cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

new chanale

Show more
Advertising posts
189Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ያልተፈተሹ ባህሪያት “ትዕግስት ስጠኝ ብለን ስንጠይቅ፤ የሚሰጠን እረጅም ሰልፍ ነው” ትላለች ጸሀፊ ትሬሲ ማክሚላን። ትዕግስትን ስንጠይቅ የሚሰጠን ትዕግስትን የምንለማመድበት መድረክና ትዕግስትን የምናዳብርባቸው ሁኔታዎች እንጂ ትዕግስት ልክ እንደተሰጥዎ ከላይ አይቸረንም። ለዛሬ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ ሀሳብ እንደሚከተለው ነው። አንዳንዴ እራሳችንን ባላሰብነው ሁኔታ ውስጥ እናገኘውና ከራሳችን የማንጠብቀው ባህሪ ሲንጸባረቅብን እንደነግጣለን። ለወትሮ እኮ እንዲህ አልነበርኩም በማለት ግራ ይገባናል። ተሳድበን የማናውቅ ሰዎች በሆነ አጋጣሚ ሌላውን ሰው ስናጥረገርገው፤ ትዕግስተኛ ነን ብለን የምናስብ ሰዎች ቀጠሮዋችን እረፈደ ብለን የታክሲውን ሹፌር ስናመናጨቀው፤ ቂመኛ አይደለሁም ስንል የከረምን ሰዎች የወደድነው ሲከዳን ለበቀል ስናደባ፤ በደላችንን ይቅር በለን እያልን ጠዋት ማታ እየጸለይን የበደሉንን ሰዎች ይቅር ማለት ሲከብደን፤የሌሎች ሰዎች ማግኘት ያስደስተናል የምንል ሰዎች እኛ የተመኘነውን ሌላው ሰው ላይ ስናየውና ሲከፋን፤ ፈራጅ አይደለንም ስንል ከርመን የእኛ ህልውና ሲነካ የፍርድ ወንበር ላይ ቁጢጥ ስንል፤ ባህሪያችን ለገዛ እራሳችን እጅግ ግራ ያጋባል። ማንነታችን የሚገለጸው እኛ ስለራሳችን ባለን አመለካከት ወይም ሌሎች ሰዎች ስለኛ ባላቸው አመለካከት ሳይሆን፤ እኛ ለሁኔታዎች በምንሰጠው ምላሽ ነው። ሰው እንቃለው የሚል ሰው ባያጋጥምም ፤ ሰው እጠላለሁ የሚል ሰው ስምተን ባናውቅም ሰው የሚንንቅና የምንጠላ ሰዎች ግን አንጠፋም። ከእኔ ከእራሴ ጭምር በውስጣችን መጥፎ ስሜት ያድራል ብለን ማሰቡ ይከብደናል፤ ይከብደናል ብቻም ሳይሆን ለማሰብም አንፈልግም። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። “እኔ” ብለን የምንጠራው ማንነት በአብዛኛው የተገነባው ባልተፈተሹ ባህሪያቶቻችን ነው። ስለራሳችን ስናወራ በአብዛኛው የምናወራው በሀሳብ ስለገነባነው ማንነት እንጂ፤ በተግባር ስለምነተገብረው ባህሪዎቻችን አይደለም። እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ በድፍረት መናገሩ ከባድ የሚሆነውም ለዚህ ነው፤ ሁላችንም ያልተፈተኑ ባህሪያቶችን አጭቀን ስለምንቀሳቀስ። አብዛኛው ባህሪያቶቻችንና አስተሳሰቦቻችን በቲዎሪ ደረጃ እንጂ በሙከራ የተረጋገጡ አይደሉም። መልካምነታችን፤ ትዕግስተኛነታችን፤ ፍትሃዊነታችን፤ ሰው አክባሪነታችን፤ እውነተኛነታችን ተገቢውን ፈተና አላለፉም። ፈተና ስል እውነተኛ ባህሪዎቻችንን እንድናጸባርቅ የሚያስገድዱን ሁኔታዎችን ነው። ጊዜ ስለተረፈን ከኋላችን ያለውን ተሰላፊ ከፊታችን ስላስቀደምነው ትዕግስተኛ ልንባል እንችላለን? በፍጹም!!! የማንኛችንም መልካምነትና ጥንካሬ በመልካም አጋጣሚዎች ሊረጋገጥልን አይችልም። በፈተናዎችና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የምናሳያቸው ባህሪያቶች ይበልጥ እኛን ይገልጹናል። ለዚህ ነው አንዳንዴ ውሳኔዎቻችንና ድርጊቶቻችን የሚያስደነግጡን። ተፈትነን ያገኘናቸው ባህሪዋቻችን ስላልሆኑ ልንጠቀምባቸው በሚገባን ቦታ ይጠፉብናል። ይህንን ማወቁ ምን ይጠቅምናል? ለሁለት ነገር ይጠቅመናል ብዬ አስባለው። አንደኛው ከውሸተኛ ማንነት ቀስ እያለ ያላቅቀናል፤ ሙሉ በሙሉ መላቀቅ ለሰው ልጅ ቢከብድም። የሚሰማንን ስሜት በካድን ቁጥርና “እኔ እኮ እንዲህ አይደለሁም” በማለት እራሳችንን በተከላከልን ቁጥር ባህሪያችንን ማሻሻል አስቸጋሪ ይሆንብናል። ከእራሳችን ጋር እየተቆራረጥን በቅዠት አለም ውስጥ መኖሩን እንለምደዋለን።በሌላ በኩል ማንነትና ባህሪያችንን ለሁኔታዎች ከምንሰጠው ምላሽ ተነስተን መዳኘት ከቻልን፤ ከእውነተኛ ምንነታችን ጋር እንቀራረባለን። የትኛው ባህሪያችን ላይ ይበልጥ ማሻሻል እንዳለብን ግልጽ ይሆንልናል። ስለራሳችን ባህሪ እርግጠኛ ሆኖ መናገሩ የሚያስከፍለው ዋጋ አለ፤ እሱም ወደ እውነት የሚወስደውን ጎዳና ያጠብብናል።እውንተኛ ማንነታችንን ለማወቅ ከፈለግን ስለራሳችን የምናስበውን ሳይሆን፤ ለሁኔታዎችና ለአጋጣሚዎች የምንሰጠውን ምላሽ ልናስተውል ግድ ይለናል። ሁለተኛው ጥቅም “እኔ ብሆን ኖሮ” በሚለው የፍርድ ዱላ እርስ በራሳችን ከመፈነካከት ያድነናል። “ የሰው ባህሪያት በሁኔታዎችና በአጋጣሚዎች አይፈጠርም፤ በሁኔታዎችና በአጋጣሚዎች ይጋለጣል እንጂ”- ዚግ ዚግለር https://t.me/joinchat/AAAAAFho5o8z4IyIQCR0pw
Show all...
