cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

FIDEL POST NEWS

Fast news about Ethiopia

Show more
Advertising posts
13 822Subscribers
+7024 hours
+5277 days
+2 47630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጥያቄ? የቸኮሌቱ እና በፕላስቲክ የታሸገ ውሃ ዋጋ በድምሩ 110 ብር ነው። የቸኮሌቱ ዋጋ ከታሸገው ውሃ ዋጋ በ መቶ ብር ይበልጣል። የታሸገ ውሃው ዋጋ በተናጥል ስንት ነው?
Show all...
👍 3
በቋሚ ፈገግታው ምክንያት ኩካካ በጣም ደስተኛ እንስሳ እንደሆነ ይታወቃል።
Show all...
😁 7
የቡድን ሰባት ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ በኢትዮጵያ ያሉ “ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ የቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ይታያሉ ያሏቸው፤ “የማያቋርጡ እና ኃይለኛ ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ። በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ይፈጸማሉ የሚባሉ “የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በደሎች ሪፖርቶች”፣ “ብርቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ” እና “የምግብ ዋስትና እጦት መስፋፋት” እንዳሰጋቸውም አስታውቀዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስጋታቸውን ያንጸባረቁት፤ በጣልያኗ ካፕሪ ደሴት ያካሄዱትን ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ዛሬ አርብ ምሽት ባወጡት መግለጫ ነው። ሚኒስትሮቹ በዚሁ መግለጫቸው፤ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በተፈረመው ግጭት የማቆም ስምምነት አተገባበር ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎችን በበጎ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል። በሰብዓዊ መብቶች እና በሲቪል ሰዎች ጥበቃ፣ ውጥረቶችን ለመፍታት በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት፣ በዕርቅ፣ በብሔራዊ ውይይት፣ የሽግግር ፍትህ እና በግጭት ወቅት ወንጀል የፈጸሙ ተጠያቂ ለማድረግ ተጨማሪ እና ዘላቂ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ አበረታተዋል። በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመካሄድ ላይ በሚገኙ ግጭቶች የሚሳተፉ ወገኖች፤ በንግግር ሰላም ለማውረድ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርበዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Show all...
👍 5👎 1
👍 1
የአንድ አመት ልጁን ከእነ ህይወቷ ለመቅበር የሞከረው ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር ዋለ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን  ቤንች ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፒክተር አለማየሁ አማረ ለክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን እንደገለፁት በወረዳው ኮሶል ቀጭን መንደር ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረው  ፀብ ምክንያት የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡ አዛዡ አክለውም በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ ፀብ እናት  የአንድ ዓመት ሴት ህፃን ልጅ ጥላ በመጥፋቷ ወላጅ አባት ቲቲዮስ ኪያግላስ የተባለው ተጠርጣሪ የአንድ ዓመት ህፃን ልጁ እያለቀሰች ስታስቸግረዉ በሁኔታው ተበሳጭቶ የአንድ አመት ልጁን  በህይወት ለመቅበር ጉድጓድ  ሲያዘጋጅ የተመለከቱ የአከባቢው ነዋሪዎች  ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣሉ፡፡ ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪውን  ጉድጓድ እየቆፈረ እያለ በቁጥጥር  ስር እንዲውል በማድረግ ህፃኗን ጉዳት ሳይደርስባት መታደግ መቻሉንና በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ ፖሊስ የህፃኗን ወላጅ እናቷን እያፈላለገ ሲሆን ህፃኗ በአሁን ሰዓት ሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ እንክብካቤ እያደረገላት እንደሚገኝ የገለፀት ፖሊስ አዛዡ በቤተሰብ መካካል አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ወቅት ችግሩን በመነጋገር መፍታት ይገባል ሲሉ ፖሊስ አዛዡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ፋስት መረጃ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን መረጃ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
Show all...
👍 6👏 1🤯 1
1
ራይድ እና ቪዛ የትራንስፖርት ክፍያን ለማቀላጠፍ ተጣመሩ፡፡ በኢትዮጵያ ቀዳሚው የጥሪ-ትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ራይድ እና ታዋቂው ዓለም አቀፍ የድጂታል ከፍያ ተቋም ቪዛ ጎብኚዎች፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች እና የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የትራንስፖርት ክፍያቸውን በራይድ መተግበሪያ አማካኝነት ለመፈጸም የሚያስችለውን ጥምረት በዛሬው ዕለት አበሰሩ። ይህ ጥምረት ጎብኚዎች፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች እና ዲያስፖራዎች የቪዛ ካርዳቸውን ብቻ በመጠቀም የመጓጓዣ ክፍያቸውን እንዲያከናውኑ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አማራጭ የማቅረቡ ጥረት ጅምር ነው፡፡ በዚህም መንገደኞች ስለ ገንዘብ እና ምንዛሪ ሳይጨነቁ በኢትዮጵያ አርኪ ቆይታ እንዲኖራቸው