👉
#አገልጋይ ዮናታን እክሊሉ
🔹
#ሠው_ሁን
የትኛው ሰው መሆን ትፈልጋላችሁ ??
-በምድራችን ትላልቅ ነገሮች እንዲከናወኑ ያደረጉት 1% የዓለማችን ሰዎች ናቸው የቀሩት 99% ድርጊቱን የሚከተሉ ሰዎች ናቸው
-የተለየ ተግባር ከመገንባት በፊት የተለየ ጠንካራ ስብእናን መገንባት ይቀድማል
-ጠንካራ ስብእናን በገነባን ቁጥር በቤተክርስቲያን ውስጥ ለረጅም ጊዜ የመቆየት አቅም ይፈጠራል
-ፀጋው በጠንካራ ስብእና አይደለም የመጣው ፀጋው ከመጣ በኋላ ግን ጠንካራ ስብእና ያስፈልጋል
#5_አይነት_ሰዎች_አሉ
1, አቋራጭ ሰዎች
2, ስህተት ፈላጊ ሰዎች
3, ወላዋይ ሰዎች
4, ጫና ፈጣሪ ሰዎች
5, የመፍትሄ ሰዎች
-------------------------------------
1, አቋራጭ ሰዎች
-ሳይጀምሩ ሚሸነፉ እና ሁሌ ሃሳብ የሚያቀርቡ ናቸው
-መፍትሄ ያለው አለቃዬ ጋር ነው ብለው ያስባሉ
-ፍፃሜያቸው ጋር ለመድረስ ችግሮቻቸውን ከመጋፈጥ ይልቅ የመሸሽ ወይም ደግሞ ሌላ ቀን እንደርስበታለን ብለው የማሰብ ባህሪ አላቸው
-ለእነሱ ችግር ሌላ ችግር ያስከትላል እንጂ መፍትሔ አይታያቸውም
2, ስህተት ፈላጊ ሰዎች
-በባህሪያቸው ችግር በመተንትን ለምን እንጀማይቻል ለማስረዳት የሚሞክሩ ናቸው
-ፍፃሜክ ጋር ስደርስ ከከፈልከው ዋጋ ጋር የማይመጣጠን ቢሆንስ ብለው ያስባሉ
-ችግሩ የማይፈታበት መንገድ መዘርዘር ትልቁ ብቃታቸው ነው
-እንዴት እንደማይቻል/ችግሩ የማይፈታባቸውን/ ሁኔታ ማስቀመጥ ደስታቸው ነው
ምሳሌ
የከሰልን ጥቁረት በሳሙና አጥበሽ አስለቅቂው፡፡
አይለቅም
የከሰሉ ያለመልቀቅ ከከሰሉ ማንነት የተነሳ እንጂ ሳሙናው የማስለቀቅ አቅም ሳይኖረው ቀርቶ አይደለም
#እናንተ የምትብራሩት እግዚአብሔር እናንተን ከሰራበት ዓላማ እንጂ በየፌርማታው ካጋጠማችሁ ነገር አንፃር አይደለም
3, ወላዋይ ሰዎች
-በችግሩ እና በችግሩ የመፍትሄ ሀሳብ መካከል እያመሳከሩ የሚኖሩ ሰዎች ናቸው!
-ይነሳሳሉ እንጂ አይነሱም!!!
-በባህሪያቸው ችግር አካፋዮች ናቸው
-ሰዎች ከግባቸው ጋር እንዲደርሱ የጠራ ሃሳብ የላቸውም
4, ጫና ፈጣሪ ሰዎች
-በችግራቸው ፊት መቆም አይፈሩም
-ይወድቃሉ በመውደቅ አያምኑም ይነሳሉ ነገር ግን ወድቀው የተነሱበት ቦታ መፍትሔ መፈለጋቸው ሁለተኛ ውድቀት ነው
-መፍትሄ ሚፈልጉት እዛው የወደቁበት ቦታ ላይ ሆነው ነው
-በጣም ጠንካራ ናቸው
-በጉልበታቸው ሊጠቀሙ ይሻሉ
5, የመፍትሄ ሰዎች
-ይወድቃሉ ነገር ግን ተመለሰው ይነሳሉ ሲነሱ ግን ከወደቁበት ቦታ ሳይሆን አንድ እርምጃ ወደ ኋላ ይመለሱና የወደቁበት ምክንያት አካባቢያቸውን በማጣራት ይጀምራሉ
-ግባቸውን ሳይሆን አካሄዳቸውን ለውጠው ወደ ህልማቸው መፍትሄ ሰጥተው ይቀጥላሉ!!!!
