cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Yiweku Zemen

መምጫዉ ቀርቧልና ወገኔ ሆይ ተዘጋጅ !!!!!!!!!!!!! ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል ወደ እርሱ ይወስደናል መከራን ከኛ ያርቃል ለዘላለም ያሳርፈናል በዚህ Channel ስለ ኢየሱስ ዳግም ምፅአትና ስለርሱ ሀያልነት ብቻ ይመሰከራል!!! ╬╬ ╬╬ ╬╬ ╬╬ ╬╬ ለአስተያየትዎ @Yiweku በDesta Denboba

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
168Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
. እበረታለሁ ዘማሪ ሳሙኤል ንጉሴ NEW AMAZING GOSPEL SONG ሼር በማድረግ ወዳጆ ያካፍሉ sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯 〽️ለበለጠ ቤተሰብ ይሁኑ〽️ ❇️ @marsilchannel ❇️ ❇️ @marsilchannel ❇️ ⚠️ይቀላቀሉን⚠️ 📲ሼር ማድረግዎን እዳይረሱ📲
Show all...
ዝማሬ🎙“ኢየሱስ ጓደኛዬ” ዘማሪ👥 🅷🅴🅻🅸🅽🅰  ርዝመት⏩ 3:45 ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻️ 🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻 ✅ @indiwbetsegaw ✅ ✅ @indiwbetsegaw
Show all...
ወሩን ሙሉ የተባረኩበት መዝሙር #በፈተና ብዛት ያጎበዝከው ልቤ🔥 #ዘማሪ አሰግድ @SisayAzusaRevivall @SisayAzusaRevivall
Show all...
❖ክፍል=ሁለት❖ ክፍል ሁለት፦ የክርስቶስ ዳግም መመለስ ሁለት ገጽታዎች፦ ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ በሁለት አይነት መልክ ነው የሚመጣው፣ የመጀመሪያ በስውር ሲሆን ሁለተኛ በግልጥ ነው። 🏁1.ስውር አመጣጡ ወይም ለቤተክርስቲያን መምጣት ጌታችን ኢየሱስ በስውርና ባልታሰበበት ሰዓት በመላእክት አለቃ ድምፅና፣ በእግዚአብሔር የመለከት ድምፅ ከሰማይ ሲገለጥ፣ በጌታ ሆነው የሞቱት ቅዱሳን ከሞት በአዲስ አካል ተነስተው፣ በምድር የሚኖሩ በሕይወት ያሉ ቅዱሳን የለበሱት አካላቸው ተለውጦ፣ በምድር የሚኖሩ በሕይወት ያሉ ቅዱሳን የለበሱት አካላቸው ተለውጦ ጌታን በአየር እና በደመና ለመቀበል በመነጠቅ የሚወሰዱበት መምጣቱ ስውር አመጣጥ ይባላል (1ተሰ.4፥16-17፣ 1ቆሮ.15፥51-54)። ምንም እንኳ ክስተቱ ስውር እና የማይታይ ቢሆንም የአማኞች መወሰድ በማያምኑት ዘንድ መገረም እና ድንጋጤ ይፈጥራል (ማቴ.24፥40-41)። ጌታ ኢየሱስ በስውር የሚመጣበት ዓላማም፦ በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያንን (አማኞችን) በንጥቀት ለመውሰድና ወደ ራሱ ለመሰብሰብ ነው(ዮሐ.14፥3፣ 1ተሰ.4:15-18)። ቤተክርስቲያንን ከታላቁ መከራ ለመጠበቅ እና ለማዳን ነው። 