cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

new chanale

Show more
Advertising posts
189Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ያልተፈተሹ ባህሪያት “ትዕግስት ስጠኝ ብለን ስንጠይቅ፤ የሚሰጠን እረጅም ሰልፍ ነው” ትላለች ጸሀፊ ትሬሲ ማክሚላን። ትዕግስትን ስንጠይቅ የሚሰጠን ትዕግስትን የምንለማመድበት መድረክና ትዕግስትን የምናዳብርባቸው ሁኔታዎች እንጂ ትዕግስት ልክ እንደተሰጥዎ ከላይ አይቸረንም። ለዛሬ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ ሀሳብ እንደሚከተለው ነው። አንዳንዴ እራሳችንን ባላሰብነው ሁኔታ ውስጥ እናገኘውና ከራሳችን የማንጠብቀው ባህሪ ሲንጸባረቅብን እንደነግጣለን። ለወትሮ እኮ እንዲህ አልነበርኩም በማለት ግራ ይገባናል። ተሳድበን የማናውቅ ሰዎች በሆነ አጋጣሚ ሌላውን ሰው ስናጥረገርገው፤ ትዕግስተኛ ነን ብለን የምናስብ ሰዎች ቀጠሮዋችን እረፈደ ብለን የታክሲውን ሹፌር ስናመናጨቀው፤ ቂመኛ አይደለሁም ስንል የከረምን ሰዎች የወደድነው ሲከዳን ለበቀል ስናደባ፤ በደላችንን ይቅር በለን እያልን ጠዋት ማታ እየጸለይን የበደሉንን ሰዎች ይቅር ማለት ሲከብደን፤የሌሎች ሰዎች ማግኘት ያስደስተናል የምንል ሰዎች እኛ የተመኘነውን ሌላው ሰው ላይ ስናየውና ሲከፋን፤ ፈራጅ አይደለንም ስንል ከርመን የእኛ ህልውና ሲነካ የፍርድ ወንበር ላይ ቁጢጥ ስንል፤ ባህሪያችን ለገዛ እራሳችን እጅግ ግራ ያጋባል። ማንነታችን የሚገለጸው እኛ ስለራሳችን ባለን አመለካከት ወይም ሌሎች ሰዎች ስለኛ ባላቸው አመለካከት ሳይሆን፤ እኛ ለሁኔታዎች በምንሰጠው ምላሽ ነው። ሰው እንቃለው የሚል ሰው ባያጋጥምም ፤ ሰው እጠላለሁ የሚል ሰው ስምተን ባናውቅም ሰው የሚንንቅና የምንጠላ ሰዎች ግን አንጠፋም። ከእኔ ከእራሴ ጭምር በውስጣችን መጥፎ ስሜት ያድራል ብለን ማሰቡ ይከብደናል፤ ይከብደናል ብቻም ሳይሆን ለማሰብም አንፈልግም። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። “እኔ” ብለን የምንጠራው ማንነት በአብዛኛው የተገነባው ባልተፈተሹ ባህሪያቶቻችን ነው። ስለራሳችን ስናወራ በአብዛኛው የምናወራው በሀሳብ ስለገነባነው ማንነት እንጂ፤ በተግባር ስለምነተገብረው ባህሪዎቻችን አይደለም። እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ በድፍረት መናገሩ ከባድ የሚሆነውም ለዚህ ነው፤ ሁላችንም ያልተፈተኑ ባህሪያቶችን አጭቀን ስለምንቀሳቀስ። አብዛኛው ባህሪያቶቻችንና አስተሳሰቦቻችን በቲዎሪ ደረጃ እንጂ በሙከራ የተረጋገጡ አይደሉም። መልካምነታችን፤ ትዕግስተኛነታችን፤ ፍትሃዊነታችን፤ ሰው አክባሪነታችን፤ እውነተኛነታችን ተገቢውን ፈተና አላለፉም። ፈተና ስል እውነተኛ ባህሪዎቻችንን እንድናጸባርቅ የሚያስገድዱን ሁኔታዎችን ነው። ጊዜ ስለተረፈን ከኋላችን ያለውን ተሰላፊ ከፊታችን ስላስቀደምነው ትዕግስተኛ ልንባል እንችላለን? በፍጹም!!! የማንኛችንም መልካምነትና ጥንካሬ በመልካም አጋጣሚዎች ሊረጋገጥልን አይችልም። በፈተናዎችና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የምናሳያቸው