cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

(WULSU) WU law students union channel

This channel is for all law students of wollo university school of law so that to share any relevant information , as much as possible. በወሎ ዩኒቨርሲቲ የ ህግ ተማሪዎች ህብረት የተመሠረተ ነው። @Join us!! @wulsu. ለማንኛውም አስታየት =- @lawstudentWU

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
129Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እንሆ ተነስቷል! እንኳን ለትንሳኤ አደረሰን! ለሁላችሁም የትንሳኤ ዓውዳመት አክባሪዎች - እንኳን ለትንሳኤ ዓውዳመትና የአውዳመት ሳምንቱ በሰላም አደረሰን እንኳን ፆመ-ልጓሙ ተፈታልን! ዓውዳመቱን ስናከብር በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ችግሮች ምክንያት ችግር ላይ የሆኑ ወገኖችን ማሰብና መዘከር የበዓሉን አላማ እንደሚያሳካ እምነቴ ነው። መልካም ትንሳኤ! መልካም የዓውዳመት ሳምንት!
Show all...
የብቻ ደህንነት የታል? አበው "አንተ ደህና እንድትሆን ጎረቤትህ ደህና ይሁን'' ብለዋል። በርግጥ በሽታ ከቤትህ እንዳይገባ ለመከላከል ጥረት ልታደረግና አግለህም ልትቆይ ትችላለህ። ውጤቱም ቢሆን ከህመሙ ከመሸሽና ከመራቅ አንፃር የማይናቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። አንተና ቤተህ እንደኮረና ካሉት ለጊዜውም ቢሆን መትረፍህ የመጠንቀቅህ ዋጋ ነው። ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ እራስን በህወት ለማቆየት የሚደረግ ጥረት ብቻውን ከህወት አጠቃላይ አላማና ዘለቂታ አኳያ ስታየው ደግሞም ጊዚያዊው የብቻህ ጥረት ለመጩ ጊዜ ዋስትና ያረጋግጥልሃል? እንዳንተና ጥሩ አድማጭህና ተባባሪህ እንደሆነው ቤተሰብህ ሁሉ: ሌላውም ዜጋ ከግድየለሽነትና ከመደንዘዝ እንዲሁም ችግሩን ብቻ ከማላዘን አልፎ ለመፍትሄውም ሊረባረብ አይገባም ትላለህ? የሰላምና የጤንነት ጉዳይ እንዲሁ በተወሰነ ሰው ጥረትና በመድሀኒት አቅርቦት ወይም በመሣሪያ ብዛት ብቻ የምትከላከለው አይደለም። አስቤዛ-መድሀኒቱም ተደራሽነቱ መሳርያውም ሆነ ሰዉ እየቀነሰና እየነጠፈ ይሄዳል። መፍትሄው ከመጀመሪያው ቀላል ነበር። ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆመው ማውረድ ያዳግታል ሆነ'ንጂ ነገሩ። እንኳን የሚነገረንን የምናውቀውን የምናስበውን የምናደርገውን ሁሉ ትክክለኛነት በቅንነት መመርመር እና ለደረስነበት እውነት ታማኝ በመሆንን ለተግባራዊነቱ በኃላፊነትና በአስተዋይነት መሰለፍን ይጠይቅ ነበር። አሁንም ቢሆን በርግጥ ከቀውሱ ለማገገምና ከችግሩ ለመውጣት እድሉ አለን። አገራችን አሁን ከተጋረጠባት የጤናና የሰላም ችግር ለመውጣት ከመሪ እስከ ተመሪ በኃላፊነትና በቁርጠኝነት በቅንነትና በታማኝነት በግልፅ መነጋገርና መወሰን ለተፈፃሚነቱም እንደየ ድርሻችን በትጋት መወጣት ይገባናል። በዚህ ስአት ስልጣን የሚያጓጓ አይደለም። ስልጣንን ብቸኛ ምርጫው የሚያደርግ ቢኖር በዚህ አጋጣሚ መፈፀም የሚፈልገው የግሉ የሆነ ድብቅ አጀንዳ ያለው የዋህ ብቻ ነው። ያም ሆነ የሚያሳካው እውነተኛ የህይወት ግብ ኑሮት ደስታ ሊያገኝበት አይችልም። ካንዱ ቀበሌ የገባ በሽታና ጦርነት እደንበርተኛው ቀበሌ ሳይደርስ አይቀርም። ደሳሳውን ጎጆ ያቃጠለ እሳት የታጠረውን ግንብ አያተርፍም። ሁሉም የጊዜ ጉዳይ ነው - እግር በተርታ እጉድጓድ ይደርሳል ነው ብሒሉ። አንተ ደህና እንድትሆን የጎረቤትህ ደህንነት ነው ዋስትናህ! ወንድምህን ገፍተህ እህትህን ጥለህ: ጎረቤት ወገንህን እያሳደድህ እንዴት ነው ዘላቂ ደህንነት የሚኖርህ? የሀኪም ምክር እየናቅህ ውስጥህን በንቀትና ግድየለሽነት ሞልተህ ሌላ ችግርም እየተጋበዝህ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ህግን ለመጣስ: የምታመልከው አምላክ የሰራልህን ህግ ከቁብ ሳትቆጥር: ለቂም ሰበብ እሰበሰብህ ልብህን በጥላቻ: እልህና ቂም ደፍነህ ከሰውነት ወደ አውሬነት እየተሸጋገርክ እንዴት ነው ደህና የምትሆነው? እንዴት ነው የኔ የምትለው ነገር ሁሉ ነገ ላንተ የሚሆነው? የነገው ቀን ላንተ የሚገባህና የሚሆንህ ለመሆኑ ምንያህል ርግጠኛ ነህ? ብሎልህ ተርፈህ ነገን ብታገኝ ብቻህን ነገ ምን ያደርግልሃል? ነገን ብታገኝ ነገ አንተ የሌሎች ነህ! - ወይም የምትጓጓው ነገር ሁሉ ያንተ አይሆንም። ምናልባት አንተ ነህ - ወንዙን ሜዳውን ተራራውን እፀዋቱን አየሩን እንደ አያቶችህ የምትወደው። ግን ይኸው መልክዓ ምድር አንተን እንደ ሚወድህ ምን ያህል ርግጠኛ ነህ? ምንም። አንተን እንደራሱ ሊወድህ የሚችለውስ የገፋኸው ጎረቤትህ- ወገንህ ነበር። መሬቱ ለያዘው ሁሉ ተገዥ ነው። አሁን ''በማን አባት ገደል ገባ'' የሚያጣላህ ቦታ የጠበበው ሰው መጥቶ ይሰፍርበታል:: መሬት እንደሆነ ግድ የላትም የሰፈረ ቢሰፍርባት:: ምናልባት ቃርምያ ምተርፍም ከሆነ ወንድምህን ያስፈጀህ ከበሽታ ያዘናጋህ የአባቶችህ ባላንጣ ይገዛሀል....
Show all...
Lecturer #wollo_university #legal_services #law #lecturer Amhara, Wollo LLB in Law or related field of study with CGPA for Male: 3.25 /Female: 3.00 Quanitity Required: 4 Minimum Years Of Experience: #0_years Deadline: March 29, 2021 How To Apply: In person to the following address: Dessie town, Wollo University Dessie Campus to Human Resource Administration Section, office no. 207 or mail through: P. O. Box: 1145 Dessie Tel. 0333115234/ 0333115232 Note: Informatics & Engineering College applicants should register at Kombolcha Campus, to Human Resource Administration Office or mail through: P. O. Box: 208 Kombolcha Tel. 0335515237 #ወሎ_ዩኒቨርሲቲ #የፍቅር_እና_የጥበብ_ዩኒቨርሲቲ #university_of_love_and_wisdom @wollouniversity13 @wollouniversity13
Show all...
