cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አላቲኖስ

የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትን፣ስንክሳር፣ የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ሥዕላትን፣ የተመረጡ የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍትና ትረካዎችን የሚያገኙበት ድንቅ ቻናል ሁለተኛ ቤታችሁን join በሉ። for any comment @natnael1201

Show more
Advertising posts
518Subscribers
No data24 hours
-27 days
-1630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

https://t.me/maheberat እንኳን አደረሳችሁ❤️
Show all...
✞ መልዐከ ጥዒና ✞ መልዐከ ጥዒና(ሰላም) ሩፋኤል ነፍሴን ታደጋት ከሲኦል ከመከራ ከሃዘን አድነኝ በክንፈ ረድኤትህ እየሰወርከኝ        ነፍሴን እየጎዳው ለስጋዬ አድልቼ እንዳልኖር በስቃይ ከአምላክ ተጣልቼ ማደሪያው እንዳልሆን ለዛ ፈታኝ ከይሲ ሃኪሜ አንተ ድረስ የነፍሴ ፈዋሲ                       /አዝ===== ሥልጣን ተሰጥቶሃል ቁስሌን ትፈውስ ዘንድ ፈታሄ ማህጸን ድኅነት የምትወድ በስምህ ስማጸን ትቆማለህ ለኔ ከቶ አያገኘኝም ፍርድ እና ኩነኔ                /አዝ===== እመካለሁ በአንተ እስከ ዕለተ ሞቴ ሁሌም ከኔ ጋር ነህ ሩፋኤል ረዳቴ ጠበልህ ፍቱን ነው እኔን ጎብኝቶኛል ከእግረ ሙቀት ስርዓት ከሞት አድኖኛል                /አዝ===== ውስጤን ታውቀዋለህ ድካም እንዳለብኝ ስበድል ሳጠፋ በፍጹም አትራቀኝ እምነቴን አጽናልኝ ልኑር ካንተ ጋራ በተሰጠህ ሥልጣን ሩፋኤል አደራ https://t.me/maheberat
Show all...
ሩፋኤል ሆይ ይቅር በለኝ አሳድገኝ ብዬ ሮጬ ከልጆች ጋር ተሯሩጬ በጠበልህ እየታጠብኩ የውሀን ጨው እየቀመስኩ ሩፋኤል አሳድገኝ እንደ ታላቆቼ አድርገኝ ብዬ እየጮውኩኝ ስጣራ ሰምተኸኛል ከልጅ ተራ ዘንድሮ ግን ተጠለልኩኝ ጠበል ሲወርድ ተሸሸኩኝ ከበረከትህ ሸሸሁኝ ከቡራኬህ አመለጥኩኝ ሩፋኤል ሆይ ይቅር በለኝ ስላበቃ ልጅነቴ በቆሸሸ ሰውነቴ በረከሰ ማንነቴ እንዳላረክስ ጠበልህን ተጠለልኩት ጥምቀትህን https://t.me/maheberat
Show all...
የአካባቢ ወጣቶች መዝሙራት

የተመረጡ የማህበራት እና የካሴት መዝሙራትን የሚያገኙበት ምርጥ channel ይቀላቀሉን ይደሰቱበታል። ለአስተየትዎ @Natnael1201

✝️  ቅዱስ ሩፋኤል✝️ ምስጢረ መለኮት አድራሽ ነህ ለእራኤል ''መድሐኒት ነው ስምህ ቅዱስ ሩፋኤል''/2/ የሱሳኑ ደዌ በጆችህ ተዳሶ አይኖቹ በርተዋል ምህረትን ለብሶ እኔ ራሴን ባየው ተስኖኛልና ከኔ አልፎ አምላኬን 'ልወቅ በጽሞና'?      አዝ--------- እረፍት ምስጋና ነውና 'አጻፍም'? ችግር የምትጋርድ በያዝኧው በሳት ፋም በሳት ስረገለ በሚፋጠን እግርህ ፈጥነህ ድረስልኝ የልቤን ስነግርህ      አዝ------- ከአህዛብ እሾህ ደግሜ እንዳልበላ እንደ ጦቢት ጋርደኝ በክንፎችህ ጥላ እግዚአቤሔር እንዲያዝህ በፍፁም ልቦና አንተን እንደሚልክ አምነዋለሁና      አዝ----------- ሰላክሬም በክፋት ቆሞብኝ ከፊቴ ናልኝ እልሀለሁ ሩፋኤል አባቴ የሰራብኝን ግፍ ባንተ ረስቻለሁ በመድሐኒት እጅህ ደስታን አግኝቻለሁ       ዘማሪ ሲስተር ሕይወት ተፈሪ https://t.me/maheberat
Show all...