ባህሪያቶች ይበልጥ እኛን ይገልጹናል። ለዚህ ነው አንዳንዴ ውሳኔዎቻችንና ድርጊቶቻችን የሚያስደነግጡን። ተፈትነን ያገኘናቸው ባህሪዋቻችን ስላልሆኑ ልንጠቀምባቸው በሚገባን ቦታ ይጠፉብናል። ይህንን ማወቁ ምን ይጠቅምናል? ለሁለት ነገር ይጠቅመናል ብዬ አስባለው። አንደኛው ከውሸተኛ ማንነት ቀስ እያለ ያላቅቀናል፤ ሙሉ በሙሉ መላቀቅ ለሰው ልጅ ቢከብድም። የሚሰማንን ስሜት በካድን ቁጥርና “እኔ እኮ እንዲህ አይደለሁም” በማለት እራሳችንን በተከላከልን ቁጥር ባህሪያችንን ማሻሻል አስቸጋሪ ይሆንብናል። ከእራሳችን ጋር እየተቆራረጥን በቅዠት አለም ውስጥ መኖሩን እንለምደዋለን።በሌላ በኩል ማንነትና ባህሪያችንን ለሁኔታዎች ከምንሰጠው ምላሽ ተነስተን መዳኘት ከቻልን፤ ከእውነተኛ ምንነታችን ጋር እንቀራረባለን። የትኛው ባህሪያችን ላይ ይበልጥ ማሻሻል እንዳለብን ግልጽ ይሆንልናል። ስለራሳችን ባህሪ እርግጠኛ ሆኖ መናገሩ የሚያስከፍለው ዋጋ አለ፤ እሱም ወደ እውነት የሚወስደውን ጎዳና ያጠብብናል።እውንተኛ ማንነታችንን ለማወቅ ከፈለግን ስለራሳችን የምናስበውን ሳይሆን፤ ለሁኔታዎችና ለአጋጣሚዎች የምንሰጠውን ምላሽ ልናስተውል ግድ ይለናል። ሁለተኛው ጥቅም “እኔ ብሆን ኖሮ” በሚለው የፍርድ ዱላ እርስ በራሳችን ከመፈነካከት ያድነናል። “ የሰው ባህሪያት በሁኔታዎችና በአጋጣሚዎች አይፈጠርም፤ በሁኔታዎችና በአጋጣሚዎች ይጋለጣል እንጂ”- ዚግ ዚግለር https://t.me/joinchat/AAAAAFho5o8z4IyIQCR0pw
Show all...
የበታችነት ስሜትን የማሸነፊያ መንገዶች(ክፍል ሁለት) ------------------------------------------------- @EthioBini ማንም ከበታችነት ስሜት ጋር የተወለደ ወይም የሚወለድ ሰው የለም፡፡ የበታችነት ስሜት ተፈጥሮአዊ ሳይሆን በአካባቢ ተጽእኖ የሚመጣ ውጤት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሰዎች ስለራሳቸው የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ከአካባቢያቸው ይማራሉ፡፡ የተማሩትን ነገር ደግሞ ትተው፣ አዲስ ነገር መማር ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የበታችነት ስሜት ሊለወጥ የሚችል አስተሳሰብ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በተፈጥሮ እንዲሁም ካደገበት አካባቢ አንጻር ልዩ በመሆኑ የበታችነት ስሜትን የሚያሸንፍበት አንድ ወጥ የሆነ አካሄድ ላይኖር ይችላል፡፡ ሆኖም በዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱ ምክሮችን ተግባራዊ ቢያደርጉ ስለራሳቸው ጤናማ/ትክክለኛ የሆነ እይታ ሊያሳድጉ ይችላሉ፡፡ 1. በሌሎች ሰዎች አስተያየት ላይ ጥገኛ አለመሆን በልጅነት ወቅት አንድ ነገር ሰርተን፣ ወላጆቻችን ወይም ትልልቆች ብለን የምናስባቸው ሰዎች ጥሩ ነው፣ ትክክል ነው፣ ጎበዝ .