cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Yiweku Zemen

መምጫዉ ቀርቧልና ወገኔ ሆይ ተዘጋጅ !!!!!!!!!!!!! ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል ወደ እርሱ ይወስደናል መከራን ከኛ ያርቃል ለዘላለም ያሳርፈናል በዚህ Channel ስለ ኢየሱስ ዳግም ምፅአትና ስለርሱ ሀያልነት ብቻ ይመሰከራል!!! ╬╬ ╬╬ ╬╬ ╬╬ ╬╬ ለአስተያየትዎ @Yiweku በDesta Denboba

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
168Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

. እበረታለሁ ዘማሪ ሳሙኤል ንጉሴ NEW AMAZING GOSPEL SONG ሼር በማድረግ ወዳጆ ያካፍሉ sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯 〽️ለበለጠ ቤተሰብ ይሁኑ〽️ ❇️ @marsilchannel ❇️ ❇️ @marsilchannel ❇️ ⚠️ይቀላቀሉን⚠️ 📲ሼር ማድረግዎን እዳይረሱ📲
Show all...
ዝማሬ🎙“ኢየሱስ ጓደኛዬ” ዘማሪ👥 🅷🅴🅻🅸🅽🅰  ርዝመት⏩ 3:45 ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻️ 🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻 ✅ @indiwbetsegaw ✅ ✅ @indiwbetsegaw
Show all...
ወሩን ሙሉ የተባረኩበት መዝሙር #በፈተና ብዛት ያጎበዝከው ልቤ🔥 #ዘማሪ አሰግድ @SisayAzusaRevivall @SisayAzusaRevivall
Show all...
❖ክፍል=ሁለት❖ ክፍል ሁለት፦ የክርስቶስ ዳግም መመለስ ሁለት ገጽታዎች፦ ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ በሁለት አይነት መልክ ነው የሚመጣው፣ የመጀመሪያ በስውር ሲሆን ሁለተኛ በግልጥ ነው። 🏁1.ስውር አመጣጡ ወይም ለቤተክርስቲያን መምጣት ጌታችን ኢየሱስ በስውርና ባልታሰበበት ሰዓት በመላእክት አለቃ ድምፅና፣ በእግዚአብሔር የመለከት ድምፅ ከሰማይ ሲገለጥ፣ በጌታ ሆነው የሞቱት ቅዱሳን ከሞት በአዲስ አካል ተነስተው፣ በምድር የሚኖሩ በሕይወት ያሉ ቅዱሳን የለበሱት አካላቸው ተለውጦ፣ በምድር የሚኖሩ በሕይወት ያሉ ቅዱሳን የለበሱት አካላቸው ተለውጦ ጌታን በአየር እና በደመና ለመቀበል በመነጠቅ የሚወሰዱበት መምጣቱ ስውር አመጣጥ ይባላል (1ተሰ.4፥16-17፣ 1ቆሮ.15፥51-54)። ምንም እንኳ ክስተቱ ስውር እና የማይታይ ቢሆንም የአማኞች መወሰድ በማያምኑት ዘንድ መገረም እና ድንጋጤ ይፈጥራል (ማቴ.24፥40-41)። ጌታ ኢየሱስ በስውር የሚመጣበት ዓላማም፦ በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያንን (አማኞችን) በንጥቀት ለመውሰድና ወደ ራሱ ለመሰብሰብ ነው(ዮሐ.14፥3፣ 1ተሰ.4:15-18)። ቤተክርስቲያንን ከታላቁ መከራ ለመጠበቅ እና ለማዳን ነው። 