cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ባ13 ወር ፀጋሽ!!! 💚💛❤️️️ ሰንደቅሽ እማማ ኢትዮጵያ🙏ሁሌም ሙሽራ ነሽ🙏

ባ13 ወር ፀጋሽ!!! 💚💛❤️️️ ሰንደቅሽ እማማ ኢትዮጵያ🙏ሁሌም ሙሽራ ነሽ🙏 ጠላቶችሽ ጠፍተው ትንሣኤሽን ያሳየን እናት ኢትዮጵያችን። አማረኛ መግባቢያ🔜የኢትዮጵያን ታላቅነት እንመሰክራለን!!! ስለ ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዝም አንልም!!! ለአስተያየትዎ👉 @emama211229

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
189Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✝✝††† እንኳን ለሰማዕታት አበው አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊ : ቅዱስ መቃርስ እና ቅዱስ ለውንትዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ ††† ††† ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ምንም እንኳ ለሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ያን ያህል ዋጋ ቢከፍሉም ትውልዱም : መንግስቱም : ራሷ ቤተ ክርስቲያናችንም ተገቢውን ክብር ሰጥተው እያሰቧቸው አይደለም:: እስኪ እንዲያው ቢያንስ እንደ ክርስቲያን : አንድም እንደ ኢትዮጵያዊ እነዚህ ነገሮቻቸውን እናስብ:: ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ከልጅነታቸው ጀምረው ትምሕርት : ትሕርምትና ደግነት ወዳጅ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ወቅቱ ኢትዮጵያ የራሷን ጳጳሳት የምትሻበት ጊዜ ነበርና በፈቃደ እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ጊዜ የሃገራችን አራት አባቶች ጵጵስናን ተሾሙ:: እነርሱም ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ እና አበው አባ ሚካኤል: አባ አብርሃም እና አባ ይስሐቅ ናቸው:: የተሾሙትም ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ/ም ነው:: አቡነ ጴጥሮስ ከተሾሙ በኋላ በሐዋርያዊ አገልግሎትና በጸሎት ተግተው ኑረዋል:: በ1928 ዓ/ም ፋሺስት ጣልያን ሃገራችንን በወረረች ጊዜ ቆራጡ ጳጳስ በዱር በገደል ለመሔድ ተነሱ:: በየበርሃው እየሔዱ አርበኞችን ሲያጽናኑ : ሲናዝዙ : ሲባርኩም ቆይተዋል:: ለሃገራቸውና ለሃይማኖታቸው ረሃብ : ጥም : እንግልትን ታግሰዋል:: በተያዙባት በዚያች ሌሊትም በጣልያኖች ለሮም እምነትና ለአገዛዙ እንዲያጐበድዱ ተጠየቁ:: ቆራጡ ሰው ግን እንቢ ቢሉ የሚደርስባቸውን እያወቁ "አይደረግም" አሉ:: በማግስቱ በአደባባይ መትረየስ ተደግኖባቸው አሁንም ጥያቄ ቀረበላቸው:: አቡነ ጴጥሮስ አፋቸውን ከፍተው ሊናገሩ ጀመሩ:- "የሃገሬ ሕዝብ ሆይ! ለሃገርህ : ለሃይማኖትህ ባትጋደል ትውልድ ይፋረድህ:: ለጣልያን ግን እንኳን ሰው ዛፍ ቅጠሉ መሬቱ እንዳይገዛለት አውግዣለሁ" አሉ:: በደቂቃዎች ልዩነት በግራዚያኒ ትዕዛዝ የመትረየስ ጥይት ዘነበባቸው:: አካላቸው ተበሳስቶ በሰንሰለት እንደ ታሠሩ መሬት ላይ ወደቁ:: አንዱ ወታደር ቀርቦ ቢመለከት ትንሽ ትንፋሽ ነበረቻቸው:: "ይሔ ቄስ አልሞተም" ብሎ ጭንቅላታቸው ላይ ተኮሰባቸው:: አቡነ ጴጥሮስ ለሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ተሠው:: ነገሩ በአርበኞች ዘንድ ሲሰማ ትግሉ ተቀጣጠለ:: ይሄ የተደረገው ሐምሌ 22 ቀን በ1928 ዓ/ም ነው:: አቡነ ጴጥሮስም በተ/መ/ድ (UN) የሺህ ዓመቱ ምርጥ ሰማዕት (MARTYR OF THE MILLENIUM) በመባል ይታወቃሉ:: ††† ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት ††† ††† ሰማዕቱ ተወልዶ ያደገው በአንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የታላቁ ቅዱስ ፋሲለደስ እና የቅድስት ሶፍያ ልጅ ነው:: ምንም በቤተ መንግስት ውስጥ ቢያድግም ከወላጆቹ ፍቅረ ክርስቶስን : ንጽሕናንና ደግነትን ወርሷል:: በተለይ ነዳያንን ሰብስቦ ዕለት ዕለት ያበላ ነበር:: (መቃርስ ማለት በልሳነ ዮናኒ ብጹዕ : ንዑድ : ክቡር ማለት ነው::) ቅዱሱ ያ የመከራ ዘመን ሲመጣ ሁሉም ቤተሰብ ስለ ክርስቶስ መሞትን በመምረጡ እርሱም ደስ እያለው የመከራው ተካፋይ ሆኗል:: ያን የመሰለ የቤተ መንግስት ክብር ስለ ክርስትና ናቀው:: ተገረፈ:: ተሰቃየ:: በእሳትም ተቃጠለ:: አንድ ጊዜም በአደባባይ የሞተ ሰው በጸሎቱ አስነስቶ "መስክር" አለው:: ከሞት የተነሳውም የክርስቶስን አምላክነት በመመስከሩ በአደባባይ የነበሩ ብዙ አሕዛብ በክርስትና አምነው ተሰይፈዋል:: ቅዱስ መቃርስን ግን ብዙ አሰቃይተው በዚህች ቀን አንገቱን ቆርጠውታል:: ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አጽሙን አፍልሶ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጾለታል:: ††† ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት ††† ††† ቅዱሱ የተወለደው በተመሳሳይ ዘመን (በቅዱስ መቃርስ) ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት ነገሥታቱን ያገለግል ነበር:: ድንግል : ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው:: እርሱ ግን ምንም ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ ይጸልየው : ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የታሸ ነውና ብዙ ጓደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት : ከክፋት ወደ ደግነት መልሷል:: የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ ጊዜም አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት : ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር:: በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር በዚህች ቀን አንገቱን ተሰይፏል:: ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና በእምነት እንጥራው:: ††† እግዚአብሔር ዐጽመ ሰማዕታትን ይጠብቅልን:: ከሰማዕታቱ ጽናትን : ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: ††† ሐምሌ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት (ኢትዮጵያዊ) 2.ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት (የፋሲለደስ ልጅ) 3.ቅዱስ ለውንትዮስ (ክቡር ሰማዕት) 4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት (ቅዳሴ ቤታቸው) 5.ቅዱስ መርካሎስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ 3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ) 4.አባ ጳውሊ የዋህ ††† "እንግዲህ አትፍሯቸው:: የማይገለጥ የተከደነ: የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና:: በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ:: በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ:: ሥጋንም የሚገድሉትን: ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ:: ይልቅስ ነፍስንም: ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ::" ††† (ማቴ. ፲፥፳፮) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/zikirekdusn
Show all...
የዲ/ዮርዳኖስ አበበ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

