cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Menz Times

ይህ ትክክለኛው የMenz Times የቴሌግራም ቻናል ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ! ════════════ ➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች ➮የባህርማዶ ያልሰተሙ ዜናዎች ➮የተለያዩ አዝናኝና አሰተማሪ ፕሮግራሞች #FastMerja ቀዳሚ የህዝብ ጆሮ አስተያየት ካሎት @TesfahunBot ለማስታወቂያ ስራ +251929212165 Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Tesfahunye12lij

Show more
Ethiopia5 820Amharic5 549The category is not specified
Advertising posts
880Subscribers
No data24 hours
-67 days
-3930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

" ከKG-12 ክፍል የያዘ ሞዴል ትምህርት ቤት ከፍቼ ጥራት ያለውን ትምህርት እንድሰጥ እውቅና አግኝቻለሁ " - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደሙ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ዓመት ከዚህ ቀደም ይሰጥ የነበረውን የማህበረሰብ አገልግሎት አድማስ እንደሚያሰፋ ዛሬ አሳውቋል። ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ኮሌጁ አስተባባሪነት ከKG-12 ክፍል የያዘ ሞዴል ትምህርት ቤት ከፍቶ ጥራት ያለውን ትምህርት ለመስጠት ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ት/ቢሮ እውቅና ማግኘቱን አሳውቋል። በ2016 ዓ.ም. የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁን የገለፀው ተቋሙ የመመዝገቢያ ጊዜና መስፈርቶቹን በቅርቡ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።
Show all...
ዘነበ መሰለኝ ይኸው ነፋስ ገፋ            ባርኔጣዬን ቀማኝ፣ ተቆጣ ሰማዩ         ጉምጉምታው ተሰማኝ፣ ይኸው ምድሩ ራሰ አቧራው ጠቆረ፣ ይኸው አፈር አፈር ይሸተኝ ጀመረ። ይኸዋ መብረቁ                    ሰማይ እያረሰ፣ ያሰጣሁት ሸማም                     ይኸው በሰበሰ፣ ዘነበ መሰለኝ ደሞ አንጠባጠበ፣ ትዝ አለኝ ያ ገላ ዐይኔም ተራገበ፣ ልቤ ቸኮል ፈጠን                  ሆዴም ደንገጥ፣ሸበር፣ ሲዘንብ እመጣለሁ                  ብላኝ እኮ ነበር። #Share አደራ For any comments @Tesfahunye12lij @Amharicpoem1221
Show all...
" ቲክቶክ " የተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያ በሀገራችን ኢትዮጵያ ጥላቻን ፣ ሁከትን ፣ ብልግናን ፣ ከባህልና ሀይማኖት ያፈነገጡ ድርጊቶችን እንዲስፋፉ እያደረገ ነው ብለው ያስባሉ ? ወይስ ሰዎች እንዲተጋገዙ ፣ ባህልና ሃይማኖት እንዲጠነክር ፣ የመረዳዳት ባህል እንዲጎለበት ፣ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ እንዲለመድ እያደረገ ይገኛል ብለው ያስባሉ ?Anonymous voting
  • ጥላቻና ሁከት፣ እርስ በእርስ አለመከባበር ፣ ብልግና ፣ ከባህል እና ሃይማኖት ያፈነገጡ ድርጊቶች እንዲስፋፉ እያደረገ ነው።
  • እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህል እንዲጎለበት ፣ ባህልና ሃይማኖት እንዲጠነክር ፣ ሰላምና ፍቅር፣ መከባበር እንዲስፋፋ እያደረገ ነው።
0 votes
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ። የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። " ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን የሚያበረታቱ " እና " የብልግና " እና " መረን የለቀቀ ጾታዊ ይዘት " ያላቸው የ " ቲክቶክ " ተንቀሳቃሽ ምስሎች " በኬንያ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች ላይ አደጋ ደቅነዋል" በማለት አቤቱታውን ደግፈው መናገራቸው ተዘግቧል። የኬንያ ፓርላማ በአቤቱታው ላይ ውሳኔ ባይሰጥም ፤ የመጀመሪያ ውይይት ግን እንዳደረገበት ተጠቁሟል። ኬንያ በአፍሪካ በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ብዛት ቀዳሚ ናት።
Show all...
“ከፋኖ እንጂ ከመንግሥት የምንቀበለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አይኖርም!” -የአማራ ህዝብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለሁ ብሏል። ከዚህ በኋላ ከፋኖ እንጂ ከመንግሥት የምንቀበለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አይኖርም ብሏል ህዝቡ።
Show all...
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ ነው፡፡ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ፤ ይህ እንቅስቃሴ የክልሉን ነዋሪ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያወከ እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ፤ የሕዝብን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም ህግ እና ስርዓት ለማስከበር የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ እንቅስቃሴው በሃገር ደህንነት እና በህዝብ ሰላም ላይ የደቀነው አደጋ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል፡፡ መንግስት ትጥቅ አንስተው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሁሉ የሰላም እና ህጋዊ መንገድን እንዲከተሉ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የታጠቁ ፅንፈኛ ቡድኖች እየፈፀሙ ባለዉ ጥቃት ምክንያት የክልሉ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡ የክልሉ መንግስትም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያጋጠመው የፀጥታ መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ፣ ሁኔታውን በመደበኛው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ፣ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት እንዲደነግግ እና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ አቅርቧል።https://www.fanabc.com/archives/205860
Show all...
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ ነው፡፡ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር […]