የበታችነት ስሜትን የማሸነፊያ መንገዶች(ክፍል ሁለት) ------------------------------------------------- @EthioBini ማንም ከበታችነት ስሜት ጋር የተወለደ ወይም የሚወለድ ሰው የለም፡፡ የበታችነት ስሜት ተፈጥሮአዊ ሳይሆን በአካባቢ ተጽእኖ የሚመጣ ውጤት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሰዎች ስለራሳቸው የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ከአካባቢያቸው ይማራሉ፡፡ የተማሩትን ነገር ደግሞ ትተው፣ አዲስ ነገር መማር ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የበታችነት ስሜት ሊለወጥ የሚችል አስተሳሰብ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በተፈጥሮ እንዲሁም ካደገበት አካባቢ አንጻር ልዩ በመሆኑ የበታችነት ስሜትን የሚያሸንፍበት አንድ ወጥ የሆነ አካሄድ ላይኖር ይችላል፡፡ ሆኖም በዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱ ምክሮችን ተግባራዊ ቢያደርጉ ስለራሳቸው ጤናማ/ትክክለኛ የሆነ እይታ ሊያሳድጉ ይችላሉ፡፡ 1. በሌሎች ሰዎች አስተያየት ላይ ጥገኛ አለመሆን በልጅነት ወቅት አንድ ነገር ሰርተን፣ ወላጆቻችን ወይም ትልልቆች ብለን የምናስባቸው ሰዎች ጥሩ ነው፣ ትክክል ነው፣ ጎበዝ .… እንዲሉን እንፈልጋለን፡፡ በጎልማሳነት ጊዜ እንዲህ ያለውን የልጅነት ወቅት ባህርይን መተው አስፈላጊ ነው፡፡ ከሰዎች ተገቢውን አስተያየት መጠየቅና ስራችንን መገምገም ጠቃሚ ቢሆንም፣ በእነርሱ አስተያየት ላይ ጥገኛ መሆን ዞሮ ዞሮ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ይጎዳል፡፡ 2. ራሳችንን ከአሉታዊ አስተሳሰቦች መለየት በመሠረቱ በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ አስተሳሰቦች የእኛን ዋጋ አይገልጹም፡፡ እኛ ዋጋ ያለን ሰዎች መሆናችን የሚለካው በእኛ ውስጥ ባለው አስተሳሰብ አይደለም፡፡ እኛ ስለራሳችን ያለን እንዲሁም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው አስተሳሰብ ምንም ያህል አሉታዊ ቢሆን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር እኛ መልካም ሰዎች ነን፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ራሳችንን/ ማንነታችንን በአእምሮአችን ውስጥ ከተከማቸው አሉታዊ አስተሳሰብ መለየት አለብን፡፡ በሌላ አነጋገር በእነዚያ አሉታዊ አስተሳሰቦች ራሳችንን መመዘን ስንተው፣ እነዚያ አስተሳሰቦች ኃይል ያጣሉ፡፡ በእርግጥ ከእኛ ጋር ለረጅም ጊዜ የቆዩ ከሆኑ፣ ከእነርሱ ጋር ዝምድና ስለፈጠርን በቀላሉና ቶሎ ላይሄዱ/ላይለዩን ይችላሉ፡፡ ሆኖም ከእነርሱ ጋር ላለመኖር ከወሰንን፣ ቀስ በቀስ ስፍራውን ይለቃሉ፡፡ በእነርሱ ስፍራ ደግሞ ተገቢ የሆኑ ሃሳቦችን እናስገባለን፡፡ እነዚያ ቀስ በቀስ ገብተው ስፍራ እንደያዙ ሁሉ፣ አዲሱና መልካም የሆነው አስተሳሰብም ዕድል ከሰጠነው ቀስ በቀስ ወደ አእምሮአችን ገብቶ ሥፍራውን ይይዛል፡፡ 3. በውድቀታችን ራሳችንን ከመኮነን ከውድቀታችን መማር በዚህ ዓለም ላይ ሰው ሆኖ በሁሉ ነገር ፍጹም የሆነ ማንም የለም፡፡ ሰዎች በመሆናችን ሁላችንም ጠንካራና ደካማ ጎኖች አሉን፡፡ እንኳን በድካማችን በጠንካራ ጎናችንም ተገቢውን ሥራ እየሰራን ልንሳሳት እንችላለን፡፡ ሰው ሆኖ መሳሳት፣ መውደቅ፣ ስኬትን ማጣት … ያለ ነገር ነው፡፡ ስህተት የማይፈጽም ሰው የለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው ስህተታችንን የምናስተናግድበት ሁኔታ ነው፡፡ በስህተታችን ራሳችንን እየወቀስን የምንሄድ ከሆነ፣ ራሳችንን ለመቀበል እንቸገራለን፡፡ ከስህተታችን ተምረን ወደፊት ማሻሻል የሚገባንን ነገር የምናስብ ከሆነ ደግሞ ራሳችንን ተቀብለን ወደፊት እንሄዳለን፡፡ ስለሆነም በህይወታችን በእኛም ሆነ በሌሎች ሰዎች በደረሰቡን ችግሮች፣ ውድቀቶች፣ አለመሳካቶችና መልካም ያልሆኑ ነገሮች ሁሉ ራሳችንን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን ከመኮነን፣ ከክፉ ነገሮች መልካምን ነገር ተምረን ወደፊት መሄድ የተሻለ አማራጭ መንገድ ነው፡፡ ያለፈውን ህይወታችንን በተጨባጭ መገምገም አስፈላጊ እርምጃ ነው፡፡ ከህይወት ጉዞ መማር የሚቻለው ተገቢ ግምገማ ሲኖር ነው፡፡ ነገር ግን በውድቀት ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ አሉታዊ የሆኑ ሃሳቦችን ማመንዠግ/ ማሰላሰል ስለራሳችን ያለንን በጎ አስተሳሰብ ክፉኛ ይጎዳል፡፡ ‹“በቂ ጊዜ ሰጥቼ ባለማጥናቴ ምክንያት ዝቅተኛ ውጤት አገኘሁ›› እና ‹‹እኔ ትምህርት የማይገባኝ ደደብ ተማሪ ነኝ›› ማለት ልዩነት አለው፡፡ የመጀመሪያው የተጨባጭ ግምገማ ውጤት ሲሆን ሁለተኛው ግን ራስን መኮነን ነው፡፡ የመጀመሪያው haሳብ ወደ እርምት ሲያመራ ሁለተኛው ደግሞ ወደ በታችነት ስሜት ያመራል፡፡ 4. ራሳችንን በፉክክር ውስጥ አለማስገባት ለበታችነት ስሜት አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከሌሎች ሰዎች ጋር ራሳችንን ማወዳደርና መፎካከር ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ውድድር ውስጥ ስንገባ፣ እነርሱ ጥሩ እኛ መጥፎዎች፣ እነርሱ አሸናፊዎች እኛ ተሸናፊዎች፣ እነርሱ ብርቱዎች እኛ ደካሞች እንደሆንን እናስባለን፡፡ እያንዳንዱ ሰው ልዩ ሆኖ የተፈጠረ ፍጡር ነው፡፡ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለው እምቅ ችሎታ አንድ ዓይነት ላይሆን ይችላል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ያደገበትና ያለበት ዓውድ ልዩነት አለው፡፡ ስለዚህ ከሌሎች ጋር ሁልጊዜ መፎካከርና ራሳችንን ከሌሎች አንጻር ከመገመት ይልቅ እኛ ዘንድ ያለውን መልካም ነገር በመለየት በተሻለ መንገድ መጠቀም የምንችልበትን መንገድ መቀየስ ይረዳናል፡፡ ከሌሎች ሰዎች ስኬት፣ ብርታት፣ መልካም ነገሮች፣ አሸናፊነት ለራሳችን መልካም ቁምነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ ስለዚህ የፉክክር የህይወት ዘይቤን በመተው ከሌሎች መማርን መልመድ ጠቃሚ ነው፡፡ 5. ስጦታችንን በመለየት ማሳደግ እያንዳንዱ ሰው ስጦታ እንዳለው ሁሉ እኛም ስጦታ አለን፡፡ ስለዚህ በውስጣችን ያለውን እምቅ ችሎታ፣ ፍላጎታችንንና ምቹ ሁኔታዎችን በመለየት ስጦታችንን በዕውቀትና በክህሎት ማሳደግ እንችላለን፡፡ ጎበዝ በሆንበት ወይም መስራትና መሆን በምንፈልገው ጉዳይ ላይ የበለጠ ዕውቀትና ክህሎትን በማጎልበት የበለጠ ፍሬያማ መሆን እንችላለን፡፡ በችሎታችን ራሳችንና ሌሎች ሰዎችን መጥቀም ስንችል ደግሞ እርካታና ደስታን እናገኛለን፡፡ ለሰዎችም አንድ በጎ ነገር ማድረግ መቻላችን ደግሞ ስለራሳችንም በጎ አስተሳሰብ እንዲኖረን ያግዘናል፡፡ 6. ባለሙያን ማማከር አንዳንድ ጊዜ የበታችነት ስሜት ስር የሰደደና የሁለንተናዊ ህይወታችንን ጤናማነት አደጋ ላይ የሚጥል ሆኖ ሲገኝ የሰለጠነ አማካሪን ማማከር አስፈላጊ ነው፡፡ እንግዲህ ራሳችንን የመቀበል ችግር ሲኖረን በአብዛኛው ከበጎ ነገር ይልቅ በህይወታችን ውስጥ ባሉ ድክመቶች፣ ጉድለቶችና ስህተቶች ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ የበታችነት ስሜት መንስኤ የሆኑ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ ተገቢውን መፍትሔ ለመፈለግ እጅግ ያግዛል፡፡ ምክንያቶቹ ከሰው ወደ ሰው የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ራሳችንን የማንቀበል ከሆነ እኛው ለራሳችን ጠላቶች ሆንን ማለት ነው፡፡ ሁልጊዜ ከራሳችን ጋር እንጣላለን፡፡ ጠላትን በውስጣችን ተሸክመን እንዞራለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ራሳችንን በመቀበል በሰላም በመኖር የበታችነት ስሜትን ማስወገድ እንችላለን! https://t.me/joinchat/AAAAAFho5o8z4IyIQCR0pw
Show all...
