በጣም ያዘንኩበት ታሪክ
#ኧረ ሴቶች😭
🚨🚨👇👇😭😭🚨🚨👇👇
የሲስን ቻናል በአጋጣሚ በቅርቡ ነበር ያወኩት ሁሉንም ትምህርቶቹን ሰምቻለሁ..ከትምህርቶቹ ጋር እያለቀስቁ ፀልያለሁ
#ትምህርትህ ቀድሞ ቢደርሰኝ ኖሮ ከዚህ ጉድ እድን ነበር😭😭😭😭።
ግልፅ ላርግልህ ሲስ ግራ እንዳትጋባ።ከልብህ ስማኝ
#ሜሪ እባላለሁ የምኖረዉ አዲስ አበባ ነዉ።24አመቴ ነዉ። ተመራቂ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ በጎን ግን ስራ ሰራለሁ።
የቸርች አገልጋይ ነበርኩ ለጌታ የተሰጠሁ ሰዉ ነኝ በጣም ጠንካራ እና ጥንቁቅ ሴት ነኝ።
......የገጠመኝን ልንገርህ አንድ ሰዉ ወደ ሂወቴ መጣ..እኔ አንድ ልምድ አለኝ ሁሌ ወንዶች የፍቅር ጥያቄ ሲጠይቁኝ ቶሎ እሺ አልልም መጀመሪያ ፀልዬ ጌታን ጠይቄ ነዉ የምወስነዉ። የልጁ ስሙ T ይባላል ዘማሪ ና ነቢይ ነዉ። ለ15ቀን ፀልዬ ልቤ ወደሱ ስላዘነበለ የፍቅር ጥያቄዉን ተቀበልኩትና ቀጠልን ለፀሎት ይደውልልኝ ነበር የሚገርምፀጋ ያለበት ልጅ ነዉ ብዙ ግዜ ታምሜ ፀልዮ ድኛለሁ።
.......ሲስ ትምህርትን ስሰማ መንፈሳዊ ከሚመስሉ ወንዶች ተጠበቁ ብለሀል ደሞ የመድረክ ህይወትና የግል ባህሪ ማንነት የተለያየም መሆኑን ነገርህናል።ነገሩን ላሳጥርልክና ከልጁ ጋ ለመጋባት ወስነን ብዙ ስቴፕ ሄደን ጌታን ሲስ በህይወቴ ለመጀመሪያ ግዜ ያፈቀርኩት እሱን ነዉ።
ግን በዝሙት ወደኩኝ ድንግል ነበርኩ ልክ አንተ ለሴቶች ተጠንቀቁ ባልክበት መንገድ ነበር የሸወደኝ 😭😭😭 ምን አለ ቀድሜ ትምህርትን በሰማው😭😭😭😭😭😭😭😭
........በዝሙት የወደኩኝ ቀን ማንም ሰው የሌለበት ቦታ ነበር የቀጠረኝ ብቻችንን ነበርን ረጅም ጊዜ አብረን ካሳለፍን በኋላ ስሜታ መጣ Sex እናድርግ አለኝ እኔም እንቢ አልኩት ከዛ በፍቅር ቃል እወድሻለሁ! ከዚህ በላይ ምን ትፈልጊያለሽ።አገባሻለሁ! በቃ አገባሻለሁ እያለ በጣም ይጮህ ነበረ። ብዙ Bible ክፍል ይጠቅስልኝ ነበረ...እስከዛሬ ሀጢያት ነዉ ሲል የነበረዉን በገዛ አፉ አጠፈዉ አሁን ደሞ እኔና አንቺ በእግዚአብሄር ፊት ባልና ሚስት ሆነን ነዉ የምንታይ በቃ ቃል ከተገባባን ቀን ጀምሮ ይለኝ ነበረ እኔን ለማሳመን የማይጥረዉ ነበር አልነበረም....በኋላም እንቢ ማለቴን ሲያይ ለካ አትወጂኝም ለካ እያስመሰልሽ ነበረ አብረሺኝ የሆንሽዉ እያለ መዉቀስ ጀመረ። ከዛ በቃ አጠመደኝ አታለለኝ ሴቶች ብርቱ ነን እንላለን እንጂ ደካማ ማንነት አለን የሲስን ትምህርት ቀድሜ ብሰማ እድን ነበር😭😭 ከዛ ልጁ አንዴ ጀምሮታል ሞት ቢመጣም ወደ ኋላ አይልም በቃ ከአቅሜ በላይ ሆነብኝ አቃተኝ...