🏁2.ግልጽ አመጣጡ ወይም ከቤተክርስቲያን ጋር መምጣት (1ተሰ.3:12፣ ይሁዳ 14-15) ጌታ ኢየሱስ በግልጽ ሲመጣ በንጥቀት ከወሰዳቸው ቅዱሳንና ከመላእክት ጋር በታላቅ ክብር ወደ ምድር የሚወርድበት አመጣጥ ግልጽ የሚመጣበት ዓላማም፦ ❖.የአርማጌዶንን ጦርነት በድል ለመፈጸም፤ አርማጌዶን፤ ከቃሉ እንደምንረዳው አርማጌዶን ማለት የመጊዶ ተራራ ማለት ነው። መጊዶ፤የጦር ሠራዊት ሰፈር ማለት ነው። በቀርሜሎስ ተራራዎች ከሰሜን ወደ ደቡብ ጋዛንና ደማስቆን የሚያገናኘው መንገድ ለመጠበቅ የተመሸገ ከተማ ነበር። መጊዶና ታዕናክ ከሳሮን ሜዳ እስከ ኢይዝራኤል ሸለቆ ባለው በተራራማው አገር አቋርጦ ወደ ሰሜን ምስራቅ የሚዘልቀውን ዋና መተላለፊያ የሚቈጣጠሩ ቦታዎች ናቸው። <<የመጊዶ ሜዳ>> ቊልፍ ቦታ ከመሆኑ የተነሣ (2ዜና 35፥22) ከጥንት ጀምሮ በተደጋጋሚ ጦርነት የተካሄደበት ስፍራ ነው። ሣልሳዊ ቱትምስ የተባለው ፈርዖን፣ የተባበረውን የከነዓንን ሰራዊት በ1468 B.C በዚሁ ቦታ ጦርነት ገጥሞ ድል አድርጎታል። እንዲሁም በ1917 ዓ.ም ታላቋ ብሪታንያ በጀነራል አለንቢ መሪነት በመጊዶ ትይዩ ባለው በኢይዝራኤል ሸለቆ ከቱርክ አገዛዝ እንዲያከትም አድርጋለች። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ እንደሚገኘው፣ የእስራኤል ሰራዊት በዲቦራና በባርቅ መሪነት የከነዓናውያንን ቅስም የሰበሩት፣ በመጊዶ አጠገብ ዲቦራ ሲሣራን ድል አደረገች (መሳ.5፥19)፤ እንዲሁም መልካሙ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮስያስ በ609 B.C ከዳግማዊ ፈርዖን ኒካዑ ጋር ጦርነት ገጥሞ በዚሁ ስፍራ ሞቶአል (2ነገ.23፥29:30)። አርማጌዶን ማለት "የመጊዶን ተራራ ወይም የመጊዶን አምባ" ማለት ሲሆን፣ ይህም ሁሉን ማድረግ በሚችል በእግዚአብሔር ታላቅ ቀን የሚሆነው ጦርነት የሚካሄድበት ሥፍራ ነው (ራዕ.16፥14)። ታላቋ የዓለም መጨረሻ ጦርነት በአርማጌዶን ይደረጋል(ራዕ.16፥16)፤ ቃሉ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ክፉን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚያስወግድ ነው። ❖.ሐሰተኛውን ክርስቶስ ለመሻር (2ተሰ.2፥8)፤ ❖.ዓመፀኞችን ለመቀበልና ለመቅጣት (ማቴ.24፥31፣ 25፥22-26፤ 2ተሰ.1፥8፤ ይሁዳ 15)፤ ❖.እሥራኤልን ከጥፋት ለማዳን (ማቴ.24፥21-22፣ ኤር.30፥7)፤ ❖.ሺህ ዓመት በምድር ላይ ለመንገስ (ራዕ.11፥15፣ 20፥4-6) የመረጃ ምንጭ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት የተወሰደ ________ይቀጥላል__________ http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD
Show all...
