cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Tesfish Hop (ኢትዮጵያዊነት ለዛ...)

ይህ የናንተ፤ የኛ የሁላችንም ድምፅ ነዉ። በቻናላችን አዝናኝና አስተማሪ ጥበባዊ ዝግጅቶች ይቀርቡበታል። ሠላም አንድነትና በጎነትን እንሰብካለን። ከፈለጉ ይቀላቀሉን። ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት @tesfahun27 @tesfa273 to subscribe tube ገፃችንን ለመጎብኘት https://youtu.be/9tTDeSzMgxk

Show more
Advertising posts
993Subscribers
No data24 hours
+67 days
-530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዛሬ የምፅፍላችሁ በሆነ አጋጣሚ ኢንተርኔት አግኝቼ ነዉ። ከአሁን በኋላ ምናልባትም የምፅፈዉ የዛሬ ሳምንት ይሆናል። ታዲያ በዚህ ሁኔታ የፃፍሁትን ፅሁፍ ሸር ባታደርጉ ተጠያቂ እናንተ ናችሁ። sheer, አድርጉት... ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ ሰላም የተገፈገች ሀገራችን አሁንም ንፁሀን እየተሰዉባት ነዉ። ለዚህም ገፈት ቀማሾች እኛ ወጣቶቹ ነን። እኛ ወጣቶቹ እድሜያችንን በብጥብጥና በሁከት፤ በጥላቻ ወሬና በመከራ ጨርሰናል። አይናችንን በንፁሀን ደምና አስከሬን ክምር አዉረናል። ልባችንን በበቀልና በጫካኔ ሞልተናል። ጥንካሬያችን ለመልካም ሳይሆን ለበቀል እንዲሆን በመንግስት ተገደናል። እዉቀታችን ለእድገት ሳይሆን ለተንኮል እንዲሆን መንግስት ራሱ አሳይቶናል። መንቀሳቀሻ አጥተን እቤት መዋል ጀምረናል። እልኽና የእንተያያለን ስሜት በመንግስት እና በህዝብ መሀል ሰፍኗል። በህዝብ አንደበት ሙሴ ተብሎ የተሞካሸዉ ሳጥናዔል የሚል ስም ተሰጥቶታል። የሀገር ጠባቂ፤ የሀገር ዘበኛ ዋልታና ማገር ተብሎ በመንግስት የተሞካሸዉ ፋኖ ቀማኛ ተብሎ ተሳድቧል። የሀገር ዘብ፤ የሀገር ጠባቂዉ መከላከያም ሰዉን እየገደለ የተቀረፀዉን ቪዲዮ በሶሻል ሚዲያ በመልቀቅ ካስመረቀን ሰንበትበት ብሏል። ሸኔም የንፁሃንን አስከሬን ክምር ፎቶ ቀርፆ፤ የእርጉዝ ሴትን ሆድ ሲቀድ አሳየን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ፈጣሪ የሚፈራ፤ አንድነቱ የተሳሰረበት ገመድ የማይላላ ነዉና እያየ አዝኖ ዝም አለ። አሁን ግን የመረረዉ ይመስላል። የህዝቡ ጥያቄ የመንግስት ቸለልተኝነትና ንቀት ገዘፈ። ተዉን ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ጯሂ፤ ሰልፍ ወዳድ፤ ጩኸታም ተባለ። ሲታገት፤ ሲዘረፍ መረረዉ። ዛሬ መጨረሻዉ ላይ ደረሰና ነፍጥ ማንሳት ሲጀምር ዘራፊ፤ ነፍጠኛ፤ፅንፈኛ የሚል ስም ተሰጠዉ። ያም ሆነ ይህ ሁሉንም አይቶ የሚፈርድ ፈጣሪ አለ። ከዛም በታች የኢትዮጵያ ህዝብ ይፈርዳል። ዋናዉ ነገር ከመሀል የተጎዳነዉ እኛ ወጣቶቹ ነን። አዎ...! እድሜያችንን ለተቀማን፤ ዘመናችንን የብጥብጥ፤ የሁከት የሆነብን እኛ ወጣቶቹ ነን። ኢትዮጵያ አምላክ ይፍረዱን። አሜን...!!! @tesfa273 @tesfa273
Show all...
👍 5
ኮሜንት ላይ ሰላምታዬን ተቀብላችሁ ለመለሳችሁልኝ ሁሉ ከልብ አመሠግናለሁ። አዲስ ነገር ለጠየቃችሁኝ ሁኔታዎች ትንሽ ከበድ ስለሚሉ በስራችን ጉዳይ አዲስ ነገር ሊኖር የሚችል አይመስለኝም። ለማንኛዉም ስምንተኛ ዙር ስልጠና መስከረም መጨረሻዎቹ ተብሎ ነበር። ምናልባት ሰላም ከተፈጠረና ሰላም ከሆነ። አልያ ግን በአማራ ክልል በተፈጠረዉ ህዝባዊ አመፅ ምክንያት ወጣቶችን መመዝገብም ሆነ መስራት ስላልተቻለ የሚሆን አይመስልም። ከአሁን በፊት ከአማራ ክልል ዉጭ ባሉ ክልሎች ወጣቶችየተመዘገቡ ሲሆን በአማራ ክልል ግን ኢንተርኔት ዝግ ስለሆነ ማስቀጠል አልተቻለም። ነገን እናያለን። ሰላም...!!! @tesfa273
Show all...
