cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሰበር ዜና

Connect with ሰበር ዜና to find daily breaking news as they happen in Ethiopia & around the globe all in one place by providing 24/7 coverage from all sources. Facebook page link https://m.facebook.com/BreakingNewsEthiopia/?ref=bookmarks

Show more
Ethiopia3 255Amharic2 573The category is not specified
Advertising posts
5 525Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጋዛ በከባድ ፍንዳታ እየተናጠች ባለበት የእስራኤል እግረኛ ሠራዊት ዘመቻውን እያሰፋ ነው! አርብ ምሽት ጋዛ ሰርጥን ያናወጡ ከባድ ፍንዳታዎችን ተከትሎ የእስራኤል እግረኛ ሠራዊት የሚያካሂደውን “ዘመቻ እያሰፋ” መሆኑን የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ተናገሩ። ለዚህ ጥቃት ምላሽ ነው በማለት ሐማስ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሱን መግለጹን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዘግቧል።በተጨማሪም የእስራኤል ሠራዊትን በጋዛ ላይ “ተከታታይ ጥቃቶችን” እየፈጸመ መሆኑ ለኤኤፍፒ ገልጿል። ሠራዊቱ በጋዛ ላይ የሚያካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ እያስፋፋ መሆኑን መግለጹን ተከትሎ፣ የጋዛ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ የጋዛ ክፍል ለቀው እንዲወጡ አዟል።ረቡዕ ሌሊት የእስራኤል ታንኮች ወደ ሰሜናዊ ጋዛ ክፍል ዘልቀው በመግባት የተመረጡ እርምጃዎችን ወስደው እንደወጡ መገለጹ ይታወቃል። ይህም ጥቃት ሠራዊቱ በጋዛ ላይ ለሚያካሂደው የቀጣይ ምዕራፍ ዘመቻ አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የታለመ መሆኑን የእስራኤል ጦር ኃይሎች ባለሥልጣናት ተናግረዋል።ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ድንገተኛ ጥቃትን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ነገ ቅዳሜ ሦስተኛ ሳምነቱን የሚይዝ ሲሆን፣ እስራኤል እግረኛ ሠራዊቷን ወደ ጋዛ ለማስገባት እየተዘጋጀች መሆኑ ሲነገር ቀይቷል። Via BBC
Show all...
👍 20😢 6 2
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሰሞኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን ሪፖርት " ኃላፊነት የጎደለው ነው " በማለት እንደማይቀበለው አስታወቀ። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ " የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈናቃዮች አስመልክቶ ባወጣው ሁለተኛው ዘገባ የፌደራል መንግስት ባደረገው ጥረት በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ተጋሩ በብዛት ወደ ቄያቸው እንደተመለሱ፤ ሰብአዊ ድጋፍም እየቀረበላቸው እንደሆነ አስመስሎ ይፋዊ ዘገባ አውጥቷል " ሲል ገልጿል። " በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጋሩ ከቄያቸው ተፈናቅለው በከፋ ሁኔታ በሚገኙበት ወቅት ፣ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ በማለት ሌተ ተቀን  ቢወተውትም የወገኖቻችን መመለስ በሚመለከት አንዳች ተግባራዊ እንቅስቃሴ ባልተደረገበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ይህን መሰል ሃላፊነት የጎደለው ዘገባ ማውጣቱ ፤ ከአሁን በፊት በትግራይ ህዝብ ላይ ሲያደርስ የነበረውን በደል የሚያስቀጥል " ነው ብሏል። የፌደራል መንግስት ይህን መሰል ሃላፊነት የጎደላቸው ዘገባዎች ሆነ ተብሎ በመዋቅሩ ሲለቀቁ የሰላም ሂደቱ የሚያውኩ ፣ መተማመን የሚያጎድሉ መሆናቸው ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢ እርምጃ ወስዶ እንዲያርም ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጥሪ ማቅረቡን በመቐለ የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ዘግቧል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከላይ ያለውን መግለጫ ካወጣው በኃላ አጭር መልዕክት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሰራጭቷል። ኮሚሽኑ " በተፈናቃዮች 2ኛ ዓመታዊ ሪፖርቱ ላይ እንደተገለጸው የጂኦግራፊ ወሰኑ ትግራይን አልሸፈነም ይህም በዝግጅቱ ወቅት ተደራሽ ስላልነበረ መሆኑን እናረጋግጣለን " ብሏል። ኮሚሽኑ የተሳሳተ መረጃን ለማረም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ (IRA) ጋር መተባበሩን እንደሚቀጥል አመልክቷል።
Show all...
