cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

News for Ethiopia (Corona Information)

እውነተኛ ታአማኒነት ያለው መረጃ ወቅቱን በጠበቀ ጊዜ ለማግኘት ቻናሉን ይጎብኙ!!

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
199Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ውሳኔ አሳለፈ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ዛሬ ታህሳስ 20/2013 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ በሀገራችን ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጎ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዬች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ወሳኔ አስተላልፏል፡፡ ለሰላማዊ ሰልፉ መካሄድ አራት መሰረታዊ ጭብጦች የተዘረዘሩ ሲሆን እነርሱም በሀገራችን ኢትዮጵያ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በተደጋጋሚ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ/መተከል አካባቢ፣በወለጋ፣በጉራ ፈርዳና በደቡብ የሀገራችን ክፍልም በሰገን ህዝቦች ቀጣና አካባቢ በጉማይዴ ህዝብ ላይ የተካሄደውን የዘር ማጥፋትን በመቃወም፤ የሱዳንን የድንበር ጥሰት በመቃወም፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ ስለሚገነባቸው ግንባታዎች ጉዳይ እና ስለ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች እስር እና ዳተኛ ስለሆነው የፍትህ ሂደት ሰላማዊ ሰልፍ ለጥር 09/2013 ዓ.ም. የተጠራ ሲሆን ሰላማዊ ሰልፉን የሚያስተባብር ግብረ - ኃይልም አቋቁሟል፡፡ @cronicvirus @cronicvirus ሀሳብም አስተያየቶችን ለመስጠት @participationvoice
Show all...
ለጃዋር መሃመድ አራት ሲም ካርዶችን ሊያቀብል ሲል ተይዟል የተባለው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ ለጃዋር መሃመድ አራት ሲም ካርዶችን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሊያቀብል ሲል ተይዟል የተባለው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ ተጠርጣሪው ግለሰብ ሃምዛ ጀማል መሃመድ ይባላል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተጠርጣሪው ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. 1ኛው ሲም ካርድ በኦ ኤም ኤን ድርጅት ስም ማውጣቱን ጠቅሶ ሶስቱ ሲም ካርዶች ደግሞ በግለሰብ ስም የወጡ መሆናቸውን ከኢትዮ ቴሌኮም መጣራቱን ገልጿል፡፡ ግለሰቡ እነዚህን ሲም ካርዶች በመያዝ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በመሄድ ጃዋር መሃመድን ልጠይቅ ነው በሚል ገብቶ ሲም ካርዶችን ለጃዋር መሃመድ ሊያቀብል ሲል መያዙንም አብራርቷል፡፡ ተጠርጣሪው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ጉዳዩ እየታየ ነው፡፡ @cronicvirus @cronicvirus ሀሳብም አስተያየቶችን ለመስጠት @participationvoice
Show all...
በመተከል ዞን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መድረሱን ወረዳው አስታወቀ። የጉምዝ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉ 207 ሰዎች መሆናቸው በወረዳው ኮማንድ ፖስት፣ የክልሉ መርማሪዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተቆጥሮ መረጋገጡን የቡለን ወረዳ አስታውቋል።ሕጻናት፣ አረጋውያን እና ሴቶች ጨምሮ "ሟቾች የተለያየ ኃይማኖት ተከታዮች በመሆናቸው የአካባቢው ሰው በተስማማበት" በጅምላ በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል። የሽናሻ፣ አገው፣ አማራ ብሔር አባላት መሆናቸው ከጅምላ መቃብሩ በመቃ በቆመ ወረቀት ተከትቧል። @cronicvirus @cronicvirus ሀሳብም አስተያየቶችን ለመስጠት @participationvoice
Show all...
ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ100 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ። ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ100 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት መፈራረማቸውን ከባንኩ የኢትዮጵያ ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡ ገንዘቡ የሴቶች የስራ ፈጠራ ፕሮጀክትን ለማገዝ የሚውል እንደሆነ ከባንኩ ትዊተር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህም ሴት ስራ ፈጣሪዎችን ስራዎቻቸውን ለማሳደግ የሚችሉበት ገንዘብ፣ ክህሎትና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል፡፡ @cronicvirus @cronicvirus ሀሳብም አስተያየቶችን ለመስጠት @participationvoice
Show all...
በግልገል በለስ ከተማ የጦር መኮንኖች እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮች እየተወያዩ ነው ! በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ያሉ መስሪያ ቤቶች በሙሉ ተዘግተው እንደሚገኙ አል ዐይን ኒውስ ዘግቧል። ከተማዋ በፀጥታ ውስጥ ነች ተብሏል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕብረት መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጄ አስራት ዴኔሮ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንና ከምክትላቸው ጌታሁን አብዲሳ ጋር በዝግ እየተወያዩ ናቸው። በግልገል በለስ ከተማ ውስጥ ስታር ሆቴል እየተካሄደ ባለው ዝግ ስብሰባ የዞን አመራሮች እንዲወጡ መደረጉን ታውቋል። የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ውጭ እንዲሆኑ መደረጉን ተሰምቷል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ጠዋት ላይ የክልሉ  ከፍተኛ አመራሮች ከዞኑ አመራሮች ጋር ውይይት እንዳደረጉ አረጋግጠዋል። አቶ አትንኩት እንዳሉት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕብረት መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጄ አስራት ዴኔሮን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መሪዎች በመተከል እየተወያዩ ነው፡፡ በመተከል ከሚፈጸመው የንጹኃን ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉ አመራሮች መኖራቸውን ተከትሎ ፣ ሌሎች አመራሮችስ እጃቸው የለበትም ወይ የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው አቶ አትንኩት የተጠረጠሩት አመራሮች ተይዘዋል እኛ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ አሁን ላይ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ከአቶ አሻድሊ እና አቶ ጌታሁን ጋር እየተወያዩ መሆኑንም አቶ አትንኩት አረጋግጠዋል፡፡ በግልገል በለስ ስታር ሆቴል ውስጥ የሚደረገውን ውይይት ተከትሎ የተለያየ እርምጃ የሚወሰድባቸው የከፍተኛ አመራሮች እንደሚኖሩ ይጠበቃልም ብለዋል፡፡ ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ @cronicvirus @cronicvirus ሀሳብም አስተያየቶችን ለመስጠት @participationvoice
Show all...
👆👆 ሰው ቀለለና በዶዘር እንዲህ ተጣለ!! አላህ ለሀገራችን ሰላም እንዲያመጣልን እጂጉን እንለምናለን!! @cronicvirus @cronicvirus ሀሳብም አስተያየቶችን ለመስጠት @participationvoice
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!