cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

እንኳን ደህና መጡ‼ ✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed ✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏

Show more
Advertising posts
206 312Subscribers
-42424 hours
+2 6737 days
-14830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሿሿ በቲክቶክ "ታማሚው ስለማይድን የተሰበሰበውን ብር ሰይጣን አሳስቶን አጠፋነው. . ." ከሞተር ወድቆ ከወገብ በታች ለማይንቀሳቀሰው አለሙ ቢጫ ለተባለ ግለሰብ የተለያዩ ቲክቶከሮች የእርዳታ ገንዘብ ቢሰበስቡም ለታማሚው ብር ሳይደርስ ቀርቶ ታማሚው ባቀረበው ተማፅኖ ብሩን የሰበሰቡት ቲክቶከሮች የተወሰነ ብር ቢመልሱም ዋነኛውና በምስሉ የሚታየው ወጣት ግን 350,000 ሺህ ብር አካባቢ ለመመለስ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ሰምተናል። ለዚህም የቀረበው ምክንያት " ታማሚው ስለማይድን ብሩን አጥፍቼዋለሁ . . . ቲክቶክ አካውንቴን ሸጬ እከፍላለሁ" የሚል ነበር።የቲክቶክ ሿሿ ይሏል ይሄ ነው።"ይሞታል ብለን"ያሳዝናል። Via: ስንታየሁ ኃይሉ
Show all...
ADVERTISMENT ታላቅ የምስራች ከDMC realestate በመሀል ከተማ በለቡ መብራት በሚገኘው  እጅግ ውብ እና ቅንጡ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በ10% ቅድሚያ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ 65,000 ካሬ ላይ ያረፈ መንደር ከstudio  እስክ 4 መኝታ ድረስ በፈለጉት የካሬ አማራጭ ከምቹ አከፋፈል ጋር ✨50/50 የባንክ አማራጮችን አዘጋጅተናል 👉studio  58 ካሬ 👉ባለ አንድ መኝታ ከ77ካሬ-98ካሬ 👉ባለሁለት መኝታ ከ123ካሬ-155ካሬ 👉ባለሶስት መኝታ ከ146-181ካሬ 👉ባለአራት መኝታ ከ177ካሬ ጀምሮ 👉የልጆች መጫወቻ 👉የመዋኛ ገንዳ 👉ጂም እና ስፓ 👉የኤሌክትሪክ መኪና charge ቦታ ሁለት አመት ባነሰ ጊዜ የቤት ባለቤት ሊያደርግዎ ተዘጋጅቷል፡፡  👉ለጥቂት ቤቶች ብቻ ከ8%-25% ቅናሽ አድርገናል Tip:- ፈጥነው ከመጡ 2ኛ እና 3ኛ floor ላይ መግኘት ይችላሉ ! ታድያ ምን ይጠብቃሉ …አሁኑኑ  ወደ DMC realestate ይደውሉና የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ይሁኑ! …….ያስተውሉ ቀድሞ የመጣ ቀድሞ ይስተናገዳል  እንዲሉ ዛሬ ነገ ሳይሉ አሁንኑ 👉☎️0977019814 እና 0961396467       በመደወል  ይመዝገቡ፡፡
Show all...
የቡድን-7 አገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ በኢትዮጵያ የሰፈነው ውጥረትና ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር የተፈራረመችው የባሕር በር መግቢያ ስምምነት እንደሚያሳስባቸው ትናንት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። አገራቱ፣ ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ "ኹሉንም የንግግር መስመሮች" ክፍት በማድረግ ውጥረቶችን እንዲያደርግቡ ጠይቀዋል። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የኢኮኖሚ ቀውስና የምግብ ዋስትና ማሽቆልቆል አሳሳቢ እንደኾኑም አገራቱ ገልጸዋል። የቡድኑ አባል አገራት፣ የመንግሥት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ዘላቂ እንዲኾን፣ ሲቪሎችን ከጥቃት እንዲጠበቁ፣ ውጥረቶች በፖለቲካዊ ንግግር እንዲፈቱ፣ እርቅ፣ የሽግግር ፍትህና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጥሪ አድርገዋል። በተያያዘ ዜና የቡድን-7 አገራት፣ ሱማሊያና ኢትዮጵያ በባሕር በር መግቢያ ዙሪያ የገቡበትን ውጥረት ለመፍታት "ኹሉንም የንግግር መስመሮች ክፍት እንዲያደርጉ" ላቀረቡት ጥሪ፣ የሱማሊያ መንግሥት ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ ባወጣው መግለጫ አሉታዊ ምላሽ ሰጥቷል። የሶማሊያ መንግሥት፣ ኢትዮጵያ ከሰሜናዊቷ ግዛቴ ሶማሊላንድ ጋር የደረሰችበትን የባሕር በር መግቢያ የመግባቢያ ስምምነት እስካልሰረዘችና የሱማሊያን አንድነት፣ ሉዓላዊነትና በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህ ሙሉ በሙሉ እስካላረጋገጠች ድረስ፣ ንግግር ማድረግ የሚሳካ ነገር አይደለም ብሏል።(Wazema)
Show all...
