በልጅ ሆኛለሁ፡፡ አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ...ችግር አለ??” ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታዉቂልኝ የምፈልገዉ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡ ልወልድ የምችለዉ በሁለት አመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል...የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ሃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ነዉ” የዚህ አጭር ተረት መሰል ታሪክ ጭብጡ፡ ሰዎች ለጥያቄዎቻቸዉና ለጸሎቶቻቸዉ መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ፡፡ በሌሎች ምስክርነት አትቅና፡፡ የራስህን የጸሎት መልስ ካላገኘህ ዉስጥህ አይሰበር ይልቅ ለራስህ እንዲህ በለዉ "ጊዜዬ እየደረሰ ነዉ ተወልዶ መሬት የረገጠ እለት ሰዎች በአድናቆት የተወለደዉን ይመለከቱታል" መንፈስ ቅዱስ የረሳሁትን እንዳይመስላችሁ ለበለጠ ክብር እያዘጋጀ ነው እንጂ . #ያልተወለደ ራዕይ እንጂ ያልተፀነስ ራዕይ የላችሁም#             ✍️ Ch ሬ                              ─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───          💯ꜱʜᴀʀᴇ🌟ꜱʜᴀʀᴇ🌟ꜱʜᴀʀᴇ💯               🔎𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒🔍                         👇👇           ✅ @beigziabiher_kal_iwuket_madeg ✅           ✅ @beigziabiher_kal_iwuket_madeg ✅           ✅ @beigziabiher_kal_iwuket_madeg
Show all...
👍 1
✏️27ቱ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት የተጻፉበት ዓ .ም📖✍️
◉ማቴዎስ፦በ70-80 ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉ማርቆስ፦በ55-60ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉ሉቃስ፦በ65-70ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉ዮሐንስ ወንጌል፦በ70-90ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉ሐዋርያት ሥራ፦በ60-65ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉ሮሜ፦በ55ዓ.ም ተጽፏል📝 ◉1ቆሮንቶስ፦በ54ዓ.ም ተጽፏል📝 ◉2ቆሮንቶስ፦በ56ዓ.ም ተጽፏል📝 ◉ገላትያ፦በ48-49ዓ.ም/በ52-56ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉ኤፌሶን፦በ60-61ዓ.ም መካከል ተጽፏም📝 ◉ፊልጵስዮስ፦በ60-61ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉ቊላስያስ፦በ60-61ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉1ተሰሎንቄ፦በ50ዓ.ም ተጽፏል📝 ◉2ተሰሎንቄ፦በ51ዓ.ም ተጽፏል📝 ◉1ጢሞትዮስ፦በ64-65ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉2ጢሞትዮስ፦በ65-66ዓ.ምመካከል ተጽፏል📝 ◉ቲቶ፦በ62-64ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉ፊልሞና፦በ60-61ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉ዕብራውያን፦በ60-70ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉1ጴጥሮስ፦በ64ዓ.ም ተጽፏል📝 ◉2ጴጥሮስ፦በ65ዓ.ም ተጽፏል📝 ◉1ዮሐንስ፦በ90-100ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉2ዮሐንስ፦በ90-100ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉3ዮሐንስ፦በ90-100ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉ያዕቆብ፦በ50ዓ.ም ተጽፏል📝 ◉ይሁዳ፦በ70-75ዓ.ም መካከል ተጽፏል📝 ◉የዮሐንስ ራዕይ፦በ90-100ዓ.ም መካከል ተጽፏል.📝 🎯ብቻችሁን አታንብቡ ለሙስሊሞች እና ክርስቲያን ሼር📲 🚩“እነሆ፤ ቶሎ እመጣለሁ፤ ዋጋዬ በእኔ ዘንድ አለ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍለዋለሁ።”✔️ 💎— ራእይ 22፥12 (አዲሱ መ.ት)💎 ⛳️ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል!🚀 🚩Jesus is Coming soon🚦
Show all...