በዚህ ቻናል መምህርዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

እናንተ ጋ በዓል እንዴት አለፈ! አቤት ሲያምርብን! ቅዱስ ገብርኤል ለቅድስት ለሃገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ያብስርልን! አሜን፫
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ❤️ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድል ያስመዘገበችበት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቋል። #ከዓለም ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ እንዲሁም #ከአፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ ነው ያጠናቀቀችው። በዓለም ሻምፒዮናው 4 ወርቆችን ያገኘን ሲሆን የዘንድሮው ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል። ከተገኙት አራት #ወርቆች 🥇 መካከል ታምራት ቶላ በማራቶን ያገኘው ወርቅ በዓለም ሻምፒዮናው በወንዶች የተገኘው #ብቸኛው ወርቅ ነው። ለሀገራቸው ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶቻችን እነማን ናቸው ? ወርቅ 🥇 🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ 🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ 🇪🇹 ጎተይቶም ገ/ስላሴ 🇪🇹 ታምራት ቶላ ብር🥈 🇪🇹 ወርቅውሀ ጌታቸው 🇪🇹 ሞስነት ገረመው 🇪🇹 ለሜቻ ግርማ 🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ ነሐስ🥉 🇪🇹 ዳዊት ስዩም 🇪🇹 መቅደስ አበበ አጠቃላይ ከተገኘው 10 ሜዳሊያ ሰባቱ በሴቶች የተገኘ ነው፤ የቀረው 3 ሜዳሊያ ደግሞ በወንዶች ውድድር የተገኘ ነው። የዓለም ሻምፒዮናው ምንም እንኳን ከፍተኛው ድል የተመዘገበበት ቢሆንም በወንዶች ውድድሮች ላይ የተሻለ መስራት እንደሚጠይቅ የሚጠቁም ነው። የአትሌቲክስ ቡድናችን ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጀግና ፣ የክብር አቀባበል እንደሚደረግለት ይጠበቃል። ውድ አትሌቶቻችን ፤ ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተጋድሎ ላስመዘገባችሁት ድል ፣ የሀገራችሁን ህዝብ ክብር ከፍ ስላደረጋችሁ ምስጋና ይገባችኃል። እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ ! @tikvahethiopia @tikvahethsport
Show all...
Addis abeba ማንኛውንም በመኖሪያ ቤትዎ፣ በመሥሪያ ቤትዎ ወይንም በሕንጻዎ የኤሌክትሪክ ችግሮች እያጋጠምዎት ይሆን?😥 ወይስ አዲስ ለሚያሰሩት ሕንጻ ወይም መኖሪያ ቤት ብቃት ያለው እና ጠንቃቃ የኤሌክትሪክ ባለሙያ ፈልገው ይሆን?🏠 ለማንኛውም የቤት ለቤት #የኤሌክትሪክ_ጥገና( Home to home electric maintenance)፣ ለቅድመ ጥንቃቄ ፍተሻ፣ ለመብራት፣ ለማሞቂያ፣ ለማሻሽያ ሥራ፣የደህንነት ካሜራ፣ የመሳሰሉትን አገልግሎቶች… #ለህንፃ_መስመር_ዝርጋታ ( #Building_Electrical_installation) ስራ እንሰራለን! ለበለጠ መረጃ👇👇👇 Contact @ashumela7 !!! 👉with attractive commissions!
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ ! ኢትዮጵያውያን የበላይ ሆነው አጠናቀዋል ! እጅግ በጣም የሚደንቅ የቡድን ስራ በታየበት የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር በጉዳፍ ፀጋይ አማካኝነት ወርቁ 🥇 ወደ ኢትዮጵያ ገቢ ተደርጓል። ነሀስም 🥉 በዳዊት ስዩም ተገኝቷል። ከፍተኛውን የቡድን ስራ የሰራችው የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ባለድሏ ለተሰንበት ግደይ 5ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ኬንያ ብር አግኝታለች። እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !! @tikvahethiopia
Show all...