… እንዲሉን እንፈልጋለን፡፡ በጎልማሳነት ጊዜ እንዲህ ያለውን የልጅነት ወቅት ባህርይን መተው አስፈላጊ ነው፡፡ ከሰዎች ተገቢውን አስተያየት መጠየቅና ስራችንን መገምገም ጠቃሚ ቢሆንም፣ በእነርሱ አስተያየት ላይ ጥገኛ መሆን ዞሮ ዞሮ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ይጎዳል፡፡ 2. ራሳችንን ከአሉታዊ አስተሳሰቦች መለየት በመሠረቱ በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ አስተሳሰቦች የእኛን ዋጋ አይገልጹም፡፡ እኛ ዋጋ ያለን ሰዎች መሆናችን የሚለካው በእኛ ውስጥ ባለው አስተሳሰብ አይደለም፡፡ እኛ ስለራሳችን ያለን እንዲሁም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው አስተሳሰብ ምንም ያህል አሉታዊ ቢሆን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር እኛ መልካም ሰዎች ነን፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ራሳችንን/ ማንነታችንን በአእምሮአችን ውስጥ ከተከማቸው አሉታዊ አስተሳሰብ መለየት አለብን፡፡ በሌላ አነጋገር በእነዚያ አሉታዊ አስተሳሰቦች ራሳችንን መመዘን ስንተው፣ እነዚያ አስተሳሰቦች ኃይል ያጣሉ፡፡ በእርግጥ ከእኛ ጋር ለረጅም ጊዜ የቆዩ ከሆኑ፣ ከእነርሱ ጋር ዝምድና ስለፈጠርን በቀላሉና ቶሎ ላይሄዱ/ላይለዩን ይችላሉ፡፡ ሆኖም ከእነርሱ ጋር ላለመኖር ከወሰንን፣ ቀስ በቀስ ስፍራውን ይለቃሉ፡፡ በእነርሱ ስፍራ ደግሞ ተገቢ የሆኑ ሃሳቦችን እናስገባለን፡፡ እነዚያ ቀስ በቀስ ገብተው ስፍራ እንደያዙ ሁሉ፣ አዲሱና መልካም የሆነው አስተሳሰብም ዕድል ከሰጠነው ቀስ በቀስ ወደ አእምሮአችን ገብቶ ሥፍራውን ይይዛል፡፡ 3. በውድቀታችን ራሳችንን ከመኮነን ከውድቀታችን መማር በዚህ ዓለም ላይ ሰው ሆኖ በሁሉ ነገር ፍጹም የሆነ ማንም የለም፡፡ ሰዎች በመሆናችን ሁላችንም ጠንካራና ደካማ ጎኖች አሉን፡፡ እንኳን በድካማችን በጠንካራ ጎናችንም ተገቢውን ሥራ እየሰራን ልንሳሳት እንችላለን፡፡ ሰው ሆኖ መሳሳት፣ መውደቅ፣ ስኬትን ማጣት … ያለ ነገር ነው፡፡ ስህተት የማይፈጽም ሰው የለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው ስህተታችንን የምናስተናግድበት ሁኔታ ነው፡፡ በስህተታችን ራሳችንን እየወቀስን የምንሄድ ከሆነ፣ ራሳችንን ለመቀበል እንቸገራለን፡፡ ከስህተታችን ተምረን ወደፊት ማሻሻል የሚገባንን ነገር የምናስብ ከሆነ ደግሞ ራሳችንን ተቀብለን ወደፊት እንሄዳለን፡፡ ስለሆነም በህይወታችን በእኛም ሆነ በሌሎች ሰዎች በደረሰቡን ችግሮች፣ ውድቀቶች፣ አለመሳካቶችና መልካም ያልሆኑ ነገሮች ሁሉ ራሳችንን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን ከመኮነን፣ ከክፉ ነገሮች መልካምን ነገር ተምረን ወደፊት መሄድ የተሻለ አማራጭ መንገድ ነው፡፡ ያለፈውን ህይወታችንን በተጨባጭ መገምገም አስፈላጊ እርምጃ ነው፡፡ ከህይወት ጉዞ መማር የሚቻለው ተገቢ ግምገማ ሲኖር ነው፡፡ ነገር ግን በውድቀት ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ አሉታዊ የሆኑ ሃሳቦችን ማመንዠግ/ ማሰላሰል ስለራሳችን ያለንን በጎ አስተሳሰብ ክፉኛ ይጎዳል፡፡ ‹“በቂ ጊዜ ሰጥቼ ባለማጥናቴ ምክንያት ዝቅተኛ ውጤት አገኘሁ›› እና ‹‹እኔ ትምህርት የማይገባኝ ደደብ ተማሪ ነኝ›› ማለት ልዩነት አለው፡፡ የመጀመሪያው የተጨባጭ ግምገማ ውጤት ሲሆን ሁለተኛው ግን ራስን መኮነን ነው፡፡ የመጀመሪያው