Add channel
  • Support
Stay updated with our news!
@telemetr_io_bot
Telegram analytics bot

The bot can:

  • analyze channel audience
  • channels intersections
CategoryNot specified
Channel location and language
አላማችን በእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት የተሞላንና የክርስቶስን ኢየሱስን ዳግም ምፅአት በመናፈቅ የሚኖር ትውልድን ማፍራት ነው!! ማራናታ!! ማራናታ!! ማራናታ!! 
1 164-1
~412
~1
35.36%
Telegram general rating
Globally
1 072 747place
of 3 824 617

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

I am sending you 1π! Pi is a new digital currency developed by Stanford PhDs, with over 25 million members worldwide. To claim your Pi, follow this link https://minepi.com/JobYTD and use my username (JobYTD) as your invitation code.
Pi Network
Pi is a new digital currency being developed by a group of Stanford PhDs. For a limited time, you can join the beta to earn Pi and help grow the network.
81
0
Use this new cryptocurrency by downloading the app n filling JobYTD as refferal code...
79
0
Use this new cryptocurrency by downloading the app n filling JobYTD as refferal code...
74
0
I am sending you 1π! Pi is a new digital currency developed by Stanford PhDs, with over 25 million members worldwide. To claim your Pi, follow this link https://minepi.com/JobYTD and use my username (JobYTD) as your invitation code.
Pi Network
Pi is a new digital currency being developed by a group of Stanford PhDs. For a limited time, you can join the beta to earn Pi and help grow the network.
77
0
👩‍🔧👩‍🏫👩‍🔬👩‍💻👀 👀👩‍🔧👩‍🏫👩‍🔬👩‍💻 ========== ራእይ========== 👩‍🔧👩‍🏫👩‍🔬👩‍💻👀 👀👩‍🔧👩‍🏫👩‍🔬👩‍💻 ➡️ ራእይ ማለት 👇👇👇 ✅ እርግጥና ሊመዘኑ የሚችሉ እሴቶችን በመከተል በምንፈፅማቸው ተልእኮዎች የምንደርስበት 'የከበረ ፍፃሜ' ነው። ✅ ነገን በእግዚአብሔር አይን ስናየው የምንመለከተው ምስል ነው። በራእይ የመኖር በረከቶች ✅ አቅርቦት የሞላበት ህይወት እንድንኖር ያደርገናል። ምክንያቱም እግዚአብሔራዊ ለሆነ ራእይ የእግዚአብሔር አቅርቦት ይኖራልና ። ✅ በክብር ውስጥ ያዘልቀናል። ራእይ የክብር መኖሪያ ነውና!!! ✅ ትውልድ ዘለቅ ተፅዕኖ ✅ በሰማይ የክብር ሽልማት ✅ ለሰዎች ሁሉ ሞዴል የሆነ ህይወት ራእይ አልባ ህይወት ➡️ እግዚአብሔራዊ አቅርቦት የለውም!! ➡️ ክብር አልባ ነው። ➡️ በሰማይ ፊት የከሰረ ህይወት ነው። ስለ ራእይ "ያንብቡ ይፀልዩ ያንብቡ" Join Us On 👉👉👉👉👇👇👇 @Hesedd 👀👀👀👀👀👀👀👀👀👀👀👀
Show more ...
608
7
