የዘማሪት ዘርፌ ከበደ ባለቤት የሆነው መኳንንት ተገኝ በትላንትናው ኮንሰርት ተከታዩን ብሏል።
ለእንግዶች "ጥሪያችንን ተቀብላችህ እግዚአብሔር ለማክበር ለመጣችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ።
ሰሞኑን ስለነበረው ግብግብ "ወንጌል ስንይዝ በጽድቅ ለመኖር ስንጥር ሁል ጊዜ ከጨለማው አለም ተግዳሮት ይመጣል"።
"ሰው ሰውን አይቃወምም ሰው ወንጌልን አይቃወምም የወንጌል ጠላት አንድ ብቻ ነው እሱም
#ዲያቢሎስ በቻ ነው"።
በቀጠና ሁለት ስለተፈጠረው "እንደኛ ሀሳብ ቀጠና ሁለት ለማድረግ ነበር እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ ደግሞ እዚህ [FBI ቤተክርስቲያን] ሆኖል"።
ስለ ቂም "እኛ ሀሳባትንን ጥለን የእግዚአብሔርን ሀሳብ ተቀብለናል የተቃወመንም ሰው የለም ያሳደደንም ሰው የለም እኛ ምን አይነት
#ጥላቻ በማንም ላይ አልያዝንም የእውነት ሁል ጊዜ ፈተና ሲመጣ ከሰው ጋር ማያያዝ የለብንም እንኳን አማኝ አህዛብ ሰይጣን ካልተጠቀመው በስተቀር እራሱ የእግዚአብሔር የሆነን ነገር አይቃቀምም"።
ስለ ሚድያ"የተፈጠረውን ነገር በአንድ አባት ልጆች መካከል በአንድ መንግስት መካከል የተፈጠረ በመሆኑ በአደባባይ ያለ ቅጥ ልናራግበው አይገባም በቤት ውስጥ በጓዳ ውስጥ የምንፈታው ነገር ነው ሁሉንም ነገር ወደ አደባባይ ስናወጣ የሚያመጣ የራሱ የሆነ ችግር አለ ወደ ወንጌል ለሚመጡ ሰዎች እንቅፋት እንሆናለን አደባባይ ላይ ያለው ነገር እረግቦ በቤት ውስጥ ብንመካከር ጥሩ ይመስለኛል"።
ለእግዚአብሔር "ጭብጨባ ለሱ ብቻ ነው የሚገባው እልልታ ለሱ ብቻ ነው የሚገባቅ ስግደት ለሱ አምልኮ ለሱ ነው የሚገባው"።
በስተመጨረሻ "የተሰበሰብነው ሲዲ ልንሸጥ አይደለም በወንድሞችና በእህቶች መካከል እግዚአብሔር ከፍ ልናደርገው ነው"።
@christ_zene
@christanzenabotShow more ...