ሰላም ለእናንተ ይሁን GENERALS 💂
ዛሬ የአንድ GENERAL ዋና የህይወት ክፍል ስለሆነው ጦርነት (WAR) እናውራ
ስለዚህ ጦርነት ላይ መጀመሪያ ጠላትን ማወቅ ግድ ነው !
እናም ጠላቶቻችን ይኸውኑ፦
1፡ አለም
2፡ ሰይጣን
3: ስጋችን
እነዚህ ጠላቶች የእኛ ብቻ ሳይሆን ክርስቶስም በስጋው ወራት የተጋፈጣቸው ነበሩ ። በዮሐንስ ከተጠመቀ በኋላ ወደ በርሀ ሄዶ ሳለ የቀረበለት ፈተና ነበር ያም ፈተና በሶስቱ ጠላቶች የተዘጋጀ ነበር ግን አልሰራም ።
አሁን ስለ መጀመሪያው ጠላት "አለም" እናውራ ይህ ጠላት ከውጭ ያለ እና የሚታይ ነው። ሰይጣንም "ወድቀህ ብትሰግድልኝ የአለምን ክብር እሰጥሃለሁ"
አለው እና የአለምን ክብር አሳየው ።
በምን እናሸንፈው?
መፅሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ መልዕክት እንዲህ ይላል"አለምን የሚያሸንፈው እምነታችሁ ነው"
ስለዚህ የእምነትን ጋሻ እናንሳ ከእግዚአብሔር የተወለደ አለምን አሸንፏል እንደሚል እንመን አሸናፊነት ከዘር በመወለድ ያገኘነው ነው!!!
አለም እርሱን ስለማታውቀው እኛንም አታውቀንም።
እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ነን እኛ የእግዚአብሔር ጀነራሎች ነን
አለምን ከነ ብልጭልጯ ጥሏት ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ፀጋ ፈፅማችሁ ተስፋ አድርጉ ።
ከፍ በሉ
ጦሩን አጠናክሩ
ተባርካችኋል
Show more ...