ሃሌ-ሉያ አንተ ሰው ሆይ ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ (4) ቡሄ መድረሱን ሰምተሃል ወይ ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ መስማቱንማ ሰምቼ ነበር ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ ከዚያ ቢያደርሰኝ ልዑል እግዚአብሔር ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ እናቴ ሆይ.......... ሆ ይህን ባየሻ ........ሆ በቁርማ ዳቦ .......ሆ ሲጥለኝ ውሻ........ሆ ደጓ ጫማዋን ......ሆ አውልቃዋለች.......ሆ ውሃ ሲጠማ.........ሆ አጠጥታዋለች......ሆ የስዋ ውዳሴ .......ሆ ሆኖኛል ውይን ......ሆ ዘሬም ብዘምር ......ሆ እኖራለሁኝ ...........ሆ ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4) በእምነት እንውጣ .ሆ ከተራራው ላይ......ሆ ይታይ ብርሃኑ........ሆ ክብሩ ኤልሻዳይ....ሆ ሙሴን እንጠይቅ...ሆ የጥንቱን ነገር .......ሆ ምን እንደሚለው ...ሆ ጌታን ሲያናግር......ሆ ድምጹን እንስማ ....ሆ እንደ ትሁትነቱ.......ሆ እንቀበለው ..........ሳ እኛም በትሩን .......ሆ ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (2) ተቁኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2) ተራራውማ ..........ሆ ነውና አምሳል.......ሆ ለቤተ ክርስቲያን...ሆ መንበረ ልዑል........ሆ ወጥተን እንጠይቅ .....ሆ ኤልያስን.............ሆ እንድንዳስሰው.....ሆ ጸጓራር ክንዱን....ሆ ሰማይ በትለጉም...ሆ ባህር ቢከፍል.......ሆ እሳት ብታወርድ.....ሆ ጠላትም ቢርድ......ሆ በሰረገላ ..............ሆ የተነጠከው...........ሆ ይህ ሁሉ ክብር .....ሆ በማን ስልጣን ነው....ሆ ለሁላችን መልካም ነው በዚህ መኖር(4) የእመብርሃን .........ሆ የምዬ ልጅ............ሆ ተጥሎ ላይቀር .....ሆ ተረስቶ ደጅ...........ሆ ሰአሊ ለነ .............ሆ ባለበት አፉ...........ሆ የጭንቁን እለት.....ሆ ተሰብሮ ሰልፉ......ሆ እንዳባቶቹ ............ሆ ቅኔን ተቀኘ.............ሆ ድንግል ስትረዳው....ሆ አይኑ ስላየ..............ሆ ተፈስሂ ደብረ ታቦር(2) ተፈስሂ አርሙኒየም (2) ባንቺ ላይ ታየ እግዚአብሔር ተፈስሂ አርሙንየም ሙሴ ስላለ ............ሆ መና ያውርዳል........ሆ ቅዱስ ኤልያስ.........ሆ ስጋ ያመጣል..........ሆ ዮሃንስንም............ሆ ጌታ ይወዳል.........ሆ መድኃኒታችን........ሆ ፈውስ ይሆነናል.....ሆ በዚህ እንድንኖር ...ሆ ዳሱን ጥለናል .....ሆ ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4) አባቴም ቤት..........ሆ አለኝ ለከት.............ሆ እናቴም ቤት ...........ሆሆ አለኝ ለከት...,..........ሆ ፍልሰታ ስትሆን.......ሆ የቆምኩባት............ሆ በድብረ ታቦር .........ሆ ያጌጥኩባት...........ሆ ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ(2) ተቀኙለት  በልልታ ላዳኙ ጌታ(2) አመት አውዳመት "ድገምና" አመት "ድገምና" ያባብዬን ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና" ይግባ በረከት "ድገምና" አመት "ድገምና" የማምዬ ቤት "ድገምና"  አመት "ድገምና" ይትረፍረፍ በእውነት "ድገምና" አመት "ድገምና" ነሩ በሀይማኖት ጽኑ በጸሎት  በተዋህዶ ቤት(4) የሰማይ ሰራዊት "በእምነት" ያድርጋችሁ "አሜን" አማኑኤል በጸጋ "በእምነት" ያኑራችሁ "አሜን" ከስጋ ወደሙ "በእምነት" ያድላችሁ "አሜን" ዘርን እደ አብርሃም "በእምነት" ያብዛላችሁ "አሜን" ይባረክ በእግዚአብሔር በእምነት ዘመናችሁ  "አሜን"/2/ እድሜና ጤናውን በእምነት ያድላችሁ "አሜን" (2) https://t.me/maheberat
Show all...