ጠጠር አንስተህ ተራራ ላይ ብትወረውር ተራራው ምንም አይሆንም ጠጠሩ ተንከባሎ እግሩ ስር ይሆናል። ያን ጠጠር አንስተህ መስታወት ላይ ብትወረውረው ግን መስታወቱ ይሰባበራል። ጠጠሩን በችግር እንመስለውና ችግር ወዳንተ ሲመጣ እንደ መስታወቱ አትሰባበር እንደ ተራራው በቁጥጥር ስር አውለው። የኔ መረጃ “ሕይወት የሁለት ነገሮች ድምር ውጤት ናት። ማግኘት አለ ማጣት አለ መወለድ አለ መሞት አለ ደስታ አለ ሀዘን አለ እንባ አለ ሳቅ አለ። ሁለቱም የህይወት አካሎች ናቸው። ህይወት እንደ ሸማኔ መወርወሪያ የሁለቱንም ጫፍ እያስነካች ትመልሰናለች። አንድ ቀን 24 ሰዓት አለው። 12ቱ ሰዓት ብርሃን 12ቱ ሰዓት ጨለማ ነው። አይ እኔ ጨለማ አልወድምና ለሊቱ ይቅርብኝ ብንል ቀናችን ጎዶሎ ነው ሚሆነው። አንድ አመትም ክረምትና በጋ አለው። አይ ጭቃ አልወድምና ክረምቱ ይቅርብኝ ብንል አመታችንም ጎዶሎ ነው ሚሆንብን ። ስለዚህ ህይወትም ያለ ችግር ደስታውን ብቻ እንኑረው ብንል ጎዶሎ ህይወት ነው ምንኖረው። አንዳንዴ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ችግር ውስጥ የሚከተን ሕይወታችንን ሙሉ ለማድረግ ነው።
Show all...
👍 1 1
መጸለይ ሲያቆሙ * መጥፎ ምግባር ይጀምራሉ። * መጸለይ ሲያቆሙ * በሕይወት አስፈላጊ ጉዳዮች ውስጥ መጥፎ ምርጫ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * በሁሉም ነገር ላይ ግድየለሽ ይሆናሉ ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * ዋጋዎን ማጣት ይጀምራሉ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * በረከቶን ማጣት ይጀምራሉ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * መንፈሳዊ ማንነቶን ያጡና ሥጋዊ ይሆናሉ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * መነሳሳትን እና ችሎታን ያጡና ስህተቶችን ማድረግ ይጀምራል። * መጸለይ ሲያቆሙ * አዲስነትን ያጡና መበስበስ ይጀምራሉ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * ነገሮችን ማጣት ይጀምራሉ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * የምረዳ ሰው ጨምሮ ሁሉንም እንደ ጠላት እና ሐሰተኛ አድርጎ ማየት ይጀምራል ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * መደበቅ ይጀምራሉ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * የሕይወትዎን ዋጋ እና ውበት ማየት ትተው ራስን ስለማጥፋት ማሰብ ይጀምራል። * መጸለይ ሲያቆሙ * አላስፈላጊ ውድድር እና ጠብ ይጀምራሉ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * ለጥንቆላ ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ፣በእግዚአብሔር ሰዎች የምተላለፉ መልእክቶችን ማዳመጥን በንቀት አመለካከት መየት ይጀምራሉ። * መጸለይ ሲያቆሙ * ለፍች መንገድ ላይ ይሆናሉ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * ብርሃንዎ ጨለማ ይሆናል ፡፡ * መጸለይ ሲያቆሙ * የቴሌቪዥን ልምዶችዎ በቂ እንደሆኑ እና ህብረት አስፈላጊ እንዳልሆነ እራስዎን ማጽናናት(ማሳመን) ይጀምራሉ። * መጸለይ ሲያቆሙ * ተፈጥሮን ጨምሮ ሁሉም ነገር እርስዎን መዋጋት ይጀምራል ፡፡ * በማንኛውም ጊዜ ፀሎት ስያቆሙ፣ * በፍጥነት በተሳሳተ ልማድ እና መንፈስ ይጠቃሉ ፣ ምክንያቱም ተፈጥሮ ባዶነትን ስለሚጸየፍ። * ያስተውሉ! * የመጸለይ ቁርጠኝነት ባይሰማዎትም እንኳ ይጸልዩ! መጸለይ እንደጀመረ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
Show all...