😬😬😬😬😬 ቅናት 😬😬😬😬😬 መንስኤው ፣ መዘዙና መፍትሔው ቅናት ምንድን ነው?? - ለሌሎች ከፍታ ፣ መሳካትና በረከት የሚሰጥ ፅኑ የሆነ ተቃውሞ፣ እውቅና አለመስጠትና እስከ መግደልም የሚያደርስ የጥላቻን መንገድ የሚያስኬድ ክፉ የሰይጣን መሳሪያና መንፈሳዊ ካንሰር ነው!! 👿👿👿 የቅናት መንስኤ 🏃‍♀🏃‍♂🏃‍♀ የውድድር መንፈስ 🏃‍♂🏃‍♀🏃‍♂ ➡️ የማይወዳደር ሰው አይበላለጥምና ሁልግዜ ውድድር ባለበት ሁሉ ስናሸንፍ ትእቢት የተሸነፍን ሲመስለን ደግሞ ቅናት ይጠናወተናል!! 😬😬😬 ♦️ ይህ ውድድር አሸነፍኩም ሆነ ተሸነፍኩም ላሉ ሁሉ ታላቅ ውድቀትን በህይወታቸው ላይ ያመጣል። ➡️ ምክንያቱም የገባንበት መንግሥት ውስጥ ውድድር የሚባል መለያ የለበሱ ተጫዋቾች የሉምና ነው። መንግሥታችን ግን የሚገዛው በውድድር ሳይሆን በትብብር በሚኖር ብቻ ነው። 🤝🤝🤝 የውድድር መንፈስስ እንዴት ሊፀናወተን። 🤔🤔🤔ይችላል? 🤔🤔🤔 ✴️ መንግስታዊ አስተሣሠብን ሳንይዝ ወይም ሳይኖረን ሲቀር 🤯🤯🤯🤯🤯 ይህም:- ♦️ ሁሉ ከርሱ ፣ በርሱ ና ለእርሱ እንደሆነ አለማወቅ ነው። ልብ ይበሉ 🔔🔔እኛም ከእርሱ መንግስትና ከሀሳቡ ጋር ካልሆንን ምንም ነን!!📣📣📣📣 😬😬😬የቅናት መዘዝ🤯🤯🤯 ➡️ በሚቀናው ሰው ልብ ውስጥ ብርቱ የሆነን የሰይጣን ፅኑ ምሽግ እርሱም ነፍሰ - ገዳይነት የሆነ ጥላቻን ያበቅላል። ይህ ወደ ዘላለም ሞት የሚያስጥልን ዘላለማዊ ፍርድ በሰውየው ላይ ያመጣል። በአጭሩ ከክርስቶስ ህይወት የተለየን ተቅበዝባዥ ያደርገናል ። 🙏🙏🙏😇 መፍትሔ 😇🙏🙏🙏 - ቅናት አጥንት ውስጥ ያለ ነቀዝን ይመሰላል። "...፤ ቅንዓት ግን አጥንትን ያነቅዛል። " ምሳ 14:30 ☢ ማንም ሰው በህይወት እያለ አጥንቱ ውስጥ ያለውን ነቀዝ ከውስጡ በማውጣት እራሱን ሊያድን አይችልም። ምክንያቱም አጥንት ከውስጣችን ያለ አካል ነው። ይህም ሰዋዊ በሆነ ምንም አይነት ጥረቶች ውስጣችንን ያለን የቅናት አቅም ማጥፋት እንደማንችል ትልቅ ማሳያና ጠቋሚ ነው። 🚆 ወደ ድል የሚወስደው መንገድ 🚆 -->> ቅናትን ለማጥፋት ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ፣ ማሰላሰልና ማድረግ ነው። ምክንያቱም:- " የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤" (ዕብ 4:12) 🗝 የኛ አጥንት ውስጥ ( ውስጠታችን) መግባት የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነውና ነው። ቃሉ እስኪለይ ድረስ ወይም የእኛን ህመም(ቅናት) መንካት እስከሚጀምርና እስኪፈውሰን ድረስ መታገስ ይገባናል። ይህም ቃሉን በማሰላሰልና በማድረግ መፅናት እንደሚያስፈልግ አመላካች ነው። ስለዚህ አጥንት ውስጥ እንዳለ ነቀዝ የሆነን ቅናት አጥንት (ውስጣችን) ድረስ መግባት በሚችል በጌታ ቃል ብቻ እንገድለዋን ማለት ነው። 👊👊 🤔🤔ለማሰላሰል የሚሆን ቃል🤔🤔 1 ቆሮ 13 1 ዮሐ 4: 8-21 ሮሜ 5:5 🔽🔽 Biblical Teachings 🔽🔽 Join Us on 👉👉👉👉@Hesedd 🗡🗡🗡🗡🗡📖📖🗡🗡🗡🗡🗡
Show more ...
525
7
😴😴ስለ ህልም ምን አይነት 😴😴 አመለካከት አለዎት ?? የእኔን አመለካከት እነሆ!! ✅ ህልም ሰዎች ተኝተው በእንቅልፍ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ በአእምሮአቸው ላይ የሚከፈትና ሊያስታውሱት በሚችል ሁኔታ የሚገለጥ ልዩ አለም ነው። ሶስቱ የህልም ምንጮች 1. እግዚአብሔር እግዚአብሔር አንዱ የህልም ምንጭና ለራሱም የመናገሪያ መንገድ ይሆንለት ዘንድ ህልምን የፈጠረ አምላክ ነው። ✅ ህልምን ከእግዚአብሔር አንፃር ስንመለከተው በመለኮት ዘንድ ለእኛ የታሰበን የትኛውንም ሀሳብ መግለጫ ሆኖ እናገኘዋለን ይህም ሀሳብ ማፅናናት ምክር ፣ምሪት፣ ተግሳፅ፣ምስጢር ሊሆን ይቻላል። " እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ሰው ግን አያስተውለውም። በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ " ኢዮብ 33:14 - 15 2. ሰይጣን ✅ ሰይጣን ሁለተኛው የህልም ምንጭ ነው። ከሰይጣን የሆኑ ህልሞች ግባቸው ሞትና ውርደትን በሰዎች ላይ ማምጣት ሲሆን ከሰይጣን የሆኑ ህልሞች ሰይጣን ለእኛ የሚያስባቸውን ክፉ ሀሳቦች የሚገለጥባቸው ልዩ መንገዶቹ ናቸው። " እናንተ ግን ለባቢሎን ንጉሥ አትገዙም የሚሉአችሁን ነቢያቶቻችሁንና ምዋርተኞቻችሁን፥ ሕልም አላሚዎቻችሁንና ቃላተኞቻችሁን መተተኞቻችሁንም አትስሙ፤" ኤር 27:9 3. ገዢ የሆኑ የግል ሀሳቦቻችን ✅ እነዚህ ገዢ ሀሳቦች በቀን ተቀን ውሎ አዳራችን የምሰራቸው ስራዎች የምናወራቸው ሀሳቦቻችን ሲሆኑ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለቱም ምንጮች ውጪ የህልማችን ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ። " ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል፤ እንዲሁም የሰነፍ ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል። " (መጽሐፈ መክብብ 5:3) እንዴት ከጨለማው የሚወረወሩ🤔🤔 ህልሞችን ለማቆም እንስራ 🤔🤔 1. ለእግዚአብሔር የሚገዛ ንፁህ ህይወትን እናዳብር!! 🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀ 2. የጠላትን ስራ:- በፆምና በፀሎት 😇 እንዲሁም በሀሳብና በተግባር 🤔🤔🤔 በመቃወም!! 🗡🗡🗡🗡🏹🗡🏹🗡🗡🗡🗡 🙏🙏🙏 መልካም አዳር 🙏🙏🙏 Join Us on the Link Below 👇👇👇👇 @Hesedd 👇👇👇👇 @Hesedd 👇👇👇👇 @Hesedd ♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
Show more ...
272
3
ዶክተር ዐቢይ አህመድ አሊ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምክር ቤቱ በመገኘት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
282
0
🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇 🙏🙏 ከሞተ በኃላ ዘሩን ያያል 🙏🙏 " እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።" ኢሳ 53:10 ኢየሱስ እራሱን እንደ ስንዴ ቅንጣት መስሎ ካለሞተችና ካልበሰበች እንደማትበዛ ብቻዋን ደግሞ እንደምትቀር አስተምሯል ። በዚህም ትምህርት ሞት የፍሬና የመብዛት ብቸኛው መንገድ እንደሆነ ይፋ አድርጎታል ። ስለዚህ ማንም ማፍራትንና መብዛትን የሚፈልግ ሁሉ በዚህ መርህ ለመሄድ መጨከን ይኖርበታል። ታላላቆቹ ሀዋሪያቶች በዚሁ መንገድ አልፈው ነበር። [" ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።" ገላ 2:20] ♦️ የዚህን ዘመን የክርስቶስ ዘሮች በዚህ ፅሁፍ መንፈስ ቅዱስ እያደፋፈረ አለ። ልትሞቱና ፍሬ ልታፈሩ ወደ ምትችሉበት አፈር (መስቀል) ጨክናችሁ ውረዱ በዚያ ብቻ ለናንተ ማፍራት የሚሆነው ዝናብ ( መንፈስ ቅዱስ) በሙላት ይገኛል። ሞታችሁ በፍሬያችሁ እልፍ ትውልድ ይነሳ። ታዛችሁ በፍቃዳችሁ ባትሞቱ ግን እናንተ ኖራችሁ እልፍ ትውልድ በውስጣችሁ እስከ ከበረው የእግዚአብሔር አጀንዳ በእናንተ ምክንያት ይሞታል። 💥 በመጨረሻ ሁለት አማራጮችን ጌታ ፊታችን አስቀምጧል እነርሱም :- ➡️ በሞታችን ትውልድ ይነሳ ➡️ ለራሳችን ኖረን ትውልድ ይሙት ዛሬውኑ እንወስን..... 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 " መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም።" ራእ 2:11 "በመንፈሳዊው አለም ትልቁ ድል ነሺ ራሱን ድል የነሳ ነው። " 🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇 Join Here 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd
Show more ...
1 085
3
ጥቂት ስለ እግዚአብሔር ቃል 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 🧒👦🧑👨🧔🧕👮‍♀👴👷‍♂👨‍🏫👨‍🚀👨‍⚖ ➡️ የእግዚአብሔር መገኘት በአንድ ሰው ምን ያህል ነው ? ወይም አንድ ሰው በእግዚአብሔር ሕልውና ምን ያህል ተውጧል ብለን ብንጠይቅ መልሱ ምን ያህል ያ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ተሞልቷል የሚል ይሆናል። ምክንያቱም የቃሉን መገኘት ከቃሉ ባለቤት መገኘት ፈፅሞ መለየት ስለማይቻል ነው። " ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው።" (መዝሙረ ዳዊት 107:20)
408
2

