cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ghion Mag ግዮን መጽሔት

https://t.me/+kQKnGzeZl1IyZmZk በኢትዮ ሐበሻ ሕትመትና ማስታወቂያ ኃ/የ/ግ/ማ ሥር ታተመው ለንባብ የሚበቁት ግዮን መጽሔት እና ኢትዮ ሐበሻ ጋዜጣ የቴሌግራም ቻናል ነዉ። ዕለታዊ ትኩስ ዜናዎች ፖለቲካዊ፣ ዘገባዎች ሃይማኖታዊና ባህላዊ ማኅበራዊና፣ ኢኮኖሚያዊ ኪናዊ ይዘት ያላቸው ጽሑፎች በስፋት ይስተናገዱበታል፡፡https://t.me/+kQKnGzeZl1IyZmZk በተጨማሪም፡-

Show more
Advertising posts
32 874Subscribers
-2224 hours
-1267 days
-55830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
The Struggle For Free Press Continues As Cracks Widen | The Reporter | Latest Ethiopian News Today

This week’s International Day to End Impunity for Crimes Against Journalists takes on renewed significance as threats to independent media in Ethiopia mount.

👍 7
"በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ሕጋዊ ስርዓትን የተከተለ ሊሆን ይገባል" የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ሕጋዊ ስርዓትን የተከተለ ሊሆን ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አሳሰበ። ምክር ቤቱ በላከው መግለጫ፤ "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ላይ ከሕግ አግባብ ውጪ አስሮ የማቆየትና ለስርጭት የተዘጋጀ የህትመት ውጤትን የማገድ ድርጊቶች እንደተፈጸመባቸውና፤ በዚህም ሳቢያ ተቋማቱ የዕለት ተዕለት ሥራዎቻቸውን ለመስራት መቸገራቸውን" ከደረሱት ሪፖርቶች መገንዘቡን ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 29 ንዑስአንቀፅ4 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው "ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሃሳቦች፣ አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ፕሬስ በተቋምነቱ የአሰራር ነፃነትና የተለያዩ አመለካከቶችን ለማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው በሕግ ጥበቃ ይደረግለታል" እንደሚል ያስታወሰው ምክር ቤቱ፤ ቢሆንም ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በአገሪቱ ሕግ መሠረት ተመዝግበውና ፍቃድ አውጥተው የሚሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ጋዜጠኞችና የህትመት ውጤት በጸጥታ ሃይሎች ከሕግ አግባብ ውጪ መታገታቸው እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡ እንደ አብነትም በኢትዮ ሃበሻ አሳታሚ ድርጅት በየሳምንቱ እየታተመ የሚሰራጨው ጊዮን መፅሄትና ዋና አዘጋጁ ነሃሴ 19/2015 በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ከአንድ ሳምንት በሃላ ዋና አዘጋጁ ያለ ክስ መለቀቁን በማስታወስ መፅሄቱ ከአንድ ወር ከ 15 ቀን በላይ አለመለቀቁን አንስቷል። በተጨማሪም የትርታ ኤፍ ኤም 97.7 የፕሮግራም ዳይሬክተርም ጳጉሜ 5/2015 ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ሃይሎች ከተወሰደ በሃላ ከአንድ ወር ከ20 ቀናት በላይ ክስ እንዳልተመሰረተበትና ፍርድ ቤትም ሊቀርብ አልቻለም ሲል ገልጿል። በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238 አንቀጽ 85 /7 "በየጊዜው የሚወጣ ህትመት ከመሰራጨቱ በፊት በጸጥታ አካላት የሚሰጥ የእገድ ትዕዛዝ የትዕዛዙ መነሻ የሆነውን አንቀጽ ወይም አንቀጾች፣ የህትመቱን ቅፅ፣ ጽሁፉ የወጣበትን እትም መገለጽ አለበት። እገዳውም ለሥርጭት በተዘጋጁ ህትመቶች ላይ ብቻ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡" ሲል በግልጽ መደንገጉንም ምክር ቤቱ አስታውሷል። "ሆኖም ጊዮን መጽሄት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለበት ጊዜ አንስቶ በአዋጁ መሰረት ተመርምሮ የጋረጠው አደጋ ስለመኖሩ ያልተረጋገጠ ሲሆን፤ ለፍርድ ቤትም በ48 ሰዓት ውስጥ የቀረበ ክስ የለም፡፡" ሲል ገልጿል። በሌላ በኩል በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል በወንጀል ሥነ-ሥርዓት የሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በዓቃቤ ሕግ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለበት በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ በግልጽ ቢደነገግም፤ የትርታ ኤፍ ኤም ጋዜጠኛ ግን ከአዋጁ ተቃራኒ በሆነ መልኩ ለሳምንታት ያለ ክስ በእስር ላይ ይገኛል።" ብሏል። የወንጀል ድርጊቶች ከመፈጸማቸው በፊት መከላከል ተፈጽሞ ሲገኝም አፋጣኝ ፍትሐዊ እርምጃዎችን በሕግ አግባብ የመውሰድ ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ የተጣለባቸው የጸጥታ አካላት፤ ጋዜጠኞችን አስሮ መረጃ መሰብሰብና አስሮ ለቀናት ክስ አለመመስረት እንዲሁም የህትመት ውጤትን ከስርጭት ማገድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማቱ ሥራቸውን በነጻነት እንዳያከናውኑ የሚያስተጓጉል ተግባር መሆኑንም አንስቷል፡፡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቀማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት፤ በሕጉ አግባብ ብቻ መከናወን ይኖርበታል ብሎ እንደሚያምንም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በመግለጫው አመላክቷል፡፡ "ይህ አለመሆኑ ግን አገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ያላት ገጽታ ላይ ጥላ የሚያጠላ ሆናል፡፡" ያለው ምክር ቤቱ፤ “ላለፉት አምስት ዓመታት የፍትህ አካሉ የተለያዩ ማሻሻያዎች እየተደረጉበት ያለ ቢሆንም፤ ጋዜጠኞችንና ተቋማቱን በተመለከተ በሕጉ አግባብ ተደጋጋሚ የመብት ጥሰቶችን ለማስቀረት ያለመቻሉ ምክር ቤታችንን በእጅጉ ያሳስበዋል፡፡" ብሏል። ችግሩ እንዲፈታም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ጉዳዩን በማሳወቅ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ በመሆኑም መንግሥት የወንጀል ተግባሮችን የመከላከል፣ የመመርመር እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ የፍትሕ ሥርዓቱ በአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማቱ ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥስቶችን በሕጉ አግባብ ብቻ እንዲመራ በማድረግ፤ ሕገ ወጥ የወንጀል ድርጊቶችን በተቻለ ፍጥነት በማረም ሕገ መንግሥታዊ ግዴታውን እንዲወጣ ምክር ቤቱ በመግለጫው ጠይቋል፡፡
Show all...
👍 9
👍 1