Repost from ግዮን-አማራ
ሰበር..! የይልቃል ከፋለ የትውልድ ቦታ አቸፈር ወንድዬ በአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ ቁጥጥር ስር ውላለች። ♨️ @Gionamhara @Gionamhara ♨️
Show all...
#ቅዱስ_ሲኖዶስ • የግጭት ተሳታፊዎች ካለፈው የጦርነት ውጤት ተማሩ። • የተፈጠረውን ችግር #በጥበብና #በማስተዋል ፤ በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ ተወያይታችሁ ፍቱ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ስብሰባ በማድረግ ወቅታዊ ሀገራዊ ሰላምን በተመለከተ አጀንዳ በመቅረጽ በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ መግለጫ ሰጥቷል፡፡    ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም መደፍረስና የእርስ በርስ ግጭቶች ምክንያት የበርካታ ወገኖቻችን ውድ ሕይወት እያለፈ እና በርካታ የሀገርና የሕዝብ ሀብትና ንብረት እየወደመ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ትገልጻለች " ብሏል። " ሰላም ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ፍጡራን መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ " ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ  " ሰላም ከሌለ ቀድሶ ማቁረብ፣ ነግዶ ማትረፍ፣ አርሶ ማምረት፣ ተምሮ ማስተማር  ወልዶ ማሳደግ፣ ወጥቶ መግባት፣ አገር መምራትና ማስተዳደር አይቻልም ። በጥቅሉ ሰላም ሲጠፋ አብረው የሚጠፉ መልካም እሴቶቻችን ብዙ ናቸው፡፡ " ሲል አስገንዝቧል። ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በቅርብ ጊዜ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ጦርነት የበርካታ ወገኖቻችንን ሕይወት የቀጠፈ ከመሆኑም በላይ ከሞት የተረፉት ወገኖቻችንም ለስደትና ለረሀብ የዳረገ ፣ ለአካልና ለእእምሮ ስብራት ያጋለጠ ከመሆኑም በተጨማሪ በርካታ አድባራትና ገዳማትን እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትን ያፈረሰ እና መተኪያ የሌላቸውን ውድ ቅርሶቻችንን ያወደመ እጅግ በጣም አስከፊ ተግባር መሆኑን አስታውሷል። በመሆኑም ፡- በሀገራችን በኢትዮጵያ የተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነትና ግጭት ተወግዶ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ልንማጸን ይገባል ብሏል። በሀገራችን በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሰላም እጦትና የእርስ በርስ ግጭት ወደፊት ሊያስከትል የሚችለው ችግር ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለአገራዊ ሰላም የበኩላቸውን ጥረት እንዱያደርጉ መልእክቱን አስተላልፏል። ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል እየተደረጉ ባሉ ግጭቶች ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች ካለፈው የጦርነት ውጤት በመማር የተፈጠረውን ችግር በጥበብና በማስተዋል እንዲሁም በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ ተወያይተው እንዲፈቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ከአደራ ጋር ታስተላልፋለች ብሏል። @tikvahethiopia
Show all...
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም እንደሚከናወን ተገለፀ። ቋሚ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ ተፈፅሟል ባለው ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ጉዳይ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንደሚካሄድ አመልክቷል። " በክልል ትግራይ በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ተፈጽሞ በመገኘቱ አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲጠራ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል። በዚህም ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ለሁሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጥሪ እንዲተላለፍ፣ 2ኛ የመክፈቻ ጸሎቱ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በ10፡00 ሰዓት እንዲከናወን 3ኛ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲካሄድ ቋሚ ሲኖዶስ ወስናል። በክልል ትግራይ ሚገኙ ብፁዓን አባቶች ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ከማዕከል በመነጠል የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት በሚል አቋቁመው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ማከናወናቸው ፤ ሃምሌ 15 እና 16  /2015 ዓ.ም እንዲሁም ሐምሌ 23 ደግሞ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ማድረጋቸው ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ፤ ዛሬ የተሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት በመቐለ ህዝባዊ አቀባበል እንደተደረገላቸው የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ፤ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳዩ #ምስሎች ከላይ ተያይዘዋል።
Show all...
" በተጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል " - የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሁሉም ብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 /2015 ዓ/ም ለተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በድጋሜ ጥሪውን አስተላለፈ። ቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት ፤ በትግራይ ክልል በአክሱም  ርእሰ አድባራት ወገዳማት ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16/2015 ዓ/ም ኢቀኖናዊና ሕገወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደተፈፀመ በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለመምከር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ/ም መጠራቱ የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያኗ የገጠማት ፈተና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ምክክር እንዲደረግበት የተጠራ አስቸኳይ  ምልዓተ ጉባኤ መኖሩ ቢታወቅም አንዳንድ ብፁዓን አባቶች ግን ከወዲሁ በተለያየ ምክንያት #እንደማይካፈሉ እየገለጹ ይገኛሉ ተብሏል። ከአቅም በላይ ያጋጠመ ችግር ቢኖርም እንኳ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ጉዳይ የሚበልጥ ባለመኖሩና የቤተ ክርስቲያን ቀኖናና አንድነት በከፍተኛ ደረጃ ሲፈተን እያዩ በጉባኤው አለመገኘት የተጠሩለት የቤተ ክርስቲያን እውነትን የመጠበቅ ተልእኮ እንደመግፋት ስለሚያስመስል በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በተጠራው ቀን በጉባኤው እንዲገኙ በድጋሜ ጥሪ ተለልፏል። በተጠራው ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ  አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳስቧል። መረጃው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት / EOTC TV ነው። @tikvahethiopia
Show all...