❖ክፍል አንድ❖ ክፍል አንድ፦የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ጌታ ኢየሱስ መጀመሪያ በሥጋ ተገልጦ እንደመጣ አሁንም ሁለተኛ ተመልሶ ቅዱሳንን ለመውሰድ እና ከእርሱ ጋር ለመኖር ከሰማይ ይገለጣል(ዮሐ.14፥1-3)። ይህ ሁለተኛ የመምጣቱ የተባረከ ተስፋ እርግጠኛ እና እውን መሆኑ የሚታወቀው ስለመጀመሪያ መምጣቱ የተናገሩት ትንቢቶች በመፈፀማቸው፣ ማለትም መወለዱ፣ መሞቱ፣ መነሣቱ እና ዕርገቱን ሁሉ ያጠቃለለው ትንቢት ተፈፅሟል። መጀመሪያ ሊመጣ ለኀጢአት የሚሰዋ በግ ሆኖ መጣ (ዮሐ.1፥29)። ተመልሶ ሲመጣ የነገሥታት ንጉሥ እና የጌቶች ጌታ ሆኖ ይመጣል (ራዕ.19፥16)። ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ የመምጣቱ እና የዓለም ፍፃሜ መቼ እንደሆነ ሲጠየቅ በዝርዝር ተናግሯል (ማቴ.24፥3-51)። ❖ ኢየሱስ በመንፈስ ሳይሆን በአካል በግልጥ ይመለሳል (ማቴ.24፥30) ❖ በድንገት ባልታሰበበት ሰአት ይመጣል(ማቴ.24፥38-42)። ❖ ሰዎች ዋናው ጉዳይ ቸል ብለው ሃሳባቸውን በምድራዊ ነገር ሲጥሉና፣ ለነገ መኖር ዋስትና ያገኙ ሲመስላቸው ሠላም እና ደህንነት ነው እያሉ ሲዘናጉ በድንገት ይመጣል (1ተሰ.5፥2-3)። ዳግም ምጽአት ዳግም ምጽአት ማለት ክርስቶስ ሁለተኛ ጊዜ መምጣት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገና እንደሚመጣ ተነግሯል፤ ማቴ.24፥30፤ 26፥64፤ ዮሐ.14፥3። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዐረገ በኋላ ሁለት መላእክቶች እንደሚመጣ ተናግሯል(ሐ.ሥ.1፥11) ፣ ሐዋርያትም ይህን አስተማሩ፤ ፊል.3፥20፤ 1ተሰ.4፥15:16፤ 2ተሰ.1፥6-10፤ ቲቶ 2፥12:13፤ ዕብ.9፥28። መምጣቱ ተስፋ ለቤተክርስቲያን ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የሚከተሉት ነገሮች ይፈጸማሉ። ❖1.ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል፤ ማቴ.24፥14፤ ቆላ.1፥6:23። ❖2.ወደ መጨረሻው ከእስራኤል ወገን ብዙዎች በክርስቶስ ያምናሉ፤ ሮሜ 11፥25-29፤ 2ቆሮ.3፥15:16። ❖3. መጨረሻ ላይ ትልቅ ክሕደት (ማቴ.24፥12፤ 2ተሰ.2፥3፤ 2ጢሞ.3፥1-7፤ 4፥3:4)፣ ከኢየሩሳሌም ውድቀት በፊት እንደ ነበረውም ታላቅ መከራ ይሆናል፤ማቴ.24፥15-22። ❖4.የዐመፅ ሰው የሚባለው የክርስቶስ ተቃዋሚ ይነሣል፤ 2ተሰ.2፥3:4፤ ራእ.20፥7-9። ❖5. በሰማይ እና በምድር አስፈሪ ምልክት እና ለውጥ ይታያል፤ ማቴ.24፥29:30። ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢየሱስ ይመጣል። ሰዎች ሳያስቡ ይመጣል። ምእመናን ቀኑን እና ሰዓቱን ባያውቅም ምልክቶች እያዩ በተስፋ ይጠባበቁታል፤ ማቴ.24፥32-44፤ 1ተሰ.5፥3:4። ኢየሱስ የሚመጣው በሥጋ (ሐ.ሥ.1፥11፤ ቲቶ 2፥13፡14፤ ራእ.1፥7)፣ በደመና ላይ (ማቴ.24፥30)፣ በመላእክት አለቃ ድምፅ፣ በእግዚአብሔር መለከት (1ተሰ.4፥16)፣ ከመላእክት ጋር (ማቴ.24፥31፤ 2ተሰ.1፥6:7) ነው። በክርስቶስ የሞቱ ይነሣሉ፤ በምድር ያሉ ሕያዋን ምእመናን ተለውጠው ይነጠቃሉ፤ ሌሎችም ይነሣሉ፤ ማቴ.24፥40:41፤ ዮሐ.5፥28፡29፤ 1ቆሮ.15፥51:52፤ 1ተሰ.4፥13-18። ኢየሱስ ከመጣ በኋላ ጻድቃንና ኃጥኣንን ይለያል፤ ማቴ.25፥31-46። ለምእመናን እንደ ሥራቸው ዋጋ ይሰጣል (ማቴ.25፥20-23፤ ሉቃ.19፥16-19፤ 2ቆሮ.5፥10)። በሰይጣን እና ባላመኑት ላይ ይፈርዳል፤ 2ተሰ.1፥6-10፤ ራእ.20፥10-15። ለኢየሱስ መምጣት እና ለፍርዱ ተዘጋጅተን መኖር ይገባናል፤ ሉቃ.21፥34-36። ስለዚህ ነቅተን በመጠበቅ (ማቴ.24፥42)፤ ተዘጋጅተን መኖር (ማቴ.24፥44)፤ ተግተን በመጠበቅ (ማር.13፥11-14)፤ ራሳችንን በመግዛት (1ተሰ.5፥4-8) እንኑር። ጌታ ሲመጣ በታላቅ ክብር ይመጣል (ማቴ.24፥30-35)። በኃይል እና በታላቅ ክብር (ማቴ.24፥30)። በእሳት ነበልባል (2ተሰ.1፥6-7) በቅዱሳን መላእክት ታጅቦ (ማቴ.25፥31፤ 2ተሰ.1፥7)። ከቅዱሳን አማኞች ጋር ይመጣል(1ተሰ.3፥12፤ ይሁዳ.1፥14-15)። ___________ይቀጥላል__________________ http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD
Show all...
