cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መልካም ምሳሌነት አላማው ለክርስቶስ ተልዕኮ

መልካም ምሳሌነት አላማው ለክርስቶስ ተልዕኮ ይህ channel ለመልካም ስራ የሚውል በመልካም አላማ የተቀናጀ ነው

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
138Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
Repost from N/a
እንዲሁ በፀጋ እንዲሁ በነፃ https://youtube.com/watch?v=X1orFShLcmE&feature=share
Show all...
✍️አንድ ክርስቲያን በክርስቶስ አምኖ ከዳነ በኃላ በምድር ላይ በዋጋ የተገዛ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ሲሆን የሰማይን ሕይወት እንዲገልጥ እና የክርስቶስ የጽድቁ እና የቅድስናው መገለጫ ለመሆን ተጠርቷል። ነገር ግን በዚህ ደካማ ስጋ ምድር ላይ ሲኖር መድከሙ የማይቀር ነው በሚደክምበትም ጊዜ በሕብረት ንስሃ በድካሙ ሊራራለት ከሚችለው እና ጸጋና ምህረትን ከሚሰጠው ከሊቀካህኑ ከኢየሱስ ጋር መጨረስ ይችላል። ✍️ነገር ግን አንድ ክርስቲያን ከሊቀካህኑ ከኢየሱስ ጋር በንስሃ መጨረስ አቅቶት ቤተመቅደስነቱን ረስቶ #በተገለጠ_ሃጥያት ውስጥ ቢገኝ እና የጌታውንም ስም ቢያሰድብ #በስጋው ጌታ #ይገስጸዋል ፍርድንም ይቀበላል። ✍️
Show all...
የአዲስ ኪዳን መካከለኛ የአዲስ ኪዳን መክከለኛ እንድ እርሱ ሌላ የሌለ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። " የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።" (ወደ ዕብራውያን 12፥24) " አሁን ግን በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ መካከለኛ እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቶአል።" (ወደ ዕብራውያን 8፥6) ሰው እና ሰው ቢጣላ በመካከል የሚገቡት አስታራቂዎች ከአንድ በላይ ቢሆኑ ምንም አይደለም። ነገር ግን ጠቡ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሲሆን ከአንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር በመካከል የሚገባና የሚያስታርቅ ሌላ መካከለኛ (አማላጅ) የለም። እግዚአብሔር አንድ ባይሆን ኖሮ ከምርጫው ብዛት የተነሳ የሰው ልጆች ግራ ሊጋቡ ይችሉ እንደነበር : እንደዚሁ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ባይሆን ወደ እግዜአብሔር የመቅረቢያው መንገድ ዝብርቅርቁ ይወጣ ነበር። በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩትን የመካከለኛነት አገልግሎት ሁሉ አጠቃሎ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ እንዲሆን የተመረቀውና የተሾመው አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ስለዚህ እርሱ ሙሴ አስቀድሞ እግዚአብሔር እንደ እኔ ያለ ነብይ ያስነሳላችኋል ያለው ነብይ ነው።(ዘዳ18፥15-17፣ሐዋ 3፥20-27፣ሉቃ13፤33) እንደ መልከ ጼድቅ የዘላለም ካህን ነው።(ዕብ 5፥6፣ዕብ3፥5፣ዕብ 7፥26፣ዕብ4÷10 የዘላለም ንጉስ ነው። (ሚክ 5፥2፣መዝ 2፡6፣ኢሳ 9፥6-7፣ሉቃ19፥32፣ራዕ 20፥4-5) የሰብአዊ መጠሪያው ስሙ የሆነው "ኢየሱስ" የሚለው ቃል እና መለኮታዊ ስሙ "ክርስቶስ"የሚለው ቃል ሁለቱም መካከለኛነቱን የሚያንጸባርቁ ናቸው። መለኮታዊነቱን የሚገልጸው "ከክርስቶስ" የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን የቃሉ መሠረታዊ አመጣጥ ግን በብሉይ " መሲህ " ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል ነው ። መሲህ (ክርስቶስ)ማለት የተቀባ ማለት ነው።በብሉይ የሚቀቡት ነቢያት፣ካህናትና ነገስታት እንደነበሩ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ሦስቱንም ማዕከላዊ አገልግሎት አጠቃሎ ለማሟላት የተቀባ(የተመረጠ) በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ብቸኛው መካከለኛ ነው።"ኢየሱስ " ማለት "እዳኝ" ማለት ነው። ኃጢአተኛን ከኃጥያት ዕዳና ፍርድ ነጻ የሚያደርገውና የሚያድነው ከእርሱ በቀር ሌላ ማንም የለም።
Show all...
ሽቶዉን ዉድ ያደረገዉ የብልቃጡ ዲዛይን አይደለም ዉስጡ ያለዉ የከበረዉ መአዛ ነዉ። እህቶቼ እኔንና /እናንተን ዉድና እርካሽ የሚያደርገን ሰዉነታችን አለባበሳችን እስታይላችን አይደለም በሰዉነታችን ዉስጥ ያለዉ የከበረዉ የእግዚአብሔር መዝገብ ነዉ። የብልቃጡ አድናቂዎችአንሁን ማለትም (የቁንጅናን የአካልን) እኔንና እናንተን ዉድ ያደረገን ግን የከበረዉ የእግዚአብሔር ማንነትና ሀሳብ ነዉ። ❤️🤗 ሰዎች የሚፈልጉትም አካላችንን አይደለም በዉስጣችን ያለዉን ነዉ። ያቺ ሴት ይዛ የመጣችዉ ሽቶ ስሰብረዉ በወጥ በሌላም ነገር የከረፋዉን ቤት መአዛ ሞላዉ። እየቀፈፈ ያለዉን የሀገሬን የቤተክርስቲያንም የብዙ ወጣት ህይወት መለወጥ የሚችለዉ ይሔ ስጋችን አይደለም እዛ ዉስጥ ያለዉን የከበረዉ የእግዚአብሔር ዉድ እቃ ነዉ ። ❤️🤗
Show all...
ነጭ ቬሎ ለብሳ ያጌጠች ሙሽሪት ጭቃ ውስጥ ገብታ ብትገኝ። ከጭቃው እንድትወጣ ከተፈለገ በትክክል ማወቅ ያለባት ነገር ምንድን ነው? 👉ጭቃ ውስጥ እንዳለች? 👉ጭቃው በጣም አስቀያሚ እንደሆነ? በእርግጥ እነዚህን ነገሮች ብታውቅ ይጠቅማት ይሆናል። ቢሆንም ግን ከጭቅው እንድትወጣ ማወቅ ያለባት ዋናው ነገር- 👉የለበሰችው ንፁህ፣ ነጭ፣ ውድ እና ጭቃ #የማይመጥነው ልብስ መሆኑን ነው። የልብሱን ንፅህና እና ዋጋ ስትረዳ የት መዋል እንዳለባት ይገባታል። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ከሐጢአት ልምምድ ለመውጣት መፍትሄው በየቀኑ ስለሰራሀው ኃጢአት ዝርዝር ቁጭ ብለህ ማሰብ ሳይሆን አንተ ያለህን #ክብር ማወቅ ነው። #የንጉስ ልጅ መሆኑን ያልተረዳ የንጉስ ልጅ ቆሻሻ ሰፈር ቢውል፣ ለምኖ ቢበላ አይገርምም❗ በየመድረኩ አሁን ያለንበት አዘቅት ይነገረናል። ግን ምን እንደለበስን አይነገረንም። አቤት! በክርስቶስ የለበስነውን ክብር ብናውቅ! ..እንኳን ኃጢአት፡ የምድር ክብሯ እራሱ አይመጥነንም እኮ! 🙏ጌታ አይኖቻችንን ይክፈትልን🙏
Show all...
----------- (ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ 4) ---------- 4፤ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ 5፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። 6፤ ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ። 7፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ። --------------- t.me/mizan_amann join join
Show all...