የአካባቢ ወጣቶች መዝሙራት

የተመረጡ የማህበራት እና የካሴት መዝሙራትን የሚያገኙበት ምርጥ channel ይቀላቀሉን ይደሰቱበታል። ለአስተየትዎ @Natnael1201

ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ። በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን። "ፃድቃኔ ማርያም ልትመረቅ ነው" እንኳን ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓልና የቤተክርስቲያን ምረቃ በሰላም አደረሳችሁ እያልን ማህበራችን ፈለገ እንድሪል መንፈሳዊ የጉዞና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ማህበር ወደ ታላቋ ፃድቃኔ ማርያም ገዳም አቅምን ያገናዘበ ታላቅ ጉዞ አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል። ⏩⏩ የጉዞ ቦታ ፦ ፃድቃኔ ማርያም ገዳም ⏩⏩ የጉዞ ቀን ፦ ግንቦት 20_21 ⏩⏩ የጉዞ መነሻ ሰዓት ፦ 12፡00 ⏩⏩ የጉዞ መነሻ ቦታ   ፦  ሸጎሌ ሩፋኤል ፣ አዲሱ ገበያ፣ ስድስት ኪሎ፣ መገናኛ ፣ ላምበረት ፣ ጣፎ አደባባይ ⏩⏩  የጉዞ ዋጋ ፦ 520 መስተንግዶን ሳይጨምር ⏩⏩ ለመመዝገብ እነዚህን ስልኮች ይጠቀሙ ፦  +251901925758  ናትናኤል +251703925758 በ telegram ለመመዝገብ 👉👉  @Natnael1201 በ Instagram ለመመዝገብ 👉👉 natnael881 ያዋሩን ማሳሰቢያ ⏩ ሰዓት ይከበር። ⏩ ጉዞው የአዳር ሲሆን መስተንግዶን አይጨምርም። ⏩ ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዳይለይዎ። አዘጋጅ ፦ ፈለገ እንድሪል መንፈሳዊ የጉዞና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ማህበር
Show all...
ትንሽ ስለ አድዋ ልበላችሁ 🔴ስለ አ ድ ዋ ጦርነት ያልተሰሙ ምስጢሮች 👉 የአድዋ ጦርነት ለምዕራባውያን አፍሪካን የመቀራመትና በውስጧ የያዘችውን እምቅ የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሥጦታ ለመጠቀም ያላቸውን ሕልም ያከሸፈ ሲሆን የኢት-ኤል ልጆች የኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያውያት የድል ዕለት ሲሆን ለአፍሪካውያን ደግሞ የነጻነት ዕለት ነው ። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጥንት ታሪኳ ጀምሮ ለጠላት የማትበገር እንደ 9 ቁጥር ቀመር የጸናች የጠነከረች ግንብ ናት ፤ ከጥንት አምላክ ለኖኅ በአራራት ተራራ ቃልኪዳኑን ‘ቀስቴን በደመና አኖራለሁ’ ብሎ የገለጸባት ። ከአራቱ አፍላጋት ዋነኛው ግዮን የሚፈልቅባት ውሃዎቿ ወተት የሆኑ እርሷም ገነት የሆነች ምድረ ገነት ኢትዮጵያ ። ቀደምት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከሀገራቸው አልፈው በፍትሕና በፍቅር የተለያዩ ብሔራትን የገዙ ነበሩ። ንጉሦቿ የፈሪሃ እግዚአብሔር፥ የሰባቱ የጥበብ ምሰሦዎች ማደሪያ የነበሩ። ከጥንት ከአዳም ጀምሮ ብዙ ነገሥታት ያስተዳደሯት ፤ የመጀመሪያውን ቋንቋ አቅፋ የያዘች ድንቅ ምድር ኢትዮጵያ። ይች ድንቅ ሀገር በያዘችው እምቅ ድብቅ ኃብተ ተፈጥሮ ምክንያትም ለዘመናት በምስጢር ማኅበራቱ የምትፈለግ ናት ፤ አድዋም ሀገሪቷን ተቆጣጥሮ የማልማትና ለራሳቸው አላማ ለመጠቀም ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ ሚሽነሪዎችን በመላክ የኢትዮጵያውያን ኃይል የሆነውን ‘ጎራዴ’ የሚሰራውን ሰው ቀጥቃጭ፥ ብራና ዳምጦ ቀለም በጥብጦ የሚጽፈውን ደግሞ ጠንቋይ እያሉ በማኅበረሰቡ ዘንድ እኒህ የተለያዩ ጥበባት እንዲነቀፉ ሲያደርጉ ቆይተዋል። 