👍 6 1
#Oromia በኦሮሚያ ክልል እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል። CDCB (Center For Development &Capacity Building ) ባወጣው ሪፖርት የቡሳ ጎኖፋን መረጃ ዋቢ አድርጎ በኦሮሚያ ክልል እስከ መስከረም ባለው ጊዜ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ከተመዘገቡት ተፈናቃዮች ውስጥ 859,000 (66%) የሚሆኑት ከምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ብቻ መሆናቸውን ይጠቅሳል። በመግለጫው የተጠቀሱት ቁጥሮች ምን ያሳያሉ ? - የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 1,292,323 መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 29 በመቶው ብቻ (374,448) ወደ መጠለያዎች መድረሳቸውን ያመለክታል። 71 በመቶ (916,606) የሚሆኑት በአካባቢው እና ራቅ ብለው በሚገኙ ማኅበረሰቦች ውስጥ ተበታትነው ይገኛሉ። - 739 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል። - ከ210,000 በላይ ህጻናት ከትምህርት ውጪ ሆነዋል። - 1,117 መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች ወደ ሥራቸው አልተመለሱም። - 208 ጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤  788 በከፊል ወድመዋል። ( ከእነዚህ ውስጥ 13ቱ ሆስፒታሎች ሲሆኑ የተቀሩት ጤና ጣቢያዎች ናቸው) በዚህ አጭር መግለጫ በምዕራብ ኦሮሚያ እና መካከለኛው አከባቢ በፌዴራል መንግስት እና በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ራሱን የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጭ ብሎ በሚጠራውና መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " የሚለው ታጣቂ ቡድን መካከል የተፈጠረው ግጭት፣ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ድንበር ላይ በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሰው " ፋኖ " በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ቡድን ጋር በሚፈጠሩ ግጭቶች ለችግሮቹ መንስዔ መሆናቸውን ይጠቅሳል። በእነዚህ ግጭቶች በተለይ ሴቶች እና ህጻናት ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው ያለው ይህ አጭር መግለጫ እናቶቻቸውን እና አባቶቻቸውን በድንገት የሚያጡ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ ነው፤ ባል የሞቱባቸው ሴቶች ለዝርፊያ እና ለ አስገድዶ መድፈር (በፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት) እና አካላዊ ጥቃት እየተጋለጡ መሆናቸውን ያነሳል። "በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ውስብስብ እና አሳሳቢ ሁኔታን ፈጥሯል። ይሄን ግጭት ለማስቆም ሁሉን አቀፍ ውይይት እና ሰላም ማስፈን ያስፈልጋል። በግጭቱ ወቅት ለተፈናቀሉ እና ችግር ውስጥ ላሉ ዜጎች አስቸኳይ የተቀናጀ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።" ሲል በCDCB የቀረበው የፓሊሲ ብሪፍ ጠይቋል።
Show all...