Kabata Tcoj: 🔥#ከሞት_በኃላ_ምርጫ_የለም🔥 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 🔆#የዘላለም_ህይወትን እንዳገኛችሁ በምድር ሳላችሁ ነው ማመን ያለባችሁ፤ ከሞት በኃላ የሚደረግ አስተያየት የለም፡፡ ለምን ድነው ዛሬ ብትሞቱ የት ትገኛላችሁ ስትባሉ ወይ ሲዖል ወይ ደግሞ ገነት፣ አንዳንዶቻቹ ደግሞ ጌታ ነው የሚያውቀው ትላላችሁ እርሱማ ድሮም ሁሉን አዋቂ አምላክ ነው፡፡ 🔆#እንዲህ_የሚል መልስ ያላችሁ እምነት የሌላችሁ ሁኖ ይሁን! ብየ ስጠይቅ አዎ የሚል መልስ አገኛለው፡፡#ዘላለምን ለመኖር ተራራ መውጣት አያስፈልግም ፣ ለብቻችሁ ድንጋይ ውስጥ መኖር አይጠበቅባችሁም! ለምን መሰላችሁ፣ ዘላለምን በራሳችሁ ሥራ ልታገኙት ስለማትችሉ፡፡ 🔆#መልካም_ስራ ሰርታችሁ ዘላለምን ልታገኙት አትችሉም፡፡ ነገር ግን አምናችሁ ልታገኙት ትችላላችሁ፤ እንደምትችሉም ቃሉይናገራል፤#እውነት_እውነት_እላችኋለሁ_በእኔ_የሚያምን_የዘላለም_ሕይወት_አለው።#ዮሐንስ ወንጌል 6፥47 #በቃ_እመኑ ተብላችዋል! ለምን እኔ ኃጢአተኛ ነኝ እንዲህ ሊሆን አይችልም ትላላችሁ! ለኃጢአታችሁ እኮ ዋጋ ተክፍሎ ነው ይሄ ውጤት የመጣው #የመስቀሉ_ውጤት_ነው 🔆#ቆይ_ሲዖል እንዳለ ያመናችሁት አይታችሁ ነው እንዴ❓እኔ አይቼ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጌታ በቃሉ አለ ስላለ ነው፡፡ እናንተም ቢሆን ቃሉን አምናችሁ ነው! እናታድያ ቃሉም እኮ #በእኔ_የሚያምን_የዘላለም_ህይወት_አለው_ይላል፡፡ 🌍#ከዚህ_ዓለም መቼ እንደምትለያዩ አታውቁም! ከሞታችሁ በኃላ ነፍሳችሁ የት እንደምትገባ አሁን ምን ያክል ታውቃላችሁ! የሚያሳዝነው ነገር ከሞታችሁ በኃላ ምንም ማሻሽያ የሚባል ነገር እንደሌለ አለማወቃችሁ ነው፡፡ ሰው ሀይማኖት ሊኖሮ ይችል ይሆናል ነገር ግን በሀይማኖቱ ሳየይሆን ዘላለምን የሚያገኘው በልጁ በክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ 🔆#ከሞታችሁ_በኃላ አይደለም የዘላለም ህይወት እንዳላቸችሁ የምታውቁት ፤ በምድር በህይወት ሳላችሁ ነው፡፡ ከሞታችሁ በኃላ እራሳችሁን ሲዖል ብታገኙ የሚሰሟችሁ መልአክት ቅዱሳን አይኖሩም፡፡ ኢየሱስም ቢሆን አይሰማችሁም፡፡ በዛን ሰዕተ የሚሰማችሁ ቢኖር በምድር ሳላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ እመኑ ስትባሉ አትመኑ እናንተ ኃጢአት አለባችሁ፣ የዘላለም ህይወት የምታገኙት በጾም በጾሎት ሥራ በመስራት ገዳም በመግባት ሕግን በመጠበቅ ነው ብሎ የሰበካችሁን የነበረውን ዳቢሎስ ብቻ ነው፡፡ #በዚያ_ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል #ማቴ 13፥50 🔆#ሰው_በክርስቶስ ኢየሱስ ሳያምን ቢሞት፡ ከሞተ በኃላ የትኛውን ያክል #ፍትሃት ቢደረግለት ምንም የሚለወጥ ታሪክ የለም፡፡ በምድር ሳለ ከጌታ ጋር #conect ሳያደርግ ከሞተ በኃላ የውስጥ ለውስጥ ሽግግር የሚባል ታሪክ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ነው፡፡ በምድር በህይወት ሳላችሁ ያመናችሁት ነው ከሞት በኃላ የምታዩት! እንጂ በስጋ ከተለያችሁ በኃላ የሚደረግ የሲዖልና የገነት ምርጫ የለም፡፡ 🔆#አሁን_ይሄን ቃል ከሰማችሁ ጀምሮ የሚያዋጣችሁን ጌታን ምረጡ፡፡ ዘላለምን ከኢየሱስ ውጪ ማንም ሊሰጣችሁ አይችልም፡፡ ምክንያቱም የሞተላችሁ እርሱ ብቻ ስለሆነ፡፡ የዘላለሙ ባለቤት መልአክት፣ ቅዱሳን ሳይሆኑ! #ኢየሱስ ነው፡፡ ኢየሱስ አለ፡ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚገባ የለም፡፡ 🔆#የዘላለም_ህይወት በፆም ፀሎት ፣ መልካም ስራን በመስራት፣ ሕግን በመጠበቅ ልታገኙት አትችሉም፡፡ መልካም ስራን መስራት በሰማይ ሽልማት ያስገኛል እንጂ ዘላለምን አያስገኝም፡፡ ለመዳን ሳይሆን መልካም ስራን መስራት ያለባቸሁ ስለዳናችሁ ነው፡፡ አለበለዚያ ትምክት ይሆንባችዋለል! በራሴ ሥራ ዳንኩ እያላችሁ በራስራችሁ መመካት ትጀምራላችሁ፣ ቃሉ ደግሞ እንዲህ ይላል #ትምክህት_እንግዲህ_ወዴት_ነው__እርሱ_ቀርቶአል፡፡#በየትኛው_ሕግ_ነው__በሥራ_ሕግ_ነውን_አይደለም_በእምነት_ሕግ_ነው_እንጂ። #ሮሜ 3፥27 🔆#አሁን_ለመዳን ሕጉ እምነት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ሰው በሕግ እንዲጸድቅ ተብሎ ነበር! ነገር ግን ሕግ ኃጢአትን የሚገልጥ ሁኖ ተገኘ እንጂ ሊያነጻ አልቻለም፡፡#ሰው_ያለ_ሕግ_ሥራ_በእምነት_እንዲጸድቅ_እንቆጥራለንና #ሮሜ 3፥28፡፡ ብዙ ሰዎች አሁን አንዴ ድነናል ሕግን ባንጠብቅም ምንም አንሆንም ብለው ያስባሉ! ለነዚህ ሰዎች ቃሉ እንዲህ ይላችዋል #እንግዲህ_ሕግን_በእምነት_እንሽራለን_አይደለም_ሕግን_እናጸናለን_እንጂ።#ሮሜ_3_31፡፡ ነገር ግን ሕግን የምጠብቀው ለመጽደቅ ሳይሆን ስለጸደቅን ነው፡፡ #አንብባችሁ_ዝም_አትበሉ_በGroup_ላይ_ላላመኑ_ጎደኞቻችሁ_Share_አድርጉላቸው፡፡ #ትውልድን_ከሲዖል_አብረን_እንታደግ፡፡🙏ተባረኩ!
Show all...
ሰላም ለሁላችሁ፦ ቅዱስ እስጢፋኖስ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በህዝብ ድንጋይ እየተደበደበ ሳለ ለጸሎት ተንበረከከ። ይህ ሁኔታ እንኳን ለመንበርከክ በስርዓት ለመሞትም ፋታ አይሰጠም ነበር። ግን ጌታው ፊት ምን ያህን በአክብሮት መጸለይ እንዳለበት እየሞተም አልረሳም። በአስቸጋሪ ሁኔታም ውስጥ እምላኩን በአክብሮት አከበረ። እኛ እየኖርን ምን ያህል ለክብሩ የሚገባ ስግደት እንሰጣለን? ስንቶቻችን ለጸሎት ከመቀመጫችን እንነሳለን? በሰላም የምኖነረው እኛ ለጌታ ሰዓት አጥሮን ምክንያት መደርደራችንን እስጢፋኖስ ቢሰማ ምን ይል ይሆን? እርሱ አምኖ ሲሞት አምኖ መኖር ምን ያህል እንደሚያስፈልገን ተረዳችሁ? እግዚአብሔርን ከወደድነው መቼም ቢሆን ለርሱ ጊዜ አለን። ለአምልኮ ጊዜ ያጣነው ሰዓት ስላጣን ሳይሆን ለርሱ ፍቅር ስላጣን ነው። ይህን ማንም እንዳይረሳ። ተሰብስበን ወደማይቀረው ዓለም መጠራታችን አይቀርም። ወደ ዘላለሙ ስፍራ መድረሳችን አይቀርም። ስለዚህ ቀን ሳለ ጌታችንን ማክበር ወደ ፍለጋው መመልከት እንጀምር። ማንም የማይሰራበት ሌሊት ይመጣልና። 🙏እባካችሁ ለሌሎች ያካፍሉት🙏
Show all...
ገናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!! ገናን ገና ያስባለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሃጥያት መስዋእትነት መወለዱ እንጂ ሌላ አይደለም። በዚህ ዘመን ግን ሰዎች በተለይም የክርስትናን እምነት በመከተል ላይ ያሉ ሰዎች እየረሱት ያለው እና ገናን ወደ ጌጣ ጌጥነት የቀየሩበት ድህረ ዘመናዊነት ዘመን ላይ ደርሰናል።ገና ዛፍ አይደለም፤ ገና ከዛፍ በተጠረበ መስቀል ላይ መስዋእት ለመሆን ኢየሱስ የተወለደበት ነው። ገና ዛፍ ላይ የሚንጠለጠል ጌጥ አይደለም ፤ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ የመስቀል ሥራ አጊጠን አለምን እንድንኮንን ስለእኛ በመስቀል ላይ ለመንጠልጥል በውልደት ሰው(እኛን) የሆነበት ነው። ገና የገና ዛፍ መብራት አይደለም፤ ገና እኛ በጨለማ(በኃጥያት) ስንኖር የነበርነውን የአለም ብርሃን ሆነን እንድናበራ ክርስቶስ ስል አለሙ ሁሉ ኃጥያት የአባቱ ቁጣ ነዶበት ብርሃን (ሕይወት) ሊፈነጥቅልን በግርግም ውስጥ የተወለደበት ነው። ገና በገና ዛፍ በጫፉ ላይ የሚሰቀል ኮከብ አይደለም፤ ገና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አለሙ ሁሉ በደል እና መተላለፍ በመስቀል መደሃኒት ለአለም ሆኖ ሰዎችን ለመፈወስ በቀራኒዮ ተራራ ጫፉ ላይ ተሰቅሎ ለማዳን የተወለደበት ነው። ገና በስጦታ ወረቀት ጠቅልለን የምንሰጠው ስጦታ አይደለም፤ ገና እግዚአብሔር አብ አንድያ ልጁን ለአለሙ መዳን የሰጠበት:ማለትም ኃጥያትን በጽድቅ፣ መርገምን በበረከት፣ ሞትን በዘላለም ሕይወት፣ሀዘንን በደስታ፣አመጽን በመታዘዝ፣ጥላቻ በፍቅር የተበረከተበት የጌታ ውልደት ነው። ስለዚህ ወገኖቼ አስተውሉ ድህረ-ዘመናዊነት ይሄንን ሊያስረሳን ቆርጦ ተነስቷልና በአጉል ስልጣኔ መሳይ ነገር :በክርስቶስ ወልደት እና ዓላማ ላይ የተነሳውን የሰውን ሃሳብ ልብ ልንለው ይገባል። "፤ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።         ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።" (ት.ኢሳይያስ 9፥6-7) እንሆኝ የገና ስጦታዬን ተቀበሉኝ። ለሌሎችም ሼር በማደረግ ስጦታዬን በማድረስ ገናን ያክብሩ። 👇👇
Show all...
ባህሪህን እወቅ በመንገድ ላይ ሲጓዝ የነበረ አንድ ሰውዬ መርዛማ የሆነ እባብ በእሳት ሲቃጠል ተመለከተና ከእሳቱ ውስጥ ሊያወጣው ወሰነ። ከእሳቱ ውስጥ ሊያወጣ ሲያነሳው እባቡ እጁ ላይ ነደፈው። ሰውዬው በድንጋጤ እባቡን ወረወረው እባቡም ተመልሶ እሳቱ ውስጥ ወደቀ። ሰውዬውም በድጋሚ ሁለት እንጨቶችን ተጠቅሞ ከእሳቱ አወጣው። እናም የእባቡ ሕይወት ተረፈ። ቆሞ ድርጊቱን ይመለከት የነበረ አንድ ሰው ወደ ሰውየው ቀርቦ "ይህ እባብ በመርዙ ነድፎህ ሳለ ድጋሚ ልታድነው የምትሞከረው ለምንድነው?" ብሎ ጠየቀው። ሰውየውም "የእባቡ ባህሪ መንደፍ ነው የእኔ ደሞ ማትረፍ ነው። ሁለታችንም ያለንን ነው ያንፀባረቅነው። ለሱ ክፉ ባህሪ ብዬ የኔን መልካም ባህሪ መለወጥ የለብኝም" ብሎ መለሰ። ክፉ ነገር በክፉ ሊመለስ አይገባም። መጥፎ ሰዎች በዙሪያህ ቢኖሩም፣ የቱንም ያህል ክፋት ቢሰሩብህ አንተ የራስህን መልካም ብህሪ አንፀባርቅ እንጂ በነሱ ውስጥ አትዋት።አንድ ቀን ከዚህ ስራቸው ታድናቸዋለህ። ሁል ጊዜም እራስህን ሁን!!!!