haሳብ ወደ እርምት ሲያመራ ሁለተኛው ደግሞ ወደ በታችነት ስሜት ያመራል፡፡ 4. ራሳችንን በፉክክር ውስጥ አለማስገባት ለበታችነት ስሜት አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከሌሎች ሰዎች ጋር ራሳችንን ማወዳደርና መፎካከር ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ውድድር ውስጥ ስንገባ፣ እነርሱ ጥሩ እኛ መጥፎዎች፣ እነርሱ አሸናፊዎች እኛ ተሸናፊዎች፣ እነርሱ ብርቱዎች እኛ ደካሞች እንደሆንን እናስባለን፡፡ እያንዳንዱ ሰው ልዩ ሆኖ የተፈጠረ ፍጡር ነው፡፡ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለው እምቅ ችሎታ አንድ ዓይነት ላይሆን ይችላል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ያደገበትና ያለበት ዓውድ ልዩነት አለው፡፡ ስለዚህ ከሌሎች ጋር ሁልጊዜ መፎካከርና ራሳችንን ከሌሎች አንጻር ከመገመት ይልቅ እኛ ዘንድ ያለውን መልካም ነገር በመለየት በተሻለ መንገድ መጠቀም የምንችልበትን መንገድ መቀየስ ይረዳናል፡፡ ከሌሎች ሰዎች ስኬት፣ ብርታት፣ መልካም ነገሮች፣ አሸናፊነት ለራሳችን መልካም ቁምነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ ስለዚህ የፉክክር የህይወት ዘይቤን በመተው ከሌሎች መማርን መልመድ ጠቃሚ ነው፡፡ 5. ስጦታችንን በመለየት ማሳደግ እያንዳንዱ ሰው ስጦታ እንዳለው ሁሉ እኛም ስጦታ አለን፡፡ ስለዚህ በውስጣችን ያለውን እምቅ ችሎታ፣ ፍላጎታችንንና ምቹ ሁኔታዎችን በመለየት ስጦታችንን በዕውቀትና በክህሎት ማሳደግ እንችላለን፡፡ ጎበዝ በሆንበት ወይም መስራትና መሆን በምንፈልገው ጉዳይ ላይ የበለጠ ዕውቀትና ክህሎትን በማጎልበት የበለጠ ፍሬያማ መሆን እንችላለን፡፡ በችሎታችን ራሳችንና ሌሎች ሰዎችን መጥቀም ስንችል ደግሞ እርካታና ደስታን እናገኛለን፡፡ ለሰዎችም አንድ በጎ ነገር ማድረግ መቻላችን ደግሞ ስለራሳችንም በጎ አስተሳሰብ እንዲኖረን ያግዘናል፡፡ 6. ባለሙያን ማማከር አንዳንድ ጊዜ የበታችነት ስሜት ስር የሰደደና የሁለንተናዊ ህይወታችንን ጤናማነት አደጋ ላይ የሚጥል ሆኖ ሲገኝ የሰለጠነ አማካሪን ማማከር አስፈላጊ ነው፡፡ እንግዲህ ራሳችንን የመቀበል ችግር ሲኖረን በአብዛኛው ከበጎ ነገር ይልቅ በህይወታችን ውስጥ ባሉ ድክመቶች፣ ጉድለቶችና ስህተቶች ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ የበታችነት ስሜት መንስኤ የሆኑ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ ተገቢውን መፍትሔ ለመፈለግ እጅግ ያግዛል፡፡ ምክንያቶቹ ከሰው ወደ ሰው የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ራሳችንን የማንቀበል ከሆነ እኛው ለራሳችን ጠላቶች ሆንን ማለት ነው፡፡ ሁልጊዜ ከራሳችን ጋር እንጣላለን፡፡ ጠላትን በውስጣችን ተሸክመን እንዞራለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ራሳችንን በመቀበል በሰላም በመኖር የበታችነት ስሜትን ማስወገድ እንችላለን! https://t.me/joinchat/AAAAAFho5o8z4IyIQCR0pw
Show all...