👍 7 2🥰 2👏 2😁 2😱 2🔥 1
ADVERTISMENT አፊያ ሙሀመድ ከፍተኛ የባህል ሕክምና እና ዘመናዊ የዋግምት አገልግሎት   የምንሰጣቸው የባህል ህክምናዎች ➢ ለውጭና ለውስጥ ኪንታሮት ➢ ለማድያት ➢ ለሱኳር በሽታ ➢ለጉበት(ለወፍ በሽታ) ➢ለጨጎራ ህመም ➢ለስፈተወሲብ ➢ለደም ግፊት ➢ለአስም ወይም ሳይነስ ➢ለሚጥል በሺታ ➢ ለእሪህና ቁርጥማት ➢ለራስ ህመም (ማይግሪን) ➢ለቺፌ ና ለጭርት ➢ለቋቁቻና ፎረፎር ➢ለእጢና ለእባጭ ➢ለወገብ ህመም ➢ለመካንነት ለወድም ለሴትም ➢ለጆሮና ለአይን ህመም ➢ለሆድ ህመም ➢ዘመናዊ የዋግምት አገልግሎት በተቋማችን እንሰጣለን። 👉ከኢትዮጵያ ባህላዊ ህክምና አዋቂዎች ማህበር በዘርፉ ህጋዊ የባህል ህክምና ፍቃድ ያለን ነን። አድራሻ:አዲስ አበባ አየር ጤና    ስልክ ቁጥር   📲0927506650                          📲0987133734                          📲0956522222 ቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/+08vmUP_ntvE5NmM0
Show all...
እስራኤል በኢራን ላይ የድሮን ጥቃት መሰንዘሯን ዛሬ አስታውቃ ነበር።ኢራን በበኩሏ በዋና ከተማዋ የድሮን ጥቃ ነበር ነገር ግን በእስራኤል የተፈፀመ አይደለም፣ብላለች።በዚህም ወደ እስራኤል የአፀፋ ምላሽ የምሰጥበት ምክንያት የለም በማለት የአለም የእለቱን ትልቅ ውጥረት ማርገብ ችላለች።
Show all...
🤣 30👍 23 14😢 4🤔 1
Update "መቂ ከተማ አንድ የአይሱዙ ሹፌር ተገድሏል፣ረዳቱ ጉዳት ደርሶበታል" ነዋሪዎች ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን መቂ አካባቢ “ የታጠቁ ኃይሎች ” በአሽከርካሪና ረዳት ላይ ጉዳት እንዳደደረሱ ፣ ከወራት በፊትም በርካታ ተሽከርከርካሪዎች ታቃጥለው እንደነበር ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ቃላቸውን የሰጡ የመቂ ነዋሪ ፥ አንድ የአይሱዚ ሹፌር ሲገደል ፣ ረዳቱ አካላዊ ጉደት እንደረሰበትና ሌሎች ተሽከርካሪዎች በጥይት እንደተበሳሱ አስረድተዋል። " የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው ሹፌሩ ተገደለ። ሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ/ም ነው የተቀበረው ፤ ረዳቱም ቆሰለ " ሲሉ ነው የተናገሩት። የተኩስ እሩምታ የተከፈተባቸው ከ7 በላይ ተሽከርካሪዎች መሆናቸውን ጠቁመው " ተዘግቦ እንኳን አየዋለሁ ብዬ ነበር የዘገበው ሚዲያ የለም " ብለዋል። ሟቹ ሹፌር መነሻውን አዲስ አበባ በማድረግ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት መቂ አካባቢ ማታ ላይ በታጣቂዎች ተኩስ እንደተከፈተበት አስረድተዋል። " ሌሎቹ ሹፌሮች ፈጣሪ አትርፏቸው አልተጎዱም። ተሽከርካሪዎቻቸው ግን በጥይት ተበሳስተዋል። ጎማው እስከ 15 ጥይት ያረፈበት አለ " ብለዋል። እኚሁ ነዋሪ ታጣቂዎች " ወደ ኦሮሚያ ተሽከርካሪ እንዳይሄድ ሰሞኑን እቀባ ጥለዋል " ያሉ ሲሆን ጥቃቱን በከፈቱ በማግስቱ " ከመከላከያ ጋ ተታኩሰዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
Show all...