👉ታሪኩ እንዲ ነው ፦👇 ታዋቂው የውጫሌ ውል በሚያዚያ 25 ቀን በ1881 ዓ.ም በውጫሌ ሰፈር የተፈጸመ ሲሆን በዚህ ውል ውስጥ ከተጠቀሱት አንቀጾች መካከል አንዱ ለአድዋ ጦርነት መነሻ እንደሆነ ይታወቃል። ይህንን ውል በጣሊያን በኩል የተዋዋለው አንቶኔሊ ሲሆን በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ አጼ ምኒልክ እንደሆኑ የታሪክ መዝገቦች ያመለክታሉ ። ጣሊያን የውጫሌ ውል የንግድና የፍቅር ነው በማለት ብትቀርብም ከመነሻው ጀምሮ ብዙ ጥርጣሬ፣ ክርክር እና ተቃውሞ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲሰማ እንደነበር ታሪክ ያስታውሳል፡፡የውጫሌ ውል 20 የተለያዩ ውሎችን የያዘ ሲሆን ከ20ዎቹ የውጫሌ ውል አንቀጾች መካከል ከአንቀጽ 3 በላይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳው አንቀጽ 17 ነው፡፡ 👉 አንቀጽ 17 በአማርኛ “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ በኢጣሊያ መንግስት አጋዥነት መላላክ ይቻላቸዋል፡፡” የሚል ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙም የኢትዮጵያ መንግስት ከፈቀደነ ከፈለጋ በኢጣሊያ በኩል ከውጭ መንግስታት ጋር ግንኙነት መመስት እንደሚችል የሚጠቅስ ነው፡፡ 👉 የአንቀጹ የጣሊያነኛ ትርጉም ግን “የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ አገር መንግስታት ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት አማካኝነት ማድረግ ይገባዋል፡፡” የሚል ነበር፡፡ ይሄም የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት በቀጥታ በጣሊያን በኩል እንዲከናወን የሚያስገድድ ነበር፡፡ ቃላት የዓለምን ሚዛን ሊቀይሩ ይችላሉ ፤ የቃላት ኃይልም እንደ እብነ አድማስ ደንጊያ የበረታ ነው። ዓለማት ሁሉ የተፈጠሩት በነቢብ በቃል ነው። በነዚህ ምክንያቶችም አጼው አለቃ አጽመ ጊዮርጊስንና ግራ አዝማች ዮሴፍ ንጉሤን እንዲመረምሩት በታዘዙት መሰረት መርምረው ይሄንን የቃላት መጭበርበር ደርሰውበታል። 👉 ብርሃን ዘኢትዮጵያ ንግሥቲቱ ጣይቱም ታላቅ ጀብድን በጦርነቱና ከዛ በፊት ሰርተዋል። የኢጣሊያውን ዲፕሎማት አንቶኔሊን ጣይቱ እንዲህ አሉት፡- “ያንተ ፍላጐት ኢትዮጵያ በሌላ መንግስት ፊት የኢጣሊያ ጥገኛ መሆኗን ለማሳወቅ ነው። ነገር ግን ይህን የመሰለው የምኞት ሃሳብ አይሞከርም!! እኔ ራሴ ሴት ነኝ።ጦርነት አልፈልግም። ነገር ግን ይህን ውል ብሎ ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ!” ። ከዚህም በኋላ አጼው ይህንን ውርደት መቀበል ስላልፈለጉ ጦርነቱ ሊከሰት እንደቻለ ታሪክ ይመሰክራል። ከዚህም በኋላ የዚህ መርሃግብር አላማ ስለ ጦርነቱ ሂደት ማብራራት ሳይሆን የተጠቀሙትን ጥበባት ማብራራት ነውና ባጭሩ የምንቀጥል ይሆናል። 