Repost from #KALTUBE
♦♦ተስፋ መቁረጥን ተስፋ አስቆርጡት♦♦ #በዚች ውጥንቅጧ በጠፋ እና ዝብርቅርቋ በወጣ ዓለም እየኖሩ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አልገጠመኝም ማለት ዘበት ነው። ምክንያቱም ተስፋ በሌላት እና በተስፋ መቁረጥ በተዘፈቀች ዓለም ውስጥ ከተስፋ ሰጪ ነገሮች ይልቅ ለቁጥር አታካች የሆኑ ተስፋን እስከነአካቴው የሚያጠፉ ነገሮች በሽ ስለሆኑ ነው። #አዎን ተስፋ ለመቁረጥ ምንም ርቀት መጓዝ አይጠበቅብንም። ለምን? በዙሪያችን ያሉ ተስፋ የቆረጡ ሰዎች፣ እንዳንጠገን አድርገው የሚሰብሩን ሁኔታዎች፣ ከሀዘንና ጭንቅ ጋር የሚያጋፍጡን ጊዜዎች/ዘመናት ወቅታቸውን ጠብቀው በራችንን አንኳኩተው ብቅ ስለሚሉ ነው። ታዲያ በዙሪያችን የምንመለከተው ሁሉ ተስፋ የማይሰጥና እንድንኖር የማያስመኝ ከሆነ እዚህ ምን እንሰራለን ሲሉ ራሳቸውን ወደ ሞት የሸኙ ጥቂቶች አይደሉም። #አንዳንዴ ስናስበው የጨለመ ነገ ባላት ምድር ላይ መኖር ትርጉም ላይሰጥ ይችላል። ይህ የሚሆነው ግን ተስፋችንን በዚች ምድር ላይ ብቻ ያደረግን እንደሆነ ነው። ዓለም ነገዋን ስታስብ ጥፋት እንደሚጠብቃት ስለምታውቅ እርሷን ተስፋ የሚያደርጉትን ሁሉ ይዛ ወደ ጥፋት ጎዳና ትነጉዳለች። #እኔ ግን ዛሬ ማውራት የምፈልገው ተስፋን አለምላሚ ስለሆነው #የእግዚአብሔር መንግስት ነው። በዚህ መንግስት ውስጥ ተስፋ ማድረግ ግዴታ ነው! ምክንያቱም መሪው የተስፋ አምላክ የሆነው እየሱስ ክርስቶስ ነውና!! ተስፋችሁን በእርሱ ስታደርጉ ዛሬ ምድር ላይ ላላችሁ ጥቂት የድካም ወራት ብቻ ሳይሆን መች እንደሚያልቅ ለማታውቁት ዘልዓለም ለተባለ የጊዜ መልህቅም ጭምር ነው። ብቻ አንዴ በእርሱ ታመኑና ተስፋችሁን በእርሱ ላይ አድርጉ። የትኛውንም ያህል ተስፋ አስቆራጭ ፈተና፣ችግርና መከራ፣መልስ የማይገኝለት እንቆቅልሽ ወደ እናንተ ቢመጣ እንኳ ከተተከላችሁበት ፅኑ የተስፋ ዓለት እንደማትነቃነቁ እና እንደማትፍገመገሙ ስለሚያውቅ ተስፋ ቆርጦ ይመለሳል እንጂ የእናንተን የተስፈኝነት ድንበር መጣስ አይችልም። #ስለዚህ የወደፊት እጣ ፈንታዋ ሞት፣ባዶነት፣ጨለማ፣ጥፋትና ውድቀት ከሆነባት ከዚች ከንቱ ዓለም ላይ የተስፋችሁን ዝናር አንሱና ከዛሬዋ ዕለት አንስቶ እስከ ዘልዓለም በህይወት፣በሙሉነት፣በብርሃን፣በተስፋ፣በደስታና በፍቅር በተሞላው የእግዚአብሔር መንግስት ላይ ተስፋችሁን በማስቀመጥ ተስፋ መቁረጥን ራሱን ተስፋ አስቆርጡት። ""ተስፋን የሰጠው የታመነ በሆነበት የተስፋ መንግስት ውስጥ ተስፋ ማድረግ ግዴታ እንጂ አማራጭ አይደለም!"" ምህረት ግርማ 💐💐💐💐 @KALTUBE @KALTUBE @KALTUBE
Show all...
Repost from #KALTUBE
♦ጉብዝናችን ለጌታችን♦   💐ወጣትነት ለእናንተ ምንድነው? ለማን እና ለምን እየኖራቹበት ነው? የእግዚአብሔር ቃል በመፅሐፈ መክብብ 12፥1-8 ላይ የሰው ልጅ በጉብዝናው ወራት ማንን ማሰብ እንዳለበት  ይናገራል። በተለይ ቁጥር 1ና7 እንዲህ ይላሉ፦ ፨መክብብ 12፥1""የጭንቅ ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤"" ፨መክብብ 12፥7 ""አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::"" 💐በክፍሉ የምንመለከተው ከየትኛውም እድሜ በላይ በወጣትነታችን ጊዜ ልናስበው እና ልንኖርለት የሚገባው እግዚአብሔር መሆኑን ነው። ብዙ ሰዎች የጉብዝናቸውን ጊዜ ፈጣሪያቸውን በማሰብ መኖር እንዲገባቸው አያውቁም። ስለዚህ በዚህ ከንቱ ዓለም ውስጥ ዛሬ ታይተው ነገ ለሚጠፉ ብልጭልጭ መልኮች ፣ረብ አልባ ለሆኑ መንከራተቶች እና የስጋቸውን ለከት የለሽ ፍላጎት ለማሟላት ሲጠቀሙበት ይታያል። እግዚአብሔርን  ሊያውቁበት፣ ሊያገለግሉበትና ለእርሱ ሊኖሩለት በሚገባቸው ለጋ እድሜ የስጋቸውን ክፉ ረሃብ ሲያስታግሱ እና የራሳቸውን ፍቃድ ሲያደርጉ ይሄ ብርቱ የጉብዝና እና ለመትጋት ምቹ የሆነው እድሜያቸው ይባክናል! 💐ይህ የሚገባቸው ደግሞ ነገር ሁሉ አልጥም በሚልበት፣ከለላ፣መሸሸጊያ፣ምርኩዝና ተገን በሚሹበት የእድሜያቸው አመሻሽ ላይ ነው። የመኖር ተስፋቸው ሲጨልም፣ወደ ሞት ደጃፍ እየተጠጉ መሆኑ ሲገባቸው ያኔ ህይወታቸውን በሚያስተማምን ዓለት ላይ ለማስቀመጥ ይሻሉ። በጉብዝናቸው፣በብርታታቸው በዚያ በመትጊያቸው ወራት ያልፈለጉትን እግዚአብሔር በእርጅና እና በድካም ዘመናቸው ይፈልጉታል። በዓለም ያባከኑትን የጉብዝና ወራት ያካካሱ ይመስል በስተእርጅና ዓለም በቃኝ ይላሉ። 💐ይህ ግን ትልቅ የህይወት ብክነት የታከለበት ስህተት ነው። የሰው ልጅ የክርስቶስን አዳኝነት እያወቀ በጉብዝና እድሜው ፈያጅ ባልሆነው ከንቱ የዓለም አዘቅት ውስጥ እየዋኘ ከርሞ ሲያረጅ፣ ሲደክም፣ደስ የማያሰኙ ዓመታት መጥተው አቅም ሲያንሰው አሁን የሰማይ ቤቴን ላስተካክል ማለቱ ስለ እግዚአብሔር ያለው መረዳት ጠባብ እንደሆነ ያመላክታል። የእግዚአብሔር መንግስት የሚጠይቀውን የአኗኗር ጥራትና ልክ እያወቁ ኃላ ደርስበታለው አሁን ትንሽ ዘና(ፈታ) ልበል ካሉ ወዲያ ዓይን ሲደካክም፣ ጉልበት ሲከዳ፣ የጭንቅ ቀናት ብቅ ሲሉ፣ የተማመኑት የለጋነት መልክ ሲጠወልግ... ጊዜው ነውና እግዜርን ላገልግል ማለት ራስን ማታለል ነው! 💐በነገራችን ላይ ይህ የወጣትነት እድሜ በሁለቱ መንግስታት ማለትም በእግዚአብሔርና በዓለም ዘንድ በብዙ ተፈላጊ ነው! ምክንያቱም ወጣትነት የብርታት፣የአቅም፣በትጋት የመስራት እና የአስተሳሰብ ፍጥነት ያለበት እድሜ ስለሆነ እንዲሁም ደግሞ ለተሰየምንለት አላማ ያለፍርሃት በፅናት የምንኖርበት ጊዜ በመሆኑ ተፈላጊነቱ እጅግ ይልቃል! 💐ታዲያ እስካሁን ይህንን የጉብዝና እድሜ ለማን እንደሰጣችሁት ባላውቅም ትክክለኛው እና አማራጭ የሌለው ጉብዝናችንን ሊጠቀምበት የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ግን ልነግራቹ ወዳለው!!! በእርሱ ዘንድ ዓለምን የሚያስንቅ ድንቅ ውበት አለ! ከስጋዊነት የሚያስኮበልል አምላካዊና አባታዊ ፍቅር አለ! ስለዚህ የፈጠረን እግዚአብሔር ከእድሜም በላይ ራሳችንን እንድንሰጠው ይፈልጋል። ልክ እንደ ሸክላ ሰሪው ሽክላውን ሰባብሮ ዳግም ለውበት እንዲሆን አድርጎ እንዳደሰው እንደዚያ ህይወታችንን ሊያድስ ዛሬም የልባችንን በራፍ እያንኳኳ በደጅ ቆሟል። ከፍተን ብናስገባው ለዘላለም የህይወት ዕረፍትን ሊሰጠን፣ ከሚያረጀው ከዚህ ጊዜያዊ ስጋችን አውጥቶ የማይሞት የማይበሰብስ አዲስ ሰውነት ሊያለብሰን፣ የሚደክመውን ፍጥረታዊ ማንነት ከእኛ አስወግዶ በማይነቃነቅ ፅኑ መሠረት ላይ ሊያንፀን እርሱ ሁሉ የሚቻለው ኤልሻዳይ ነው!!  