Repost from #KALTUBE
♦♦ተስፋ መቁረጥን ተስፋ አስቆርጡት♦♦ #በዚች ውጥንቅጧ በጠፋ እና ዝብርቅርቋ በወጣ ዓለም እየኖሩ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አልገጠመኝም ማለት ዘበት ነው። ምክንያቱም ተስፋ በሌላት እና በተስፋ መቁረጥ በተዘፈቀች ዓለም ውስጥ ከተስፋ ሰጪ ነገሮች ይልቅ ለቁጥር አታካች የሆኑ ተስፋን እስከነአካቴው የሚያጠፉ ነገሮች በሽ ስለሆኑ ነው። #አዎን ተስፋ ለመቁረጥ ምንም ርቀት መጓዝ አይጠበቅብንም። ለምን? በዙሪያችን ያሉ ተስፋ የቆረጡ ሰዎች፣ እንዳንጠገን አድርገው የሚሰብሩን ሁኔታዎች፣ ከሀዘንና ጭንቅ ጋር የሚያጋፍጡን ጊዜዎች/ዘመናት ወቅታቸውን ጠብቀው በራችንን አንኳኩተው ብቅ ስለሚሉ ነው። ታዲያ በዙሪያችን የምንመለከተው ሁሉ ተስፋ የማይሰጥና እንድንኖር የማያስመኝ ከሆነ እዚህ ምን እንሰራለን ሲሉ ራሳቸውን ወደ ሞት የሸኙ ጥቂቶች አይደሉም። #አንዳንዴ ስናስበው የጨለመ ነገ ባላት ምድር ላይ መኖር ትርጉም ላይሰጥ ይችላል። ይህ የሚሆነው ግን ተስፋችንን በዚች ምድር ላይ ብቻ ያደረግን እንደሆነ ነው። ዓለም ነገዋን ስታስብ ጥፋት እንደሚጠብቃት ስለምታውቅ እርሷን ተስፋ የሚያደርጉትን ሁሉ ይዛ ወደ ጥፋት ጎዳና ትነጉዳለች። #እኔ ግን ዛሬ ማውራት የምፈልገው ተስፋን አለምላሚ ስለሆነው #የእግዚአብሔር መንግስት ነው። በዚህ መንግስት ውስጥ ተስፋ ማድረግ ግዴታ ነው! ምክንያቱም መሪው የተስፋ አምላክ የሆነው እየሱስ ክርስቶስ ነውና!! ተስፋችሁን በእርሱ ስታደርጉ ዛሬ ምድር ላይ ላላችሁ ጥቂት የድካም ወራት ብቻ ሳይሆን መች እንደሚያልቅ ለማታውቁት ዘልዓለም ለተባለ የጊዜ መልህቅም ጭምር ነው። ብቻ አንዴ በእርሱ ታመኑና ተስፋችሁን በእርሱ ላይ አድርጉ። የትኛውንም ያህል ተስፋ አስቆራጭ ፈተና፣ችግርና መከራ፣መልስ የማይገኝለት እንቆቅልሽ ወደ እናንተ ቢመጣ እንኳ ከተተከላችሁበት ፅኑ የተስፋ ዓለት እንደማትነቃነቁ እና እንደማትፍገመገሙ ስለሚያውቅ ተስፋ ቆርጦ ይመለሳል እንጂ የእናንተን የተስፈኝነት ድንበር መጣስ አይችልም። #ስለዚህ የወደፊት እጣ ፈንታዋ ሞት፣ባዶነት፣ጨለማ፣ጥፋትና ውድቀት ከሆነባት ከዚች ከንቱ ዓለም ላይ የተስፋችሁን ዝናር አንሱና ከዛሬዋ ዕለት አንስቶ እስከ ዘልዓለም በህይወት፣በሙሉነት፣በብርሃን፣በተስፋ፣በደስታና በፍቅር በተሞላው የእግዚአብሔር መንግስት ላይ ተስፋችሁን በማስቀመጥ ተስፋ መቁረጥን ራሱን ተስፋ አስቆርጡት። ""ተስፋን የሰጠው የታመነ በሆነበት የተስፋ መንግስት ውስጥ ተስፋ ማድረግ ግዴታ እንጂ አማራጭ አይደለም!"" ምህረት ግርማ 💐💐💐💐 @KALTUBE @KALTUBE @KALTUBE