🏁2.ግልጽ አመጣጡ ወይም ከቤተክርስቲያን ጋር መምጣት (1ተሰ.3:12፣ ይሁዳ 14-15) ጌታ ኢየሱስ በግልጽ ሲመጣ በንጥቀት ከወሰዳቸው ቅዱሳንና ከመላእክት ጋር በታላቅ ክብር ወደ ምድር የሚወርድበት አመጣጥ ግልጽ የሚመጣበት ዓላማም፦ ❖.የአርማጌዶንን ጦርነት በድል ለመፈጸም፤ አርማጌዶን፤ ከቃሉ እንደምንረዳው አርማጌዶን ማለት የመጊዶ ተራራ ማለት ነው። መጊዶ፤የጦር ሠራዊት ሰፈር ማለት ነው። በቀርሜሎስ ተራራዎች ከሰሜን ወደ ደቡብ ጋዛንና ደማስቆን የሚያገናኘው መንገድ ለመጠበቅ የተመሸገ ከተማ ነበር። መጊዶና ታዕናክ ከሳሮን ሜዳ እስከ ኢይዝራኤል ሸለቆ ባለው በተራራማው አገር አቋርጦ ወደ ሰሜን ምስራቅ የሚዘልቀውን ዋና መተላለፊያ የሚቈጣጠሩ ቦታዎች ናቸው። <<የመጊዶ ሜዳ>> ቊልፍ ቦታ ከመሆኑ የተነሣ (2ዜና 35፥22) ከጥንት ጀምሮ በተደጋጋሚ ጦርነት የተካሄደበት ስፍራ ነው። ሣልሳዊ ቱትምስ የተባለው ፈርዖን፣ የተባበረውን የከነዓንን ሰራዊት በ1468 B.C በዚሁ ቦታ ጦርነት ገጥሞ ድል አድርጎታል። እንዲሁም በ1917 ዓ.ም ታላቋ ብሪታንያ በጀነራል አለንቢ መሪነት በመጊዶ ትይዩ ባለው በኢይዝራኤል ሸለቆ ከቱርክ አገዛዝ እንዲያከትም አድርጋለች። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ እንደሚገኘው፣ የእስራኤል ሰራዊት በዲቦራና በባርቅ መሪነት የከነዓናውያንን ቅስም የሰበሩት፣ በመጊዶ አጠገብ ዲቦራ ሲሣራን ድል አደረገች (መሳ.5፥19)፤ እንዲሁም መልካሙ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮስያስ በ609 B.C ከዳግማዊ ፈርዖን ኒካዑ ጋር ጦርነት ገጥሞ በዚሁ ስፍራ ሞቶአል (2ነገ.23፥29:30)። አርማጌዶን ማለት "የመጊዶን ተራራ ወይም የመጊዶን አምባ" ማለት ሲሆን፣ ይህም ሁሉን ማድረግ በሚችል በእግዚአብሔር ታላቅ ቀን የሚሆነው ጦርነት የሚካሄድበት ሥፍራ ነው (ራዕ.16፥14)። ታላቋ የዓለም መጨረሻ ጦርነት በአርማጌዶን ይደረጋል(ራዕ.16፥16)፤ ቃሉ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ክፉን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚያስወግድ ነው። ❖.ሐሰተኛውን ክርስቶስ ለመሻር (2ተሰ.2፥8)፤ ❖.ዓመፀኞችን ለመቀበልና ለመቅጣት (ማቴ.24፥31፣ 25፥22-26፤ 2ተሰ.1፥8፤ ይሁዳ 15)፤ ❖.እሥራኤልን ከጥፋት ለማዳን (ማቴ.24፥21-22፣ ኤር.30፥7)፤ ❖.ሺህ ዓመት በምድር ላይ ለመንገስ (ራዕ.11፥15፣ 20፥4-6) የመረጃ ምንጭ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት የተወሰደ ________ይቀጥላል__________ http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD
Show all...
የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት/The knowledge of Bible/

“በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።” — ሮሜ 1፥16 “For I am not ashamed of the gospel of Christ, for it is the power of God to salvation for everyone who believes, for the Jew first and also for the Greek.” -Rom.1:16

❖ክፍል አንድ❖ ክፍል አንድ፦የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ጌታ ኢየሱስ መጀመሪያ በሥጋ ተገልጦ እንደመጣ አሁንም ሁለተኛ ተመልሶ ቅዱሳንን ለመውሰድ እና ከእርሱ ጋር ለመኖር ከሰማይ ይገለጣል(ዮሐ.14፥1-3)። ይህ ሁለተኛ የመምጣቱ የተባረከ ተስፋ እርግጠኛ እና እውን መሆኑ የሚታወቀው ስለመጀመሪያ መምጣቱ የተናገሩት ትንቢቶች በመፈፀማቸው፣ ማለትም መወለዱ፣ መሞቱ፣ መነሣቱ እና ዕርገቱን ሁሉ ያጠቃለለው ትንቢት ተፈፅሟል። መጀመሪያ ሊመጣ ለኀጢአት የሚሰዋ በግ ሆኖ መጣ (ዮሐ.1፥29)። ተመልሶ ሲመጣ የነገሥታት ንጉሥ እና የጌቶች ጌታ ሆኖ ይመጣል (ራዕ.19፥16)። ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ የመምጣቱ እና የዓለም ፍፃሜ መቼ እንደሆነ ሲጠየቅ በዝርዝር ተናግሯል (ማቴ.24፥3-51)። ❖ ኢየሱስ በመንፈስ ሳይሆን በአካል በግልጥ ይመለሳል (ማቴ.24፥30) ❖ በድንገት ባልታሰበበት ሰአት ይመጣል(ማቴ.24፥38-42)። ❖ ሰዎች ዋናው ጉዳይ ቸል ብለው ሃሳባቸውን በምድራዊ ነገር ሲጥሉና፣ ለነገ መኖር ዋስትና ያገኙ ሲመስላቸው ሠላም እና ደህንነት ነው እያሉ ሲዘናጉ በድንገት ይመጣል (1ተሰ.5፥2-3)። ዳግም ምጽአት ዳግም ምጽአት ማለት ክርስቶስ ሁለተኛ ጊዜ መምጣት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገና እንደሚመጣ ተነግሯል፤ ማቴ.24፥30፤ 26፥64፤ ዮሐ.14፥3። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዐረገ በኋላ ሁለት መላእክቶች እንደሚመጣ ተናግሯል(ሐ.ሥ.1፥11) ፣ ሐዋርያትም ይህን አስተማሩ፤ ፊል.3፥20፤ 1ተሰ.4፥15:16፤ 2ተሰ.1፥6-10፤ ቲቶ 2፥12:13፤ ዕብ.9፥28። መምጣቱ ተስፋ ለቤተክርስቲያን ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የሚከተሉት ነገሮች ይፈጸማሉ። ❖1.ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል፤ ማቴ.24፥14፤ ቆላ.1፥6:23። ❖2.ወደ መጨረሻው ከእስራኤል ወገን ብዙዎች በክርስቶስ ያምናሉ፤ ሮሜ 11፥25-29፤ 2ቆሮ.3፥15:16። ❖3. መጨረሻ ላይ ትልቅ ክሕደት (ማቴ.24፥12፤ 2ተሰ.2፥3፤ 2ጢሞ.3፥1-7፤ 4፥3:4)፣ ከኢየሩሳሌም ውድቀት በፊት እንደ ነበረውም ታላቅ መከራ ይሆናል፤ማቴ.24፥15-22። ❖4.የዐመፅ ሰው የሚባለው የክርስቶስ ተቃዋሚ ይነሣል፤ 2ተሰ.2፥3:4፤ ራእ.20፥7-9። ❖5. በሰማይ እና በምድር አስፈሪ ምልክት እና ለውጥ ይታያል፤ ማቴ.24፥29:30። ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢየሱስ ይመጣል። ሰዎች ሳያስቡ ይመጣል። ምእመናን ቀኑን እና ሰዓቱን ባያውቅም ምልክቶች እያዩ በተስፋ ይጠባበቁታል፤ ማቴ.24፥32-44፤ 1ተሰ.5፥3:4። ኢየሱስ የሚመጣው በሥጋ (ሐ.ሥ.1፥11፤ ቲቶ 2፥13፡14፤ ራእ.1፥7)፣ በደመና ላይ (ማቴ.24፥30)፣ በመላእክት አለቃ ድምፅ፣ በእግዚአብሔር መለከት (1ተሰ.4፥16)፣ ከመላእክት ጋር (ማቴ.24፥31፤ 2ተሰ.1፥6:7) ነው። በክርስቶስ የሞቱ ይነሣሉ፤ በምድር ያሉ ሕያዋን ምእመናን ተለውጠው ይነጠቃሉ፤ ሌሎችም ይነሣሉ፤ ማቴ.24፥40:41፤ ዮሐ.5፥28፡29፤ 1ቆሮ.15፥51:52፤ 1ተሰ.4፥13-18። ኢየሱስ ከመጣ በኋላ ጻድቃንና ኃጥኣንን ይለያል፤ ማቴ.25፥31-46። ለምእመናን እንደ ሥራቸው ዋጋ ይሰጣል (ማቴ.25፥20-23፤ ሉቃ.19፥16-19፤ 2ቆሮ.5፥10)። በሰይጣን እና ባላመኑት ላይ ይፈርዳል፤ 2ተሰ.1፥6-10፤ ራእ.20፥10-15። ለኢየሱስ መምጣት እና ለፍርዱ ተዘጋጅተን መኖር ይገባናል፤ ሉቃ.21፥34-36። ስለዚህ ነቅተን በመጠበቅ (ማቴ.24፥42)፤ ተዘጋጅተን መኖር (ማቴ.24፥44)፤ ተግተን በመጠበቅ (ማር.13፥11-14)፤ ራሳችንን በመግዛት (1ተሰ.5፥4-8) እንኑር። ጌታ ሲመጣ በታላቅ ክብር ይመጣል (ማቴ.24፥30-35)። በኃይል እና በታላቅ ክብር (ማቴ.24፥30)። በእሳት ነበልባል (2ተሰ.1፥6-7) በቅዱሳን መላእክት ታጅቦ (ማቴ.25፥31፤ 2ተሰ.1፥7)። ከቅዱሳን አማኞች ጋር ይመጣል(1ተሰ.3፥12፤ ይሁዳ.1፥14-15)። ___________ይቀጥላል__________________ http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD
Show all...
የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት/The knowledge of Bible/

“በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።” — ሮሜ 1፥16 “For I am not ashamed of the gospel of Christ, for it is the power of God to salvation for everyone who believes, for the Jew first and also for the Greek.” -Rom.1:16

🇪🇹🔥🔥🔥🔥🇪🇹 🎤🎼🎹🥁🎷🎺🎸🎻🎻🎸🎺🎷🎸🎹🎼🎤 🎤🎼🎹🥁🎷🎺🎸🎻🎻🎸🎺🎷🎸🎹🎼🎤 🎹🎸@EnglishGospelSongs 🎹🎸 🎹🎸@EnglishGospelSongs 🎹🎸
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!