💐ጉብዝናችንን በሰጠነው በዚያ ቅጽበት  በህይወታችን የማያልቅ ሰላም፣እረፍት፣ደስታን እናገኛለን። የመንፈስ ፍሬዎች በህይወታችን ይገለጣሉ፣ ከራሳችን አልፈን ለሌሎች ከሞት የማምለጥ ምክንያት እንሆናለን፣ እድሜ የሰጠን የሁሉ ፈጣሪ ኢየሱስ ሲመጣ በፊቱ ለመቅረብ የማናፍር ባሪያዎቹ እንሆናለን። ስለዚህ ገና በእድሜያችን ጠዋት ላይ ያለን ብርቱ ወጣቶች ጉብዝናችንን የፈጠረንን ጌታ እግዚአብሔርን በማወቅ፣ በማመንና በማገልገል እንቋጭ እላለሁ!                 ጌታ ይርዳን!!!                                            ምህረት ግርማ        💐share💐share💐share💐                    @KALTUBE                    @KALTUBE                    @KALTUBE
Show all...
Repost from #KALTUBE
ምክር ቢጤ        #እንደ አንበሳ# ተመላለሱ Proverbs 28 (አማ) - ምሳሌ 1: ኀጥእ ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ያለ ፍርሃት ይኖራል። በጫካ ውስጥ;- 1.  ግዙፉ ዝሆን ነው; 2.  ረጅሙ ቀጭኔ ነው; 3.  ጥበበኛው ቀበሮ ነው; 4. በጣም ፈጣኑ አቦሸማኔ ነው። ሆኖም፣ አንበሳ ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ ምንም አይነት ባህሪና ማንነት ባይኖረውም የጫካው ንጉስ ነው። ለምን?❓ ምክንያቱም፡- 1. አንበሳ ደፋር ነው፣ በልበ ሙሉነት ይሄዳል, ማንኛውንም ነገር ይደፍራል እና ፈጽሞ አይፈራም። 2. አንበሳው ሊቆም እንደማይችል ያምናል. 3. አንበሳ ኃላፊነት የሚወስድ ነው። 4. አንበሳ ማንኛውም እንስሳ ለእሱ ምግብ መሆኑን እንጂ አሳሳቢ እንደሆነ አይቆጥርም 5. አንበሳ በቀላሉ ተስፋ አይቆርጥም። 👉ስለዚህ... በህይወት ውስጥ 1. በጣም ፈጣን መሆን ላያስፈልግህ ይችላል። ሩጫ ለፈጣኖች ስላይደለ። (መክ 9:11) 2. በጣም ጠቢብ  መሆንም ላያስፈልግህ ይችላል። እንጀራ ለጠቢባን ስላይደለ (መክ 9:11) 3. በጣም ብሩህ(አዋቂ) መሆንም ላያስፈልግህ ይችላል። ሞገስ ለአዋቂዎች ስላይደለ) (መክ 9:11) ✨አንዳንዴ የሚያስፈልግህ *ድፍረት* ብቻ ነው። ቅዱስ ድፍረት ማለቴ ነው። የሚያስፈልግህ *እንደገና ለመሞከር ፍላጎትህ* ብቻ ነው። የሚያስፈልግህ * እምነት * *የይቻላል መንፈስ ነው። የሚያስፈልግህ በጌታ ላይ መተማመን ብቻ ነው። 👉አንበሳ 20 ሰአታት ይተኛል እና ለ 4 ሰዓታት ይሠራል ከዛ ስጋ ይበላል። 👉 ዝሆን ግን ለ24 ሰአት ይሰራል እና ሳር ይበላል።     ✨ሁል ጊዜ ሻምፒዮን ወይም አሸናፊ ለመሆን ከሁኔታዎች ጋር ባለዎት አቀራረብ የህይወትዎ ስልት በጣም አስፈላጊ ነው።    በአንበሳነት ስሜት ውስጥ ይቆዩ! ይህ ስሜት  ያ የአሸናፊዎች ስሜት ነው። ባለመፍራትዎ የሚሸነፉ ብዙ የህይወት ተግዳሮቶች አሉ። Proverbs 28 (አማ) - ምሳሌ 1: ኀጥእ ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ያለ ፍርሃት ይኖራል። ✍ነቢይ መሳይ አለማየሁ 💐ለወዳጆቻችሁ ሼር 👇👇👇👇 @KALTUBE @KALTUBE @KALTUBE
Show all...
WIFI setagegnu or be datam behone awerdachehute semute plise hiwote keyare temrt new
Show all...
ብዙ ስለደከምን አይደለም ህይወት የሚከናወነው፡፡ ስኬት እና መከናወን የሚገኘው ከሰማይ አምላክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገርም የሰማዩ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባርያዎቹ ተነስተን እንሰራለን፡፡ መከናወን የሚገኘው ከሰማይ አምላክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡" እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።" (መዝሙረ ዳዊት 127:1)
Show all...
ትካዜህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል (መዝ 54(55) ÷ 22) :: ማብራሪያ ሰዎች ተክዘው ስታዩ ምን ይሰማችኋል? የምትወዷቸው ሰዎች ደግሞ ተክዘው አዝነው ስትመለከቱስ ምን ይሰማችኋል? ብዙ ጊዜ ሰዎች ተክዘው ስናይ ደስ አይለንም፤ ለራሳችንም ጥሩ ስሜት አይሰማንም፡፡ በተለይ የምንወዳቸውና የምንጫወታቸው ሰዎች ሲሆኑ እኛም እነርሱ ስሜት ውስጥ በመግባት እናዝንላቸዋለን፡፡ ሰው የሞተበት ወዳጃችን ጋር ሄደን ወዳጃችን ወደ ቤቱ መጥተው ከሚያለቅሱ ሰዎች ሁሉ ጋር ሲያለቅስ ስናየው አንገታችንን በማቀርቀር እኛም እናዝናለን፡፡ ላዘኑ ሰዎች የማዘን ልምድ ብዙዎቸን አለን፡፡ ከሆነልን ደግሞ በምንችለው ሁሉ ልናረጋጋቸውና ከተከዙበት ነገር ልናወጣቸው እንሞክራለን፡፡ እንግዲህ እኛ እንደዚህ እንደምናስብ ሁሉ እግዚአብሔርም ስንተክዝ ዝም የሚለን አምላክ ሳይሆን ትካዜህን በእኔ ላይ ጣል ፤ እደግፍሀለሁ ያለ አምላክ ነው፡፡ በነገር ሁሉ ሊረዳን የሚፈልግ አምላክ ነው ያለን፡፡ እንደ ተከዙ ሰዎች ሁሉ እኛም የምናስበቸው ነገሮች እንደምናስባቸው ሳይሆኑ ሲቀሩ ትካዜ ውስጥ እንገባለን፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች እንተክዛለን፡፡ በትካዜአችንም ሰዓት የፈጠረን አምለክ ይረዳናል፡፡ እግዚአብሔር በሁሉም ነገር የሚረዳን አምላክ ነው፡፡ በተከዝን ሰዓት ደግሞ ቅርባችን ነው፡፡ ያስተከዘንን ነገር ብንሰጠው በቶሎ ይደግፈናል፡፡ የሚረዳን አምለክ እያለ ለእግዚአብሔር ትካዜአችንን ባለመስጠት ለረጅም ጊዜ ትካዜ ውስጥ መቆየት የለብንም፡፡ መነሳት አቅቶት መሬት ላይ የተቀመጠ ሰው እጁን ሲሰጠን ደግፈን እንደምናስነሳው ትካዜአችንን ለእግዚአብሔር ስንሰጠው ይደግፈናል፡፡ ትካዜአችንንም ያስረሳናል፡፡
Show all...