sticker.webp

223
2
Downlaod and fill the survey then when u reach 5000 pts u will be paid..
201
0
Eyob Yewondwossen has invited you to try SagaPoll. Click here to download the app and both you and your friend will get additional points. https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sagaconsumer&referrer=utm_source%3DSagaPollApp%26utm_medium%3DShareLink%26utm_campaign%3DSagaPollApp%26code%3DQD2PX
SagaPoll - Apps on Google Play
SagaPoll is an Africa online survey community that gives you a voice
205
0
☁️☁️የክብር ህይወት ምስጢራት☁️☁️ " እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።" 2ኛ ቆሮ 3:18 ❇️ የሰው ልጅና ፍጥረት 🦅👩‍🎓👱‍♂🌎 በእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ክብር ተፈጥሮአል። 🏃‍♂👴🧓👵🧒👦👩🌎👱‍♀👨‍🏭👨‍🏫👨‍🔬👩‍🚀👨‍✈️🎅🦅🤵🦁👩‍✈️👨‍💼👨‍🔧👨‍🎤👨‍🎓👶 " .... ፥ በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ። " ኢሳ 43:67 ➡️ ይህ በእግዚአብሔር የተፈጠረ ፍጥረት ግን ለሰው ይገዛው ዘንድ ተሰጥቶአልና ሰው ለእግዚአብሔር ክብር መኖር ከቻለ ፍጥረት ሁሉ አብሮ ለእግዚአብሔር ክብር ይሆናል ማለት ነው። እንዴት የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር ክብር 🤔🤔 ይኑር?? 🤔🤔 ✅ የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር ክብር ይኖር ዘንድ በተለይ አማኝ ሁለት ነገሮች እጅግ ያስፈልጉታል። እነርሱም የእግዚአብሔር ቃል መገለጥና የመንፈስ ቅዱስ ሀይል ናቸው። እነዚህ ሁለት ነገሮች የሌሉበት ቦታ ሁሉ መንፈሳዊ ድካምና የሰይጣን ጭቆና ይበረታል። እስኪ ጥቂት ስለ እነዚህ ሁለት መንፈሳዊ ቁልፎች እንመልከት። 💥የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ💥 📖💥💥📖💥📖💥📖💥💥📖 ➡️ የእግዚአብሔር ቃል በህይወታችን መልካሙን መንገድ እንድንሄድ የሚያበራ መብራት ነው። ነገር ግን በህይወታችን ላይ ይህንን የመንገድ ብርሀን መጠቀም የምንችለው የቃሉ ፍቺ ሲያበራልን ብቻ ይሆናል። ለዚህም ነው የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ቀደም ብለን የጠቀስነው። ስለዚህ በየትኛውም መንፈሳዊ Dimension መገለጥ የመንገዳችን ብርሀን ነውና ቃሉን እንዲያበራልን ጌታን መጠየቅ አለብን። ልናውቀው የሚገባው ሌላው ነገር ደግሞ የቃል መገለጥ በቀጥታ የሚገናኘው ከነፍሳችን እንደሆነ ነው። ነፍስ በዋነኛነት በመንፈሳዊው አለም የመገለጥ እውቀት ናፋቂ ናትና። " ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል። " መጽሐፈ ምሳ 19:2 በዚህ ክፍል መፅሀፉ ነፍስ ሊያተርፋትና በመንገዷ እንዳትስት የሚያደርጋትን እውቀት ማጣቷ መልካም እንዳልሆነ ይመሰክራል ይህም እውቀት የመገለጥ እውቀት ነው። ➡️ እግዚአብሔር ሆይ ለሚያምኑ ሁሉ አሁን ቃልን የሚገልጥ የመገለት መንፈስ ይህንን በሚያነቡት ሁሉ ላይ እንዲመጣ በኢየሱስ ስም እፀልያለሁ! አሜን!!🔥🔥 ሀይል /የእግዚአብሔር ሀይል/ ☄☄☄☄☄☄☄☄☄☄☄☄ ሀይል ስራን የመስራት ብቃት ነው። እግዚአብሔር ልጆቹ እርሱን ይመስሉና በቤቱ ስራ ላይ በብቃት እንዲያገለግሉ መንፈሳዊ ሀይልን ይሰጣል። የትኛውም መንፈሳዊ ስራ ያለ ሀይል ፈፅሞ ሊሰሩ አይችሉም። አንድ አማኝም ለእግዚአብሔር ክብር ሊኖር የሚችለው መንፈሳዊው ሀይል አብሮት እስካለ ጊዜ ድረስ ነው። ➡️ መንፈሳዊውን ሀይል እግዚአብሔር የሚሰጠው ለመንፈሳችን ሲሆን ይህም መንፈሳችን በዚህ ሀይል ለነፍሳችን በተገለጠው እውነተኛ እውቀት ለእግዚአብሔር ክብር መኖር እንድንችል ያደርገናል። ✅ ይህም ወደ አንድ መንፈሳዊ መርህ ይወስደናል ይህም:- ለነፍሳችን ➡️ የቃሉ መገለጥ ለመንፈሳችን ➡️ የእግዚአብሔር ሀይል ስንቀበል ወደ በክብር የመገለጥ ህይወት ያመጣናል ማለት ነው። ❌🚷Caution // ጥንቃቄ🚷❌ ♨️ ከሁለቱ አንዱ(የቃሉ መገለጥ ወይም ሀይል ) ሲጎድል መንፈሳዊ ህይወት ከክብር የጎደለና ለክብር የማይሆን ይሆናል። 🙏🙏🙏 መልካም አዳር 🙏🙏🙏 📖📖Biblical Teachings📖📖 Join us on the link Below 👇👇👇👇👇👇👇 @Hesedd @Hesedd @Hesedd 📖🗡📖🗡📖🗡📖🗡📖🗡📖🗡
Show more ...
769
5
ትእግስት 🙏🙏🙏🙏🙏Patience 🔥🔥🔥😢😢😢😢😢😢🔥🔥🔥 በህይወታችን እግዚአብሔር እንዲሰራ ጊዜ የሚሰጠው ነገር ትዕግስት ይባላል። ትዕግስት የሌለው አማኝ እግዚአብሔር በህይወቱ እንዳይሰራ ጊዜ የማይሰጥ አማኝ ነው። ስለዚህ ሁሌም መታገሳችን እግዚአብሔር በህይወታችን ላይ ስራውን ይሰራ ዘንድ ጊዜ መስጠት እንደሆነ አንዘንጋ ። Pls ሊንኩን ለሌሎች በማጋራት ጠቃሚ መልእክቶችን እንዲካፈሉ ያድርጉ ስለ መልካም ትብብራቹ ጌታ ይባርካችሁ!! @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd
472
4
የአዲስ ኪዳን መፅሀፍቶች የተፃፉበት ጊዜ 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 🗡🗡🗡🗡🗡🗡🗡🗡🗡🗡🗡🗡 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨 ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧 ➡️ ማቴዎስ፦በ70-80 ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ ማርቆስ፦በ55-60ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ ሉቃስ፦በ65-70ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ ዮሐንስ ወንጌል፦በ70-90ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ሐዋርያት ሥራ፦በ60-65ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ ሮሜ፦በ55ዓ.ም ተጽፏል!! ➡️ 1ቆሮንቶስ፦በ54ዓ.ም ተጽፏል!! ➡️ 2ቆሮንቶስ፦በ56ዓ.ም ተጽፏል!! ➡️ ገላትያ፦በ48-49ዓ.ም/በ52-56ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ ኤፌሶን፦በ60-61ዓ.ም መካከል ተጽፏም!! ➡️ ፊልጵስዮስ፦በ60-61ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ ቆላስያስ፦በ60-61ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ 1ተሰሎንቄ፦በ50ዓ.ም ተጽፏል!! ➡️ 2ተሰሎንቄ፦በ51ዓ.ም ተጽፏል!! ➡️ 1ጢሞትዮስ፦በ64-65ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ 2ጢሞትዮስ፦በ65-66ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ ቲቶ፦በ62-64ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ ፊልሞና፦በ60-61ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ ዕብራውያን፦በ60-70ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ 1ጴጥሮስ፦በ64ዓ.ም ተጽፏል!! ➡️ 2ጴጥሮስ፦በ65ዓ.ም ተጽፏል!! ➡️ 1ዮሐንስ፦በ90-100ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ 2ዮሐንስ፦በ90-100ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ 3ዮሐንስ፦በ90-100ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ ያዕቆብ፦በ50ዓ.ም ተጽፏል!! ➡️ ይሁዳ፦በ70-75ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! ➡️ የዮሐንስ ራዕይ፦በ90-100ዓ.ም መካከል ተጽፏል!! Share it Pls @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd
Show more ...
291
14