-ከወደቁበት ቦታ ለመጀመር የሚያስቡ ሰዎች ናቸው
-የመፍትሔ እንጂ የችግር አካፋዮች አይደሉም
-መሪውን ከያዙ በኋላ አካባቢያቸውን ያያሉ
-ግባቸው ጋር ለመምጣት ሃይልን ከጥበብ ጋር ይጠቀማሉ
-ችግርን የመፍትሔ ሌላ ዘዴን የመፈለጊያ አድርገው ይጠቀሙበታል
-ወደ ኀላ መመለስ መሸነፍ አይደለም
-ወደ ኋላ መመለስ እና ትዝታም ማስወገድ አንዱ የመፍትሄ አካል ነው
ምሳሌ
እጮኝነት ጀምሮ የተቋረጠበት ሰው ሌላ ከመጀመሩ በፊት ትውስታን/ትዝታ ማጥፋት አለበት
#ግብ ሳይሆን አካሄድ ነው የሚቀየረው
#ትናንት የወደቅንበት የህይወት ክፍል መማሪያ እንጂ ግብ መቀየሪያ መሆን የለበትም
#ተቃዋሚ ያልገጠማችሁ ትክክል ስለሆናችሁ ሳይሆን ስራ ስላልጀመራችሁ ነው
#አስቸጋሪ ነገር ሲገጥማ ችሁ በጉልበት (በስልጣን) ሳይሆን በእውቀት ግጠሙት
#እንደገና ማረፍ ከሄዳችሁበት ወደ ኋላ መመለስ ግባችሁ ጋር የምደርሱበት አካሄድ ነው
#ጫና ብቻውን ያጋጫችኋል እንጂ አያስኬዳችሁም
#መርገጥ ብቻ ሳይሆን መልቀቅም አንዱ የመንዳት ጥበብ ነው
#አካባቢን መቃኘት መፍትሄ ነው
የሚተኩስብህ ወታደሩ ሳይሆን ያዘዘው ጄኔራሉ ነው ስለዚህ የተኮሰብክ ሳይሆን ያዘዘብህ ነው ጠላት
#ህልማቸውን የሚያሳኩ ሰዎች ድርጊታቸውን የሚያከናውኑበት አካሄድ አላቸው
#አንተ ውስጥ ያለውን አንተ ታውቀዋለህ ወደ ኋላ መመለስህ ባንተ ውስጥ ያለውን እንዲያወሩ ለማረግ ዕድል መስጠት ነው
#ጋሻና ጦር የሆነ ወቅት ሰርቷል ማለት አሁን ላይ ይሰራል ማለት አይደለም
#አገልጋዮች ናችሁ በፍጹም እንዳታወላውሉ በወደቃችሁበት ቦታ መፍትሔ እንዳትፈልጉ
#አገልጋይ ግቡን እንጂ የማይለውጠው ወደ ግቡ የሚደርሱበትን አካሄድ ይቀይራል
#ዮርዳኖስ ስትረግጠው እንጂ አጠገቡ ስለቆምክ አይደለም የሚቆመው
#መድረክ ላይ ስትቆም ዓለምን እያየክ ነው ማውራት ያለብክ የዛኔ ነው ትልቅ አገልጋይ የምትሆነው
#ችግር ሲፈጠር መጣያ አታድርግ መፍትሔ መፈለጊያ አድርገህ ተጠቀምበት
#ስለዚህ በተራ ሰው እና በዋና ሰው መካከል ያለዉ ልዩነት ግብን ጠብቆ መጓዝ እና ግብን ጠብቆ መቅረት ነው
#በመጨረሻው እና በሌሎች ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ጥበብ እና የሃይል አጠቃቀም የጭንቀት እና የመፍትሔ ሰዎች የመሆን በቂ ነው።
@melkaam_wetat_2013
@melkaam_wetat_2013
@melkaam_wetat_2013
@melkaam_wetat_2013
@melkaam_wetat_2013
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
♨️🚄♨️♨️♨️🚄♨️🚄♨️♨️♨️♨️🚄
🔥♨️🔥♨️🔥♨️♨️♨️🔥♨️♨️♨️🔥♨️🔥🔥🚄♨️♨️🚄🔥🔥🚄🚄🔥🔥🔥♨️
Show more ...