#እስኪ-አንብቧት #አይ_ሞታሞት ማይክል ጃክሰን ለ150 አመት ያህል መኖር ይፈልግ ነበር ፡፡ በዚህም ምክንያት 12 ሀኪሞችን በቤቱ በየቀኑ ከራስ ፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ይመረምሩት ነበር ፡፡ የሚመገበዉም ምግብ ከመመገቡ በፊት በላብራቶሪ ገብቶ ይመረመር ነበር ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም 15 ሰዋች ደግሞ መስራት ስላለበት የሰውነት እንቅስቃሴ ይቆጣጠሩ ነበር ፡፡ የሚተኛበትም አልጋ ትልቅ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የመኝታ ቤቱን ኦክስጂን መጠኑን ያስተካክል ነበር ፡፡ በውጭም እንዳጋጣሚ ከሰውነት አንዱ ከተጎዳበት የሰውነት አካል የሚሰጡ ሰዋች ዘወትር በተጠንቀቅ ነበሩ ፡፡ ይህ ሁላ ሲሆን ማይክል ጃክሰን 150 አመት የመኖር ህልም ነበረዉ ፡፡ ነገር ግን ሊሳካለት አልቻለም ፡፡ ሁሉም በነበር አለፈ ፡፡ በሰኔ 25 ፣ 2009 G.C በ 50 አመቱ ልቡ መስራት አቆመ ፡፡ የነዛ 12 ሀኪሞች ርብርብ ምንም ሊሰራ አልቻለም ፡፡ ከዚህ በላይ የ ሉሳንጀለስና የካሊፎርኒያ ሀኪሞች ጥምረት ያመጣው ለውጥ አልነበረም ፡፡ የእድሜዉን አጋማሽ በሀኪሞች ክትትል የሚጓዘዉ 150 አመት የመኖር ህልሙን ሊያሳካ አልቻለም ፡፡ የማይክልን የመጨረሻ የምር ቆይታ በአለም 2.5 ሚሊዮን ህዝብ በቀጥታ ተከታትሎታል በታሪክም በብዙ ሰዉ የታየ የቀጥታ ስርጭት ሁኗል ፡፡ በሞተበትም ቀን የአለማችን ትልልቅ Internet መፈለጊያዎች እነ Wikipedia , Twitter , AOL'S ተጨናንቀዉ መስራት አቁመዉ ነበር ፡፡ ማይክል ሞትን መፈተን አስቦ ነበር ሞት ግን ቀድሞ ፈተነዉ ፡፡ በዚህ ቁሳዊ አለም ምንም የማይዘዉ ሞት የሚፈትኑትን አብዝቶ ይፈትናል ፡፡ ✅✅✅✅✅ አሁን ይህን ልብ ብለን እናስብ ! ❖ለምን ቁሳዊ ህይወትን አብልጠን እንወዳለን? ❖በዚህ አለም ትልቅ የምንሮጥለት ነገር ምንድን ነዉ? ❖ለምን በመንጋ አስበን በመንጋ ኑረን በመንጋ እንሞታለን ? ❖ሕይወታችን የሚነዳዉ ሀሳባችንን በመለወጥ ነዉ ወይስ ልብስና መልካችንን በመለወጥ ? ከዚህ ሁሉ ግን የማይካድ አንድ ብቸኛ ሀቅ አለ ። እዚች ምድር ተተምናልን ከተሰጠችን እድሜ ባሻገር ዘለዓለም መኖር መቻሉ ነው። ስጋዊ ሞት ሊያስቀረው የማይችለው ዘለዓለም የሚባል ህይወት አለ። እሱንም ኢየሱስ ክርስቶስ የሚባል ስለ ሰዎች በደልና መተላለፍ ስጋ ለብሶ በቀራኒዮ የከፈለውን ዋጋ በመቀበል እንዲው በእምነት በቻ የሚገኝ የዘለዓለም ህይወት ነው። ዮሐንስ 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ¹⁷ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። ¹⁸ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። ኤፌሶን 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹-² በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ³ በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ⁴ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ⁵ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ⁶-⁷ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው አንብበው ከጨረሱ ሌሎችም እንዲያነቡት ሼር ያድርጉት
Show all...
ውስጥህ ሲደሰት.... ደስታህን በኑሮህ ከሚገጥሙህ ሁኔታዎች ጋር አታገናኘው፤ ደስታ ማለት የችግር አለመኖር አይደለም፤ በችግር ውስጥ እያለፍክ መሳቅ ነው። ነገሮች ምርጥ ሲሆኑማ ሁሉም ይደሰታል እኮ፤ አንተ ግን በአምላክህ እና አጠገብህ ባሉ መልካም ነገሮች ሁሌም ደስተኛ ሁን። ውስጥህ ሲደሰት ውጪህ ላይ ይገለጣል፤ ከዛ አንተ ደስተኛ ስለሆንክ አለም አብራህ ትስቃለች፤ ከባድ የመሰለህ ነገር ተራ ሲሆን ታየዋለህ፤ ሰዎች የደስታህን ምንጭ ለማወቅ ሲሉ አክብረው ያደምጡሀል፤ አንተ ጋር ማውራት ወይ አብሮህ መሆን የማይፈልግ የለም፤ ያንተ ስራ መገረም ብቻ ይሆናል። ወዳጄ መቼም የማይተው አምላክ እንዳለህ ማሰቡ ራሱ የደስታ ጥግ ነው። ደስታ የሞላበት ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Show all...
Repost from GOSPEL TV ETHIOPIA
.....መስቀሉን ታግሶ! ✍ በአውሮፕላን እየበረርን ሆነን የሚያበሳጭ ነገር ቢገጥመን "ወራጅ አለ!" አውርደኝ አንልም ነገር ግን ነገሮችን ዋጥ አርገን መዳረሻችን እስክንደርስ ወይም አይሮፕላኑ መሬት ላይ እስኪያርፍ ድረስ እንታገሳለን። "እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን" ያዕቆብ 5: 13 #ትዕግስት_የጸጋ_ስጦታ_ሳይሆን_የምናልፍበት_የሕይወት_ትግል_ጽናት_ውጤት_ነው!! አንድ ሰው ወደ አቀደው ቦታ ለመድረስ አስቦ መሄድ ሲጀምር የሚገጥሙትን ፈታኝ ነገሮች በትዕግስት ማሳለፍ ካልቻለ ብዙ ነገሮችን ያጣል ። “አብርሃምም በትዕግሥት ከጠበቀ በኋላ የተሰጠውን ተስፋ አገኘ።” — ዕብራውያን 6፥15 (አዲሱ መ.ት) በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ያሉ አባቶች ወደ ፍፃሜያቸው የደረሱት ስለአመኑ ብቻ ሳይሆን ስለታገሱም ጭምር ነው። ጌታችን ኢየሱስም በፊቱ ያለውን ደስታ በእምነት በመመልከት የመስቀልን መከራ ታግሶ በማለፍ ሄዳል። መስቀልን ከመታገስ ውጭ ምንም ማድረግ አይቻልም። “የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።” — ዕብራውያን 12፥2 (አዲሱ መ.ት) የትዕግስት ጉዞ ለጊዜው መራራ ቢሆንም ፍሬው ግን እጅግ ጣፋጭ ነውና እንታገስ። «ምክንያቱም የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ። ምንም የማይጐድላችሁ ፍጹማንና ምሉኣን እንድትሆኑ ትዕግሥት ሥራውን ይፈጽም።» ያዕቆብ 1 : 3 - 4 መልካም ቀን ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ @GospelTvEthiopia @GospelTvEthiopia
Show all...