ሰላም ለእናንተ ይሁን። ዛሬም አጋጣሚ ጠፍቼ ከነበርሁበት ተመልሼ ከተፍ ብያለሁ። ደና ናችሁ? እንዴት ከረማችሁ? እስኪ ድምፃችሁን አሰሙኝ። @tesfa273
Show all...
ሰላም እንደምን አላችሁ ዉድ ተከታዮቼ...! ሁሉ ሰላም..? እግዚአብሔር ይመስገን። በእኛ አካባቢ ማለትም በመላዉ የአማራ ክልል ኢንተርኔት ከተዘጋ ቀናት ተቆጥረዋል። በዚህም ምክንያት እኔ እና እናንተ የምንገናኝበት ቻናል ዝግ ሁኖ ቆይቷል። ዛሬ ፈጣሪ ፈቅዶ በሆነ ታምራዊ ሁኔታ ብቅ ብያለሁ። እና ግን እንዴት ናችሁ...? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደና ነኝ። ሰላም ከጠፋ ግን ሰንበትበት ብሏል። ምን ሰላም መጥፋት ብቻ... ፈጣሪ በአምሳሉ ዉብ አድርጎ የፈጠረዉና ወደ ምድር ወርዶ የተሰቀለለት የሠዉ ልጅ ህይወት እየተቀጠፈ ነዉ። እኔ ደና ነኝ።ብዙ ወገኖቼ ግን ሞተዋል። አዎ...ይሄ ሰላም ከሆነ ሰላም ነኝ። ለመሆኑ እናንተ እንዴት ናችሁ...? በተለይም በበጎ ፈቃደኝነት በተለያዩ አካባቢዎች ተሰማርታችሁ እየሠራችሁ ያላችሁ ወጣቶች.... ስራ እንዴት ነዉ? እርግጠኛ ነኝ በአማራ ክልል ያለዉ የሰላም ዕጦት እረፍት ሳይነሳችሁ አይቀርም። የምትሰሙት ወሬ ያማችኋል። ምንም ማድረግ አይቻልም። ብቻ ግን ፍርድ ለሚሰጠዉ ፈጣሪ አሳስቡ። ወደ ፈጣሪ ፀልዩ። አንድ ቀን ሁሉም አልፎ ብሩህ ቀን ይመጣል። በእያላችሁበት የሰላም ባለቤት ሰላም ያድላችሁ። አስታዉሱ... ኢትዮጵያ ታበፅዕ እደዊሃ ሀበ እግዚአብሔር። ሰላም....!!! @tesfa273 @tesfa273
Show all...
ከሰሞኑ በአማራ ክልል የተከሰተዉ ጦርነት ሙሉ በሙሉ የመንግስት ጥፋትና መንግስት ሆን ብሎ ያስጀመረዉ እንደሆነ አብዛኛዉን የሚያስማማ ነዉ። በተደጋጋሚ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በማን አለብኝነት ችላ ብሎ ያለፈበት መንገድም የህዝብን ንቀት ያሳዬ ነበር። 63 ንፁሀን በታገቱ ማግስት የታገቱትን ለማስፈታት ምንም እንቅስቃሴ ሳያደርግ ለምን ብለዉ ለጠየቁ ሰዎች መቅጫ ያለዉን ጦሩ ወደ አማራ ክልል ይዞ ከተፍ ማለቱ ደግሞ ለህዝቡ ሞትም ሆነ ርዕስ በርስ ጦርነት ዴንታ የለሽ መሆኑ ታይቷል። ለማንኛዉም በትዝብት ላይ ነን። የኑሮ ዉድነት እየደቆሰዉ ያለ ይህ ህዝብ አሁን ሁሉ ነገር አስጠልቶት ዉሀ ልግባ እያለ ይገኛል። ለፈጣሪ ህግ የሚገዛ ሁሉ ይህ ነገር ፈጣሪ የማይወደዉና የተወገዘ በመሆኑ ሁሉም ሊያወግዘዉ ይገባል። ሰላም ለሀገራችን @tesfa273
Show all...
ሰላም.....!!! @tesfa273
Show all...
ሁሌም ራስህን ሁን! ራስህን ከማንም ጋር በፍጹም አታወዳድር። 1. ልዩነትዎን ይቀበሉ እና በጉዞዎ ላይ ያተኩሩ። 2. ፍፁምነት በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቅዠት መሆኑን ይወቁ። 3. ስኬት እና ደስታ ለሁሉም ሰው የተለያዩ የጊዜ ሰሌዳዎችን እንደሚከተሉ ይቀበሉ። 4. ላላችሁ ነገር ምስጋናን አዳብሩ እና ለራስ ርህራሄን ይለማመዱ። 5. የግል እድገትን በሚያበረታታ ደጋፊ ማህበረሰብ እራስዎትን ይከበቡ። መልካም ምሽት @tesfa273 @tesfa273
Show all...
''Know thy purpose, change the world.'' Michael Jackson 🌹🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹 👇👇👇 ይቀላቀሉን @tesfa273 @tesfa273
Show all...
እንዴት በራስ መተማመናችሁ ከፍ ታደርጋላችሁ! 👍 ተናገሩ 👍ሁሌም ዝግጁ ሁኑ 👍አጭር ግቦች አስቀምጡ 👍ጥሩ ልበሱ 👍ራሳችሁን ጠብቁ 👍አዲስ ነገር ተማሩ 👍በጎነትን ተለማመዱ 👍ጠንካራ ጎናችሁን አስፉ 👍በጎ በሚያስቡ ሰዎች ራሳችሁን ክበቡ @tesfa273
Show all...
''Agoal without aplan is just awish'' Antoine Dr saint. @tesfa273
Show all...