Show all...
📖 # God's_word 1. # It is milk: it nourishes and nourishes. (1 Peter 2: 2) 2. # Bread: You need to live. (Matthew 4: 4) 3. # It is honey: it tastes good. (Ps 19:10) 4. # It is a strong food: it strengthens. (Hebrews 5: 12-14) 5. # Gold: Your treasure. (Ps 19:10) 6. # Light: It guides you along the way. (Ps 119: 105) 7. # It is a medicine: it heals you. (Proverbs 4:22) 8. # It is a mirror: it shows you clearly. (James 1: 23-25) 9. # It is a hammer: it breaks. (Jeremiah 23:29) 10. # It is fire: it heats up. (Jeremiah 23:29) 11. # It's raining: it grows. (Isaiah 55: 10-11) 12. # He is your friend: He advises you. (Ps 119: 24) 13. # It is water: it purifies. (Isaiah 5:26) 14. # It is cleanser: cleanses from sin. (Psalm 119: 9) 15. # It's a law book: Thank you for following the law. (Psalm 119: 1) 16. # The_fruit_of_life: gives birth; It grows. (Matthew 13:23 / James 1:18) 17. # It is a sharp sword: it cuts. (Hebrews 4:12) 18. # It_is_the_Sword of the Spirit: You will fight it. (Ephesians 6:17) 19. # It is a song: it is sung. (Ps 119: 54) 20. # The_word_takes_today !!! (Hebrews 4:12)‌‌
Show all...
📖 #የእግዚአብሔር_ቃል 1. #ወተት ነው፦ መግቦ ያሳድጋል። (1ኛ ጴጥ 2፥2) 2. #እንጀራ ነው፦ ለመኖር ያስፈልጋል። (ማቴ 4፥4) 3. #ማር ነው፦ ይጣፍጣል። (መዝ 19፥10) 4. #ጠንካራ ምግብ ነው፦ ያበረታል። (ዕብ 5፥12-14) 5. #ወርቅ ነው፦ ሃብትህ። (መዝ 19፥10) 6. #መብራት ነው፦ በመንገድ ይመራሃል። (መዝ 119፥105) 7. #መድሃኒት ነው፦ ያድንሃል/ይፈውስሃል/። (ምሳ 4፥22) 8. #መስታወት ነው፦ ገልጦ ያሳይሃል። (ያዕ 1፥23-25) 9. #መዶሻ ነው፦ ይሰባብራል። (ኤር 23፥29) 10. #እሳት ነው፦ ያሞቃል። (ኤር 23፥29) 11. #ዝናብ ነው፦ ያበቅላል። (ኢሳ 55፥10-11) 12. #ጓደኛህ ነው፦ ይመክርሃል። (መዝ 119፥24) 13. #ውሃ ነው፦ያነፃል። (ኢሳ 5፥26) 14. #አፅጂ ነው፦ ከሀጢአት ያነፃል። (መዝ 119፥9) 15. #የህግ መፅሀፍ ነው፦ እንደ ህጉ ብትሄድ ያስመሰግንሃል። (መዝ 119፥1) 16. #የህይወት_ፍሬ ነው ፦ ይወልዳል፤ ያሳድጋል። (ማቴ 13፥23/ያዕ 1፥18) 17. #ስለታም ሰይፍ ነው፦ ይቆርጣል። (ዕብ 4፥12) 18. #የመንፈስ_ሰይፍ ነው፦ ትዋጋበታለህ። (ኤፌ 6፥17) 19. #መዝሙር ነው፦ ይዘመራል። (መዝ 119፥54) 20. #ቃሉ_ዛሬም_ይሰራል!!! (ዕብ 4፥12)
Show all...
ሁሉን ብእርሱ እንችላለን!!  " ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።" ( ፊልጵ 4፥13) ስሙኝ   አንድ  ዝሆን ነበረ  አሉ  እናም  አንድ  ቀን   በሚኖርበት ይህንድ  ቤንጋል  ከተማ  ትልቅ  የሰርከስ  ትእይንት  ላይ  ይሳተፋል። በጣም  የሚገርመው  ያንን  የሚያህል  ዝሆን  ለሰርከስ  ትእይንት  የሚመራው  ደግሞ  ብእድሜ  እስራዎች  ውስጥ  ያል  ልጅ  ነበር እናም  ያ  አንድ  ፍሬ  ልጅ  ያን  የሚያክል  ዝሆን  ብትንሽ  ልምጭ  ነገር  አየሸነቆጠ  የተለያየ  ትእይንት  እንዲያሳይ  ካደረግው  በኋላ አካባቢው  በትልቅ  ጭብጨባ  ተናጋ: እናም በዛ  ቦታ  ከተሳተፉት  ተመልካቾች  መካከል:  አንደኛው  ከትእይንቱ  ባሻገር  ይህን የሚያህል  ዝሆን  በዚህ  ትንሽ  ልጅ  ልምጭ  መገላበጡ  ያስግርመውና  ትእይንቱ  ከለቀ  በኋላ  ከድንኴኑ  በስተጀርባ  ልጁን  አግኝቶ በምን  ቀመር  እንዲህ  እንደሆነ  ይጠይቀዋል  : እናም  ልጁ ከሰውይው  የተሰውረ  የሚመስለውን  ነገር  ይነግረው  ጀመር  እንዲህ ሲል:  ይገርምሃል  ለሰርከስ  የሚሆኑትን  ዝሆኖች  የምናሰለጥናቸው  ከህጻንነታቸው  ጀምረን  ነው  ይህንንም  የምናደርገው  እንዲመቸን  እነርሱን  ለመግራት  ነው : ታዲያ  ከዚያ  የህጻንነት  እድሜ  ጀምሮ  እስከ ጉርምስናቸው  ማብቂያ  አካባቢ  :በሁለት  ዛፍና ዛፍ  መካከል  በጠንካራ  ገመድ  ታስረው  እንዲቀለቡ  እናደርጋለን  እናም  ይታዘዙትን  እንዲያደርጉ በዱላ  እንመታቸዋለን  እናም እንቢታቸው  ከበዛ  ይዱላውን  ኃይል  እንጨምራለን  እናም  ድብድባው  ዚበዛባቸውና  የታሰሩበት  ገመድ  ሲጠነክርባቸው ሳይወዱ በግዳቸው  የተባሉትን   ማድረግ  ይጀምራሉ የዚያን  ጊዜ  እንፈታቸውና  ከእነሱ  በፊት  ወደተገሩት  ዝሆኖች  እንቀላቅላቸውና  የተላያየ  ልምምድን  በጋር  ማድረግ  ይጀምራሉ : ከዚያ  በኀላ  እንኳን  ምንም  ያህል  ሰውነታቸው  እየገዘፈ  እንኳ  ቢሄድም  የኋለኛው  ዘመናቸው  ልምምድ  ተጽእኖ  ስላለባቸው  የክር  ያክል  ቀጭን  ገምድ  እንኳን  ብታስራቸው  የመበጠሰ  እቅማቸው  በስልጠናው  ስለተነፈጉ እቅም  ያጥራቸዋል  በመሆኑም ለመበጠስ  እንኳ  አይሞክሩም:  ስለዚ  ልምጯ  በተንኮሰቻቸው  ቁጥር  የሚባሉትን  ከማድረግ  ውጭ  ሌላ  እቅም  በውስጣቸው እንዳለ  እንኳን  አይረዱም  በማለት  ለሰውይው  ገለጻ  አደረገለ ።   ይህን  ታሪክ  ሳነብ  ምን  እንደ  ነካኝ  ታውቃላችሁ  በውስጣችን  ትልቅ  የእግዚአብሔር  አቅም  እያለ  አስረው  የያዙን  " አትችልም"  አትችይም "  የሚል  ድምጽ  ፈጥኖ  ሲከበን፣ በልጅነታችን  ፣ከወላጆቻችን ፣  ከጎረቤት፣  ከመምህሮችችን፣  ከአካባቢያችን  የሰማናቸው  አሉታዊ  ንግግሮች  ሕሊናችንን ያጨናንቃሉ።  እናም  የእኛም  አእምሮ  ይህንን  ተቀብሎ  ያስተጋባል  እምሮ  በደረሰበት  ውጫዊ  ተጽእኖ  ውስጣዊ  መረጃን በመቆናጠጥ  ገመዱን  ያስራል  ይህም  ገመድ  ትምህርትን  ያነሳል ፣  ፍጥረትን ይዳስሳል  ፣ ትውልድን  ያወሳል  እንዲህ  እና  እንዲያ ስለ  ማንነታች  ክንቱነት  ገመድን  ያጠብቃል  :  እነዚህ  ድምጾች  ድምጽ  ብቻ  ቢሆኑ  ባልከፉ፤  ነገር  ግን  ከታሪካችን፣ ከገጠመኞቻችን ፣  በዙሪያችን  ካሉ  ጠንቅቀን  ከምናውቃቸው  እውንታ  መሰል  ክስተቶች  ጋር  ተዛምዶ  ስላላቸው  ያለማመንታት እንቀበላቸውና  ጫና  ያደርጉብናል  : በእርግጥም  የቀድሞ  ያልተሳኩ  ሙከራዎቻችን  ፣ የኑሮ  መደባችንን፣  የገንዘብ  አቅማችንን ፣የትምህርት  ደረጃችንን፣  የቆዳ  ቀለማችንን.... የምንመለከት  ከሆነ  እንደ  ቤንጋሊው  ዝሆን  በውስጣችን  ታላቅ  ኃይል  ይዘን በታናሽ  እጅ  የምንመራ ፣  ሳንወድ  የሌላውን  ፈቃድ  የምናድርግ  የጠላት  መጫወቻ  ልንሆን  እንችላለን።  ነገር  ግን  በቀድሞ የሽንፈት  ታሪካችንና  በአሁኑ  ውጪያዊ  ገጽታችን  በውስጣችን  ያለውን  ከሁሉ  የሚበልጥ  ኃይል  እርሱም  ክርስቶስን ከተመለከትን  " እትችልም"  " አትችይም"  የሚለንን  የሐሰት  ድምጽ  " ኃይልን በሚሰጠኝ  በክርስቶስ  ሁሉን  እችላለሁ!"  በሚል የድል  ድምጽ  ሽረን  የተገለጠልንን  የእግዚአብሔርን  ፈቃድ  በራሳችን  ዘመን  ፈጽመን  ማለፍ  እንችላለን። " እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።" (የዮሐንስ ወንጌል 15:5)
Show all...