ውድድር ጀምር ! ህይወት ያለውድድር ወደፊት እንድትሄት አታደርግህም ! ውድድር ከሌለባት ወደኋላ ነው የምትሄደው ፤ ነገር ግን ዋናው ቁም ነገር የምትወዳደረው ከማን ጋር መሆኑን መለየት ነው! ከሰዎች ጋር ወይስ ከራስህ ጋር ? እኔ የምመክርህ ምን እንደሆነ ታውቃለህ ውድድርህን ከራስህ ጋር አድርገው ከትላንት ማንነትህ ጋር ተወዳደር ፤ የሰዎችን እማ ያለፉበትን ነገር ምን ታውቃለህ ምን እንደገጠማቸው ምን እንደሚያስቡ ምን እንደሚፈልጉ በምን ታውቃለህ ከምናቸው ጋር ነው የምትወዳደረው ? በዚህች ምድር ላይ እኮ ጠንቅቀህ የምታውቀው አንተን ራስህን ብቻ ነው ስለዚህ ትላንትህን ታሪክህን እምነትህን ድልህን አስበው ዛሬ ላይ ደግሞ ምን እንዳለህ እየው ከዛም ከትላንቱ የበለጠ ለማሸነፍ ታጥቀህ ተነሳ ራስን እነደማሸነፍ ትልቅ ድል የለም ! የድል ቀን ተመኘን 🙏 @Inspire_ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Show all...
ልባችንን በእግዚአብሔር እናበርታ። እንዲህም ሆነ፤ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ በመጡ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በደቡብ አገርና በጺቅላግ ላይ ዘምተው ነበር፥ ጺቅላግንም መትተው በእሳት አቃጥለዋት ነበር፤ ሴቶቹንና በውስጥዋም የነበሩትን ሁሉ ከታናሽ እስከ ታላቅ ድረስ ማርከው ነበር፤ ሁሉንም ወስደው መንገዳቸውን ሄዱ እንጂ አንድስ እንኳ አልገደሉም ነበር። ዳዊትና ሰዎቹም ወደ ከተማ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በእሳት ተቃጥላ፥ ሚስቶቻቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም ተማርከው አገኙ። ዳዊት ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለማልቀስ ኃይል እስኪያጡ ድረስ አለቀሱ። የዳዊትም ሁለቱ ሚስቶቹ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያ ተማርከው ነበር።ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻቸው የሕዝቡ ሁሉ ልብ ተቈጥቶ ነበርና ሕዝቡ ሊወግሩት ስለ ተናገሩ ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አበረታ (1ሳሙ 30÷1-26) ። ማብራሪያ ዳዊት በዚህ ጊዜ የሚኖረው በስደት አገር በፍልስጥኤም ነው፡፡ የሚኖርባትም ከተማ ጺቅላግ ትባላለች፡፡ ከዳዊት ጋር አብረው ከእስራኤል ወደ ስደት አገር የወጡት 600 ሰዎች ናቸው፡፡ ዳዊትና ጦርነት የሚችሉ ሰዎች ለሶስት ቀናት በጺቅላግ አልነበሩም፡፡ ሲመለሱ የጠበቃቸው አስደንጋጭ ነገር ነበር፡፡ ከተማዋ በጠላቶቻቸው በእሳት ተቃጥላ ነበር፡፡ በተጨማሪም ጠላቶቻቸው (አማሌቃውያን) ሴቶችንና በከተማ የነበሩትን ከትንሽ እስከ ሽማግሌ ድረስ ማርከው ወስደው ነበር፡፡ የዳዊት ሁለት ሚስቶቹና የሰዎቹ ሚስቶችና ልጆቻቸው ተማርከው ተወስደው ነበር፡፡ ዳዊትና ሰዎቹ ማልቀስ እስኪያቅታቸው ድረስ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፡፡ የዳዊት ሰዎች ለደረሰባቸው ሀዘን ዳዊትን ተጠያቂ እንደሆነ በማሰብ ሊወግሩት ተመካከሩ፡፡ ጎልያድን ለመግደል ያልተጨነቀው ዳዊት በዚህ ጊዜ እጅግ ተጨነቀ፡፡ ዳዊት በስደት አገር የሚኖረው ንጉሡ ሳኦል ሊገድለው ስለሚፈልገው እንዳይሞት ብሎ ነው፡፡ ንጉሥ የማይከሰስበት ግዜ ስለሆነ ስደት መረጠ፡፡ እንዳይሞት ብሎ ከሀገሩ የወጣው ዳዊት ሞት አንዣበበበት፡፡ በዚህ ላይ ሁለት ሚስቶቹ በመማረካቸው ሀዘን ላይ ነው፡፡ በጣም ተጨንቋል፣ነገሮች እንደዚህ ተደራርበውበት ልቡን በአምላኩ በእግዚአብሔር አበረታ፡፡ ነገሮች ሲደራረቡብን እግዚአብሔር ግን በኔ ላይ ይህን ለምን ያመጣብኛል? በማለት ሊከፋን ይችላል፡፡ አንዳንዶች፤- እየለመንኩት እንዲህ ካመጣብኝ ለምን እጸልያለሁ? በማለት ጸሎት የሚተዉ አሉ፡፡ ደዊት የደረሰበት መከራ ታላቅ ነው፡፡ የበረታውም በአምላኩ በእግዚአብሔር ነው፡፡ ምንም ነገር ቢገጥመን ልባችንን በእግዚአብሔር እናበርታ፡፡ የሚገጥሙን ነገሮች ከእግዚአብሔር በላይ አይደሉም፡፡ ጥሩ ያልነው ነገር ከእጃችን ቢያመልጥ ሌላ የተሻለ ሊሰጠን እንደሚችል በማሰብ ልባችንን በእግዚአብሔር እናበርታ፡፡ የማንወጣው የሚመስለንን የእግዚአብሔርን ታላቅነቱን በማሰብ ልባችንን በአምላካችን እናበርታ፡፡ እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ከደረሰበት መከራ ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር ስላለው ህብረት ዋጋ ይሰጣል እንጂ አያጉረመርምም፡፡ በመከራው ውስጥም ሆኖ እግዚአብሔርን ማምለኩንና በእግዚአብሔር መታመኑን ይቀጥላል፡፡ ለሚያልፍ መከራ አምላኩን አይተውም፡፡ ዳዊት ልቡን ካበረታ በኋላ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቆ ተከታትሎ ደረሰባቸው፡፡ ማርከው የወሱዱአቸውን በሙሉ አስመለሰ፡፡ ያ ያስጨነቀው ነገር በእግዚአብሔር ልቡን በማበርታቱ እንዲያውም ከጠላቶቹ ምርኮ ይዞ አንዲመለሰ ምክንያት ሆነው፡፡ የሚገጥሙን ተግዳሮቶች ያለንን ነገር ሊያሳጡን ብቻ ሳይሆን የሆነ ነገርም ሊያስጨምሩልን ጭምር ስለሚመጡ እኛ በእግዚአብሔር ልባችንን እናበርታ፡፡ ዳዊት መጀመሪያ ላይ ተጨነቀ፤ በመቀጠል ግን በእግዚአብሔር ልቡን አበረታ፡፡ በተለያየ ምክንያት ለተጨነቅን ሰዎች እንደ ዳዊት ልንጨነቅ እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር ካስጨነቀን ነገር በላይ መሆኑን በማሰብ ልባችንን እናበርታ፡፡ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ስናስብ ያስጨነቀንን ነገር ሁሉ እንረሳለን፡፡ በእግዚአብሔር ልብን ማበርታት ታዲያ እንደዚህ አይደል!
Show all...