እሱ ከባድ ስሜት ዉስጥ ነዉ እኔ ደግሞ በተራዬ ህመም ዉስጥ ገባሁ ድንግል ነበርኩኝና በጣም እየጮህኩ በጣም አመመኝ በጣም። በጣም ዉዝግብ ያለ ስሜት ዉስጥ ገባው ሀጢያት ነዉ እያለ ሲሰብከኝ የነበረ ልጅ አሁን ራሱ በገዛ ፈቃዱ አደረገዉ።ህይወቴን ነበረ የጠላሁት በጣም ምርር ብዬ አለቀስኩ በጣም ተቆጨሁ በጣም ተፀፀትኩ... ለሱ ደስታ እና እርካታ ስል አምላኬን በደልኩት። እሱ ግን ምንም አልመሰለዉም ብዙ ልምድ አለዉ ብዙ ላይፍ አሳልፏል ከዛ ምንም አልመሰለዉም አገልግሎት አለኝ ብሎ ሄዶ መድረክ ላይ ቆሞ አገልግሎ ተመልሶ መጣ።..የመጀመሪያዬ ክብሬን የሰጠሁትን አገባዋለሁ ብዬ አምን ነበርና በቃ ሙሉ ለሙሉ እሱን ለማግባት በብዙ ነገር መዘጋጀት ጀመርኩ...እንዲህ እንዲ እያለ ቀናቶች ሄዱ።ከዛ የሆነቀን ጋብቻዉን ትንሽ እንደሚያዘገየዉ ነገረኝ።ለምን?ብዬ ስጠይቀዉ እግዚአብሄር ሸክም ሰጠኝ አሁን ቸርች ልከፍት ነዉ...የራሴን ጣጣ ልጨርስና ከዛ እንጋባለን አለኝ። እኔም ተስማማሁ። የቤት ኪራይ ልከፍልለትና አንዳንድ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለመግዛት ራሴን አዘጋጀው ለጌታ ስል ሁሉን ተዉኩ አሁን ሙሉ ግዜ አገልጋይ ነኝ ምንም ብር የለኝም ብሎኝ ነበር እና እኔም አምኜበት እና ይሄንን ነገረ ተቀብዬዉ ነበር የገባሁበት። ታሪኩ ብዙ ነዉ ግን ላሳጥርልህና ከዛም ቆየና ደሞ እግዚአብሄር ተናገረኝ አለ እእእ ምን ስለዉ "ከተጋባችሁ ትፋታላችሁ" አለ ስለዛ መለያየት አለብኝ ብሎ አለኝ እኔ ደሞ ከዚህ በፊት በትንቢት ባልሽ ነው ተብዬ ነበር። አደለም በዉኔ በህልሜም አስቤ የማላቀዉ ፈተና ነበረ የገጠመኝ.... በጣም ታመምኩ ለ 1ወር ከ15ቀን ስራ ተዉኪ ሆስፒታል ገባህ ልቤን:-ጨጓራዬን በቃ ሁለ መናዬ በሽተኛ ሆንኩ። በጣም ተሰቃየሁ። ራሴ ላይ ጉዳት ለማድረስ ብዙ ሞከርኩ...ይባስ ደሞ በዚህ ሁላ መከራ ዉስጥ ....በህይወቴ እንዳንቺ አይነት ሴት ገጥሞኝ አያዉቅም ለኔ ያደረግሽዉን ሁሉ እግዚአብሄር ዉለታሽን ይመልስልሽ ሁሌም በልቤ ትኖሪያለሽ ብሎኝ እኔን ለመርሳት ሲል blocked አደረኝ። በቃ ለማዉራት የሚከብድ ስቃይ ተሰቃየሁ እጅግ ልቤ ቆሰለ ሁሉም ጓደኞቼ ይህንን መቀበል አቃታቸዉ እናቴም ልቧ አዘነ ከዛ እንደገና አንድ ነገር ሆነ ልጁ ሚሴጅ ፃፈ አሁንም ይቅር አላልሽኝም ወይ አለ በሆላም ሲያወራኝ በጣም መዉቀስ ጀመረ.. ለሱ ደስታ ስል እኔ ግን በሀዘን እና በጉዳት ለኖርኩባቸዉ ግዜአት ክፍያዉ ይሄ ሆነ። መልሶ እኔን ወቀሰኝ። ከአንቺ ጋር እንዲ እሆናለሁ ብዬ አስቤም አላቅም ነበረ። በሀጢአት ጣልሽኝ አገልግሎቴን ወደ ኋላ አረግሽብኝ...