በ2009 “ሩሃማ” የሚለውን የመጀመሪያ ዝማሬዋን ለህዝብ አቅርባለች።
በዚህ ዝማሬዋ በብዙዎች ምእመናን ዘንድ ታዋቂነትን እያተረፈች የመጣችው ዘማሪት ዘርፌ “በ2013” መንፈስ ቅዱስ የሚለው ዝማሬዋን አውጥታለች።
ታዲያ በእነዚህ ጊዜያት የዝማሬዎቿ ግጥሞች ጥንካሬ በቀላሉ ተወዳጅ ለመሆን ችላ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ለዘርፌ ይሄ ሁሉ መንገድ ቀላል አይደለም ምክንያቱም ከዘፈን አለም ስለ መጣች እሷን በቀላሉ ለመቀበል ከባድ አድርጎት ነበር።
በዚህ ምክንያት በወሰን ደበበ ማንደፍሮ የተጻፈ “ፓራሜራ” የሚል በቀድሞ በህይወቷ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን ፊልም ሰርታ ለህዝብ አቅርባ እንደነበር
ይታወሳል።
“ስለ እኔ የሚማልደው” የሚለው የመጀመሪያ ዝማሬዋ እና “ትልቅ ነህ” እንዲሁም "የፍቅርህ ምርኮኛ" የተሰኙ ነጠላ (Single) ዝማሬዎችን አቅርባለች።
ምንም እንኳን በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ ስለ አገልግሎታቸው ጥያቄ በሚነሳባቸው አገልጋዮች ዘንድ ሄዳ ማገልገሏ ብዙዎችን ሲያስቆጣ እና ብዙዎች በሷ ላይ ያላቸውን እምነት ሲቀንስ አስተውለናል።
ግን ስለ ወንጌል ቆርጦ የተነሳ ሰው ስድብና ዝልፊያ አይደልም ድብደባንም ለመቀበል ዝግጁ እንደሆነ የሷ እንቅስቃሴ ማሳያ ነው።
“በህይወቴ ሳለው ለእግዚያብሄር እቀኛለሁ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ” የሚል መፈክር ያለት ተወዳጇ ዘማሪት ዘርፌ ከበደ እንዳለችውም ክርስቶስን ለማገልገል እና የሚበረታባትን ወጊያ በአደባባይ ለመጋፈጥ ወስና ከገባች ሰነባበተች።
ከሰሞኑ "ጸድቂያለሁ" የተሰኘ አዲስ አልበም ለበረከት ይሆንልን ዘንድ ይዛልን መጥታለች።
ለማንኛውም ግንቦት 14/2014ዓ.ም በ8:00ሰዓት በቀጠና 2 ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን አዳራሽ በድምቀት ይመረቃል።
"ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
@christ_zene
@christanzenabotShow more ...