cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢየሱስን እንተንፍስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን

ኢየሱስ በቂ ነው ►ኢየሱስ ብቻ ይሰበክ ►ብቻውን ይወራ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ድንቅ ግጥም ➥ ከእንግዲህ አትጠይቀኝ ✋✋ ገጣሚ ➥ ሳሚ #END_TIME_REVIVAL🔥🔥🔥🔥🔥 ▷ @ItsTime4Revival ◁ ▷ @ItsTime4Revival ◁ ▷ Join Us◁ #REVIVAL_IS_NEAR🌨🌨🌨
Show all...
... ሪቫይቫል ወይ ሞት 🙏🙏 🚦ሪቫይቫል ያስፈልገናል ስንል ወደ ጨለማ የምናደርገውን ጉዞ እናቁም ማለታችን ነው ። 🚦እግዚአብሔር ሪቫይቫልን እንዲያመጣልን የምንለምነው ቤተክርስቲያን በዚህ ዘመን ተልዕኮዋን ዘንግታ ማብቂያው በማይታወቅ እንቅልፍ ውስጥ ስለገባች ነው ። 🚦ሪቫይቫል የሚያስፈልገን ያልዳኑ ብዙ ነፍሳት ስላሉ ብቻ ሳይሆን ክርስቲያኖች እራሳቸው መዳናቸው እስኪያጠራጥር ድረስ ወደ መንፈሳዊ ውድቀት እያመሩ ስለሆኑም ጭምር ነው ። በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ከመፅሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ተንሸራታ መንገዷን የጥፋት ማድረግ የመረጠች ይመስላል ። 🚦የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ በዚህ ዘመን የሚያስፈልገው ከ ሪቫይቫል ውጪ ቤተክርስቲያን ለገባችበት ውድቀት ሌላ መፍትሄ ስለሌለ ነው ። እግዚአብሔር ሪቫይቫል የሚያመጣው እኛን ለማስገረም እና ለማስደመም አይደለም ፣ ከመንፈሳዊ ድንዛዜ አውጥቶን ታላቁን ተልዕኮ እንድናስፈፅም እንጂ ። 🚦ወይ ሪቫይቫል መጥቶ ወደ መንፈሳዊ ከፍታ እንወጣለን ወይ አሁን የያዘን ድንዛዜ ወደ ሲዖል ይዞን ይወርዳል ። ሪቫይቫል የቅንጦት ጉዳይ አይደለም ፣ ወይ ሪቫይቫል ወይ ሞት !! #END_TIME_REVIVAL🔥🔥🔥🔥🔥 ▷ @ItsTime4Revival ◁ ▷ @ItsTime4Revival ◁ ▷ Join Us◁ #REVIVAL_IS_NEAR🌨🌨🌨
Show all...
... ፖለቲካ ያለቦታው በዚህ #ዘመን በእግዚአብሔር ስም የሚነግዱ የእግዚአብሔርን ቤት እንደራሳቸው ኩባንያ የቆጠሩ እና የእግዜር #ፖሊሶች ነን ብለው በስርዓት ስም የራሳቸውን ፍላጎት የሚያስፈፅሙ #ወንበዴዎች ተበራክተዋል ። ቤተክርስቲያንን ከመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ እና ከእግዚአብሔር ክብር #ያፋቱ ለሚቀጥለው ትውልድ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የማይገለጥበትን ደረቅ ክርስትና እና የእግዚአብሔርን ክብር ማያመጣልንን ባዶ #ስርዓት ሊያወርሱ የቆረጡ አንዳንድ የዘመኑ #ፈሪሳውያን በአደገኛ እና ክፉ ዘመን የተወለደውን የ 21ኛውን ክፍለ ዘመን #ትውልድ ዋጋ እያስከፈሉት ነው ። ከዚህም በተጨማሪ በእነዚህ የእግዜር ፓሊስ ነን ባይ ፈሪሳውያን ስርዓት የቁም #እስረኛ እና የህሊና እስረኛ የሆኑ አራጋቢዎች በ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ንግድ ያስመረራቸው ወጣቶች እና ታዳጊዎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ #ለማደናቀፍ የሚሰሩትን ስራ እንደ ፅድቅ ቆጥረው በእግዚአብሔር ስም ከሚካሄደው ንግድ ተካፋይ ሆነው ተገኝተዋል ። የሚያሳዝነው ደግሞ እንደ እነዚያ ወጣቶች እና ታዳጊዎች ሆነውም ምንም ችግር እንደሌለ እና ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነ የሚያወሩ መኖራቸው ነው ። ከዚህም በላይ የሚያስተዛዝብ ነገር ቢኖር ከ ቤተክርስቲያን በዚህ ነገር ምክንያት ተሰደው የወጡም ሆነ በራሳቸው ስርዓቱን ተቃውመው የወጡትን እንደ #ሰይጣን መልዕክተኞች መቁጠር መጀመራቸው እና እራሳቸውን መሰረት እንደያዙ በዓለት ላይ እንደ ተተከሉ መቁጠራቸው ነው ። በዚህ ዘመን ግንዱ ክርስቶስ መሆኑ ቀርቶ ቤተክርስቲያን ሆናለች ገበሬው አብ መሆኑ ቀርቶ መሪዎች ሆነዋል በ ፈሪሳውያን #ቀመር መሠረት ማለት ነው ። ከቤተክርስቲያን የወጡ ወጣቶች ከግንዱ ተቆርጠው እንደተጣሉ ይቆጠራሉ ፣ ከአባልነት የተሰረዙ ከሕይወት መዝገብ እንደተሰረዙ ይቆጠራል ። የእግዚአብሔርን ድምፅ እየሰማ ቤተክርስቲያንን የሚመራ እንደ #ሙሴ ያለ መሪ ጠፍቶ እንጂ ወጣቱ ዓመፀኛ ሆኖ አይደለም ። የተቀባ እና የፀጋ ስጦታ የተቀበለ ሁሉ ዓመፀኛ እና ትዕቢተኛ ተደርጎ እስኪቆጠር ድረስ ብዙ ወጣቶች ሲወጡ ታዝበን ወይ ጉድ ብለናል ፣ ግን እስከመቼ ?? እግዚአብሔር ያያል ፣ እግዚአብሔር ልባችንን ያያል ፣ ሊባርኩን እየተገባ እንደ ሚያሟርቱብን አይሆንም ። እግዚአብሔር ይፈርዳል ፣ ይሄን ትውልድ ለጥፋት አሳልፎ አይሰጥም ። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እየተሰደዳችሁ እየተሰደባችሁ ያላችሁ ወጣቶች ለእናንተ ትልቅ ክብር አለኝ ። ጊዜው ደርሷል እነ አስጢን ይወርዳሉ እነ አስቴር ይነግሳሉ ። ✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊ ወይ Theocracy ወይ Democracy ✋✋✋✋✋✋✋✋✋✋✋✋
Show all...
🙏🙏 ታላቅ የ ሪቫይቫል ጥሪ 🙏🙏 🚨የመመለስ እና የመታደስ ጊዜ ለ ክርስቲያኖች 🚨🚨🚨 "፤ እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።" የዮሐንስ ራእይ 2: 5 በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ ክርስቲያኖች ሁላችሁ ይህንን ድምፅ ስሙ 🎤🎤 #ሪቫይቫል ያስፈልገናል 🌧🌧 ጊዜውም ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ጉብኝት ጊዜ ነው 🔥🔥 የእግዚአብሔር #ክብር የሚገለጥበት 🌧🌧🌧 ከለመድነው ነገር እንውጣ ወደ ክብሩ ሙላት እንገስግስ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ እየመጣ ያለ ከባድ ደመና አለ !! 