ቢያንስ እንዲህ እንዲህ...ልታረጊ ትችይ ነበረ ያ ነገር እንዳይፈጠር ማረግ ትችይ ነበረ እያለ ይበልጥ በፀፀት አቆሰለኝ።ይህንን ተናግሮኝ ድጋሚ ብሎክ አደረገኝ።.በዚህ ጭንቀት ውስጥ የሲስን ቻናል ሼር ተደረገልኝ ከዛ ቻናሉን ጆይን ብዬ ያለ እንቅልፍ ነበረ የሚነጋልኝ ከዛ በቃ ብዙ voice ማዳመጥ ጀመርኩ ከዛ በጣም ልቤ ተነካ በጣም አለቀስኩ። እንደአጋጣሚ ሁኖ እዛዉ ግሩፕ ላይ አንዱ ልጅ የሲስ ስልክ ያለዉ እባካችሁ ተባበሩኝ ብሎ ሌላዋ ስትልክለት ወዲያዉ ወሰድኩና ስልኩ ላይ ሚሴጅ ፃፍኩለት። በሞት እና ህይወት 1እርምጃ ነበረ የቀረኝ። ከጌታም ጋር ተጣልቻለሁ እንዴት ላወራዉ እንደምችልም አላቅም...በጣም ስለጨነቀኝ የሆነ የሚሰማኝ ሰዉ እፈልግ ነበረ። ሚሴጅ ስፅፍልህ ቆይ እስኪ ጌታ ምን ይለኝ ይሆን አንዴ ልስማዉ ለመጨረሻ ግዜ ብዬ ነበረ..ከዛ ትንቢት ፃፍክልኝ የተናገርከኝ ነገር አስደንግጦኝ ነበረ። "እግዚአብሄርን ከአጠገብሽ ሆኖ አየሁት! በፍቅር አይኑ ሱያይሽ" ነበረ ያልከኝ። በጣም ጮህኩኝ ደሞም ደስም አለኝ። ከዛም የማልረሳዉ ንግግርህ ልቤ ዉስጥ የቀረዉ "የከበረዉ ተዘጋጅቶልሻል ከዚህ በኋላ የተዋረደዉ በህይወትሽ አይፀናም" ብለህ ሚሴጅ ፃፍክልኝ በጣም ነበረ ደስ ያለኝ። በስልክም ደግሞም እንደ ገና ፀለይክልኝ በጣም ተስፋ ያገኘሁት "እየሱስን ከአጠገብሽ አየሁት በፍቅር አይኖቹ ሲያይሽ" ባልከኝ ሰአት ነበረ።.....ተስፍዬ ሁሉ ለመለመ ሁፈይይይ አሁን ጌታ ደርሶልኛል ተመስገን ማለት ጀመርኩ አሁን ህይወቴን ጌታ ቀይሮታል ትምህርትም ስራም ጀምሪያለሁ በሲስ ትምህርት ኢየሱስን አገኘሁት ተቀየርኩ።
🚨በጌታ ፍቅር ታዘዙኝ ....ሰላም ሲሳይ ነኝ ይሄን ታሪክ ያነበባቹ ሁሉ ሴቶች ከሁለት አይነት ወንዶች ተጠንቀቁ የሚለውን ትምህርት ለምታቋቸው ክርስቲያን ሴቶች በየግሩፑ ልቀቁ በግሩፑ እየገባቹ ለማታቋቸው ሴቶች ላኩ ብቻ ለሴቶች ሁሉ ሼር አድርጉ ለምቷቋቸው ሴቶች ሼር እንዲያደርጉ ንገሯቸው ትምህርቱ ከዚህ ፁፍ እላይ አለ
@SisayAzusaRevivall
@SisayAzusaRevivallShow more ...