Show all...
Repost from #KALTUBE
♦ጉብዝናችን ለጌታችን♦   💐ወጣትነት ለእናንተ ምንድነው? ለማን እና ለምን እየኖራቹበት ነው? የእግዚአብሔር ቃል በመፅሐፈ መክብብ 12፥1-8 ላይ የሰው ልጅ በጉብዝናው ወራት ማንን ማሰብ እንዳለበት  ይናገራል። በተለይ ቁጥር 1ና7 እንዲህ ይላሉ፦ ፨መክብብ 12፥1""የጭንቅ ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤"" ፨መክብብ 12፥7 ""አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::"" 💐በክፍሉ የምንመለከተው ከየትኛውም እድሜ በላይ በወጣትነታችን ጊዜ ልናስበው እና ልንኖርለት የሚገባው እግዚአብሔር መሆኑን ነው። ብዙ ሰዎች የጉብዝናቸውን ጊዜ ፈጣሪያቸውን በማሰብ መኖር እንዲገባቸው አያውቁም። ስለዚህ በዚህ ከንቱ ዓለም ውስጥ ዛሬ ታይተው ነገ ለሚጠፉ ብልጭልጭ መልኮች ፣ረብ አልባ ለሆኑ መንከራተቶች እና የስጋቸውን ለከት የለሽ ፍላጎት ለማሟላት ሲጠቀሙበት ይታያል። እግዚአብሔርን  ሊያውቁበት፣ ሊያገለግሉበትና ለእርሱ ሊኖሩለት በሚገባቸው ለጋ እድሜ የስጋቸውን ክፉ ረሃብ ሲያስታግሱ እና የራሳቸውን ፍቃድ ሲያደርጉ ይሄ ብርቱ የጉብዝና እና ለመትጋት ምቹ የሆነው እድሜያቸው ይባክናል! 💐ይህ የሚገባቸው ደግሞ ነገር ሁሉ አልጥም በሚልበት፣ከለላ፣መሸሸጊያ፣ምርኩዝና ተገን በሚሹበት የእድሜያቸው አመሻሽ ላይ ነው። የመኖር ተስፋቸው ሲጨልም፣ወደ ሞት ደጃፍ እየተጠጉ መሆኑ ሲገባቸው ያኔ ህይወታቸውን በሚያስተማምን ዓለት ላይ ለማስቀመጥ ይሻሉ። በጉብዝናቸው፣በብርታታቸው በዚያ በመትጊያቸው ወራት ያልፈለጉትን እግዚአብሔር በእርጅና እና በድካም ዘመናቸው ይፈልጉታል። በዓለም ያባከኑትን የጉብዝና ወራት ያካካሱ ይመስል በስተእርጅና ዓለም በቃኝ ይላሉ። 💐ይህ ግን ትልቅ የህይወት ብክነት የታከለበት ስህተት ነው። የሰው ልጅ የክርስቶስን አዳኝነት እያወቀ በጉብዝና እድሜው ፈያጅ ባልሆነው ከንቱ የዓለም አዘቅት ውስጥ እየዋኘ ከርሞ ሲያረጅ፣ ሲደክም፣ደስ የማያሰኙ ዓመታት መጥተው አቅም ሲያንሰው አሁን የሰማይ ቤቴን ላስተካክል ማለቱ ስለ እግዚአብሔር ያለው መረዳት ጠባብ እንደሆነ ያመላክታል። የእግዚአብሔር መንግስት የሚጠይቀውን የአኗኗር ጥራትና ልክ እያወቁ ኃላ ደርስበታለው አሁን ትንሽ ዘና(ፈታ) ልበል ካሉ ወዲያ ዓይን ሲደካክም፣ ጉልበት ሲከዳ፣ የጭንቅ ቀናት ብቅ ሲሉ፣ የተማመኑት የለጋነት መልክ ሲጠወልግ... ጊዜው ነውና እግዜርን ላገልግል ማለት ራስን ማታለል ነው! 