sticker.webp

379
2
😴😴ስለ ህልም ምን አይነት 😴😴 አመለካከት አለዎት ?? የእኔን አመለካከት እነሆ!! ✅ ህልም ሰዎች ተኝተው በእንቅልፍ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ በአእምሮአቸው ላይ የሚከፈትና ሊያስታውሱት በሚችል ሁኔታ የሚገለጥ ልዩ አለም ነው። ሶስቱ የህልም ምንጮች 1. እግዚአብሔር እግዚአብሔር አንዱ የህልም ምንጭና ለራሱም የመናገሪያ መንገድ ይሆንለት ዘንድ ህልምን የፈጠረ አምላክ ነው። ✅ ህልምን ከእግዚአብሔር አንፃር ስንመለከተው በመለኮት ዘንድ ለእኛ የታሰበን የትኛውንም ሀሳብ መግለጫ ሆኖ እናገኘዋለን ይህም ሀሳብ ማፅናናት ምክር ፣ምሪት፣ ተግሳፅ፣ምስጢር ሊሆን ይቻላል። " እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ሰው ግን አያስተውለውም። በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ " ኢዮብ 33:14 - 15 2. ሰይጣን ✅ ሰይጣን ሁለተኛው የህልም ምንጭ ነው። ከሰይጣን የሆኑ ህልሞች ግባቸው ሞትና ውርደትን በሰዎች ላይ ማምጣት ሲሆን ከሰይጣን የሆኑ ህልሞች ሰይጣን ለእኛ የሚያስባቸውን ክፉ ሀሳቦች የሚገለጥባቸው ልዩ መንገዶቹ ናቸው። " እናንተ ግን ለባቢሎን ንጉሥ አትገዙም የሚሉአችሁን ነቢያቶቻችሁንና ምዋርተኞቻችሁን፥ ሕልም አላሚዎቻችሁንና ቃላተኞቻችሁን መተተኞቻችሁንም አትስሙ፤" ኤር 27:9 3. ገዢ የሆኑ የግል ሀሳቦቻችን ✅ እነዚህ ገዢ ሀሳቦች በቀን ተቀን ውሎ አዳራችን የምሰራቸው ስራዎች የምናወራቸው ሀሳቦቻችን ሲሆኑ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለቱም ምንጮች ውጪ የህልማችን ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ። " ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል፤ እንዲሁም የሰነፍ ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል። " (መጽሐፈ መክብብ 5:3) እንዴት ከጨለማው የሚወረወሩ🤔🤔 ህልሞችን ለማቆም እንስራ 🤔🤔 1. ለእግዚአብሔር የሚገዛ ንፁህ ህይወትን እናዳብር!! 🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀ 2. የጠላትን ስራ:- በፆምና በፀሎት 😇 እንዲሁም በሀሳብና በተግባር 🤔🤔🤔 በመቃወም!! 🗡🗡🗡🗡🏹🗡🏹🗡🗡🗡🗡 🙏🙏🙏 መልካም ቀን🙏🙏🙏 Join Us on the Link Below 👇👇👇👇 @Hesedd 👇👇👇👇 @Hesedd 👇👇👇👇 @Hesedd ♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
Show more ...
777
8
ምን ያህል ሞተናል🤔?? 😳😳😳!! 🙏🙏 ይህንን ጥያቄ ሁላችንም ቀጥሎ ከሚሰጠው ማብራሪያ በኃላ 🙏🙏🙏 እንድንመልሰው ይሁን!! 🙏🙏🙏🙏🙏 👨‍⚕ በህክምናው ሳይንስ ዶክተሮች ከአንዳንድ ከባድ አደጋ የተረፉ ሰዎችን የጉዳት መጠን ከሚያውቁበት መንገድ አንዱ የተጎዳው ሰው ለተጎዳበት ቦታ 🤕 ንክኪ የሚሰጠው ምላሽ ነው 😭😬። ይህም ሰውየው የተጎዳበት ቦታ ሲነካ በህመም ስሜት ውስጥ መሆኑ የቦታው የጉደት መጠን በቦታው ላይ ሞትን አለማስከተሉን ሲያሳይ ምንም አይነት የህመም ስሜት ካልተሰማው ደግሞ በቦታው ላይ ጉዳቱ ሞት እንዳስከተለ እንዲረዱ ያደርጋቸዋል። ስለዚህም ዶክተሮቹ ቦታው ሌላውን የአካል ክፍል በማበስበስ እንዳይገለው ተቆርጦ እንዲወጣ በማድረግ መፍትሔ ይሰጣሉ። ➡️ ይህንን እውነታ ወደ ግል ህይወታችን እንመልሰውና ህዝብ ሲፈናቀል ፣ ሀጥአት መድረክ ላይ ሲወጣ ፣ፅድቅና እውነት 📖 ሲደበቁ ፣ፍቅር ሲቀዘቅዝ፣ እምነት ሲጠፋ እያየን ነው። ግን ግን ስንቶቻችን ነን ይህ ቤተክርስቲያን ⛪️ ላይ ያለ ጉዳት አሞን ከላይ የጠቀስኳቸው ነገሮች ሲሆኑ 🤕 የህመም ጩከትን 🤕😰 የምንጮከውና እንፈወስ ዘንድ ከጌታ ዘንድ ረድኤትን 