ያግዛል። የራይድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳምራዊት ፍቅሩ “ለጎብኚዎች፣ በኢትዮጵያ ለሚኖሩ የውጭ አገር ሰዎች እና ለዲያስፖራ አባላት ይህንን አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የክፍያ አማራጭ ለማቅረብ ከቪዛ ጋር መጣመራችን አርክቶናል'' ብለዋል። አያይዘውም “ትብብሩ የኤፌዲሪ መንግስት በቅርቡ ካስጀመረው የድጂታል ኢትዮጵያ 2025' ትልም ጋር በጥብቅ ከመተሳሰሩ በተጨማሪ፤ የራይድን መተግበሪያ ለመጠቀም በጎብኚዎች በኩል የታየውን ፍላጎት በብቃት ለማስተናገድ ያለንን ተነሳሽነት ያመላክታል" ሲሉ አክለዋል። በኢትዮጵያ የቪዛ ዳይሬክተሩ አቶ ያሬድ በበኩላቸው “ቪዛ የተቀላጠፈ እና አስተማማኝ የድጂታል ክፍያን ለሁሉም እና በሁሉም ቦታ ለማዳረስ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል። “ከራይድ ጋር የተጀመረው ጥምረት በዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ አስተማማኝነቱ የተመሰከረለትን የቪዛ ክፍያ ሥርዓት በማቅረብ የኢትዮጵያን የጉዞ እና ቱሪዝም ዘርፍ ለመደገፍ ተቋማቸው ያነገበውን ቁርጠኝነት እንደሚያመላክት" ጠቅሰዋል። ራይድ በቀልጣፋ የሞባይል መተግበሪያ እና በ8294 የጥሪ ማዕከል አማካኝነት በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መንገደኞችን ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር የሚያገናኝ ፈር ቀዳጅ የጥሪ-ትራንስፖርት ድርጅት ነው። ራይድ ከተመሰረተበት ከ2006 ዓ.ም አንስቶ የአፍሪካዊያንን የዕለት ተዕለት ኑሮ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳለጥ ያለመ ተዓማኒ፣ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተጋ ይገኛል። በኢትዮጵያ በሦስት ከተሞች የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቋሚ ደንበኞችን በብቃት ያገለግላል። እንዲሁም በዛሬዉ እለት ከራይድ ጋር ጥምረቱን  ያደረገዉ  ቪዛ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ደንበኞቹ፣ ለንግድ እና የገንዘብ ተቋማት እና ለመንግታዊ ድርጅቶች የድጂታል ከፍያንየሚያከናውን ዓለም አቀፋዊ ተቋም ነው። ቀዳሚ ተልዕኮውም ግለስቦች፣ የንግድ ድርጅቶች እና ኢኮኖሚዎች ኦይበልጥ እንዲጎለብቱ እና እንዲሳለጡ ማስቻል ነው። ቪዛ በዓለም ዙሪያ ከ 200 በላይ ሀገራት የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች አሉት። ድጂታል ኢትዮጵያ “የአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ዋነኛ መገለጫ የሆነውን የድጂታል ትራንስፎርሜሽን በይፋ ተቀላቅሎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምራለች፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በኢፌዲሪ መንግስት አስተባባሪነት “ድጂታል ኢትዮጵያ 2025” የተሰኘ መርሐ ግብር ተቀርፆ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ፈጣን እና የተሳለጠ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊለውጥን ለመተግበር የድጂታል ቴክኖሎጂን ያማከለ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂ ተነድፏል። የድጂታል መታወቂያ፣ የድጂታልክፍያ እና የሳይበር ደህንነት ውጥኖች የዚህ ስትራቴጂ ቁልፍ ነጥቦች ናቸው። ለዚህም የዲጂታል ክፍያን ቀልጣፋ ለማድረግ አቢሲኒያ እና እናት ባንክ አንድ ላይ በመሆን እንደሚሰሩ አብስረዋል።
Show all...
👍 7 1
ቤተልሔም ወልዴ በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ሻምፒዮና ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ከደቡብ አፍሪካ አቻዋ ጋር የተጋጠመችው ቤተልሄም ወልዴ በበቃኝ አሸንፋለች፡፡ የመላው አፍሪካ ሻምፒዮኗ ቤተልሄም ወልዴ በሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ሀይለኛ ቡጢ በማሳረፍ ነው በዳኛ ውሳኔ ያሸነፈችው፡፡ በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያን የወከሉት አቡዱሰላም አቡበከር፣ አቡበከር ሰፋን እና ኤርሚያስ መስፍን በተጋጣሚዎቻቸው መሸነፋቸውን ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Show all...
5😁 3
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በአዲስ መልክ ተዋቀረ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት ባደረገው ስብሰባ ውሳኔ አሳልፏል። ኮሚቴው በአዲስ መልክ እንዲዋቀር መነሻ የሆነው ጥቅምት 19/2016 በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የፀደቀው የተሻሻለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደርያ ደንብ ሲሆን በደንቡ አንቀፅ 46 (ቁጥር 2) ላይ ቋሚ ኮሚቴዎች የሚቋቋሙበት ሁኔታ ሲገልፅ "ከብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በቀር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይም ምክትል ሰብሳቢ ሆኖ መስራት ይችላል። " ይላል። የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴን አወቃቀር እና አሠራር ገለልተኛ ለማድረግም አባላቱ ከሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ውጪ እንደሚሆኑ በደንቡ ላይ ተቀምጧል። በዚህም መሠረት የተሻሻለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደንብ ለፊፋ ተልኮ እንዲፀድቅ በመደረጉ ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር የተወሰነ ሲሆን ከዚህ ቀደም በኢንተርናሽናል ዳኝነት ሲያገለግሉ የቆዩ ግለሰቦች በአመራርነት ተመርጠዋል። በአዲሱ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ የተመረጡት አባላት የሚከተሉት ናቸው:- ዋና ሰብሳቢ - ሸዋንግዛው ተባባል ምክትል ሰብሳቢ - ሊዲያ ታፈሠ አባል - ለሚ ንጉሤ አባል - ክንዴ ሙሴ አባል - ክንፈ ይልማ
Show all...
👍 6