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሕግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ዝርዝር ማውጫ ሰንጠረዥ ከቅጽ 1 እስከ 24 በ፦ ዋስይሁን ኃይለማርያም እና የኋላሸት ታምሩ አዘጋጆቹ በዚህ ጊዜ በመስፍን ታፈሰ እና ጓዶቹ (MTA) የሕግ ቢሮ በአሶሲየትነት በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ይህን ስራ አዘጋጆቹ በግላቸው የሰሩት እና የሚሰሩበትን ተቋም ያካተተ ወይም የሚወክል አይደለም። ይህ ማውጫ የሚያገለግለው ለትምህርት እና ለመረጃ ምንጭነት ብቻ ነው። በዚህ ማውጫ ዝግጅት ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያዘጋጀው ከ ቅጽ 1 እስከ 16 ማውጫን በመጠቀም የቀሩትን ቅጾች አጠቃለን አዘጋጅተናል። አዘጋጆቹ ይህን ማውጫ በሚያዘጋጁበት ጊዜ በውስጡ ያሉትን መረጃዎች እውነታነት ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ጥረት አድርገዋል፡፡ ይህ ማውጫ ሲዘጋጅም ትክክለኛ መረጃ እንዲይዝ በማሰብ ነው፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ማውጫ ላይ ሊኖሩ በሚችሉ ስህተቶች፣ ግድፈቶች፣ ጉድለቶች እንዲሁም አለመስማማቶች ሊከሰቱ ለሚችሉ ጉዳቶችም ሆነ ኪሳራ አዘጋጆቹ ምንም አይነት ኃላፊነት እንደማይወስዱ ያሳውቃሉ። ይህ ማውጫ በዋነኛነት የመረጃ ምንጭ እንዲሆን እና ለሕግ ማህበረሰቡ ቀላል እና ፈጣን ማጣቀሻ እንዲሆን የተዘጋጀ ቢሆንም ቀጥታ የባለሞያ ምክር ወይም ድጋፍ አይተካም። ይህን አይነት አገልግሎት ከተፈለገ ከባለሞያ መጠየቅ አለበት፡፡
Show all...
⚖የወንጀል ህግ የክስ ፍርሞች To get different law books Join👇 ╔═══════════╗ ⚖ 👨‍⚖ @ethiolawblog For any legal books You can contact me 👇👇👇 @ashufish Or @ethiolawblogbot
Show all...
Exit Exam ውጤት #በትንሽ ነጥብ ልዩነት ያልመጣላችሁ ውድ የህግ ቤተሰቦች ውጤት በወጣ በ15 ቀን ውስጥ remark (እንደገና ይታረምልኝ) ጥያቄ በህግ ት/ቤታችሁ በኩል በፅሁፍ በማመልከት መጠየቅ ትችላላችሁ። ለበለጠ መረጃ የህግ ት/ቤታችሁን ሄድ ፤ ዲን ወይም ሀላፊ በመጠየቅ እንደገና ለማሳረም መስፈርቱን የምታሟሉ ከሆነ ብቻ ሂደቱን ጠብቃችሁ እንድታመለክቱ እናበረታታችኋለን። We go together‼️ #ሼር #አለ #Share #ALE 🟢 @lawsocieties 🟡 @lawsocieties 🔴 @lawsocieties
Show all...
የ#5ኛ ዓመት የህግ Exit Exam ውጤት ተለቋል❗️
Show all...
የ#5ኛ ዓመት የህግ Exit Exam ውጤት ተለቋል❗️ https://t.me/joinchat/WVoHA4pKC2hqoJTp
Show all...
Exit Exam 🟢🟡🔴 እየታረመ ነው እስከ ቅዳሜ ታርሞ ያልቃል ተብሎ ይታሰባል። 🟢🟡🔴 ቀጣይ ሂደቱ እስከ ጥር መጨረሻ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። እስከ የካቲት 1 ውጤት ለተፈታኞች ይለቀቃል የሚል ጊዜአዊ እቅድ ተነድፏል።🟢🟡🔴 ምንጭ #አለ #ALE
Show all...
Lecturer #debark_university #legal_services #law #lecturer Amhara, Debark LLB in Law or related field of study Quanitity Required: 4 Minimum Years Of Experience: #0_years Deadline: January 23, 2021 How To Apply: In person to the following address: Debark University, to Human Resource Directorate Office
Show all...
Tap to view details / ዝርዝሩን ለማየት ይሄንን ይጫኑ