😭 7👍 5
" ... ሕገወጡ የድርጅቱ #ኦንላይን_ሲስተም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " - አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ከሰሞኑ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ አዋልሶ ጨምሮ 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወቃል። ይህንን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛል። #የግል አስተያየታቸውን ካጋሩት ውስጥ የቀድሞ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ሱሌማን ደደፎ አንዱ ናቸው። አምባሳደር ሱሌማን ፤ የተወሰደው እርምጃ የዘገየ ቢሆንም የይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል። ነገር ግን ይህ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል። " እነዚህ ሰዎች ዘርግተው የሚጠቀሙበትና በበርካታ ደላሎች የሚሠራበት ሕገወጡ የድርጅቱ #ኦንላይን_ሲስተም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " ብለዋል። አምባደሩ ፤ " ዛሬም የኢትዮጵያ ፓስፖርት በበርካታ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በደላሎች ሱቆች ውስጥ በይፋ በመቸብቸብ ላይ ይገኛል  " ሲል ገልጸዋል። " ዜጎቻችን ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ እስከ 60,000 ብር የሚጠየቁበት፣ ከቪዛና ከፓስፓርት እድሳት እያንዳንዱ አገልግሎት ጠያቂ $100 ዶላር ላልታወቀ ግለሰብ ወይም ተቋም የሚከፍልበት አሠራር ዛሬም ስላለ በሥራ ላይ ያለው የኦንላይን ሲስተም scrap ተደርጎ በአዲስ መተካት ይኖርበታል። " ብለዋል። ኦንላይን የቪዛ ጥያቄ አሁንም ሁለት ሦስት ጊዜ ካልተከፈለበት መልስ እንደማይሰጥ ይታወቃል ሲሉም አክለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ፤ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ፤ ከክልል እስከ ፌዴራል ያሉት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥብቅ መፈተሽ አለባቸው ብለዋል። " ካሉን ቁልፍ የደህነት ተቋማት መካከል የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ መ/ቤት ምን ዓይነት ውርደት/ውድቀት ውስጥ እንደከተተን አይተናል። " ያሉት አምባሳደሩ " ተቋሙ ብቻውን ለዚህ አልበቃም፤ የባሰም እንዳለ ምንም ጥርጥር የለውም፣ በየዕለቱ የምናየውና የምንሰማው ጉዳይ ስለሆነ። " ሲሉ ገልጸዋል። " ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ በሕጋዊ መንገድ ለማደስ ሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ የሚጠየቅበት አገር ውስጥ መሆናችንን ስናስብ እጅግ በጣም እንደነግጣለን "ም ብለዋል። " መንግሥት ብዙ ቅድሚያ የሚሰጣቸው (Priorities) ቢኖሩትም የሥልጣን ብልግናና የአስተዳደር በደሎች፣ በተለይም ሌብነት አሁን ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ጉዳዮች መካከል መሆን ይኖርባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል። በዚህም ኢሚግሬሽን ብቻውን እንዳልበሰበሰ ታውቆ ከክልል እስከ ፌዴራል ያሉት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥብቅ መፈተሽ አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል።
Show all...
👍 4 1