💪💯 እነዛን ሰዎች አስታውስ! 💪💯 በህይወትህ ትልቅ ዋጋ ያላቸው ሰዎች እነማናቸው ? በከበዱ የህይወት አጋጣሚ ወቅት አብረውህ የነበሩ ፣ ወድቀህ ተጥለህ በነበረበት ጊዜ ያስታወሱህ ፣ ከውድቀትህ ያነሱህ ፣ በአይዞባይነት የደገፉህ ፣ በስብራትህ ወቅት ከጎንህ የቆሙ እነርሱ ሰዎች እነማናቸው? የት ናቸው ? ምንላይ ናቸው ? ድጋፍህን ይፈልጉ ይሆን ? እርዳታህስ ያስፈልጋቸው ይሆን ? አስበሃቸው ታውቃለህ ? ዛሬ ላለህበት ደረጃ ምን አበርክተው ይሆን ? 💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! እነዛን ሰዎች አስታውስ ፤ እነዛን ሰዎች ወደኋላ ተመልከት ፤ ፈልጋቸው ፤ ጠይቃቸው ፣ ለምስጋናም ቢሆን እጅህን ዘርጋላቸው ። ዛሬ የትም ብትደርስ የሆነ ጊዜ ሰዎች ረድተውሃል ፣ ዛሬ ጥሩ የሚባል ቦታ ብትገኝ የሆነ ጊዜ ሰዎች እንዲያግዙህ ተማፅነህ ነበር ። ለአፍታ ዞር ብለህ ያለፈ ህይወትህን ተመልከት ፣ ታሪክህን ቃኝ ፣ ከባድ ጊዜያትህን አስታውስ ። በዛን ሰዓት ማን አብሮህ ነበር ? ማን ሲደግፍህ ነበር ? ማንስ አበረታታህ ፣ ተስፋ ሰጠህ ፣ ህይወትህን አስቀጠለ ፣ ወደፊት አራመደህ ? ቀን ሲጨልም ወዳጅ ይሸሻል ፣ ሃብት ሲጠፋ ችግር ሲያይል አስታዋሽ ይጠፋል ፣ ሰው ሁሉ ያለውን ሲያሳድድ ያጣውን ፣ የተራቆተውን ፣ ባዶውን የቀረውን ማንም ዞር ብሎ አያየውም ። 💪💯 አዎ! ማንም ማድረግ እየቻለ ፣ አቅሙ እያለው ዞሮ ማለፍን በመረጠበት ወቅት ዞሮ ከማለፍ ቀርበው የጠየቁህን ፣ ፊት ከመንሳት ለጥያቄህ ትኩረት የሰጡትን ፣ ሊረዱህ የሞከረቱን ብርቱ የህይወት አጋሮችህን እንዳትረሳ ። መተባበር ፣ መረዳዳት ፣ መደጋገፍ ቀን የከፋ እለት ፣ ችግር የሰፋ እለት ፣ እጦት የበዛ ጊዜ ነውና እውነተኛ ወዳጅም የሚለየው በዛኑ ወቅት ነው ። በደህናው ቀን ማንኛውም ሰው ይፈልግሃል ፤ ይጠይቅሃል ፤ ሊቀርብህ ፣ ሊያግዝህ ይሞክራል ። የእውነት ሲደክምህ ፣ ሰው ስታጣ ፣ ባዶነት ሲወርስህ ፣ ጉልበት ሲከዳህ ሊደግፍህ የመጣ ግን እርሱ የምንጊዜውም ልባዊ ወዳጀህ ፣ ቅን አሳቢ አዛኝህ ነው ። ሲኖርህ አትርሳው ፣ ቀን ስለወጣልህ አትዘንጋው ፣ ቀና ስላልክ ፊት አትንሳው ምንም ቢሆን እዚ ለመድረስህ አሻራውን አሳርፎብሃል ፣ አስተዋፅዖም አድርጎልሃልና ። ውለታን አስታወሽ ፣ የክፉ ቀን ወዳጁን የማይረሳ በእርግጥም በሰውነት ሰው የሆነ ፣ በማንነትም የላቀ ነውና እነዛን ሰዎች በፍፁም አትርሳቸው ፣ በልብህ ያዛቸው በመንገድህ ሁሉ አስታውሳቸው ፣ ለምስጋናም ቢሆን ጊዜ አትጣ ። ═════════❁✿❁ ═════════ 💪💯 እነዚህን አነቃቂ ፅሁፎች በምስል አስደግፈን በዩቲዩብ ቻናላችን ልናቀርብ ሙሉ ዝግጅት ጨርሰናል እናንተም በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://youtube.com/channel/UCJiGc3vKQtBmULwP5qlFvtg 💪💯 አንብባችሁ #ሼር አላደርግ ስትሉ #ብሞት እንኳን #የማትቀብሩኝ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ #ልሙትላችሁ  ሆሆ ፣ ለማንኛውም አሁንም #ሼር አድርጉልን የቴሌግራም ቻናላችንንም ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇 https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
Show all...
ክፉ አድራጊውን በቸርነቱ አጸደቀው፡፡ ከተሰቀሉት ከክፉ አድራጊዎቹም አንዱ፡- አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን? ራስህንም እኛንም አድን ብሎ ሰደበው።ሁለተኛው ግን መልሶ፡- አንተ እንደዚህ ባለ ፍርድ ሳለህ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን? ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው። ኢየሱስንም፡- ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው።ኢየሱስም፡- እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው ( ሉቃ (የሉቃስ ወንጌል) 23፥39-43) ፡፡ ማብራሪያ በገነት ከኔ ጋር ትሆናለህ የተባለው ክፉ አድራጊው ያደረገው ስራ ሊያሰቅለው የሚገባ ነገር ነበር፡፡ ከፉ አድራጊው በገዛ አንደበቱ፡- ላደረግነው ነገር የሚገባንን ቅጣት እየተቀበልን ነው ብሎ ነግሮናል፡፡በዚህ በመጨረሻው ሰዓት ላይ ይህ ክፉ አድራጊ ያለው መልካም ሥራ ምንም ነበር፡፡ ሊያሰቅለው የሚችል ክፉ ስራ ብቻ ነበር ያለው፡፡ ሌላኛው ወንጀለኛ (ክፉ አድራጊ) ክርስቶስን፡-ራስህንም እኛንም አድን ባለው ሰዓት በገነት ትኖራለህ የተባለው ወንጀለኛ እግዚአብሔርን አትፈራምን? ብሎታል፡፡ምንም እንኳን እርሱ ራሱ እግዚአብሔርን መፍራት አጥቶ ለመሰቀል የሚያበቃውን ወንጅል ቢፈጽምም፡፡ ይህ ወንጀለኛ ክፉ ነገር በማድረጉ እንዲሰቀል ተፈረዶበት ፍርዱን እየተቀበለ ÷ ኢየሱስ ክርስቶስን፡- በመንግስትህ በመጣህ ግዜ አስበኝ ሲለው ÷ኢየሱስ ክርስቶስም ፡-እውነት እልሀለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ የልብህን ሰርተህ፣ ወንጀል ፈጽመህ ባለቀ ሰዓት ማጣፊያው ሲያጥርህ ነው ፡-አሁን አስበኝ የምትለኝ አላለውም፡፡በሰራው ክፉ ስራ እስከ መሰቀል ያደረሰውን ወንጀለኛ በተጨማሪ ሰዓት ብለው ይሻለኛል አጸደቀው፡፡ከዛ የጠበቀው ሞት ነበር፤አሸለበ፡፡በዛው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሄደ፡፡ ለምትደግፉት ቡድን በተጨማሪም ሰዓት ጎል ልትጠብቁ ትችላላችሁ ፡፡ ክፉ አድርጎ እንዲሞት ለተፈረደበት ወንበዴ መጽድቅ ግን እንዴት ይታሰባል? ቸሩ አባት፡- ባለቀ ሰዓት እንዲህ በማለትህ እማራለሁ ብለህ አስበህ ነው? በል አትልፋ አላለውም፡፡የመጨረሻ አንድ ሰከንድ ላይም ብንሆን ይቅር በለን እንበለው ፡፡በሞት አፋፍ ላይ እንኳን ሆነን ማረን እንበለው ይቅር ይላል፡፡ ወንጀለኛ የተባለውን አጸደቀ፤ መሀሪ መሆኑን ለማሳየት ከዚህ በላይ ምስክርነት ምን እንግዲህ ይምጣ ፡፡ ሩጫ ላልሮጠ እንዴት ሜዳሊያ ይጠለቅለታል? የሮጠስ ቢሆን መጨረሻ ወጥቶ አንደኛ እንደወጣ ተወዳዳሪ ሜዳሊያ እንዴት ይጠለቅለታል? ይህ የማይሆን ነው፡፡ ክርስቶስ ግን የማይሆነውን አደረገ ማለቴ ወንጀለኛውን(መልካም ሥራ ያልነበረውን)፡- ዛሬ በገነት ከኔ ጋር ነህ አለው፡፡በዚህ ክፉ አድራጊ ላይ የሚያስገርም ምህረቱን ገለጸ፡፡ አምነነው መከተላችንን አንተው፡፡ስለ ዛሬ ነው የምናወራው፡፡ነፍሱን የሰጠን መንግስቱን አይከለክለንም፡፡ነፍሱን ሊሰጠን ያልሳሳ መንግስተ ሰማያትን ሊሰጠን አይሳሳም፡፡ክፉ አድርጎ ላደረገው ክፉ ስራ ስቅላት የተፈረደበትን ወንጀለኛ አጸደቀው፡፡ለመጀመሪያ፡-ዛሬ በገነት ከኔ ጋር ነህ ያለው ይህን ወንጀለኛ ነው፡፡ ስለ ምህረቱና ደግነቱ ምን ይባላል? መገረም መገረም ከመገረም ውጭ ምንም የምነለው እኛ የለንም፡፡ያስገረመን ደግሞ አባታችን መሆኑን ስናስበው ደስ ይለናል፡፡ሁሌም ስለዛሬዋ ቀን እናስብ፡፡ነገ የኛ ይሁን አይሁን እርግጠኞች አይደለንም፡፡ለዚህ ክፉ አድራጊ የራራ አምላክ ለኛም ርኅሩኅ ነው፡፡አምነነው ለተከተልነው ነፍሱን የሰጠን መንግስቱን ያወርሰናል፡፡ነፍሱን ያልነፈገን መንግስቱን አይነፍገንም፡፡
Show all...