🤲 የምንጠይቀው?? ሰቆ ኤር 5÷17 - 21 ➡️ እውነቱ ግን ብዙዎቻችን በክርስቶስ አካል ላይ ያለና እየሆነ ያለ ጉዳት ወደ ማይሰማን ደረጃ ላይ ደርሰናል። ይህም ደግሞ የግል መንፈሳዊ ህይወታችን ምን አይነት የጉዳት መጠን ላይ እንዳለ🤕🤕 ያሳያል ። በርግጥም ደግሞ በሞት አፋፍ ላይ ነን ። ኦ ጌታ ሆይ ፤መልሰን ማረን ፤ ተዋርደናል፤ መንፈሳዊ እርዛት ታርዘናል፤ በጠቅላላው የማንጠቅም ሆነናል😢😥! ♦️ ጌታ ደግሞ ስራውን ይሰራ ዘንድ ህያዋንን ይፈልጋልና [ ጌታ ህያው ስለሆነ ከህያዋንና ከነቁት ጋር ብቻ ስለሚሰራ ] ሀሜት ፣ጥላቻ፣ ዝሙት፣ መገፋፋት፣ መለያየትን ትተን በክርስቶስ ፍቅር እንፈወስና ለእግዚአብሔር ክብር እንሆን ዘንድ ዛሬ ከእንቅልፋችን እንንቃ። 🙏🙏🙏ቀኑ ቀርቧል🙏🙏🙏 " ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።" ሮሜ 13:11 " መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። " ራእ 3:22 "መልካም ምሽት " "Biblical Teachings" መልእክቱን ከወደዱት ለሌሎች ያጋሩ 👍 JOIN US 👉👉👉👉👇👇👇👇 @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd
Show more ...
474
6
👀 🧠🧠 አእምሮን ማደስ 🧠🧠 👀 ይህን ሀሳብ ሳነሳ አንድ በልጅነቴ የሰማውት ውሀ የጠማት ወፍ ታሪክ ትዝ አለኝ ። ወፏ በጥም ተቃጥላ ውሀ እየፈለገች ሳለ መጠኑ ከፍ ባለ እቃ ውስጥ ጥቂት ውሀ ታገኛለች ነገር ግን የምትደርስበት አይደለምና በጥም ከመሞቷ በፊት በቀራት አቅምና ጊዜ ጠጠሮችን በእቃው ውስጥ በመጨመር ይህንኑም ነገር የውሀው መጠን ጨምሮ ለመጠጣት ቅርብ እስኪሆን ድረስ ባላት አቅምና ጊዜ የጊዜውን ወሳኝ ስራ በመከወን ጥሟን ቆርጣ ለሞት የቀረበ ህይወቷን አትርፋለች ። የመንፈስ ቅዱስ አብርሆት ፣ የእግዚአብሔር ቃል ፣ የቅዱሳን ህብረት ሁሉና የመሳሰሉት የማይገባን እውቀትና ልምምድ ከውስጣችን በማስወጣት አእምሮአችንን እንድናድስ ከእግዚአብሔር የተሰጠን አቅም ቢሆንም ለሰይጣን ክስና ለቀኑ ክፋት ጊዜን ሰጥተን ማገልገል ብንችል እንኳ ( ባልታደሰ አእምሮ ማገልገል የተለመደ እየሆነ ነውና) የምናድሰው አእምሮና ህይወት ግን አይኖርም እንደ ብልኋ ወፍ የተሰጠንን አቅም መልካሙ ፍሬ እንዲያፈራ በማነፅ ክፉውን ደግሞ ከስሩ በመንቀል እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚያስብና የሚኖር አዕምሮን እንጎናፀፍ መልእክቴ ነው። 😊😊😊😊😊😊 👍 የድል ቀን ይሁንልን 👍 @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd
Show more ...
529
4
ቅንነት.. .. ቅንነት .. ስለ እግዚአብሔር.. . ስለ ሰውና ስለ ራሳችን ትክክለኛ የሆነ ( መፅሀፍ ቅዱሳዊ የሆነን እውቀት ከመያዛችን የተነሳ የሚኖረን የከበረ ማንነት ሲሆን ቅንነት የክርስቶስ ልብና እግዚአብሔር ሁሉን የሚያይበት አይኑ ነው። ይህ ቅንነት ባለበት ሰው ጠላቶቹ የሚያደርጉትን አያውቁም ለማለት.... ሲያሳድዱት ለመፀለይ... ሲረግሙት ለመመረቅ ቀላል ይሆንለታል... ስለ ጠላቶቹ ሰዎች የሚያውቀው እውቀት ይህን እንዲያደርግ ብቻ ይፈቅድለታልና... ዛሬ ነገሮችን በክርስቶስ ልብ ለምን ማስተናገድ አቃተን.. .. ለክፉ ... ክፉ .. ለመልካም መልካም አንዳንዴም ለመልካም ሳይቀር ክፉ መመለሳችን ለምን ይሆን... ውስጣችን የክርስቶስ ልብ እንዳይገለጥ ያደረገው ይህ ቅን ያልሆነ ጠማማ ወይም ክርስቶሳዊ ያልሆነ እውቀት ነው። ይህን ካልኩኝ ዘንዳ ነገርን ሁሉ በክርስቶስ ( በተለይ ሰውን ) ብቻ ማወቅ ለመራራትም ሆነ በእግዚአብሔራዊው እውቀት ለመራመድ ወሳኝ ነውና የእውቀታችን ሚዛን ክርስቶስ ይሁን እያልኩ መልካም ቀን እመኛለሁ 😊😊 ከወደዱት ያጋሩት ይቀላቀሉን @Hesedd @Hesedd
Show more ...
188
1