🌧🌧 ሰይጣንም ከእኛ ቀድሞ ነቅቷል ፣ ስለዚህም እንዳንነቃ በተለያዩ ነገሮች ሊያዘናጋን እየሞከረ ይገኛል ። እጅ እየተጠቋቆምን እጁ መጥታ ሳትነካን እንዳታልፍ ። በወሬ ተጠምደን እስከ መቼ ፣ መንፈስ ቅዱስ ይስራ 🔥🔥 ክብሩ ይገለጥ 🌧🌧 ባዶ ሆነን የሰው #ስርዓት ብቻ እያከናወንን የፕሮግራም ቅደም ተከተል ለማስጠበቅ ብቻ እየተሯሯጥን 🏃‍♂🏃‍♂ እስከመቼ 😔😔 #እንንቃ ፣ የእግዚአብሔር ክብር ካልተገለጠ የእኛ መሰብሰብ ብቻውን ዋጋ የለውም 😔😔 የሰዎች ችሎታ ብቻ እያየን የእግዚአብሔር እጅ ሳናይ ነፍሳት ሳይድኑ ሰዎች ከአጋንንት እስራት ሳይፈቱ በሽተኞች ሳይፈወሱ የሰዎች ሕይወት በቃሉ ሳይቀየር ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ሳይጠመቁ ስንት አመት ባዶ ሆነን ገብተን ባዶ ሆነን ወጣን 😒😒 ደረቅ ሆነን ገብተን ደረቅ ሆነን ወጣን ፣ #የሚመስል ነገር አያስፈልገንም ☹️☹️ እውነተኛው የመንፈሱ እሳት በ ቤተክርስቲያን ውስጥ መለኮስ አለበት 🔥🔥🔥 በዚህ ክረምት አንድ የፀሎት እንቅስቃሴ በመላው ኢትዮጵያ #መቀጣጠል 🔥🔥 አለበት ። ሌሎች የፀሎት ርዕሶቻችን ለጊዜው ይቀመጡ ፣ የትም አይሄዱም ። ሪቫይቫል የቅንጦት ጉዳይ አይደለም ✊✊ የሞት እና የሕይወት ጉዳይ እንጂ ። ሁላችንም በዚህ ክረምት ስለ ሪቫይቫል አጥብቀን እንፀልይ ። ቢያንስ ለ #አንድ ሰዓት በዚህ ርዕስ እንፀልይ 🙏🙏 #ለመሪዎች መልዕክት አለኝ 🎤🎤 ለመሪዎች ነው ያልኩት የሚሰማቸው የሚከተላቸው የሚቀበላቸው ትውልድ ላላቸው መሪዎች ይሄ መልዕክት ይድረስልኝ ። የምትመሩትን መንጋ ወደዚህ አስደናቂ የመንፈስ ቅዱስ ሪቫይቫል ይዛችሁ በመግባት አዲስ ታሪክ ስሩ ። መግደርደርም መንደርደርም አያስፈልግም ያለነው አዲስ ኪዳን ላይ ለዚያውም በመጨረሻው ዘመን ላይ ነው ያለነው ። በብዙ የእግዚአብሔር ሰዎች ትንቢት የተነገረለት በመፅሐፍ ቅዱስም የተፃፈ የመጨረሻው ዘመን ሪቫይቫል #ሊገለጥ ጊዜው ደርሷል ። "፤ ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።" የማቴዎስ ወንጌል 24: 14 "፤ ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤" ትንቢተ ኢዮኤል 2: 28 #END_TIME_REVIVAL🔥🔥🔥🔥🔥 ▷ @ItsTime4Revival ◁ ▷ @ItsTime4Revival ◁ ▷ Join Us◁ #REVIVAL_IS_NEAR🌨🌨🌨
Show all...
ተፅዕኖ መፍጠር ➥ ክፍል አንድ ምን ያህል ሰዎች ይህን ነገር ያውቁታል 🤔🤔 ተፅዕኖ ምንድነው ?? ሁሌም የማይቀሩ #ሦስት ጥያቄዎች አሉ ምንድናቸው ?? ይሄንን ትምህርት #ማዳመጥ ከብዙ አደጋ☠ ያድናችኋል !! #END_TIME_REVIVAL🔥🔥🔥🔥🔥 ▷ @ItsTime4Revival ◁ ▷ @ItsTime4Revival ◁ ▷ Join Us◁ #REVIVAL_IS_NEAR🌨🌨🌨
Show all...
" በመላው ኢትዮጵያ #ኤሌክትሪክ💡 እንዲዳረስ የግድ በየወረዳው ግድብ መሰራት የለበትም ፣ አንድ ሁለት ግድብ በደንብ #ከተሞላ 🌧🌧 አገሪቱ #ታበራለች 💥💥 እንደዚሁ በኢትዮጵያ ላይ ከባድ #ሪቫይቫል እንዲነሳ አንተ..." 🔥🔥 ይሄንን መልዕክት ከሰማህ በኋላ ታሪክህ #ይቀየራል 🌧🌧 #END_TIME_REVIVAL🔥🔥🔥🔥🔥 ▷ @ItsTime4Revival ◁ ▷ @ItsTime4Revival ◁ ▷ Join Us◁ #REVIVAL_IS_NEAR🌨🌨🌨
Show all...
💥💥💥ልዩ የክረምት የፀሎት ጊዜ 💥💥💥 ከ ሐምሌ 1 - ነሀሴ 30 ለ #60 ቀናት የሚቆይ የእግዚአብሔርን #ክብር መገለጥ የመጨረሻውን ዘመን የመንፈስ ቅዱስ #ሪቫይቫል የምትናፍቁ ሁላችሁ ይህንን እንቅስቃሴ ተቀላቀሉ 🙌🙌 #በፀሎት እየመጣ ላለው አስደናቂ ሪቫይቫል እንዘጋጅ 🙏🙏🙏🧎‍♂🧎🧎🧎🧎‍♀🧎‍♀🧎‍♀🧎
Show all...