3👍 1
ዮሐንስ በፅድቅ መንገድ ሲመጣ ያመኑት እነ ማን ናቸው?Anonymous voting
  • ጋለሞቶች
  • ቀራጮች
  • እግረኞች
  • ሀ እና ለ
0 votes
2ኛ ጢሞቴዎስ 3 ¹ ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። ² ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ³ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ⁴ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ ⁵ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። ⁶-⁷ ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና። ⁸ ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው፥ እውነትን ይቃወማሉ። ሮሜ 1 ¹⁸ እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤ ¹⁹ እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። ²⁰-²¹ የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ²² ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ ²³ የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ። ²⁴ ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ²⁵ ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን። ²⁶ ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ ²⁷ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። ²⁸ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ²⁹ ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት ሞላባቸው፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ፥ ³⁰ ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚያንገላቱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ ³¹ የማያስተውሉ፥ ውል የሚያፈርሱ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት ያጡ ናቸው፤ ³² እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም። በሌሎች ቻናሎች ውስጥ አይታችሁ ይሆናል ግን ብዙዎችን ለማንቃት ነው #ሼር_አድርጉት_እሺ_በጌታ ፀልዩ የኢትዮጵያ እጣፈንታ ይህ እንዳይሆን 1- ሁሉም የአለም ሀገራት ከታላላቅ ኃያላን ጋር መልካም ግንኙነት ለመመስረት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ (ሴት/ሴት ወይም ወንድ/ወንድ) መቀበል እንዳለባቸው አሜሪካ አረጋግጣለች።  በአሁኑ ጊዜ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ሕጋዊ የሆነባቸው 34 አገሮች አሉ፡ አንዶራ፣ አርጀንቲና፣ አውስትራሊያ፣ ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ ብራዚል፣ ካናዳ፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ኮስታሪካ፣ ኩባ፣ ዴንማርክ፣ ኢኳዶር፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ አይስላንድ፣ አየርላንድ፣  ሉክሰምበርግ፣ ማልታ፣ ሜክሲኮ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኒውዚላንድ፣ ኖርዌይ፣ ፖርቱጋል፣ ስሎቬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስፔን፣ ስዊድን፣ ስዊዘርላንድ፣ ታይዋን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አሜሪካ እና ኡራጓይ። 2- ጀርመን ከአሁን በኋላ የዘር ግንኙነት የለም የሚለውን ህግ ፈርማለች ማለትም ወንድም እና እህት እናት እና ወንድ ልጅ አባት እና ሴት ልጅ ወዘተ.. 3-የሚያሚ ከተማ አሁን የህዝብ የወሲብ ግዢ ከተማ ተባለች።  