🇪🇹🔥🔥🔥🔥🇪🇹 🎤🎼🎹🥁🎷🎺🎸🎻🎻🎸🎺🎷🎸🎹🎼🎤 🎤🎼🎹🥁🎷🎺🎸🎻🎻🎸🎺🎷🎸🎹🎼🎤 🎹🎸@EnglishGospelSongs 🎹🎸 🎹🎸@EnglishGospelSongs 🎹🎸
Show all...
መሰማት ያለበት መልዕክት: ለሁሉም ክርስቲያን ይድረስ!!
Show all...
Baleaderawoch nen @Yiwekuzemen
Show all...
#ወዳጄ በሁለት አሳና በአምስት እንጀራ አምስት ሺህ ህዝብ ባጠገበ ጌታ ትምናለህ?        ካመንክማ የወር ደመወዜ ትንሽ ነው፣ ኑሮዬ የቁጥ ቁጥ ነው የችርቻሮ ነው እያልክ አትዘን። የምታምነውን አምላክ እግዚአብሔርን ጠይቀው የሚያስፈልግህን የምታገኝበት በር ይከፍትልሃል፤ አንተም ጠንክረህ ስራ።         ሰውን ሰው ያረገው ስራ ነው የሚሉትን እየሰማህ ስራ ስለሌለህ ከሰው ያነስክ አይምሰልህ፤ በርህን በራስህ ላይ ዘግተህ አንገትህን ጉልበትህ መሀል ቀብረህ አታልቅስ። ሰውን ሰው ያደረገው ስራ ሳይሆን ክርስቶስ ነው፣ ምህረቱ ነው። "የምትኖረው ስለሮጥክ አይደለም። እንጀራ የምትቆርሰው አለቃህ ደስ ስላለው አይደለም። እየጠሉህ እየተፈራረሙብህ እያደሙብህም እግዚአብሔር ያኖርሃል።"        የእንጀራህ ጌታ እርሱ ነውና የአንተ ዕጣ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነው። እንኳን አለቃህ መስሪያ ቤቱ ፈርሶ አንተ ግን ትኖራለህ። የምትኖረው መስሪያ ቤትህ እስካተረፈ አይደለም እግዚአብሔር በጀቱን እስከሰፈረልህ ድረስ ነውና። እስከዛሬም ድረስ ሰርተህ ከኖርከው በስጦታ የኖርከው ይበልጣል። የእንጀራ ዋስትና እግዚአብሔር ነው። በተሰጠህ እግዚአብሔርን አመስግነው።       ሰው ስላንተ የሚያስበው ክፋትን ይሆናል ማግኘትህን ሳይሆን መቸገርህን ይመኝልህ ይሆናል፤ ሰው የሚክብልህ ከፍ የምትልበትን ሳይሆን የምትቀበርበትን ይምስልህ ይሆናል። የአንተ አምላክና አባት ግን የሚያስብልህ ሀሳብ መልካም ነው።        " ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። " ትንቢተ ኤርምያስ 29 : 11               ሰላማዊ ቀን ይሁንላችሁ!                       ✍በአዶኒ ይቀላቀሉን 👇 @adonigospel
Show all...