እግዚአብሔርን ማወቅ
Show all...
ማደግና መስጠት! የሰውን ልጅ ደስታ ሙሉ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው ። #የመጀመሪያው ማደግ ነው ፤ ከትላንት የተሻለ ማንነት፣ ዕውቀትና ልምድ እየጨመርክ እያደክ መሄድ ለአይምሮህ ሰላም ይሰጥሀል ። #ሁለተኛው ደግሞ መስጠት ነው ፤ ካለህ ላይ ጊዜህን ፣ ገንዘብህን ፣ ዕውቀትህን ወይ ሀሳብህን ስትሰጥ የመንፈስ እርካታ ይኖርሀል ። ወዳጄ በየቀኑ ማደግና መስጠት ፀባይህ መሆን አለበት ። የደስታ ቀን ተመኘን ።
Show all...
Repost from GOSPEL TV ETHIOPIA
የወርቅ እንቁላል ✍️ አንድ ገበሬ ብዙ ዳክዬዎች ነበሩት ከብዙዎቹ ዳክዬዎች መካከል አንዷ ዳክዩ የወርቅ እንቁላል ትጥል ነበር። ታዲያ አንድ ቀን ገበሬው በሆዷ ውስጥ ብዙ የወርቅ እንቁላል አለ ብሎ ስላሰበ ብዙ የእንቁላል ወርቅ ካላት ደግሞ በቶሎና በቀላሉ ሀብታም መሆን እችላለሁ ብሎ ስላመነ ብዙም ሳያስብበት የዳክዬዋን ሆድ ቀዶ ይመለከታል፤ ሲመለከትም ያገኘው አንድ የወርቅ እንቁላል ብቻ ነበር። ብዙዎቻችን በየቀኑ ከሚደረግልን ጥቃቅን ነገሮች ተነስተን ከማመስገን ይልቅ በአንድ ጊዜ የሆነን ነገር ለማግኘት የስግብግብ ህይወት ውስጥ እንገባለን። በዚህ ታሪክ ውስጥ የምንረዳው መልእክት ''ስግብግብነት ወደ ከፍተኛ ኪሳራ ያመራል'' የሚለው ነው። “ነገር ግን እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት ጋር ትልቅ ትርፍ ነው።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥6 (አዲሱ መ.ት) #ያለኝ_ይበቃኛል_እንድናመሰግን_ሲያደርግ_ስግብግብነት_ደግሞ_ለማጉረምረም_ይዳርጋል። ይህ ገበሬ ዛሬ ያለውን እንደ ቀላል ባያይና በየቀኑ በሚያገኘው ቢያመሰግንስ? ታሪኩ ሌላ ይሆን ነበር። ስለዚህ ያለንን ይዘን እያመሰገንን ሌላ ጥሩ ነገር መጠበቅ እንችላለን። ብዙ ጊዜ በሕይወት ወደፊት ለሚመጣው ትልቅ ግምት እንሰጣለን ፤ ያለፈውን እናጋንናለን ነገር ግን የዛሬውን እናቃልላለን። ይልቅስ በአሁኑ እና በዛሬ በማመስገን እንኑር። መልካም የምስጋና ቀን ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ 🔻🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻🔻 @GospelTvEthiopia @GospelTvEthiopia @GospelTvEthiopia
Show all...
💪💯 ከምንጩ ተገናኝ! 💪💯 ፍላጎትህን አንተ እወቀው እንዴት አገኘዋለሁ ፣ እንዴት እደርስበታለሁ የሚለውንም ለአምላክህ ስጠው ። የፈለከውን ስላወክ ፣ በትንሹም ቢሆን ጥረት ስለጀመርክ ፣ አዋጩን አቅጣጫ ስለያዝክ እንዴትም አድርጎ ፣ አቆይቶም ይሆን አፍጥኖ ፣ አቅልሎም ሆነ አክብዶ ያሰብከውን ነገር በእጅህ የሚያስገባ ድንቅ አምላክ አለህ ። ያንተን ሃላፊነት ስትወጣ እርሱም አሻራውን ያሳርፍብሃል ፣ ስራውን ይሰራብሃል ። ከፈጣሪህ ጋር በሰራህ ቁጥር ከፍላጎትህ በላይ ለድል ትበቃለህ ፤ ካሰብከው በላይ ከፍ ትላለህ ፤ ደስታህን ያለልፋት ታገኘዋለህ ። 💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! ከምንጩ ተገናኝ ፣ መሰረቱን ያዝ ፤ የሰራህን ፣ ያበጃጀህን ፣ የፈጠረህን አግኘው ። ድንቅ የሚያደርግ ፣ ተዓምር የሚሰራ ፣ መሰናክሎችህን የሚሰባብር ፣ ፊትለፊትህን የሚያስተካክል ፣ እርምጃህን የሚያፈጥን ፣ ህመምህን የሚያክም ፣ መንፈስህን የሚያነቃ ፣ አንተነትህን ከፍ የሚያደርግ እፁብ ድንቅ አባት ፣ ግሩም አምላክ እንዳለህ አስታውስ ። ፈልገህ ባትገናኘውም በቅርብህ አለ ፣ ሁሌም ውስጥህ አለ ፣ በደጃፍህ ይመላለሳል ፤ በህይወትህ ውስጥ ድርሻ ትሰጠው ዘንድም ዘወትር ይጠባበቅሃል ። 💪💯 አዎ! አምላኩን የያዘ ፣ ከአስገኚው የተገናኘ ፣ ከፈጣሪው የተቆራኘ ሰው ምንም አይጎድልበትም፣ ምንም አያንሰውም ፣ ምንም አያጣም ። ህይወቱ ሙሉ ፣ ሃሳቡ ግሩም ፣ ተግባሮቹ አስደናቂ ፣ እያንዳንዱ እርምጃው የበረከቱ መገለጫዎች ናቸው ። የከበደህ ነገር ቢኖር ከፈጣሪህ ጋር ተወያይ ለእርሱ ስጠው ፤ ሃሳብህ ቢከብድህ ፣ ፍላጎትህ ከአቅምህ በላይ ቢሆን ፣ እንደማይሳካ ፣ እንደማይሆንልህ ከተሰማህ ጭንቀትህን አዋየው ፣ ፍላጎትህን ግልፅ አድርግለት ፣ ባንተ ላይ እንዲሰለጥን ፣ ባንተ ላይ ተዓምራትን እንዲያደርግ ፣ ጥበቡን እንዲገልፅብህ ፍቀድ ። 💪💯 አዎ! ፍላጎትህን ካወክ ፣ መንገድህን ከጀመርክ አንድ የሚመራህ አካል እንደሚኖር አትጠራጠር ። የመንገዱን ባለቤት ይዘህ መዳረሻው አይጠፋህም ፤ ምሉዕ በኩሉ የሆነን አምላክ ይዘህ የሚጎድልህ ነገር አይኖርም ፤ መሰረቱን ይዘሃልና አትስጋ ፤ ዋናውን አግኝተሃልና ሀሳብ አይግባህ ። ጥያቄህ እስኪመለስ መጠየቅህን እንዳታቆም ፣ የፈለከው በእጅህ እስኪገባ በፅናት ተፋለም ፣ የልብህ መሻት እስኪፈፀም ከፍለጋህ አትገታ ። በየትኛውም የህይወት ጉዞ ፈጣሪህን አስቀድም ፣ ነገሮችን አስቀድሞ ያበጃጅልህ ዘንድ ስልጣን ስጠው ። ምንም ነገር ከመጀመርህ በፊት አምላክ አብሮህ እንደሆነ እመን ፤ ፍላጎትህም በእርሱ ሃይል በአንተ ብርታት እንደሚፈፀም ተማመን ። ═════════❁✿❁ ═════════ 💪💯 አንብባችሁ #ሼር አላደርግ ስትሉ #ብሞት እንኳን #የማትቀብሩኝ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ #ልሙትላችሁ ሆሆ ፣ ለማንኛውም አሁንም #ሼር አድርጉልን የቴሌግራም ቻናላችንንም ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇 https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
Show all...
🌼🌼🌼happy new year 🌼🌼🌼
Show all...