ስማቹን አስቀይሩ ለእናንተ የማይመጥን፣ስራቹን የማይገልፅ፣አቅማቹን የማይስተካከል ስም ካላቹ አሁኑኑ አስቀይሩት፤ ያዕቆብ አታላይነቱን አልወደደውም ያዕቆብ ተብሎ ሲጠራ ትዝ የሚለው አታላይነቱ ነው ለዚህም ነው ስም ቀያሪውን አምላኩን ሲያገኘው ካልባረከኝ አለቅህም ያለው የያዕቆብ ትክክለኛ ስም እስራኤል ነበር ያዕቆብ የእርሱ ስም አልነበረም እናንተም የናንተ ባልሆነ ማንነት ጊዜያቹን አትጨርሱ አሁኑኑ የእናንተን እውነተኛ ማንነት እወቁት ያኔ በህይወታቹ ታሪክ መስራት ትጀምራላቹ
Show all...
#ችግር_አለ?? "ዝሆንና ውሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ውሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ውሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡  እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች፡፡ በአስራ ስምንተኛዉ ወር ውሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት “እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርግዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡  ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነው ልጅ በልጅ ሆኛለሁ፡፡ አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ...ችግር አለ??”  ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታውቂልኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር እኔ የተሸከምኩት የውሻ ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡  ልወልድ የምችለዉ በሁለት አመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል...የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ሃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ፍሬ ነዉ” አለቻት።  የዚህ አጭር ተረት መስል ታሪክ ጭብጡ፡  ሰዎች ለጥያቄዎቻቸውና ለጸሎቶቻቸዉ መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ፡፡ በሌሎች ምስክርነት አትቅና፡፡ ቀስት እጅግ በተለጠጠ ቁጥር የሚደርስበትም እርቀት ይጨምራልና።  የራስህን የጸሎት መልስ ካላገኘህ ውስጥህ አይሰበር ይልቅስ በርታ ለራስህ እንዲህ በለዉ "ጊዜዬ እየደረሰ ነዉ ተወልዶ መሬት የረገጠ እለት ሰዎች በአድናቆት የተወለደዉን ይመለከቱታል ጌታ ታላቅን ነገር በኔ ሊያደርግ ቀርቧል እግዚአብሔር መልካምና ታማኝ ነዉ" ።  " በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል። " ( ምሳ 27፥18)
Show all...
🙆🙆🙆🙆🙆🙆🙆🙆‍♂🙆‍♂🙆‍♂🙆‍♂🙆‍♂🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂ ስሙኒ ይቀራል… ከአንድ ሰው በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ ድንች የሚሸጥ ምሲኪን ሰው ነበረ። የቤቱ ባለቤት ሁሌም ወደ ውጪ ሲወጣ ይህንን ምስኪን ሰው ይመለከተው ነበረ። ቀኑን ሙሉ ብርድና ጸሀይ እየተፈራረቀበት ኑሮን ለማሸነፍ መድከሙ ስላሳዘነው በአቅሙ ሊረዳው ወሰነ። ነጋዴው አንዷን ድንች በ50 ሳንቲም ነበር የሚቸረችረው። ታዲያ ይህ ሰው ምስኪኑን ነጋዴ ለመርዳት በማሰብ በየቀኑ የአንድ ድንች ዋጋ እየሰጠው ለመሄድ ወሰነ። በየቀኑ 50 ሳንቲሙን እየሰጠው በአንጻሩ ምንም ድንች ሳይቀበል ይሄዳል። ከብዙ ጊዜ በኋላ ይህ ሰው እንደለመደው 50 ሳንቲሙን አኑሮለት ጉዞውን ቀጠለ። ድንገት ከኋላው “ጌታዬ” የሚል ጥሪ ይሰማል። ዞር ብሎ ሲመለከት ምስኪኑ ነጋዴ ነበር በሩጫ የደረሰበትና የጠራው። ሰውየው በፈገግታ “ከስንት ጊዜ በኋላ ለምን በቀን በቀን 50 ሳንቲም በነጻ እየሰጠሁ እንደማልፍ ሊጠይቀኝ ነው ያስቆምከኝ?” አለው ነጋዴው ግን እያለከለከ “አይደለም ኸረ” ሲል መለሰ። ይሄኔ ሰውየው ግራ ገብቶት “እና ለምን አስቆምከኝ?” ቢለው “የድንች ዋጋ 75 መግባቱን ልነግርዎት ነው፤ እናም ስሙኒ ይጎድላል” አለው አሉ። ክብር ይግባውና ክርስቶስ ኢየሱስንም ልክ እንደዚህ የምንከተለው ብዙ ነን። እኛን ለመርዳትና እኛን ለማገዝ ውድ ህይወቱን ቢሰጠን እኛ ግን ከሰጠን ነፍሱ በላይ መኪና አልሰጠኸኝም ቤት አልሰጠኸኝም ብለን ከቦልት በፈጠነ ሮጠን ልንይዘው የምንገሰግስ ብዙ ነን። ይሄ የሰው ልጅን የአልጠግብ ባይነትና ያለማመስገንን ባህሪ የሚያንጸባርቅ ነው። ሰዎች አመስጋኝ ፍጡሮች ነን ብዬ አላምንም። ልክ እንደዚህ ምስኪን ነጋዴ ነጻ በሚሰጠን ነገር ላይ እንኳን እንደራደራለን። የእኛ ባልሆነው ሀብት እንሟገታለን። በቸርነት በተሰጠን ነገር ሁሉ ይበልጥ እንጠይቃለን። ሃምሳ ሳንቲም ለምን በነጻ ተሰጠኝ ሳይሆን ለምን ስሙኒ ጎደለ የሚል አመለካከት ስላለን እኮ ነው አብዛኛዎቻችን ባለን ነገር መደሰት የሚያቅተን። ዛሬም ክርስቶስን አምናለው እከተላለው የምንለው እኛም እንዴት ነፍሱን በነፃ ሰጠኝ? እንዴት ስለኔ ብሎ ያን ሁሉ መከራ ተቀበለ? አንልም። የስሙኒዋ ቦታ ጎደለች ብለን ለምን ብር አጣሁ? ለምን ስራ አጣው? አይወደኝም! እንደውም በስፍራው የለም! እንላለን። እኛን ድግሞ ይቅር ካላለን ማንን ይቅር ሊል ነው ፡፡ በነጻ የሚሰጠንን 50 ሳንቲም ሳይሆን የኑሮዋችንን ዋጋ እራሳችን ተምነን ቀሪው ጎደለ ብለን እንሟገታለን። ስዎች የሚሰጡንን ነጻ ፍቅር፤ ነጻ ክብር፤ ነጻ እምነት ዋጋ የማንሰጠው ቀሪውን ስሙኒ ስለምናስብ ነው። እኛ በባህሪያችን ነጻ የሆነን ነገር ዋጋ አንሰጠውም እንደውም አንድ ተናጋሪ ሰዎች አይምሮዋችንን በደንብ የማንጠቀምበት ነጻ ስለተሰጠን ነው ሲል ሰምቸው ግርምት ጭሮብኝ ነበር። እውነት እኮ ነው፤ የላፕቶፓችንን ያህል አይምሮዋችንን ዋጋ አንሰጠውም። ላፕቶፓችንን ቫይረስ እንዳይነካው የምንጠነቀቀውን ያህል አይምሮዋችን እንዳይበከል አንጠነቀቅም። የሚያስደንቀው ግን የሰው ልጅ በምንም ያህል ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችላቸው ሀብቶቹ በሙሉ በነጻ የሚያገኛቸው ናቸው። በ50 ሳንቲሙ ያልተደሰተና ያላመሰገነ ሰው ስሙኒ ቢጨመርለት ምን ዋጋ አለው? በበዛው ያላመሰገነው ባነሰውማ ምስጋናን አያዘንብም። በየቀኑ የሚቸረን 50 ሳንቲም ከበቂ በላይ ነው፤ አንዳንዴ ስሙኒው ይቀራል ብለን ሰጪውን ባናስቀይም መልካም ነበር፤ ነገር ግን ሰው ነን!!! ብዙ ጊዜ ደስታችንን የሚነጥቀን የ “ስሙኒ ይቀራል” አይነት አመለካከታችን ነው። የተሰጠንስ 50 ሳንቲም? የተሰጠን ነጻ ፍቅር፤ ነጻ ክብር፤ ነጻ እምነት፤ ነጻ ጤንነት፤ ነጻ ተስፋ? ከምንም በላይ ነጻ ህይወትስ? እግዚአብሄር ያለውን ትልቁን ሀብት ክርስቶስን ሰቶናል። ዛሬ ስሙኒ ቀረብን ብለን እባካችሁ እናንጎራጉር ለእስካሁኑ ምህረት ያርግልን ከእንግዲህ ግን የልባችን ሚዛን ካለችበት ትንቃና የተከፈለላትም እውነት ታስተውል ታመዛዝን t.me/mizan_amann join join group t.me/mizan_aman join
Show all...