#ብሔራዊ_ፈተና ባለፉት ሁለት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት ግን እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው። ምን የተቀረ ነገር ኖሮ ነው ? የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑን በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ማብራሪያ ሰጥታዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦ " የፈተናው ክብደ እና ቅለት ከሆነ ምንም የተቀየረ ነገር የለም። የፈተና አሰጣጥ እና ዝግጅት ሂደት አለ፤ እራሱን የቻለ ሳይንስ አለው በጣም እንዳይከብድም በጣም እንዳይቀልም። እስከ ዛሬ ሲሰራ ከነበረው ምንም የተለየ ነገር የለም። የተለየው ፈተና አሰጣጡ ነው። ፈተና አሰጣጡ ያመጣው ለውጥ ምንድነው ከተባለ ፤ ከዚህ በፊት ፈተናዎች በየትምህርት ቤት ነው የሚሰጡት ፈተና መታተም ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ፣ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ፈተናዎቹ ይሰረቃሉ። ፈተና ሲሰረቅ የነበረው በተደራጀ መልክ ነው በክልሎች ፈታኞች በየክልሉ ሲሄዱ ትልቅ ግብዣ ተደርጎ ጉቦ ተሰጥቷቸው ተማሪዎቹ እንዲኮራረጁ ይደረጋል። ውጤቱ ትርጉም ያለው አልነበረም። እኔ ትምህርት ሚኒስቴር የመጣሁ ጊዜ በሁለተኛው ሳምንት ፈተና ሰጥተን ነበር በድሮው አሰጣት ፎርማት ያኔ ነው የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ ነው ብለን ፖሊሲ ያደረግነው ፣በወቅቱ ፈተና አሰጣጡን አልቀየርንም ነበር ያኔ ያለፈው 48% ነው። አንዳንድ ክልሎች 70-80 በመቶ አሳልፈዋል። በምንም አይነት የተማሪዎቹ ችሎታና ብቃት አይደለም። ... መሰረቅ መኮረጁን ለማወቅ ዳታውን ከተታትሎ ማግኘት ይቻላል፤ ግልፅ ነው። ፈተናው እራሱ የተማሪዎች ችሎታና ብቃት መለኪያ አልነበረም። ያንን ነው የቀየርነው። ከምንም በፊት የሰራነው በተማሪዎች ጭንቅላት ውስጥ በስርቆት፣ በማጭበርበር  ፣ ሌላ ሰው በማስፈተን ፣ በመኮረጅ የሚገኝ ትምህርት የለም የሚል ነው። ይሄን አውቀው እንደ ችሎታቸው እንዲያጠኑ ነው ያደረግነው። የዛ ውጤት፣ እንደ ሀገር ያለንበትን ልክ ነው ያሳወቀን። በዚህም ይሄ ነው የትምህርት ስርዓቱ ካልን በኃላ ሪፎርሞችን በተግባር አውለን አንድ ትውልድ ቢበላሽብን ቀጣዩን እንዴት እናድናለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው። " እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ በ2014 እና በ2015 በድምሩ 1,741,619 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውስደዋል። ከነዚህ ውስጥ ያለፉት በድምሩ 57,301 ተፈታኞች ናቸው። በዚህ ልክ ተፈታኝ ተማሪዎች መውደቃቸው ዜጎችን ያስደነገጠ ቢሆንም ከነዚህ ተማሪዎች በፊትም ፈተናው አሰጣጡ በዚህ መንገድ ቢሆን ውጤቱ ከዚህ እንደማይለይና የትምህርት ስርዓቱ ውድቀት ከታች ጀምሮ የመጣ እንደሆነ የሚገልጹ በርካቶች ናቸው። ለዚህ ውድቀት ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ ኃላፊነት እንዳለበትና ተማሪዎቹን ከሚያስተምሯቸው መምህራን ብቃት አንስቶ ፣ የትምህርት ቤቶች የጥራት ጉዳይ፣ የግብዓት አቅርቦት ሁሉ ሊፈተሽ የሚገባው እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑ ይነሳል።
Show all...
👍 11 2👏 1
" የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ አይቻልም "- አዲስ አበባ ፖሊስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ለ #ኤፍቢሲ በሰጠው ቃል ፤ የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ በፍጹም የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል። ፖሊስ ምን አለ ? - ህብረተሰቡ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ የተከለከሉ ነገሮችን በፍጹም መያዝ አይገባውም። ለሚኖሩ ፍተሻዎችም መተባበር አለበት። - በየአካባቢው በሚደመሩ ደመራዎች አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። - ከዚህ በፊት ደመራ ተደምሮባቸው የማያውቁ ቦታዎች #የጸብ_መነሻ እንዳይሆኑ የድሮዎቹን መጠቀም ይገባል። - ርችት መተኮስ በፍጹም ክልል ነው። ክልከላው የተደረገው ርችትን ሽፋን በማድረግ ህገወጦች ህገወጥ የጦር መሳሪያቸውን የሚሞክሩበት ጊዜ በመሆኑ ነው። ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ ሆነ ተቋም በህግ አግባብ እርምጃ ይወሰድበታል።
Show all...