💐በነገራችን ላይ ይህ የወጣትነት እድሜ በሁለቱ መንግስታት ማለትም በእግዚአብሔርና በዓለም ዘንድ በብዙ ተፈላጊ ነው! ምክንያቱም ወጣትነት የብርታት፣የአቅም፣በትጋት የመስራት እና የአስተሳሰብ ፍጥነት ያለበት እድሜ ስለሆነ እንዲሁም ደግሞ ለተሰየምንለት አላማ ያለፍርሃት በፅናት የምንኖርበት ጊዜ በመሆኑ ተፈላጊነቱ እጅግ ይልቃል! 💐ታዲያ እስካሁን ይህንን የጉብዝና እድሜ ለማን እንደሰጣችሁት ባላውቅም ትክክለኛው እና አማራጭ የሌለው ጉብዝናችንን ሊጠቀምበት የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ግን ልነግራቹ ወዳለው!!! በእርሱ ዘንድ ዓለምን የሚያስንቅ ድንቅ ውበት አለ! ከስጋዊነት የሚያስኮበልል አምላካዊና አባታዊ ፍቅር አለ! ስለዚህ የፈጠረን እግዚአብሔር ከእድሜም በላይ ራሳችንን እንድንሰጠው ይፈልጋል። ልክ እንደ ሸክላ ሰሪው ሽክላውን ሰባብሮ ዳግም ለውበት እንዲሆን አድርጎ እንዳደሰው እንደዚያ ህይወታችንን ሊያድስ ዛሬም የልባችንን በራፍ እያንኳኳ በደጅ ቆሟል። ከፍተን ብናስገባው ለዘላለም የህይወት ዕረፍትን ሊሰጠን፣ ከሚያረጀው ከዚህ ጊዜያዊ ስጋችን አውጥቶ የማይሞት የማይበሰብስ አዲስ ሰውነት ሊያለብሰን፣ የሚደክመውን ፍጥረታዊ ማንነት ከእኛ አስወግዶ በማይነቃነቅ ፅኑ መሠረት ላይ ሊያንፀን እርሱ ሁሉ የሚቻለው ኤልሻዳይ ነው!!  💐ጉብዝናችንን በሰጠነው በዚያ ቅጽበት  በህይወታችን የማያልቅ ሰላም፣እረፍት፣ደስታን እናገኛለን። የመንፈስ ፍሬዎች በህይወታችን ይገለጣሉ፣ ከራሳችን አልፈን ለሌሎች ከሞት የማምለጥ ምክንያት እንሆናለን፣ እድሜ የሰጠን የሁሉ ፈጣሪ ኢየሱስ ሲመጣ በፊቱ ለመቅረብ የማናፍር ባሪያዎቹ እንሆናለን። ስለዚህ ገና በእድሜያችን ጠዋት ላይ ያለን ብርቱ ወጣቶች ጉብዝናችንን የፈጠረንን ጌታ እግዚአብሔርን በማወቅ፣ በማመንና በማገልገል እንቋጭ እላለሁ!                 ጌታ ይርዳን!!!                                            ምህረት ግርማ        💐share💐share💐share💐                    @KALTUBE                    @KALTUBE                    @KALTUBE
Show all...