👉 #ቅባት #የምትፈልጉ #ከሆነ ስለ #ክርስቶስ #ለመካድ፤ #ለመሰደብ፤ #ለመገፋት፤ #ለመወገር፤ #ለመነቀፍ እራሳቹን #አዘጋጁ🔥🔥🔥 👉 ስለ #ክርስቶስ ስም #ብትነቀፉ #የክብር #መንፈስ #የእግዚአብሔር #መንፈስ #በእናንተ ላይ #ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:14) 👉 #ከባድ #ክብር በምድራችን #በኢትዮጵያ #ለገለጥ ስለሆነ #ተዘጋጁ #ሃያላን🔥🔥🔥🔥 @Binarevivalist @Binarevivalist @Binarevivalist
Show all...
👇👇 የቃል ጊዜ 👇👇 📚📚ፓ/ር ግዛቸው ታደሰ ከ 🅰.🅰 📚🪔 ርዕስ🪔📚 ⏳⌛️የአለም መድኃኒት ተወልዶአልና ሌላ መድኃኒት አንፈልግ። @chirstEnatsebarki ⏳✝⌛️✝⏳✝⌛️✝⏳
Show all...
Faarsote Umi : Maala'linanni Baxilli Faarsaancho : Maarihun Mokonnini Join us @Gatote_Suusa ☝☝☝☝
Show all...
. አለፍኩብህ ዘማሪያን ፓ/ር ዳዊት,ተከስተ,እንዳለ New Amazing Gospel Song 🎄ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ🎄 sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯 ✅ @adadisemezemur ✅ ✅ @adadisemezemur ✅ 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺 📲ሼር ማድረግዎን እዳይረሱ📲 👇Subscribe For More👇 https://youtu.be/9AZqw7YPerc 🎄🎄🎄🎄🎁🎁🎁🎁🎄🎄🎄🎄
Show all...
(የሉቃስ ወንጌል 12 ) ------------ 1፤ በዚያን ጊዜ የሕዝብ አእላፍ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ተሰብስበው ሳሉ፥ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው። 2፤ ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። 3፤ ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፥ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። 4፤ ለእናንተም ለወዳጆቼ እላችኋለሁ፥ ሥጋን የሚገድሉትን በኋላም አንድ ስንኳ የሚበልጥ ሊያደርጉ የማይችሉትን አትፍሩ። 5፤ እኔ ግን የምትፈሩትን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎን እላችኋለሁ፥ እርሱን ፍሩ።
Show all...
(መዝሙረ ዳዊት 66 ) ------------ 1፤ በምድር ያላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥ 2፤ ለስሙም ዘምሩ፥ ለምስጋናውም ክብርን ስጡ። 3፤ እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ ሥራህ ግሩም ነው፤ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ። 4፤ በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥ ለአንተም ይዘምራሉ፥ ለስምህም ይዘምራሉ። 5፤ ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ፤ ከሰው ልጆች ይልቅ በምክር ግሩም ነው። 6፤ ባሕርን የብስ አደረጋት፥ ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፤ በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል። 7፤ በኃይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ ዓይኖቹ ወደ አሕዛብ ይመለከታሉ፤ ዓመፀኞች ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያድርጉ። 8፤ አሕዛብ ሆይ፥ አምላካችንን ባርኩ፥ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ። 9፤ ነፍሴን በሕይወት ያኖራታል፥ እግሮቼንም ለመናወጥ አልሰጠም።
Show all...
(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3 ) ------------ 1፤ ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። 2፤ ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ 3፤ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ 4፤ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ 5፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። 6-7፤ ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና። 8፤ ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው፥ እውነትን ይቃወማሉ።
Show all...
"፤ እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፤ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።" (ኦሪት ዘፍጥረት 19: 29)
Show all...