👉 የክተት አዋጁ የታወጀው በመስከረም 1888 ዓ.ም ላይ ሲሆን አዋጁ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ገጽታ ነበረው። 😱 የካቲት 23 1888 አጼው በቅዳሴ ላይ እያሉ አንድ መልእክተኛ በጆሯቸው ተጠግቶሸ የጣሊያኖችን ጦር መንቀሳቀስ ሹክ አላቸው ፤ አጼው ላይ ግን ምንም የፊት ገጽታ ለውጥ አልታይም። ይልቁንም ፊታቸውን ወደ ቤተ መቅደሱ በማዞር የቅዳሴ ሥነ-ሥርዓቱን በአግባቡ ፈጸሙ! የቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት ሲጠናቀቅም ሰራዊታቸውን እንዲዘጋጁ አዘዙ። 👉 ውጊያውም በነግህ ተጀመረ፤ የኢጣሊያ ወታደሮች ተኩስ እንደጀመሩም አሸን የመሰለው ጀግናውና ኩሩው ኢትዮጵያዊው አርበኛ፥ ገበሬ ሆ! ብሎ ዘመቱባቸው። ✝ሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰራቸው ታዓምራት ውስጥ አንዱ ይህ ተጽፏል። “ በዚህም ዕለት ይኸውም የካቲት 23 ቀን በሮማውያንና በኢትዮጵያውያን መካከል ከፍተኛ ጦርነት ሆነ፡፡ ወዲያውም በሰማይ ታላቅ ተአምር ተደረገ፡፡ ይኸውም የቀስተ ደመና ምልክት ታየ፡፡ ከዚያም ቀስተ ደመና ውስጥ መልኩ አረንጓዴ የሚመስል ጢስ ይወጣ ነበር፡፡ ከዚያም ጢስ ውስጥ እንደክረምት ነጎድጓድ ያለ ድምፅ ተሰማ፡፡ ከዚያም የነጎድጓድ ድምፅ የተነሣ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሽብር ሆነ፡፡ ለመዋጋትም አልቻሉም፡፡ ይልቁንም ኃያሉ ገባሬ ተአምር ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምባ ላይ ፈረስ ተቀምጦ ከነፋስ ሩጫ ይልቅ እየተፋጠነ በአየር ላይ በተገለጠ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም እያሉ ወደቁ፡፡ ‹የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላካቸው ሊረዳቸው መጣ፡፡ እንግዲህ ማን ያድነናል› አሉ፡፡ ምድር ጠበበቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ የአትዮጵያ ሠራዊት የሮምን የጦር ሠራዊት ፈጁዋቸው፡፡ የተረፉትንም ማረኳቸው፡፡ ፈጽመውም እስኪያጠፏቸው ድረስ በሮማውያን ላይ በእግዚአብሔር ሥልጣን የኢትዮጵያውያን እጅ እየበረታች ሄደች፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ሣህለ ማርያም በእግዚአብሔር ኃይልና በተአምራት አድራጊው በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የሮማውያንን የጦር ሠራዊት በጦርነት ድል አድርጎ የድል አክሊል ተቀዳጀ፡፡ ” በማለት የቅዱስ ጊዮርጊስ ተዓምር ስለ አድዋ ጦርነት እንዲህ በአጭሩ ያስቃኘናል ። በጦርነቱ ላይ በመላዋ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ የተሳተፉበት ሲሆን ልዩ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ሰዎችም አሉ። የካቲት ከቲት ከቲቶት የተባለችው ወርም የዘርን መወቃት እንደምትገልጸው ሁሉ ኢትዮጵያውያንም ሮማውያንን ድል አደረጉ ።....... 👇ቀጣይ ለማንበብ 👇 @Maheberat @Maheberat For Any comment @Natnael1201
Show all...