Repost from #KALTUBE
ምክር ቢጤ        #እንደ አንበሳ# ተመላለሱ Proverbs 28 (አማ) - ምሳሌ 1: ኀጥእ ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ያለ ፍርሃት ይኖራል። በጫካ ውስጥ;- 1.  ግዙፉ ዝሆን ነው; 2.  ረጅሙ ቀጭኔ ነው; 3.  ጥበበኛው ቀበሮ ነው; 4. በጣም ፈጣኑ አቦሸማኔ ነው። ሆኖም፣ አንበሳ ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ ምንም አይነት ባህሪና ማንነት ባይኖረውም የጫካው ንጉስ ነው። ለምን?❓ ምክንያቱም፡- 1. አንበሳ ደፋር ነው፣ በልበ ሙሉነት ይሄዳል, ማንኛውንም ነገር ይደፍራል እና ፈጽሞ አይፈራም። 2. አንበሳው ሊቆም እንደማይችል ያምናል. 3. አንበሳ ኃላፊነት የሚወስድ ነው። 4. አንበሳ ማንኛውም እንስሳ ለእሱ ምግብ መሆኑን እንጂ አሳሳቢ እንደሆነ አይቆጥርም 5. አንበሳ በቀላሉ ተስፋ አይቆርጥም። 👉ስለዚህ... በህይወት ውስጥ 1. በጣም ፈጣን መሆን ላያስፈልግህ ይችላል። ሩጫ ለፈጣኖች ስላይደለ። (መክ 9:11) 2. በጣም ጠቢብ  መሆንም ላያስፈልግህ ይችላል። እንጀራ ለጠቢባን ስላይደለ (መክ 9:11) 3. በጣም ብሩህ(አዋቂ) መሆንም ላያስፈልግህ ይችላል። ሞገስ ለአዋቂዎች ስላይደለ) (መክ 9:11) ✨አንዳንዴ የሚያስፈልግህ *ድፍረት* ብቻ ነው። ቅዱስ ድፍረት ማለቴ ነው። የሚያስፈልግህ *እንደገና ለመሞከር ፍላጎትህ* ብቻ ነው። የሚያስፈልግህ * እምነት * *የይቻላል መንፈስ ነው። የሚያስፈልግህ በጌታ ላይ መተማመን ብቻ ነው። 👉አንበሳ 20 ሰአታት ይተኛል እና ለ 4 ሰዓታት ይሠራል ከዛ ስጋ ይበላል። 👉 ዝሆን ግን ለ24 ሰአት ይሰራል እና ሳር ይበላል።     ✨ሁል ጊዜ ሻምፒዮን ወይም አሸናፊ ለመሆን ከሁኔታዎች ጋር ባለዎት አቀራረብ የህይወትዎ ስልት በጣም አስፈላጊ ነው።    በአንበሳነት ስሜት ውስጥ ይቆዩ! ይህ ስሜት  ያ የአሸናፊዎች ስሜት ነው። ባለመፍራትዎ የሚሸነፉ ብዙ የህይወት ተግዳሮቶች አሉ። Proverbs 28 (አማ) - ምሳሌ 1: ኀጥእ ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ያለ ፍርሃት ይኖራል። ✍ነቢይ መሳይ አለማየሁ 💐ለወዳጆቻችሁ ሼር 👇👇👇👇 @KALTUBE @KALTUBE @KALTUBE
Show all...
WIFI setagegnu or be datam behone awerdachehute semute plise hiwote keyare temrt new
Show all...
ብዙ ስለደከምን አይደለም ህይወት የሚከናወነው፡፡ ስኬት እና መከናወን የሚገኘው ከሰማይ አምላክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገርም የሰማዩ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባርያዎቹ ተነስተን እንሰራለን፡፡ መከናወን የሚገኘው ከሰማይ አምላክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡" እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።" (መዝሙረ ዳዊት 127:1)
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!