Wirro Xallinoonni ! ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ "Yesuusa" Yaanno Su'ma Mittu Qaaqqi ilamanno Yannara Koo/tee Bandihu Gedenaanni Umisiha ikkino Su'ma Fushshinannisi. Su'mu Mitto Mancho Wolu Manchinni Badate Horonsi'neemmo Qaaleeti. Konni kaiminnino Hagiirso,Fullaasa,Affini,Nageesso,Dureessa....Wkl Yaamamanni Mannu Woshshamanna La'neemmo. Ikkollana Kuni Mannaho Su'minanni Su'mi Aleenni Xawinsintenni Gede Mitto Mancho Wolu Manchinni Badate ikkinnina Su'mini Su'mi Mancho Xawisa Hoogara Dandaanno Tunceenyuwa Baete. konniraati Mittu Manchi "Dureessa" Yaanno Su'ma Afi're Hee'renni Buxicho ikke, Araarso Yinoonnihu Gaance Kalaqanni,Qeelle Yinoonnihu Qeelamanni ,Atoote Yinoonnihu Baashaawanni, Afi'ra Yinoonnihu Hoongu Giddoonni Hee'rannohu Dikkonna Dikkaanchu Xaada Gimbo Yinannintenni Gede Su'munna Annu Xaada Hoogatenni Kalaqantanno Bolbolleeti. (Konne Aleenni Horonsi'roommo Su'ma Afidhinoonni Manna Sao Xa'mi'ra Baxeemmo.) Yesuusi Su'mi Kayinni Aleenni La'nummo Gedee Woshshamishshu Su'ma Di"ikkino. Yesuusinna Su'misi Xaaddinoreeti ; Su'misi Raawe Ayimmasi Xawisannoho. Yesuusa Yaanno Su'mi Tiro "Kaaliiqi Xagicho" Yitannote. kuni Su'mi Giddosi iimiidi Wolqa ikkanna Wolqaameessa Su'maati ; Su'misinni Xiwamaasine Hurtino,Danqootu Coyi'ra Dandiitino,Laanshaabbu Lekkansanni Hadhino,Konni Su'minni Sheexaanu Rufammo ; Baalu Coyinni Roore Kayinni Ninkera Su'misinni Hegere Baonni Gata ikkitinonke. Ayirrinyu Bayru Su'misira ikko. Yesuusira "Yesuusa" Yaanno Su'ma illacha Tunge uynoonnihu Di"isiraati ; Yesuusi umisi Umisi Su'minni Sheexaane Difushshino,xibba Dihursino . Kayinnilla Ganteemmo Gede kunni Xagicho ikkino Su'mi Aamaminohu Ninkeraati. ( "Gato wolewa Ayewano Dino Gatote Hasiisannonkehu Mannaho Uynoonni Su'mi Gordoho Woroonni Wolu Dino." Soq 4:12) Xagge ikkannohu Kuni Su'mi Soqqamaasineti Nafa Diaamammo. Kayinnilla konni Su'minni Masalonke Soorri'neemmo Gede kuni Su'mi Ninke Mannaho Aamaminonke. Yesuusi Su'minni Techo Konni Su'muwate Aliidi Su'minni Agarama Hattono Hura ikkitonke ! Su'muwate Aliidi Su'ma #YESUUSA ! Maqote Bue : Tuqu Xaadooshshe. ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ✍ @BTLEDA ⤴️ Injiihero Wolehono Tuqisi ! ℐᝪⅈℕ ႮՏ:- @Gatote_Suusa ☝☝☝☝☝☝☝ Miiloo'me ;Miiloonse !
Show all...
Ayyaanaame Telegraamete Chaanaale. Tenne Chaanaalera Mii'loo'mitiniro Gatonniwa Qolte Bobbaasiissaata Suusu Sokkuwa 👉 Faarso 👉 Borro 👉 Misilla (Graphics)..wkl Afidhinanni. ℐᝪⅈℕ ႮՏ @Gatote_Suusa
Show all...
(የማርቆስ ወንጌል 4 ) ------------ 3-4፤ እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ። ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት። 5፤ ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀና ጥልቅ መሬት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤ 6፤ ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ። 7፤ ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው፥ ፍሬም አልሰጠም። 8፤ ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠ፥ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ።
Show all...
(የሉቃስ ወንጌል 12 ) ------------ 15፤ የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ አላቸው። 16፤ ምሳሌም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ አንድ ባለ ጠጋ ሰው እርሻ እጅግ ፍሬያም ሆነችለት። 17፤ እርሱም፦ ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ? ብሎ በልቡ አሰበ። 18፤ እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ 19፤ ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ። 20፤ እግዚአብሔር ግን፦ አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው። 21፤ ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ዘንድም ባለ ጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው።
Show all...
(የማቴዎስ ወንጌል 7 ) ------------ 21፤ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። 22፤ በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። 23፤ የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
Show all...