AnimatedSticker.tgs

279
2

AnimatedSticker.tgs

250
1
“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።” መዝሙር 65፥11 🌼🌻Happy New Year🌻🌼 @Hesedd @Hesedd @Hesedd
168
1

4_6037381003377379028.mp4

211
4

mp4.mp4

174
2
173
2
ትንሽ መቀበል ወይንስ ትንሽ 🤔መስጠት 🤔 🔥 ሰይጣን ጥቂት ሰጥቶ ብዙ ይቀበለናል !!! 💦 ኢየሱስ ጥቂት ሰጥተነው ብዙ ይመልስልናል !!! ስለዚህ ከሚቀበል (ከሰይጣን) ይልቅ የሚሰጥ (ለእግዚአብሔር) የተባረከ ነው !!! Join Us 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Hesedd @Hesedd @Hesedd
438
3
😳 እናንተ ደካሞች ማለት የሚችል ብርቱው ጌታ ብቻ ነው። ይህ ጥሪ ለአለም ህዝብ ሁሉ ቢሆንም ወደ እርሱ የሚመጣ ብቻ ግን ያርፋል ። እንግዲህ ያረፍን እረፍታችን ወደ እርሱ መጥተን እንደነበር ማረጋገጫ ነው። አሁን ከሸክም ጋር አይደለንም። 😄 ነገር ግን 🤔 አሁንም ሸክም ያለበት የህይወት ክፍል ካለ የትናንቱ ጌታ ዛሬም ወደ እኔ ኑ እያለ ነውና ወደ እርሱ ሄደን እንረፍ መልዕክቴ ነው። " ወደ እርሱ እንሂድ እርሱም ያሳርፈናል " ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ መልካም ምሽት @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd
422
3
🧶🧷🧷🧶መርፌው እና ክሩ🧶🧷🧷 ➳መርፌና ክር በጣም የተቃረኑ ናቸው።ነገር ግን በጣም የተዋደዱና የተፈላለጉ ናቸው።ክሩ ልፍስፍስ በራሱ እንኳ መቆም የማይችል ጥሶ ለማለፍ የማይሞክር ነው።🧶🧶🧶🧶 🧷🧷🧷መርፌው ላይ ሲታሰር ግን ውስብስቡን መንገድ እየጣሰ፤ከፊት ያለውን እየወጋ በመጨረሻ ብቅ ይላል። 🧶🧷መርፌው ብቅ ሲል የታዘለችው ክርም እንደጎበዝ ብቅ ትላለች ።ደካማዋ ክር ከመርፌው ጋር በመታሰርዋ አለመቻልዋ መቻል አግኝቶ የተቀደደውን ትሰለፋለች ፤የተበተነውን ትሰበስባለች ። 🙄🙄🙄 ልክ እንደ ክሩ እኛም ደካሞች ፣ሳንጀምር የሚደክመን ልፍስፍሶች፣ውስብስቡን መንገድ መጓዝ የማይቻለን መንገድ ቀሪዎች ነን ። በክርስቶስ ላይ ስንታሰር ግን እንፀናለን🏋️‍♂️🏋🏻‍♀️ጥሰን የምንወጣ ከፊታችን ያለውን ሁሉ የማንፈራ ፣ የማንችለውን ዉስብስብ መንገድ በመርፌው ጀርባ ላይ ሆነን ብቅ እንላለን ። ፡፡፡፡ዋናው አለመቻላችን አይደለም፣በሚችለው ጌታ ላይ በእምነት መታሰራችን ነው ። ።።።።።።ዲያቆን አሸናፊ እንደፃፈው ።።። ከ @maranatatube የተወሰደ መልካም ቀን Join Us 👇👇👇👇👇👇 @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd
Show more ...
414
7
1⃣1⃣1⃣ መንፈሳዊ ልህቀት 1⃣1⃣1⃣ ♦ 1.ምን ማለት ነው ?? ♦ 2.ለምን አስፈለገ ?? ♦ 3. እንዴት በልህቀት እንኑር ?? 1. ልህቀት ምንድን ነው ?? ልህቀት:- ማለት መብለጥ ፣ ማሸነፍ ፣ የበላይ መሆን ፣ መግዛት ወ.ዘ.ተ ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ከበለጠው ፣ ካሸነፈው ፣ የበላይ ከሆነው ፣ ከገዛው የሚበልጥ ማንም የለም ማለት ነው። ቀለል አድርጎ ለመረዳት ልክ በተማሪዎች ውጤት አሰጣጥ መሰረት ከ Excellent የሚበልጥ ውጤት እንደሌለ ሁሉ አንድ ሰው በሆነ የተለየ መለኪያ ልህቀት አለው ማለት ልህቀት ባገኘበት መለኪያ ከዚያ ሰው የተሻለ የለም ማለት ነው። ሁሉም ከዚያ ሰው በታች ናቸው። ይገዛሉ ተበልጠዋልና !! ♦ የዚህ ልህቀት ምንጭ ከሁሉ በሁሉ የላቀው እግዚአብሔር ነው። ማንም እርሱን ተጠግቶና አብሮት ኖሮ ልህቀት ውስጡ ያልገባበት ከቶ የለም !! ✴️ በአዲሱ ኪዳን