ይህም ማለት፡ በመንገድ ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመስጊድ ፣በገበያ ፣በኳስ ሜዳ ሴክስ ከፈለጋችሁ በማንኛውም ሰአት ያለችግር መደሰት ትችላላችሁ 4-ካናዳ አውሬነትን ፈቀደች(ከእንስሳት ጋር ወሲብ) 5- በስፔን: የብልግና ፊልሞች በሁለተኛ ደረጃ እና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተፈቅዶላቸዋል.  6- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ዝሙት አዳሪነት ፈቃድ ተሰጥቷል.  ማርግ ሉከር በ10 ዓመቷ የጾታ ደስታ የሚሰማት ማንኛዋም ወጣት ሴት ልጅ፣ ማንም ሊከላከልላት አይገባም ሰውነቱ እንዴት እንደሚሰራ እወቅ 7- በመጨረሻም አሜሪካ የሰይጣን አብያተ ክርስቲያናት በይፋ እንዲከፈቱ ፈቅዳለች። ውድ ወንድሞች እና እህቶች መጨረሻው ቀርቧል፣ የክብር ጉዞው እየቀረበ ነው። ሰዎች ትኩረታቸው እየተከፋፈለ ነው እና ዲያቢሎስ ከመለኮታዊ ምህረት ለማስወገድ ከፍተኛውን የነፍስ ቁጥር ከእሱ ጋር መጎተት ይፈልጋል።  እንጠንቀቅ።  አንድ ደቂቃ ካሎት...ይህንን መልእክት ሼር ያድርጉ።  በቤተክርስቲያን ውስጥ ለምን እንተኛለን፣ እና በመጠጥ ቤቶች ውስጥ እንነቃለን?  ስለ ኢየሱስ ማውራት በጣም ከባድ የሆነው ግን ለማማት ቀላል የሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ግን የቆሸሹ መልዕክቶችን መልሶ መላክ ቀላል የሆነው ለምንድነው? ይህን መልእክት ለጓደኞችህ ልትልክ ነው ወይስ ችላ ልትለው ነው?  እግዚአብሔርን የምትወዱ ከሆነ ይህንን መልእክት በ60 ሰከንድ ውስጥ ለእውነተኛ የቅርብ ጓደኞችዎ ይላኩ።       አግዜር ይባርክህ.  አሜን!!! በአሁኑ ጊዜ የፆታ ብልግና ዓለምን እያናጋ ነው።   አምላክ እንዲህ ብሏል፡- “የሰው ልጅ አምስት ነገሮችን የሚወድበት አምስት ነገሮችን የሚረሳበት ጊዜ ይመጣል።   1. የዚችን ዓለም ተድላ ይወዳሉ የፍርዱንም ቀን ይረሳሉ።   2. ገንዘብን ይወዳሉ እና ገንዘቡን እንዴት እንዳገኙ እና እንዳወጡት የተጠያቂነት ቀን ይረሳሉ.   3. የተፈጠሩትን ይፈራሉ ፈጣሪንም ይረሳሉ።   4. ውብ መኖሪያ ቤቶችን ይወዳሉ መቃብራቸውንም ይረሳሉ.   5. ኃጢአትን ይወዳሉ እና የእግዚአብሔርን ይቅርታ መፈለግን ይረሳሉ።   እስቲ ይህን አስብበት?.......   1. የዘላለም ሕይወት = ነፃ   2. የቤተክርስቲያን መግቢያ = ነፃ   3. የክርስቶስ ማዳን = ነፃ   4. የእግዚአብሔር ፍቅር = ነፃ   5. የሕይወት እስትንፋስ = ነፃ   ሀ. ሲጋራ = ክፍያ   ለ. ዝሙት አዳሪነት = ክፍያ   ሐ. አልኮል = ክፍያ   መ. የምሽት ክለብ መግቢያ ክፍያ = ክፍያ   ሠ. ዓለምን የሚገዙ ኃይሎች = ክፍያ   ታዲያ ለምንድነው ሰዎች ገነት ነፃ እያለች ለገሃነም የሚከፍሉት?
Show all...
የቅርቤ ከሲዖል መውጣቴ ይበቃኝ ነበረ በዚያ አላበቃም ፍቅሩ ጨመረ ቀረበኝ አልሆንኩም ብቸኛ አምላኬ ልክ እንደ ጓደኛ ሳይዘው ሳይገድበው ትልቅነቱ አብሮኝ ነው ኢየሱስ ትሁቱ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ (2X) ከእስትንፋሴ ይልቅ የቅርቤ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ ከእስትንፋሴ ይልቅ ይልቅ የቅርቤ ነህ ፊትህን ተርቤ መቼ መቼ አጣሁህ የሆድ የውስጤን ታውቀው የለም ወይ ሳልተነፍስ ውዴ ኢየሱስ ሰው ሚያውቀው ጉብዝናዬን መቼ አየ ገመናዬን ሸፍነኸው ጉድለቴን ሚታየው ግን ሙላቴ የቅርቤ... ዞር ብዬ ወደ ኋላ መንገዴን ሳይ የአንተ እንጂ የእኔ ኮቴ አይታይ አባጣ ጎርባጣውን እኔ መውጣቴ ይዘኸኝ ልክ እንደ እናቴ ምንም ባሳዝንህ በድካሜ ታግሰኽ አቆምከኝ መድህኔ ሰው ሚያውቀው... በሰዎች መሐል ወይም ለብቻዬ ድምፁን ያሰማኛል አብሮኝ ነው ጌታዬ በዚህ ሂድ በዚያ ሂድ እያለኝ ጠላት የማሰውን አለፍኩኝ አምላኬ የመከረኝን ሰምቼው አለፍኩኝ ስንቱን የቅርቤ... ሰው ሚያውቀው... የቅርቤ... የቅርቤ በረከት ተስፋዬ New song sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ማርከን ዜማ @Markenzema_bot በዚህ ቻናል የማይደመጥ መዝሙር የለም ብቻ ምን አለፋችሁ join ይበሉ 👇 https://t.me/+S2wsmZMSQp3vcGxp https://t.me/+S2wsmZMSQp3vcGxp
Show all...