ብዙ ሰዎች ስለ "ቶ" መስቀል ጠይቃችሁን ነበር በቃላችን መሰረት👇👇👇 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 'ቶ' መስቀል (አንቅህ) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 'አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል' [መስቀሌን በመስቀሌ ላይ አኑር/አስቀምጥ] የዚህን እጅግ የረቀቀ አባባል የምንረዳው በትርጓሜ እና በምርምር ነው። መስቀል ከእየሱስ በፊት የነበረ እና ያለ ነው። ምሳሌነቱም የሰው ልጅ የቁጥር መልክ ነው። ስለሆነም 'ተ' ን ሰብእ ድረስ ስንቆጥረው 'ቶ' ሳብኡን ወይንም ሰባተኛውን እናገኛለን። ይህንን ነው እንግዲ ምንም መነሻና መድረሻ ቃል ሳይጨምሩ ከነአጠራሩ በግዕዙ #'አንቅህ' [#ankh] ወይም የህይወት ምልክት በማለት የሚጠሩት ። 'ቶ' ራስ ያለው ሰው ወይም ሰብእ ማለት ነው። ሰብእ ማለት ሰው ማለት ነው ይህውም ከሰባት ባህርያት ከአራቱ የሥጋ በህርያት ውሃ፣ አፈር፣ እሳት፣ ነፍስ እንዲሁም ከሶስቱ የነፍስ ባህርያት ህያውነት፣ ልባዊነት፣ ንባባዊነት የተፈጠረ ነው። ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት ኢትዮጵያውያን ነገስታት መስቀል በትረ መንግስታቸው ወይም መለያቸው ነበር።በቀደሙ ዘመናት ደግሞ ኢትዮጵያውያን ነገስታት በሄዱበት እና በተቀመጡበት ቦታ ሁሉ በእጃቸው ይይዙት ነበር።ይህም የበትረ መንግስት ቀዳሚ ምሳሌ መሆኑ ነው። “ቶ” ሠባተኛዋ ቁጥር በመሆኗ ፍፁምነትን የምታመለክት ነች፡፡ ትልቁ ከዚህ በላይ ያለው ሚስጥር አባቶቻችን ከመፅሐፍ ቅዱስ ትርጔሜ ሲተነትኑ በሰማይ መላዕክት ዘንድ ውጊያ ሆነ ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ከሣጥናኤል ጋር ሲዋጉ ሁለት ጊዜ ተሸንፈዋል፡፡ በሶስተኛው እንዲያሸንፉ ሲልካቸው ይህን ቀስተደመና ቀርፆ፣ ይህን ምልክት የኮከቡን ቅርፅ የ“ቶ” ቅርፅ ያለው መስቀል በየክንፋቸው ቀርፆላቸዋል። 'ኤል'የሚለውንም ሚስጢራዊ ስም አትሞባቸዋል።ይህን ካደረገላቸው በኋላ ተመልሰው ወደ ውጊያው ቢሄዱ ሳጥናኤል ሀይላቸውን ሊቋቋመው አልቻለም ውድቀቱ ፈጠነ ሽንፈቱ የከፋ ሆነበት ፅልመትን አልብሰው ወደ በርባኖስ ውስጥ ጥልቅ ጨለማ ላይ ወረወሩት። ሰወች 'ቶ'ን የህይወት ምልክት አድርገዉ የሚወስዱት ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ነዉ::የሚገርመዉ ደግሞ ይህ ምልክት አገልግሎት ላይ የዋለዉ ከክርስቶስ ልደት በፊት 3000 አመታት ቀደም ብሎ ጥንት ግብፃዉያን ቶኔቶር ብለዉ በሚጠሯት ሀገር ነዉ:: ግብፃዉያን እንደሚሉት የፒራሚድ ግንባታ ጥበብን የተማሩት ከቶኔቶር (የአሁኗ ኢትዮጵያ) ሰወችና አማልክቶች ነዉ:: በ670 አ.