👍 10😢 9💔 6
ሸገር ከተማ እስከ የመንግስት ቢሮዎች እስከ ምሽት 4:00 ክፍት ተደረጉ😳 በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ከተሞችን በማቀናጀት የተፈጠረው ሸገር ከተማ አስተዳደር ከትናንት ጀምሮ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑ ተሰምቷል። ከትናንት ሚያዝያ 10/2016 ዓም ጀምሮ በሸገር ከተማ በአስራ ሁለቱም ክፍለ ከተማ ከጠዋት 2:30 እስከ ምሽት 4:00 ሰዓት አገልግሎት የመስጠት ስራ መጀመሩ ነው ዛሬ የተሰማው።ፋስት እንደዘገበው በከተማ አስተዳደሩ ቅዳሜ ሙሉ የስራ ቀን እንዲሆን ተወስኗል። 👉 የበርካቶች አስተያየት ጅምሩ ጥሩ ነው።ነገር ግን ሸገር ከተማ ያለ ሙስና ቀን አይን በአይን አልተቻለም እንኳንስ ምሽት የሚል ነው።በእጅ መንሻ ካልሆነ ሰዎች ፍፁም አገልግሎ የማያገኙበት ብቼኛ አስተዳደር እያስባለው ነው የሚሉት አስተያየት ሰጭዎች ሰዓት ከመጨመር አይን ያወጣውን የመልካም አስተዳደር ጥሰት ማረም ቢቀድም ጥሩ ነው ይላሉ።የምሽት ስራ በአዲስ አበባ ከተማም ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ መገለፁ ይታወሳል።
Show all...
👍 47😁 27 4😱 3
የአማራ ክልል ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም ይቅርታውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሠጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በክልሉ የይቅርታ አሠጣጥ መመሪያዎች መሠረት በበጀት አመቱ ሁለተኛ ዙር በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን አንስተዋል። በይቅርታው በማረሚያ ቤት ቆይታቸው በመታረምና በመታነፅ አርአያነት ያሳዩ፣ ከተበዳይ ወገኖች ጋር እርቅ የፈፀሙ፣ አስፈላጊውን ካሳ የከፈሉ እና ለማህበረሠቡ የወንጀልን አስከፊነት እንደሚያስተምሩ የታመነባቸው 1 ሺህ 431 ወንድ እንዲሁም 29 ሴት ታራሚዎች ይቅርታ እንደተደረገላቸው ገልፀዋል።  በተጨማሪም መስተዳድር ምክር ቤቱ የተሠጣቸውን ይቅርታ ባለመጠበቅ ሌላ ወንጀል ፈፅመው በቻግኒ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አምስት ግለሠቦችን ይቅርታ መሰረዙንም ኃላፊው ጠቁመዋል። የህግ የበላይነት የሁለንተናዊ ለውጥ እና ለዘላቂ ሠላም መሠረት ነው ያሉት ኃላፊው፤ በክልሉ በሚታየው የፀጥታ ችግርና በሌሎችም አጋጣሚዎች ከማረሚያ ቤት የወጡ  ፍርደኞች እና ጉዳያቸው በሂደት ላይ የነበሩ ታራሚዎች ተመልሠው በህግ እንደሚዳኙም ገልፀዋል።( AMC)
Show all...
👍 61 6😁 5😱 2🎉 2
ADVERTISMENT ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ 👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ 🔰ምን ይፈልጋሉ? 📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን ✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል 🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ 📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን ☎️ይደዉሉልን ያማክሩን 📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)                     ቁ.2 መርካቶ                     ቁ.3 ተክለሀይማኖት 0904040477 0911016833
Show all...
👍 7 2
ተይዘዋል‼ ወላይታ ሶዶ ወንድማችን በከፍተኛ ህመም ታሟል በሚል ማጨበርበር ወንጀል የተሰማሩ ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ በወላይታ ሶዶ ከተማ በቁጥጥር ሰር ዋሉ፡፡ በወላይታ ሶዶ እና በ በተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር በህመም ሰም ማጨበርበር ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ በወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊሰ በቁጥጥር መዋላቸውን ለዝግጅት ክፍላችን መረጃ የሰጡን የወለይታ ሶዶ ከተማ ህብረተሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ዋና ሳጅን አድማሱ ሶሞኖ ገልጸውልናል፡፡ በማጨበርበር ወንጅሉ የተሰማሩት ግለሰቦች አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸውን የተናገሩት ሀላፊው ከተለያዩ አከባቢዎች በመምጣት መኪና በመከራየት ሀሰተኛ የህመም ማሰረጃ በማዘጋጀት በዚህ በማጨበርበር ወንጅል መሰማራታቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህ የማጨበርበር ወንጅል የተሰማሩት ግለሰቦች በዚህ እኩይ ተግባራቸው ምክንያት ከአሰራ ዘጠኝ ሺህ ብር በላይ ከህብረተሰቡ በማጨበርበር መሰብሰባቸውን ተናግረው፡፡ በወላይታ ሶዶ ከተማ ማንኛውም አጠራጣሪ ለማጨበርበር የሚዳርጉ ጉዳዮች ሲያጋጥም ህብረተሰቡ የተለመደውን ጥቆማ እንዲያደርግ የወንጅል መከላከል ዘርፍ ሀላፊው አጽኖኦት በመሰጠት ተናግረዋል ፡፡ Via wolaita Zone Government Communication affairs department
Show all...
👍 29 9😱 3😭 3🎉 2😁 1