❖ክፍል አንድ❖
ክፍል አንድ፦የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት
ጌታ ኢየሱስ መጀመሪያ በሥጋ ተገልጦ እንደመጣ አሁንም ሁለተኛ ተመልሶ ቅዱሳንን ለመውሰድ እና ከእርሱ ጋር ለመኖር ከሰማይ ይገለጣል(ዮሐ.14፥1-3)። ይህ ሁለተኛ የመምጣቱ የተባረከ ተስፋ እርግጠኛ እና እውን መሆኑ የሚታወቀው ስለመጀመሪያ መምጣቱ የተናገሩት ትንቢቶች በመፈፀማቸው፣ ማለትም መወለዱ፣ መሞቱ፣ መነሣቱ እና ዕርገቱን ሁሉ ያጠቃለለው ትንቢት ተፈፅሟል። መጀመሪያ ሊመጣ ለኀጢአት የሚሰዋ በግ ሆኖ መጣ (ዮሐ.1፥29)። ተመልሶ ሲመጣ የነገሥታት ንጉሥ እና የጌቶች ጌታ ሆኖ ይመጣል (ራዕ.19፥16)። ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ የመምጣቱ እና የዓለም ፍፃሜ መቼ እንደሆነ ሲጠየቅ በዝርዝር ተናግሯል (ማቴ.24፥3-51)።
❖ ኢየሱስ በመንፈስ ሳይሆን በአካል በግልጥ ይመለሳል (ማቴ.24፥30)
❖ በድንገት ባልታሰበበት ሰአት ይመጣል(ማቴ.24፥38-42)።
❖ ሰዎች ዋናው ጉዳይ ቸል ብለው ሃሳባቸውን በምድራዊ ነገር ሲጥሉና፣ ለነገ መኖር ዋስትና ያገኙ ሲመስላቸው ሠላም እና ደህንነት ነው እያሉ ሲዘናጉ በድንገት ይመጣል (1ተሰ.5፥2-3)።
ዳግም ምጽአት
ዳግም ምጽአት ማለት ክርስቶስ ሁለተኛ ጊዜ መምጣት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገና እንደሚመጣ ተነግሯል፤ ማቴ.24፥30፤ 26፥64፤ ዮሐ.14፥3። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዐረገ በኋላ ሁለት መላእክቶች እንደሚመጣ ተናግሯል(ሐ.ሥ.1፥11)
፣ ሐዋርያትም ይህን አስተማሩ፤ ፊል.3፥20፤ 1ተሰ.4፥15:16፤ 2ተሰ.1፥6-10፤ ቲቶ 2፥12:13፤ ዕብ.9፥28። መምጣቱ ተስፋ ለቤተክርስቲያን ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የሚከተሉት ነገሮች ይፈጸማሉ።
❖1.ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል፤ ማቴ.24፥14፤ ቆላ.1፥6:23።
❖2.ወደ መጨረሻው ከእስራኤል ወገን ብዙዎች በክርስቶስ ያምናሉ፤ ሮሜ 11፥25-29፤ 2ቆሮ.3፥15:16።
❖3. መጨረሻ ላይ ትልቅ ክሕደት (ማቴ.24፥12፤ 2ተሰ.2፥3፤ 2ጢሞ.3፥1-7፤ 4፥3:4)፣ ከኢየሩሳሌም ውድቀት በፊት እንደ ነበረውም ታላቅ መከራ ይሆናል፤ማቴ.24፥15-22።
❖4.የዐመፅ ሰው የሚባለው የክርስቶስ ተቃዋሚ ይነሣል፤ 2ተሰ.2፥3:4፤ ራእ.20፥7-9።
❖5. በሰማይ እና በምድር አስፈሪ ምልክት እና ለውጥ ይታያል፤ ማቴ.24፥29:30።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢየሱስ ይመጣል። ሰዎች ሳያስቡ ይመጣል። ምእመናን ቀኑን እና ሰዓቱን ባያውቅም ምልክቶች እያዩ በተስፋ ይጠባበቁታል፤ ማቴ.24፥32-44፤ 1ተሰ.5፥3:4።
ኢየሱስ የሚመጣው በሥጋ (ሐ.ሥ.1፥11፤ ቲቶ 2፥13፡14፤ ራእ.1፥7)፣ በደመና ላይ (ማቴ.24፥30)፣ በመላእክት አለቃ ድምፅ፣ በእግዚአብሔር መለከት (1ተሰ.4፥16)፣ ከመላእክት ጋር (ማቴ.24፥31፤ 2ተሰ.1፥6:7) ነው። በክርስቶስ የሞቱ ይነሣሉ፤ በምድር ያሉ ሕያዋን ምእመናን ተለውጠው ይነጠቃሉ፤ ሌሎችም ይነሣሉ፤ ማቴ.24፥40:41፤ ዮሐ.5፥28፡29፤ 1ቆሮ.15፥51:52፤ 1ተሰ.4፥13-18። ኢየሱስ ከመጣ በኋላ ጻድቃንና ኃጥኣንን ይለያል፤ ማቴ.25፥31-46። ለምእመናን እንደ ሥራቸው ዋጋ ይሰጣል (ማቴ.25፥20-23፤ ሉቃ.19፥16-19፤ 2ቆሮ.5፥10)። በሰይጣን እና ባላመኑት ላይ ይፈርዳል፤ 2ተሰ.1፥6-10፤ ራእ.20፥10-15። ለኢየሱስ መምጣት እና ለፍርዱ ተዘጋጅተን መኖር ይገባናል፤ ሉቃ.21፥34-36።
ስለዚህ ነቅተን በመጠበቅ (ማቴ.24፥42)፤ ተዘጋጅተን መኖር (ማቴ.24፥44)፤ ተግተን በመጠበቅ (ማር.13፥11-14)፤ ራሳችንን በመግዛት (1ተሰ.5፥4-8) እንኑር። ጌታ ሲመጣ በታላቅ ክብር ይመጣል (ማቴ.24፥30-35)። በኃይል እና በታላቅ ክብር (ማቴ.24፥30)። በእሳት ነበልባል (2ተሰ.1፥6-7) በቅዱሳን መላእክት ታጅቦ (ማቴ.25፥31፤ 2ተሰ.1፥7)።
ከቅዱሳን አማኞች ጋር ይመጣል(1ተሰ.3፥12፤ ይሁዳ.1፥14-15)።
___________ይቀጥላል__________________
http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GODShow more ...
የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት/The knowledge of Bible/
“በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።”
— ሮሜ 1፥16
“For I am not ashamed of the gospel of Christ, for it is the power of God to salvation for everyone who believes, for the Jew first and also for the Greek.”
-Rom.1:16