👍 7👎 2
#Update ኢትዮ ቴሌኮም 630 ሺ ደንበኞቹ ዛሬ ይፋ ያደረገውን የ5G ኔትወርኩን መጠቀም ይችላሉ ብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ እንዲሁም በአዳማ ከተሞ በሙከራ ደረጃ ሲያቀርብ ቆይቶ ዛሬ በይፋ በአዲስ አበባ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል። ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከው በአዲስ አበባ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ነበር። በቀጣይም በሙከራ ደረጃ በአዳማ ከተማ አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል። ይህ የ5G ኔትዎርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ተደራሽነቱን አስፍቶ ለተጠቃሚዎች መቅረቡን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በነበረው ይፋዊ የማብሰሪያ መድረክ ላይ ተናግረዋል። እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገለጻ በኢትዮጵያ ይህንን አገልግሎት በአዲስ አበባ 145 ሳይቶች ላይ የ5G ኔትዎርክ ማስፋፊያ የተደረገ ሲሆን 630 ሺ ደንበኞቹ ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም የሚያስችል ቀፎ (Device) መኖሩን አስታውቀዋል። ይህ አገልግሎት ከተዘረጋባቸው ቦታዎች መካከል ከመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ኤርፖርት፤ ከመስቀል አደባባይ መገናኛ CMC እንዲሁም ወደ ሰሚት የሚወስደው መንገድ፤ ከመስቀል አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ድረስ፤ ከመስቀል አደባባይ ሜክሲኮ ሳር ቤት እንዲሁም ልደታ ከመስቀል አደባባይ ለገሀር ቸርቸል ጎዳና ይህ መሰረተ ልማት የተዘረጋላቸው አከባቢዎች ናቸው ተብሏል። ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በመግለጫቸው ተቋሙ በቀን በአማካይ ወደ 2,087 GB የዳታ ትራፊክ መኖሩን የገለጹ ሲሆን ከዚህ ውስጥም የ4G አገልግሎቱ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ጠቁመዋል። በአለማችን ወደ 110  ሀገረት በአፍሪካ ደግሞ 16 ሀገራት ይህንን አገልግሎት የጀመሩ ሲሆን አሁን ላይ 1.3 ቢሊዮን ተጠቃሚዎችን የ5G ኔትዎርክ ተጠቃሚ መሆናቸው በመድረኩ ተገልጿል።
Show all...
9👍 4🥰 1
#ጅግጅጋ " እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ " - አባት በጅግጅጋ ከተማ የተደፈረችው ልጅ አባት ምን አሉ ? አባት ኡጋስ አረብ በጅግጅጋ ከተማ ወረዳ 13 ተብሎ በሚጠራው ቦታ ልጃቸው በራሳቸው ሰራተኞች ከተደፈረች በኃላ መገደሏን ገልጸዋል። ለቢቢሲ ሶማሊ ክፍል አባት ኡጋስ አረብ ፦ " እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ። እለኔ ልጅ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በዚህ መንገድ ሕይወታቸው ለጠፋ ሁሉ ፍትሕ እንዲሰፍን እጠይቃለሁ። በወቅቱ መኝታ ቤቴ ውስጥ ተኝቼ ነበር። ቤት ውስጥም ከእኔ ውጭ ትልልቅ ሰዎች አልነበሩም። ልጄ ጋር ሄጄ ሳያት እየተነፈሰች አልነበረም ደረቷንም በመጫን እንድትተነፍስ ለማድረግ ሞከርኩ። አንገቷንም ሳየው ገመድ ተጠምጥሞባት ታንቃለች። ገመዱን ቆርጬ ወደ ሐኪም ወሰድኳት። ለሕክምና ወደ ሆስፒታል አፋፍሰን ብንወስዳትም ሕይወቷ አልፏል። በሞባይል ጥገና ሱቄ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ አራቱ ሠራተኞቼ በድርጊቱ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። አንደኛው ሠራተኛዬ ጠፍቷል። " ሲሉ ተናግረዋል። Via BBC Somali
Show all...