የምስጋና መስዋእት!! " ሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ፤ እስራኤልም፥ ስማኝ፥ ልመስክርብህ፤ አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ። ስለ ቍርባንህ የምዘልፍህ አይደለሁም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው። ከቤትህ ፍሪዳን ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም፤ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና። የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥ የምድረ በዳ አራዊትም በእኔ ዘንድ ናቸው። ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና። የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን? ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤ " (መዝ 50፥7-14) ሰው ማንኛውንም መንፈሳዊ ተግባራት እያደረገ የእግዚአብሄርን አላማ ሊስተው ይችላል፡፡ሰው ወደ እግዚአብሄር እየፀለየ ፀሎቱ የተሳሳተ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር እየሰጠ ከእግዚአብሄር ጋር ሊተላለፍ ይችላል፡፡ እስራኤላዊያን ለእግዚአብሄር መስዋዕት ይሰዉ ነበር ፡፡ ነገር ግን መስዋእታቸው በግዴታ ላይ የተመሰረተ ይመስል ነበር፡፡ እግዚአብሄር የጠየቅከው ይህን ነው አይደል ያውልህ ብለው ወርውረው የሚሄዱ ነው የሚመስለው፡፡ እግዚአብሄር የፈለገውን ዋናውን የምስጋና ልብ ከእነርሱ ስላላገኘ ህዝቡ ከእግዚአብሄር ጋር ተላልፏል እግዚአብሄርም ይወቅሳቸዋል፡፡ እግዚአብሄርም መስዋእት እንዲያቀርቡለት ሲጠይቅ ምን እንደፈለገና ምን እንዳልፈለገ በዚህ ክፍል ሲናገራቸው እናያለን፡፡ እግዚአብሄር መስዋእትን ወይም አንድን ነገር እንድናደርግለት ሲፈልግ በምስጋና ልብ እንድናደርግለት ምስጋናን ፈልጎ እንጂ ነገሩን ፈልጎት አይደለም፡፡ እስራኤላዊያንን መስዋእት አምጡ ሲል ስጋ አምሮት ወይም ደም የሚጠጣ ሆኖ ሳይሆን መስዋእቱ ተሸክሞት የሚመጣውን ምስጋና ማየት ስለፈለገ ነው፡፡ እግዚአብሄር መስዋእት አድርጉልኝ ሲል ሃብትን መጨመር ፈልጎ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ባለጠጋ አምላክ ነው፡፡ ወይም ስንሰዋውና ስናጣው ብቻ ደስ ብሎት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ታዲያ ለምንድነው አንድ ነገርን እንድናደርግለት ወይም መስዋእት እንድናደርግለት የሚፈልገው ብለን ብንጠይቅ መልሱ እግዚአብሄር ምስጋናን ስለሚፈልግ ነው፡፡ በምናደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሄር ከእኛ ሁል ጊዜ የምስጋናን ልብ ይጠብቃል፡፡ እግዚአብሄር ንጉስ ስለሆነ እግዚአብሄር ኩሩ ስለሆነ በምስጋና ልብ ያላደረግነው ማንኛውም መስዋእት አይደሰትበትም አይመለከተውም፡፡ "አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤" (ዘፍ 4፡4) እኛ ደስ ደስ ሲለን ምስጋና በምስጋና እንደምናደርገው ትንሽ ሲጎድል ደግሞ ዝም እንደምንለው ሳይሆን እግዚአብሄር ሁልጊዜ ምስጋናችንን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ስጋን ባይበላም ምስጋናን ግን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ምስጋናን ሁሌ በመፈለጉ የተነሳ ሁኔታዎች ቢጨላልሙም ባይመስለንም እንኳን በእርሱ ታምነን ምስጋናን እንድንሰጠው ይጠብቃል፡፡ በደህናው ጊዜ ብቻ ሳይሆን በአስቸጋሪ ጊዜም እግዚአብሄር ከሚታመኑት የምስጋናን መስዋዕትን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የሚጠማውና የሚራበው ምስጋና፡ ማጉረምረም ሲያሰኘን ሁሉ ነገር እግዚአብሄርን እንዳናመሰግን ሲያስፈራራን፡ የዛን ጊዜ የምናመሰግነውን ነው፡፡ በተለይ ነገሮች ሁሉ አይሆንም አይሳካም አይከናወንም ሲሉን እግዚአብሄርን የምናመሰግነው ምስጋና እንደ ሽቱ በእግዚአብሄር ዘንድ የተወደደ ነው፡፡ ነፍሳችን ማጉረምረም ሲያምራት እምቢ ብለን የምንሰዋው ምስጋና ነው የምስጋና መስዋእት የሚባለው፡፡ " ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። " (መዝ 43፥5) መስዋእታችን የልባችንን ምስጋና እንዲሸከም ስለተፈለገ ነው እንጂ፣ እግዚአብሄር መስዋእት የምናደርገውን ነገር ፈልጎትና ቸግሮት አይደለም፡፡ እስራኤላዊያን የልባቸውን ምስጋና የመወርወር ያህል ጥለው ይሄዱ ስለነበረ እግዚአብሄር ምስጋናን የተሸከመ መስዋዕትን ነው የምፈልገው እያለ ሲወቅሳቸው እንመለከታለን፡፡ የመስዋእቱ አላማ የተሸከመው ምስጋና እንጂ ስጋው አይደለም እያለ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት በእውነትና በመንፈስ እንሰዋ ዘንድ ጸጋና ማስተዋል ይሁንልን።
Show all...
😍 ኢየሱስ በኩር ነው😍 🏆Prototokos😇 #አስፈላጊ ሆነው የተገኙት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላት ከአማርኛው ይልቅ የእንግሊዝኛው ከግሪኩ ጋር ስለሚስማሙ የእንግሊዝኛውን ተጠቅመናል 🌴 "15 Who is the image of the invisible God😻, the 👏#firstborn 👏of every creature:" (Colossians 1:15) እዚህ ጋር #በኩር ወይም firstborn የሚለው ቃል በግሪኩ "prototokos" ማለት ሲሆን ትርጉሙም " የቀደመ፥ የመጀመሪያ " ማለት ነው። (Refference : Strongs Dictionary of Hebrew and Greek) ይህ "prototokos" የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ኢየሱስ ከፍጥረት በፊት የነበረ፥ ቀድሞም የነበረ መሆኑን ለመግለጽ ነው አንዳንድ ወገኖች ይህንን ክፍል በመውሰድ ኢየሱስ አለም ከመፈጠሩ በፊት በአብ የተፈጠረ ነው ይላሉ። ነገር ግን ክፍሉን በጥንቃቄ ለተመለከተው ይህ ምልከታ ስህተት መሆኑ ልብ ይሏል "15 ...the firstborn #of every creature:" (Colossians 1:15) እዚህ ጋር "..the firstborn of all creation " ነው የሚለው። ይህም በቀጥታ ሲተረጎም "#የፍጥረት ሁሉ በኩር" ተብሎ ይተረጎማል💦 የዚህ ትርጉም ኢየሱስ የፍጥረት ቀዳሚ፥ በፊትም የነበረ ማለት ነው። ሐዋሪው ጌታን የፍጥረት በኩር ያለበት ምክነያት ኢየሱስ ከፍጥረት ጋር በመነጻጸር ያለውን ቀዳሚነት ለማሳየት ነው🔥 ሐዋሪያው ኢየሱስ የፍጥረት አካል ነው ማለት ቢፈልግ ኑሮ "#ከፍጥረት ሁሉ በኩር"⚡️ ይል ነበር። ይህንን እውነታ ከሚቀጥለው ቃል እንመልከት "18 ...the firstborn #from the dead; that in all [things] he might have the preeminence." (Colossians 1:18) የዚህኛው ቀጥታ ትርጉም "...ከሙታን ሁሉ በኩር" ነው ⭐️የዚህ ትርጉም፥ ኢየሱስ ከሙታን መካከል የነበረ እንደሆነ ነገር ግን በመነሳቱ ቀዳሚ እንደሆነ ያሳያል። 🌻ጌታ ከሙታን አንዱ ስለነበር from የሚለውን ተጠቅሟል። ነገር ግን ኢየሱስ ከፍጥረት አንዱ ስላልሆነ of ብሏል። ይህም ክርስቶስ ከፍጥረት ጋር በመነጻጸር ቀዳሚ መሆኑን ለማሳየት ነው 🍀አስተውሉ በዛኛው ላይ of ብሎ እዚህኛው ላይ from ይላል። from ማለት #ከ ማለት ሲሆን፥ ያ አካል ከእዛ ነገር አንዱ ነው ወይም ነበር ማለት ሲሆን፥ of ግን #የ ማለት ሲሆን ያ አካል ከእዛ ነገር ጋር በተነጻጻሪነት መቅረቡን ያሳያል። የእዛ ነገር አካል ነው ማለት ግን አይደለም 🌲ብዙ ወገኖች የሚሳሳቱት "Prototokos" 🕊የተሰኘው የግሪክ ቃል በኩር ወይንም firstborn ተብሎ ስለተተረጎመ ነው፥ እንጂ ቀጥተኛ ትርጓሜው ቀዳሚ ማለት ነው ስለዚህ በዚህ መሠረት ሐዋሪያው🐆 ጌታን ከፍጥረት ጋር አነጻጽሮ ቀዳሚ፥ በፊትም የነበረ መሆኑን ሲገልጽ ከሙታን ግን አንዱ እንደነበር ነገር ግን በመነሳቱ የትንሳኤ ቀዳሚ መሆኑን አስተምሮል። ☃እውነትም ኢየሱስ በኩር ነው⛄️
Show all...
#ሠርቼ_ሳይሆን_ተቆጥሮልኝ...... ❇️ እኔ በራሴ ደካማ ነኝ! #አልችልም! በመልካም ማንነት በጥንቃቄ ብራመድም ለጥቂት ነው እንጂ ፤ ተመልሼ እወድቃለሁ ፤ እንዲሁም እነሳለሁ። እድሜዬን በሙሉ ጠንካራ ሁኜ ያለምንም ስህተት መኖር አልችልም! ህጉንም ሁሉ መጠበቅም አልችልም! ምክንያቱም ፍጹም አይደለሁም። ✝ በዚህ ሁኔታም ፤ ህግን በመጠበቅ እና በመልካም ሥራ የሚጸድቅ ማንነት የለኝም!.... #ብቁ_አይደለሁም ፤ እራሴን አላምንም! ምክንያቱም እጅግ ደካማ ነኝ [በመንፈስም ደሃ ነኝ]። #በሥራዬ_ብጸድቅ ፤ ነገ ደግሞ ስደክም ጽድቄን አጣዋለሁ። በእኔ ኃይል እና በሥራዬ ቢሆን ዛሬ ላይ ባልደረስኩ ነበር። #እንደ_ሥራዬ ቢሆንማ አጠቃላይ ውጤቴ የከፋ ነበር። በሥራዬ ቢሆን ፤ እንኳን በእግዚአብሔር ፊት #ልጸድቅ ይቅርና ፤ በሰዎች ፊት እንኳን ጻድቅ አልባልም ነበር። ✝ አሁን ግን #የምጸድቀው_በሥራዬ_አይደለም! 😁 የምጸድቅበት አዲስ ተስፋ መጥቷል ፤ እርሱም #እምነት ይባላል። ያገኘሁትም #ጽድቅ የራሴ አይደለም! #ተቆጥሮልኝ እንጂ። በራሴ በየትኛውም ሥራ #የእግዚአብሔርን_ጽድቅ ላገኘው ስለማልችል ፤ #እንዲሁ_ተቆጠረልኝ ፤ ያውም የራሱ #የእግዚአብሔር _ጽድቅ። እኔ መሥራት ስላልቻልኩ #ልጁ ሥራዬን ሠራልኝ እና ለእኔ ለደካማው #ተቆጠረልኝ። ልጁ በሠራው እኔ እንዲሁ በእምነት ገባሁ ፤ ልጁ ህጉን በሙሉ መፈጸሙ ለእኔ #ተቆጠረልኝ ፤ ያለ ኃጢአት መመላለሱ ለእኔ #ተቆጠረልኝ። ሮሜ 3÷28፤ [ #ሰው_ያለ_ሕግ_ሥራ_በእምነት_እንዲጸድቅ >>#እንቆጥራለንና<<። ] ሮሜ 4 (Romans) 5፤ [ #ነገር_ግን_ለማይሠራ_ኃጢአተኛውንም_በሚያደድቅ_ለሚያምን_ሰው_እምነቱ_ጽድቅ_ሆኖ >>#ይቆጠርለታል<<። 6፤ [ እንደዚህ ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር >>#ያለ_ሥራ<< ጽድቅን #ስለሚቆጥርለት ስለ ሰው ብፅዕና ይናገራል። ] 22፤ [ ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ >>#ተቆጠረለት<<። 23፤ ነገር ግን፦ >>#ተቈጠረለት<< የሚለው ቃል #ስለ_እርሱ_ብቻ_የተጻፈ_አይደለም፥ >>#ስለ_እኛም<< ነው እንጂ፤ 24-25፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው >>#ለምናምን_ለእኛ >>#ይቈጠርልን_ዘንድ<< አለው። ] ገላትያ 3 (Galatians) 8፤ [#መጽሐፍም እግዚአብሔር >>#አሕዛብን_በእምነት_እንዲያጸድቅ >>#አስቀድሞ_አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። ] ✝ እግዚአብሔር #በልጁ_ስም በማመኔ ብቻ #የልጁን_ጽድቅ ለእኔ ለኃጢአተኛው እንዲሁ ከቆጠረልኝ ፤ ታዲያ ኃይማኖት የምን #ምቀኝነት ነው? ፤ ለምንድነው "#ለመጽደቅ_መሥራት_አለብህ" የምትለኝ? እህ!!!!!!...... ቆይ መቼም በሥራዬ ፈጽሞ መጽደቅ እንደማልችል ስለሚያውቅ መስሎኝ እግዚአብሔር እንዲሁ #በነጻ ፤ ማመኔን ጽድቅ አድርጎ #የቆጠረልኝ። ወይ ሃሳብህን አስተካክለው ፤ "#ስለጸደክ_መስራት_አለብህ" በለኝ። እንዲህ ስላልከኝም አይደለም ፣ መልካም መስራት የኔ አዲሱ ሰው ማንነት life system ነው። ሮሜ 8 ÷ 33፤ [ #እግዚአብሔር_የመረጣቸውን_ማን_ይከሳቸዋል? >>#የሚያጸድቅ_እግዚአብሔር_ነው፥ #የሚኰንንስ_ማን_ነው? ] ሮሜ 10 (Romans) 3፤ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። ✝ እወድሃለሁ አንተ ወንድሜ! ይህ ጽድቅ ለእኔ ብቻ እኮ አይደለም #ላንተም ነው! እመን! #ይቆጠርልሃል! በሥራ ካልክ እውነቱን ልንገርህ መቼም አትጸድቅም! እግዚአብሔር የራሱን ጽድቅ ሊሰጥህ ይፈልጋል ፤ ታዲያ አንተ ለምን የእርሱን ትተህ #የራስህን_ጽድቅ ለማቆም ትጥራለህ? እርሱ እንዲሁ በነፃ ስለሰጠህ?...... የምትድነው እኮ #በራስህ_ጽድቅ ሳይሆን በራሱ #በእግዚአብሔር_ጽድቅ ነው።
Show all...