1
Show all...
ሲፒጄ ከአስቸኳይ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እየታሰሩ ነው  አለ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ ረቡዕ ጳጉሜ 01/2015 ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በሳምንታት ውስጥ የተፈፀሙ የጋዜጠኞች እስር እንዳሳሰበው በመግለጽ፤ በሙያቸው ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችን በሙሉ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቋል፡፡ ላለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለይ በፖለቲካ ውጥረት እና ግጭት ወቅት ተደጋጋሚ የጋዜጠኞች እስር ይከናወናል ያለው ሲፒጄ፤ በቅርቡ በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ በታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አባይ ዘውዱ፣ ይድነቃቸው ከበደ እና ፍቃዱ ማኅተመወርቅ የተባሉ ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል ሲል አስታውቋል፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞች በአማራ ክልል ስላለው ግጭት እና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመዘገባቸው ምክንያት መታሰራቸውን ተረድቻለው ሲልሜ ሲፒጄ በመግለጫው አካቷል፡፡ የአማራ ሚዲያ ማዕከል የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ዋና አዘጋጅ አባይ ዘውዱ ነሐሴ 04/2015 በፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥጥር ሥር ውሎ፤ ነሐሴ 15/2015 ወደ አዋሽ አርባ መወሰዱንም ተረድቻለሁ ብሏል። ፌዴራል ፖሊስ አባይ ዘውዱን በምን ምክንያት በቁጥጥር ሥር እንዳዋለው እንዳልገለጸለት እና ፍርድ ቤት አለመቅረቡን ቤተሰቦቹ ነግረውኛል ነው ያለው፡፡ አፍሪ ነጋሪ የተሰኘ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን መስራች ይድነቃቸው ከበደ እንዲሁ፤ ሐሙስ ነሐሴ 11/2015 ከመኖሪያ ቤቱ ተይዞ ለእስር መዳረጉን በመግለጽ፤ ነሐሴ 15/2015 ፍርድ ቤት ቀርቦ ፖሊስ “ፀረ-ሰላም አካላትን” በመርዳት እና “አመፅን ለማነሳሳት” ቪዲዮዎችን በመስራት ወንጀል እንደጠረጠረው ጠበቃው ሄኖክ አክሊሉ ነግሮኛል  ብሏል፡፡ በድጋሚ ነሐሴ 26/2015 ፍርድ ቤት ቀርቦ በ6 ሺሕ ብር ዋስ ተፈቷል ሲል ጠበቃውን ጠቅሶ አብራርቷል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የጊዮን መፅሔት ዋና አዘጋጅ ፍቃዱ ማህተመወርቅ ነሐሴ 19/2015 በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሉን እና ፍርድ ቤት አለመቅረቡን ነገር ግን ነሐሴ 29/2015 ያለ ክስ ከእስር መለቀቁን ከባለቤቱ ተገንዝቤያለሁ ሲል ሲፒጄ በመግለጫው አካቷል፡፡ "አሁንም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሕዝቡ በተለያዩ ግጭቶች ዙሪያ የተለያዩ ዘገባዎችን እና አስተያየቶችን ማግኘት በሚፈልግበት ጊዜ በጋዜጠኞች ላይ እያነጣጠሩ ነው።" በማለት የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በሥራቸው የታሰሩትን ጋዜጠኞች በሙሉ መፍታት አለባቸው በማለት አሳስቧል፡፡ "አማራ ክልል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመገናኛ ብዙኃንን ለማፈን እንደማይውል ማረጋገጥ ይገባል።" ሲሉ ከሰሃራ በታች የሲፒጄ ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ ተናግረዋል፡፡
Show all...
👍 17
#ሰበር_ዜና ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ከእስር ተፈታ የግዮን መጽሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ከስምንት ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከእስር ተፈትቷል። ጋዜጠኛው ከአንድ ሳምንት በፊት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ሳምንታዊዋን የግዮን መጽሔት ሕትመት አጠናቅቆ ለማከፋፈል በሒደት ላይ በነበረበት ሰዓት ከመጽሔቱ ሙሉ ዕትም ጋር መታሰሩ ይታወሳል። ከታሰረበት ዕለት አንስቶ ላለፉት ቀናት ፍርድ ቤት ያልቀረበው ጋዜጠኛው በዛሬው ዕለት በዋስ መለቀቁን ማረጋገጥ ተችሏል።
Show all...
👍 25
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!