👍 7 2😢 1
#ኢትዮጵያ " ደም አፋሳሽ ግጭቶች በአስቸኳይ ይቁሙ " በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚታዩ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በአስቸኳይ ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲቆሙ ጥሪ ቀረበ። ይህን ጥሪ ያቀረበው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነው። ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች በንግግርና በምክክር መፍታት ሲገባ በተለያዩ አካባቢዎች እና በተለያዩ ወገኖች እየተወሰዱ ያሉ የኃይል እርምጃዎች የሀገራችን ኢትዮጵያን ደህንነትና ህልውና በመፈታተን ላይ መጥተዋል ሲል አሳውቋል። ኮሚሽኑ " የተቋቋምኩበትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረኩ ባለሁበት በዚህ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየታዩ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች ሥራዬን አዳጋች እያደረጉት ይገኛሉ " ብሏል። የኮሚሽኑ ምክር ቤት ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ/ም ባደረገው ልዩ ስብሰባ በመላው ሀገራችን የሚታዩ ግጭቶች በአስቸኳይ ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ ቆመው የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ አሉን የሚሏቸውን ልዩነቶች ወይም ጥያቄዎች በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በምክክር እንዲፈቱ አስቸኳይ ሀገራዊ ጥሪ አቅርቧል። ለዚህም ተግባራዊነት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለድርሻ አካላትን በማቀራረብ፣ የልዩነት አጀንዳዎችን ሰብስቦ ለማወያየትና ለማመካከር አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑን ያ አሳውቋል። (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
Show all...
👍 9 8😁 1
#Amhara በአማራ ክልል የተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት በከፍተኛ ጥንቃቄ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲገኝለት 8 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት " የሰላም እና ዘላቂ መፍትሄ ጥሪ " መግለጫ አቀረቡ። ጥሪውን ያቀረቡት ፦ 👉 የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)  👉 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል  👉 የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር  👉 የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት  👉 አዲስ ፓወርሀውስ  👉 የኢትዮጵያ ሴቶችና ሕፃናት ማኅበራት ኅብረት  👉 የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች  👉 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት  👉 ሴታዊት ንቅናቄ ናቸው። ድርጅቶቹ በአማራ ክልል ውስጥ የተከሰተው ግጭት እጅግ አሳስቦናል ብለዋል። በመሆኑም  የሚመለከታቸው አካላት፦ - ግጭቶች በሰላማዊ ዘዴዎች የሚፈቱባቸውን መንገዶች ለማግኘት የሲቪል ማኅበራት ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የእምነት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኃንና የአገር ሽማግሌዎች የተከሰተው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የበኩላቸውን ግፊት እንዲያደርጉ ፤ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተጀመሩ የሰላም ጥረቶችና ሥምምነቶች በአማራ ክልልም በሚንቀሳቀሱ ወገኖች እና በፌዴራሉና የክልሉ መንግሥታት መካከል መደረግ የሚችልበት ዕድል እንዲፈለግ ፤ - ትጥቅን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች በሰብዓዊ መብቶች እና በሰብዓዊ ሕግጋት (humanitarian laws) እንዲመሩ እና የንፁኃን ደኅንነት እንዲጠበቅ፤ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች፣ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ እና ሌሎችም ጉዳቶች በክልሉ እንዳይፈፀሙ ከፍተኛ የመከላከል ሥራዎች እንዲከናወኑና የተጠያቂነት ስርዓት እንዲዘረጋ ፤ - በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ወቅት የፀጥታ አካላት ያልተመጣጠነ ኃይል እንዳይጠቀሙ ፣ ብሔርን መሠረት ያደረጉ ማግለሎች እና ጥቃቶች እንዳይስፋፉ እና የጅምላ እስሮች (indiscriminate mass arrests) እንዳይከናወኑ ፤ - የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ብዙኃን መገናኛዎች ግጭት አገናዛቢ አዘጋገብን እንዲተገብሩ፣ የሐሰተኛ እና የተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እንዲገቱ፣ እንዲሁም ሐቁን የሚያንፀባርቁ መረጃዎችን ብቻ ለዜጎች በማድረስ ከግጭት አባባሽነት እንዲቆጠቡ ፤ - ዝርዝር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ለማስፈጸም የሚወጡ መመሪያዎችና ደንቦች ለዜጎች ተዳራሽ በሆኑ አማራጮች በተከታታይ እንዲደርሱ ጥሪ አቅርበዋል። (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
Show all...
👍 8 2