🟠 የሚያስፈልጋችሁ ብዙ ነገሮች ከመሰሉዋችሁ ተሳስታችኋል፡፡ ብዙ ነገር አይደለም የሚያስፈልጋችሁ፡፡ አንድ ነገር ብቻ ነው የሚያስፈልጋችሁ፡፡ ለሁሉም ነገር አንድ ነገር ብቻ ነው የሚያስፈልጋችሁ፡፡ ትዝ ይላችኋል ኢየሱስ ወደ ማርታ ቤት በገባ ጊዜ ማርታ ብዙ ነገር የሚያስፈልግ መስሏት ብዙ ትጨነቅና ትታወክ ነበር፡፡ ያም በቂ ሳይሆን ቀርቶ በተጨማሪ ማርያም መጥታ የሚያስፈልገውን አብረው እንዲያዘጋጁ ፈለገች፡፡ ብዙ ሰውና ብዙ አገልጋይ እንደማርያም ነው፡፡ ብዙ ነገር የሚያስፈልግ መስሎት ይጨነቃል፣ ይታወካል፡፡ ደግሞም ያም አይበቃውም፡፡ አስገራሚ ነው፡፡ ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ ”የሚያስፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው” (ሉቃ 10፡42 አ.መ.ት)፡፡ ሃሌሉያ! ሃሌሉያ! ኢየሱስ የሚያስፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው ያለው ስለምን ጉዳይ ነው? ስለሁሉም ነገር ነው፡፡ ስለማንኛውም ነገር ሁሉ የሚያስፈልገው አንድ ብቻ ነው፡፡ ያ አንድ ነገር ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ሃሌሉያ! ኢየሱስ ብቻ!! ኢየሱስን ማግኘት!! ምክንያቱም እግሩ ስር ተቀምጣ ስለነበረችው ማርያም እንዲህ አለ ”ማርያም እኮ የሚሻለውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእርሷ አይወሰድም” (ሉቃ 10፡42 አ.መ.ት)፡፡ ትክክለኛው የሚያስፈልገው አንድ ነገር ኢየሱስን ማግኘት ነው፡፡ ማርያም ያንን ስላገኘች አትታወክም አትጨነቅም፡፡ ኢየሱስ አላችሁ?? በቃ የሚያስፈልገው ነገር አላችሁ፡፡ ለምንም ነገር የሚያስፈልገኝ አለኝ እኔ፡፡ የለኝም ወይም ጎድሎኛል የሚል ሃሳብ የለኝም፡፡ ኢየሱስ እኮ ነው ያለኝ፡፡ አንድ ነገር ነው የሚያስፈልገው እሱም ኢየሱስ ነው፡፡ እሱም አለኝ፡፡ ኢየሱስ አለኝ፡፡ ኦ ሃሌሉያ!! ሃሌሉያ!! ሁሉም ነገር ከኢየሱስ ስለሚመነጭ በቃ ኢየሱስ ስላላችሁ የሚያስፈልጋችሁ ሁሉ አላችሁ፡፡ ይሄን እውነት መንፈስ ቅዱስ በልባችሁ አግዝፎና ጠብቆ እንዲያኖረው በኢየሱስ ስም እፀልያለሁ፡፡ ከዚህ ቀን ጀምሮ የሚያስፈልጋችሁ ነገር የጎደላችሁ መስሎ እንዳይሰማችሁ!! በፍፁም!! ኢየሱስ እኮ ነው ያላችሁ፡፡ 🟠 ሌላ እውነት የሆነ ቃል ላሳያችሁ፡፡ አስደናቂ እውነት ነው፡፡ ሁልጊዜ አስታውሱት፣ እያንዳንዱን ቃል ደግሞ አስተውላችሁ ተመልከቱት… ”በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እርሱን በማወቅ ለህይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገንን ሁሉ የመለኮቱ ሀይል ሰጥቶናል” (2ጴጥ 1፡2 አ.መ.ት)፡፡ የጠራንን ጌታ ስናውቅ በቃ ሁሉም የሚያስፈልገን ከእርሱ ውስጥ ይመነጫል፡፡ ስለዚህ የሚያስፈልገው አንድ ነገር የጠራን ጌታ ነው፡፡ ትዝ ትላችኋለች ማርያም የጠራት ኢየሱስ እግር ስር ቁጭ አለች፡፡ ኢየሱስን አገኘችው፡፡ ለሁሉም ነገር የሚያስፈልገውን አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ እኔ ኢየሱስን ካገኘሁት በኋላ ምንድነው ሌላ የሚያስፈልገኝ ነገር? ኢየሱስን አግኝታችሁት ካልተደሰታችሁ መቼ ልትደሰቱ ነው? ስታገቡ? ሲሳካላችሁ? ስትወልዱ? የምትፈጉትን ስታገኙ? እንዴ!! ኢየሱስስ? ኢየሱስ እኮ አሁን አላችሁ፡፡ በቃ እሱ ነው የሚያስፈልገው አንድ ነገር፡፡ እሱም አላችሁ፡፡ ኢየሱስ አላችሁ!! ሃሌሉያ! ሃሌሉያ! እዚህ ላይ ብቻ አተኩሩ፡፡
Show all...
ዲያጎን የተባለ ፈላስፋ በመንገድ ሲያልፍ አንድ በጣም ውብ የሆነ ሁለመናው የተዋበ ግን ተንኮለኛ ሰው ተመለከተና "ቤቱስ ያምራል ያደረበት ግን የማይረባ ነው አለ። የውጭ ሰውነታችን የውስጠኛው ሰውነታችን አገልጋይ፣ባርያ እና ስራ አስፈፃሚ ነው። የውጭ ሰውነታችን የራሱ ፈቃድ የለውም። አፍ (አንደበት) አእምሮ ሲያዘው ይረግማል አእምሮ ሲያዘው ይመርቃል አእምሮ ሲያዘው ይዘምራል አእምሮ ሲያዘው ይዘፍናል አእምሮ ሲያዘው ያሞግሳል አእምሮ ሲያዘው ይሰድባል። በውጭ የምናያቸው የሰውነታችን ክፍሎች ምንም የሆነ የራሳቸው ፈቃድ የላቸውም። በእግዚአብሔር ፊት የሚያምር መልበስም የማይረባ መልበስም ታጥቦ መቆምም ቆሽሾ መታየትም ዋጋ የለውም። ሰው ወደሚታየው ፊትና ሰውነት ልብስ ይመለከታል። እግዚአብሔር ግን የማይታየውን እና የተሰወረውን ልቦናችንን ያያል። የሚያምር ልብስ ንፁህና ውድ ጫማ ማራኪ ፊት ደስ የሚል ሽቶ ብዙ መባና መስዋዕት የእግዚአብሔር የህይወት መስፈርት አይደሉም። እግዚአብሔር በእኔ ደስ የሚሰኘው ልብሴን ሳጥብ ኪሴን ሳሳብጥ ፊቴን ሳሳምር ሳይሆን ልቦናዬን ሳነፃለት ውስጤን በእምነት ስሞላው ነው። ኤፌሶን 3፥16-17 "በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር..." ይላል። ስለዚህ እግዚአብሔር የውስጥን ሰውነት መጠንከር እና የልብን እምነት ይመለከታል። "ልብን እና ኩላሊትን" የሚለው ቃሉ እነሱን ያያቸዋል ሳይሆን ለሰው የተሰወረውን የሰውን ማንነት ይመረምራል ማለት ነው። አንዳንድ ጊዜ እከሌ ሞተ ሲባል አሁን አይቼው ነበር እኮ ትናንት እኮ አብረን ነበርን.....ምናምን ይባላል። ሰውየው ድንገት አልሞተም ቆሞ ሄደ እንጂ ውስጥ አልቆ ነበር ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር "አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ" ነው የሚለው ሰው ግን ጥፍሩን ፀጉሩን ፊቱን ነው የሚጠብቀው። ፊታችን ቢበላሽ አንሞትም ጥፍራችን ቢነቀልም እንኖራለን ፀጉራችንም ባያምር ምንም ላይቀርብን ይችላል ልባችን ውስጣችን የተበላሸ ቀን ግን ብዙ ነገሮች ይበላሻሉ። እግዚአብሔር የሚባርከው መጀመሪያ ልብን ነው በእግዚአብሔር በረከት የልቡ ዕይታ የተስተካከለ ሰው ምንም ነገሮች ውበት ባይኖራቸው የነገሮችን መልካም ጎን እያየ ይደሰታል። ሰው ዕይታው ካልተስተካከለ ባለው 99 ብር መደሰት ትቶ በጉደለው 1 ብር ያለቅሳል። ሰውነትህን ልብስህን ጠረንህን እና ውበትህን ለራስህ እና ለሰዎች ጠብቅ የውስጥህን ነገር ደግሞ ለእግዚአብሔር አስውብለት። ውስጣችን የሚገነባው በእግዚአብሔር መንፈስ እና በክርስቶስ ላይ ባለን የእምነት ልክ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር የውስጣችንን ጥንካሬ እና በልባችን ያለውን ክርስቶስ ይመለከታል ይመረምራል ይመዝናል። በውስጡ ያልጠነከረ ሰው የውጩ መጠንከር የትም አያደርሰውም። ✍ አገልጋይ ምናሴ #ተባርካችኋል #SHARE_SHARE
Show all...