አ በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረዉ ንጉስ ቲርሀቅ እየሩሳሌም የኦሶር ንጉስ በሆነዉ በሰናክሬም ስትወረር ለእየሩሳሌም መከታ ሆኖ ሲዘምት ሀያላን ከሚባሉ ወታደሮች ጋሻ ላይ የቶ ምልክት እንደተቀረፀና ንጉሱም በ'ቶ' ቅርፅ የተሰራ መስቀል ማሰሩን የሚያስረዱ የድንጋይ ላይ ፅሁፎች ተገኝተዋል:: . የ'ቶ' ምልክት የተፈጠረዉ በቅርብ ግዜ ነዉ ለሚሉ ሰወች 'ቶ 'የተፈጠረዉ አለም ሲፈጠር ነዉ' ብል እዉነት እንጅ ዉሸት አይሆንም::ለዚህ ማስረጃየ ደግሞ የሰዉ ልጅ የተፈጠረዉ በ'ቶ' ቀመር መሆኑ ነዉ:: . ይህ ምልክት ግብፅ በሚገኙ የዋሻ ስእሎች ላይ የህይወትን ገፀ ባህሪ ይዞ እንደነበር የሚያስረዳ ሲሆን ይህ ምልክት አገልግሎት የጀመረዉ ኢትዮጵያ ላይ ከሆነ ግብፅ ላይ እንዴት ተገኘ? ብሎ ለሚጠይቅ ግብፅ ላይ የነገሱት 18 ኢትዮጵያዊ ንጉሶች ተጠቃሽ ናቸዉ:: ሜምኖን የተባለዉ ኢትዮጵያዊ የግብፅ ንጉስ ከ1320 አ.አ እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 አ.ም የቆመ ሀዉልት እንደነበረዉና ሀዉልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሀይ ሲያርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበር ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል::ክራር ደግሞ የኢትዮጵያ የባህል መሳሪያ መሆኑ አጀብ ያስብላል:: በሳባዉያን የዋሻ ላይ ስእሎችና ማህተሞች ላይ 'ቶ' ተመስሎ ጣቱን የቀሰረ ምስል እንዳለ (አስቻለዉ ከበደ የተባለ ፀሀፊ ከርከቤዴል ሳዶፍ) በሚል መፅሀፉ አስፍሮታል::ሳባዉያን ሰዉን ለመሳል 'ቶ'ን መጠቀማቸዉ ያጋጣሚ ይመስላችሁአል? አይደለም። #ዴርቶጋዳ፣ #ራማቶሀራ፣ #ዣንቶዣራ፣ #ዮራቶራድ፣ #ዮቶድ፣ #ዮቶር፣ወ.ዘ.ተ ቃላት በቶ ፊደል የተመሰረቱ ና የቶ ን የፊደል ትርጉም መነሻ አድርገው የተመሰረቱ ቃላት ናቸው።ስለሆነም የ 'ቶ' ምልክት አገልግሎት ላይ የዋለዉ ከክርስቶስ ልደት በፊት 3000 አመታት ቀደም ብሎ ጥንት ግብፃዉያን #ቶርኔተር ወይም #ቶኔቶር ብለው የሚጠሯት የስልጣኔ ምንጭ ከሆነችው ከኢትዬጵያ ምድር ነው።'ቶ' የህይወት ምልክት ነው። ቶኔቶር ማለት የአምላክ ሀገር ማለት ነው።ቶኔቶር ተብላ የምትጠራው ሀገር ደግሞ ኢትዬጵያ ናት።ይህ የ'ቶ' ፊደል ቅርፅ ሰማያዊ ነው(ከሰማይ የወረደ)ነው።የሚሉ የስነፅሁፍ ምሁራና ተመራማሪዋች የሀይማኖት አባቶች አሉ። ስለ ቶ መስቀል ይህንን ካልኩ ዘንድ ይበቃል ነገር ግን ምን ያህሎቻችው ስለ #'ቆ' መስቀልስ ታውቃላች? የአዳም በትር የሚባለው። ከ ቶ መስቀል በላይ ታላቅ ሃይል እና ታላቅ ምስጢር ስላለው ቆ መስቀል። ሚስጥሩ እንዳይታወቅ ስሟ ከታሪክ መዛግብት ላይ የተሰረዘችው ታላቋ #ንግስት_ኢተያ ከጣና ሃይቅ ይዛው የሰጠመችው እና ይህወቷን የሠዋችለት ምስጢር፤ ወደፊት የሚመጣው ታላቁ ባለትንቢቱ ንጉስ ቶዎድሮስ ሲነግስ ከጣና ይዞት የሚወጣው የ ቆ መስቀል ብትር። ይቀጥላል… #share #share #share @Maheberat @Maheberat For any comment @Natnael1201
Show all...
እነ አቶ አካለ ወልድ ሞገስ በሕገወጥ መንገድ ልብሰ ጵጵስና ካለበሷቸው መነኮሳት መካከል በቀድሞ ስማቸው አባ ንዋየ ሥላሴ አክሊሉ ባደረጉት ሥራ ተጸጽተው በዛሬው ዕለት ይቅርታ ጠየቁ ! https://t.me/maheberat
Show all...
መምህር ምሕረተአብ አሰፋ እና የማንቂያ ደውል አገልጋዮች ዲ/ን አማኑኤል አያሌው እንዲሁም ዲ/ን ኪሩቤል አሰፋ በዛሬው ዕለት ታፍነዋል ! https://t.me/maheberat
Show all...