🍇ያማረውንና የጣፈጠውን የአንደበታችሁን ፍሬ ጌታ በጊዜው ያብላችሁ 🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇 🍇 በምላስ ላይ ትልቅ ኃይል እንዳለ ያወቀ ሁሉ ከእኛ ጋር በአየሩ ላይ ይህንን ያውጅ 🍇 "ምላሴ ፅድቅህን ሁልጊዜ ምስጋናህን ይናገራል 🍇 የእግዚአብሔር ዘር--የእግዚአብሔር ቃል ራሱ እግዚአብሔር ነው እኔም የተወለድኩት ከእግዚአብሄር ነው ስለዚህ የእግዚአብሔር ዘር ነኝ 🍇 እግዚአብሔር በእውነት ቃል አስቦ ወልዶኛል 🍇 ዳግመኛ የተወለድኩት ከሚጠፋ ዘር አይደለም በህያውና ለዘላለም በሚኖር ከእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ 🍇 እግዚአብሔር ባለበት ሁሉ እኔ አለሁ እኔ ባለሁበት ሁሉ እግዚአብሔር አለ 🍇 ከመለኮት ባህሪ ተካፍያለሁ 🍇 መለኮትን ተሸክሚያለሁ 🍇 የክርስቶስ ሙላቱ ነኝ 🍇 በአንደበቴ የመትከል የመፍጠር የመንቀል የመስራት የመፈወስ ሃይል አለ 🍇 የእግዚአብሔር ሙላት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ አለ 🍇 እግዚአብሔር ጋር የሌለ ነገር በእኔ ውስጥ አለ 🍇 በሽታ በእሱ ዘንድ የለም በእኔም የለም 🍇 ሞት በእርሱ የለም በእኔም የለም 🍇 ጨለማ በእርሱ ዘንድ የለም በእኔም የለም 🍇 ድህነት በእርሱ ዘንድ የለም በእኔም የለም 🍇 አባቴ ደስታ ነው እኔም ደስታ 🍇 አባቴ ፍቅር ነው እኔም ፍቅር 🍇 አባቴ ሠላም እኔም ሠላም 🍇 አባቴ ባለፀጋ እኔም ባለፀጋ 🍇 አባቴ ዲታ እኔም ዲታ 🍇🍇🍇ያማረውንና የጣፈጠውን የአንደበታችሁን ፍሬ ጌታ በጊዜው ያብላችሁ 🍇🍇🍇 እልፍ ጊዜ ሃ... ሌ ... ሉ ... ያ
Show all...
መግቢያ ወደ ሮሜ ሰዎች ጸሓፊውና የተጻፈበት ዘመን የሮሜን መጽሐፍ የጻፈው የሐዋርያው ጳውሎስ እንደሆነ (1፡1) ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ይሁን እንጂ መልዕክቱን ከጳውⶀስ አፍ ሰምቶ ቀለም ከብራና ያገናኘልን “ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።” (16:22) ብሎ ፤ ጤርጥዮስ የተባለው ሰው የሮሜን መልዕከት እንደጻፈልን ከሰላምታ ጋር ገልጾልናል። ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ56 – 58 ዓ.ም ገደማ እንደተጻፈ የሚታመነው ይህ መልዕክት ጳውሎስ በሶስተኛው የወንጌል ጉዞ ለሶስት ወር በግሪክ ቆሮንጦስ በተቀመጠ ጊዜ (ሐዋ ሥራ 20: 2 – 3) እንደሆነ ይታመናል። ታሪካዊ ዳራ ምንም እንኳ የሐዋርያው ጳውሎስ የሮሜን ሰዎች በአካል ሄዶ ባያያቸውም በ 1: 8 ላይ “እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማች አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።” እያለ በሮሜ ያሉትን ቅዱሳን ሲያመሰግን እንመለከታለን። በሮሜ ያለችው ቤተክርቲያን ማን እንደመሰረታትና እንዴት እንደተመሰረተች መጽሐፍ ቅዱሳችን በቀጥታ የሚነግረን ነገር የለም። ነገር ግን የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ላይ በበዓለ ኃምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስ በኃይል ሲወርድ “…መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።” 2:4 ብሎ እንደሚጠቁመን ፤ በተለያዩ ሀገራት ፋሲካን ሊያከብሩ የመጡ አይሁዳውያን ፤ የመጡበትን ሀገር ቋንቋ ሐዋርያቱ ሲናገሩ ሰምተው ተገርመውና ተደንቀው “የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።” 2:11 ብለው እንደተናገሩ እናስተውላለን። ከእነዚህ ሰዎች መካከል ቁጥር 10 ላይ “…በሮሜም የምንቀመጥ…” በማለት በግልጽ ከሮም የመጡ ሰዎች የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራ እንዳዩ ይጠቁመናል። ስለዚህ ከዚህ ክፍል በመነሣት ወንጌል ከእየሩሳሌም ተነስቶ ወደ ሮም እንደሄደ ይታመናል። የሐዋ 2:39 ላይ ያለውን ክፍል እንደተጨማሪ ማብራሪያ ተመልክተን ወደ መልዕክቱ ይዘት እንግባ። • “የተስፋው ቃል…” – ማለትም ወንጌሉ • “ለእናንተና…” – ከተለያዩ ሀገራት የፋሲካን በዓል ሊያከብሩ የመጡትን • “ለልጆቻችሁ…” – ለሚቀጥለው ትውልድ • “ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።” ይህም ወንጌልን ሰምተው ሊድኑ ያሉ የሰው ልጆችን ሁሉ ያጠቃልላል ።የሮሜ መልዕክት ይዘት የሮሜ መጽሐፍ መልዕክት ከጳውሎስ መልዕክቶች ሁሉ ጥልቅ ሥነ መለኮታዊ እውነትን የያዘና ልብ ማራኪ ሲሆን ረጅምም ነው። የሮሜ መጽሐፍ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች የተመደበ ሲሆን ፤ እነዚህም፦ 1. ጽድቅ ያስፈልገናል /Righteousness Needed/1:18 – 3:20/ 2. ጽድቅ ቀርቦልናል /Righteousness Provided/ 3:21 – 8:39 3. በጻድቁ ጸድቀናል /Righteousness Justified/9:1 – 11:36/ 4. ጽድቁን ተለማምደናል /Righteousness Practiced/12:1 – 15:13/ በክርስትና ዕምነት መሠረታዊ አስተምህሮዎች ላይ የተመሠረተው ይህ የሮሜ መልዕክት ኀጢአት፣ ጸጋ ፣ ቅድስና ፣ጽድቅ ፣መጽደቅ እምነት፣ድነት እና ትንሣኤ ምን ማለት እንደሆኑ ከሌሎች የጳውሎስ መልዕክቶች ይልቅ ጎልተው ይታያሉ። በ16 ድንቅ ምዕራፎች የተጻፈው ይህ መልዕክት ዋና ሊያስተላልፈው የሚፈልገው ፤ “የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጧል” የሚል ታላቅ ሃሳብ ያለው አስተምህሮ ነው። የመልዕክቱ መሪ ጥቅስ በምዕራፍ 1:16-17 ላይ የሚገኘው ቃል ነው። እንደሚከተለው ይነበባል፦ “በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። 17 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።” በሮሜ መልዕክት ውስጥ ብዙ ትልቅ ጭብጥ ያላቸው ጥቅሶች ቢኖሩም ፤ ይህ ክፍል ግን የመልዕክቱን ዋና ሃሳብ የያዘ ቃል ነው። “ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ…” ብሎ የጀመረው ጳውሎስ መልዕክቱን ሲጠቀልል “ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን ፤ አሜን።” በማለት በምስጋና (ዶክሶሎጂ) ይህንን ድንቅ መልዕክት ይዘጋዋል። @benc_nonam join join @bencnonam group #ብላቴናው_ተፈሪ t.me/teferi2530
Show all...
የአገልጋይ ስብራት ክፍል-2 የዖዛ ስብራት 2ሳሙ.6:5-9 ”ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆም በከበሮም በነጋሪትና በጸናጽል በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱ ነበር። ወደ ናኮንም አውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ። የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ድፍረቱ በዚያው ቀሠፈው፤ በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በዚያው ሞተ። እግዚአብሔርም ዖዛን ስለ ሰበረው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም የዖዛ ስብራት ተብሎ ተጠራ። በዚያም ቀን ዳዊት እግዚአብሔርን ፈራና፡- የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ይመጣል?” አለ። እግዚአብሄር በዘሁ.4፡15 ላይ አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ፥ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ ሲል አዝዞአል፡፡ ኦዛ ግን በእግዚአብሄር ታቦት አካባቢ ቸልተኝነት አሳይቶ ነበር፡፡ ማስተዋል በሌለው ሁኔታ የእግዚአብሄር ታቦት የሚንቀሳቀስበትን መንገድ ሳይጠነቀቅ ቀረ፤ ታቦቱን ማጉዋጉዋዝ ስለነበረባቸው ሰዎች ምንም እስከማይመስለው ቸል አለ፡፡ ኦዛ ታቦቱ በአባቱ ቤት በመቀመጡና እርሱም ብዙ ጊዜ አብሮት በመቆየቱ ምንነቱን ፈጽሞ ዘነጋ፡፡ ስለዚህ እስከዚያች የመቅሰፍት ሰአት ድረስ አግዚአብሄር ለራሱ ነገር የሚጠነቀቅ እስካይመስለው ስርአቱን ረሳ፡፡ ኦዛ የተቀሰፈው በታቦቱ አካባቢ ሲከናውን ስለነበረው አገልግሎት ሳይሆን የአገልግሎቱን ስርአት ባለመጠበቁና ለእግዚአብሄር ቃል ባሳየው ቸልተኝነት ነበር፡፡ ንጉስ ዳዊት የታቦቱ ወደ ስፍራው መመለስ አስፈላጊነት ስለገባው በብዙ ምስጋናና ደስታ ወደ ማረፍያው እየወሰደው ነበር፡፡ በኦዛ ላይ የተፈጠረው ስብራት ግን ወደ ሀዘንና ፍርሀት ውስጥ ከተተው፡፡ እንዲህ ከሆነ እንዴት ታቦቱ ከእኛ ጋር መጉዋዝ ይችላል ሲል ታቦቱን ከመውሰድ ተገታ፡፡ የእስራኤልን ደስታ በቅጽበት ያጠፋው ያ አስፈሪ የእግዚአብሄር ቅጣት በአገልግሎት አካባቢ ለሚኖር እንቅስቃሴ ማስጠንቀቂያ ይልካል፡፡ ለእግዚአብሄር የተቀደሱትን ነገሮች በቸልተኝነት መመልከት፣ ጥድፊያ በሚገፋው የራስ ውሳኔ ቃሉን ያላማከለ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ እግዚአብሄርን ባለመፍራት ስጋዊ የሆኑ ውሳኔዎች ውስጥ መግባት የኦዛ ስብራትን የመሰለ ቅጣት ያስከትላል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ባለን ህብረት ልባችንን አጥብቀን መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር አውቀዋለሁ በሚል ልበ-ሙሉነት ቸልተኝነትን ማንጸባረቅ ከባድ ጥፋት እንደሚያስከትል የኦዛ አገልግሎት ላይ የተፈጠረው ሁኔታ ያስተምራል፡፡ ሁላችንም እግዚአብሄር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡በተመሳሳይ የናዳብና የአቢዩድ ህይወት በአገልግሎት አካባቢ ሊደረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ያስገነዝባል፡፡ ዘሌ.10:1-5 ”የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በእግዚአብሔርም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ። እሳትም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ በላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሞቱ። ሙሴም አሮንን፡- እግዚአብሔር፡- ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀድሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው አለው፤ አሮንም ዝም አለ፡፡ ሙሴም የአሮንን አጎት የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ፡- ቅረቡ፥ ወንድሞቻችሁንም ከመቅደሱ ፊት አንሥታችሁ ከሰፈር ወደ ውጭ ውሰዱአቸው አላቸው። እነርሱም ቀርበው አነሡአቸው፥ ሙሴም እንዳለ በቀሚሳቸው ከሰፈር ወደ ውጭ ወሰዱአቸው።” በናዳብና አብዩድ ሕይወት የልብ ኩራት፣ ያለመታገስና ቅንአት ነበር፡፡ በዚያ መንፈስ ሆነው የእግዚአብሄርን እሳት ሊያቀርቡ ሞከሩ፣ ሆኖም ሞገስ ሳይሆን መቅሰፍት በራሳቸው ላይ ሳቡ፡፡እግዚአብሄር በአገልግሎት ወደ እርሱ በሚቀርቡ ሁሉ እንደሚቀደስ ተናግሮአልና ያን በማያንጸባርቅ አካሄድ ማገልገል ፍርድ ይጋብዛል፡፡ ናዳብና አቢዩድ አስቀድሞ የነበራቸው ልምምድ ብዙ ነበር፡-እግዚአብሄር ህዝቡን ከግብጽ ሲያወጣ ያደረገውን ታላላቅ ታምራት የተመለከቱ ናቸው፤ ነጐድጓድና መብረቅ ከባድም ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በሲና ተራራ ላይ ሲገለጥ አይተዋል፤ ሙሴ አሮንም ናዳብም አብዩድም ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወደ እግዚአብሔር ወጥተው በርሱ ፊት ሰግደዋል፣የእስራኤልን አምላክ አይተዋል፣በዚያ ስፍራ በፊቱ በልተዋል ጠጥተዋልም፡፡ ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ እነዚህ ሁለት ሰዎች ልዩ እሳት (መሰዊያ ላይ የሚነደውን የእግዚአብሄር እሳት ሳይሆን እራሳቸው ያዘጋጁትን እሳት) ይዘው አግዚአብሄር ፊት ቀረቡ፡፡ ያቀረቡት እሳት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ፣ እንዲያውም ያቀረቡት እሳታቸው ከእግዚአብሄር ዘንድ ሌላ የመቅሰፍት እሳት ጠራባቸው፡፡ ናዳብና አቢዩድ የነበራቸው ታላላቅ የአገልግሎት ልምምድ በመቅሰፍት ከመመታት አላዳናቸውም፡፡ ምክንያቱም በእግዚአብሄር ፊት ሊያቆማቸው የሚችለው እንደቃሉ የሆነ ግንኙነት እንጂ ያሳለፉት መንፈሳዊ ልምምድ እንዳልሆነ ስላላስተዋሉ ነው፡፡ ይቀጥላል... ምንጭ፦ tsionvoice.com
Show all...
🙏ማረን🙏 ሳንፈለልገው ያስፈለገን፣ ጥለነው የጠቀመን፣ ሚጠቅመንን ወዲያ ጥለን፣ ማይጠቅመንን ስንል ስጠን፣ ያለን በዝቶ ምን ይሰጠን። ላለመኖር ምክንያት ፈጥረን፣ ላለን ደስታ እሩቅ ሁነን፣ ካዘናችን ጎን ቁጭ ብለን፣ ፍጥረታትን ሁሉ ረግመን፣ ካምላካችን እምነት ጎሎን፣ ሲጨመረን ጎደለብን፤ ሲበዛልን አነሰብን፤ ብለን ፈጣሪን አምርረን፣ ከፍጥረታት በላይ ሁነን፣ ፍጥረታትን ግዙ ተብለን፣ ተማረክን እጅ ሰጠን ፣ ከፍጥረታት በታች ሆንን፤ በኛው ድክመት አማረርን ፣ ፈጣሪያችንን አሳዘንን፣ ባለማወቅ ስተት ሰራን፣ አምላካችን ይቅር በለን🙏 ያለንንም ባርክልን፣ በደላችንንም ሰርዝልን፣ እንደ ደግነትህም አንተው ማረን። ማረን 🙏 ማረን🙏 ማረን🙏
Show all...
“ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም።”                   ( ሉቃስ 1፥37 )         ፍጥረታችን ከጭንቀት ነፃ የሆነ አይደለም። ስለዚህ እንጨነቃለን። የምንጨነቀው የሚያስጨንቅ ነገር ስላለ ነው። ከጭንቀት ውስጥ አንዲት መስመር ጥቅም አናገኝም። ጭንቀትን ብዙ ነገሮች ይፈጥሩታል። በእኛ ሀገር ያለው የጭንቀት መንስኤ ድህነት ነው። እንደ ድህነት አስከፊ ነገር የለም። ድህነት መጥፎ ውሳኔ እንድትወስኑ ያደርጋችኋል። የሰው ፊት ያሳያችኋል፣ ያሰርቃችኋል፣ ያስዋሻችኋል፣ የማትፈልጉትን ውሳኔ ያስወስናችኋል።         ጭንቀት ውስጥ የገባ ሰው ያስጨነቀው ነገር እሚያልፍ አይመስለውም ነገር ግን ላያልፍ የመጣ ምንም ነገር የለም እግዚአብሔርን መመልከት ከቻልን እናልፈዋለን። ወዳጆቼ ቤታችሁ ፈራሽ ነውና ተነሱ ብሎ መንግስት ቢያውጅባችሁና ጎናችሁን ማሳረፊያ አንዳች ባይኖራችሁ እኔ አለሁላችሁ መኖሪያችሁ የዘለዓለም አምላክ እግዚአብሔር ነኝ ያለው ጌታ አለላችሁ፤ አዕምሯችሁን አስጨንቆ የሚይዝ ችግር ቢገጥማችሁ አዕምሮን ሁሉ የሚያልፍ ሰላም ያለው ጌታ ከናንተ ጋር ነው፤ ትሞቻለሽ የቀረሽ የወራት እድሜ ነው ብሎ ሀኪሙ ቢያረዳሽ አይዞሽ ሞቶ የሸተተውን አልዓዛርን ከመቃብር ያወጣ ጌታ ዛሬም ካንቺ ጋር ነው። የሰማችሁት ድምፅ ተስፋ አስቆራጭ አስጨናቂ ቢሆንም ድምፅን በድምፅ የሚሽር ጌታ ከናንተ ጋር ነው።          እግዚአብሔር መልዓኩ ገብርኤል ወደ ድንግል ማርያም ልኮ ትወልጃለሽ የሚል ብስራት ነገራት። ትወልጃለሽ ያላት አግብታ ልጅ እምቢ ስላላት አይደለም፤ ሳታገባም የመውለድ ጉጉት አድሮባት ስለነበር አይደለም። ድንግል ማርያም ብስራቱን ስትሰማ የአስራ አምስት ዓመት እድሜ ያላት ትንሽ ልጅ ናት። በማርያም እድሜ ሊታሰብ የሚችለው ጠንክሮ መማር፣ ለቤተሰቦቿ መታዘዝ የሚል እንጂ የመውለድ እቅድ አይደለም።          እግዚአብሔር ግን ልጅነትን ያልጠገበች ትንሿን ብላቴና እናት አደረጋት። እናት ለመሆን ሴትነትን፣ እናትነትን፣ ድርሻን፣ ኃላፊነትን፣ ሙያን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል። እግዚአብሔር ግን የተፈጥሮ ህግ ከሚለው አልፎ የሚሰራ አምላክ ነውና ማርያምን ለእናትነት መረጣት።          ወዳጆቼ ዛሬ ይሄንን ለማድረግ ይሄ ያስፈልገኛል፣ ይሄ ስለሌለኝ ይሄኛው ጉዳዬ አይሳካም የሚል ስሌት ውስጥ ካላችሁ እግዚአብሔርን ጣልቃ አስገቡት። እርሱ ምንም በሌለበት አንዳች መስራት ይችላል። ወንድ የማታውቀው ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳለች ይህ በተፈጥሮ ህግ አይታሰብም ለእግዚአብሔር ግን የሚሳነው የለም። ያንተም ገዳይ ከአቅምህ በታች ቢሆን፣ ያንቺ ጉዳይ ከእውቀትሽ ከጥበብሽ በላይ ቢሆን፣ የናንተ ጉዳይ ከብልሃታችሁና ከችሎታችሁ በላይ ቢሆን አይዟችሁ ከጉዳያችሁና ከችግራችሁ በላይ የሆነ እግዚአብሔር አለ። እርሱ የሚሳነው የለምና ጉዳያችሁን ይሰራላችኋል። የዕረፍት ቀን ይሁንላችሁ።
Show all...
Add a comment