የልህቀት በር ዳግም መወለድ ሲሆን ይህም ደግሞ ሰው የክርስቶስ ኢየሱስን ጌትነት በተቀበለ ጊዜ እውን የሚሆን ነው። ሰው ዳግም ሲወለድ ለልህቀት ይወለዳል ። ☢ ምክንያቱም ከሁሉ በላይ ከላቀው ጌታ ተወልዷልና !! ይህም ልህቀቱ በኑሮ ሲተረጎም በሀጥያት ... በሰይጣን 👹 ... በዚህ አለም እንዲሁም በአለሙ ስርአት ላይ የሆነ የበላይነት... ገዢነትና ድል መንሳት ሆኖ ይገለጣል ። ስለሆነም ይህ ልህቀትን የሚኖር አማኝ በሚሄድበት ቦታ ሁሉ ከላይ የተጠቀሱት ሀይላት ይገዛሉ ይህም ደግሞ ስራቸው በመፍረሱና 🔥 በመሸነፋቸው በግልፅ የሚታይ ይሆናል። ስናጠቃልለው ልህቀት ኑሮ ሲሆን ይህም ከኑሮዎች ሁሉ የሚበልጠውና እጅግ በጣም ጥሩ የሆነው ኑሮ በዚህ ኑሮ እግዚአብሔር ክብሩን ይገልጣል። በዚህ ኑሮ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴና ስራ በተግባርና በግልጥ ይታያል። ልህቀት ኑሮ ነው። ለዚያውም እውነተኛ የክብር ኑሮ !! 2. ለምን ልህቀት አስፈለገ ?? ✝ ልህቀት ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት እግዚአብሔርን ለመግለጥና ልዕልናውን በይፋ ለማሳየት ነው !! ልህቀት በሌለበት ቦታ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ በክብር አይገለጥም ። እርሱ ባልተገለጠበት ቦታ ሁሉ ደግሞ ሰይጣን እጅግ ተመችቶትና መንግስቱን መስርቶ በግልጥ ይገዛል ። ስለሆነም እግዚአብሔርና መንግስቱ 🕎 የመንግስቱም ሁሉን መግዛት ( ልዕልና ) ይገለጡ ዘንድ ልህቀት ግድ ነው። 3. እንዴት በልህቀት እንኑር ?? 💡መጀመሪያ ላይ እንደገለፅኩት ልህቀት ኑሮ እንደሆነ ሁሉ መንፈስም እንደሆነ ማወቅ ጥበብ ነው። ዳን 6:3 "3 Then this Daniel was preferred above the presidents and princes, because an excellent spirit [was] in him; and the king thought to set him over the whole realm." (Daniel 6:3) 💦💦💦🔥🔥💦💦🔥🔥💦💦💦 🕊 በዚህ ክፍል የልህቀት መንፈስ ተብሎ ሊተረጎም የሚገባው ክፍል መልካም መንፈስ ተብሎ ተተርጉሟል ። ይህ ብዙ የሚያስከፋ ባይሆንም ሙሉ የመፅሀፉን ሀሳብ ለማስተላለፍ ግን ትንሽ አስቸጋሪ ይሆናል ። ✴️ ቀደም ብዬ የጠቀስኩት የልህቀት ኑሮ ከልህቀት መንፈስ ሊነጠል ፈፅሞ አይችልም። በእግዚአብሔር ቃል 📜 የተገለጠውን የልህቀት ህይወት ( ኑሮ) በቃሉ 📜 መንፈስ ካልሆነ በቀር ለመኖር ማሰብ ሞኝነትና ከንቱ ምኞት 😞😞😞 የማይቀመስም ነው በቃሉ የተገለጠውን ህይወት በቃሉ መንፈስ መኖር የግድ ይላል። ቃሉ ህይወት መንፈስም ነውና። ስለሆነም ሁልጊዜ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለ ብርቱ መንፈሳዊ ቁርኝትና 🤝🤝🤝 ለእግዚአብሔር የተሰጠ ማንነት በልቀት እያደጉ ለመሄድና በሀይልም ለመገለጥ መሰረት ናቸው። ነገር ግን አንድን ነገር ልናውቅ ይገባል ይህም ነገር ሁሉ ሙሉ ሀይሉ በአንድ ጊዜ አይገለጥም። ይህም ልክ ከብርሀን ሀይልና ተፅእኖው ጋር ይመሳሰላል.. ... ሙሉቀን እስኪሆን እየተጨመረ ይሄዳል .. ልህቀትም ሙሉ ክብሩ ይገለጥ ዘንድ ወደ ሙላቱ እየተጨመረ ይሄዳል። .. ይቀጥላል.. ከወደዱት ለሌሎች 10 ሰዎች ያጋሩት 😘😁" Biblical Teachings "😁😘 👍 Join Us 👍 @Hesedd @Hesedd @Hesedd👈 👉@Hesedd @Hesedd @Hesedd
Show more ...
489
6

file

211
0
“ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤” ሮሜ 12፥11 @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd
199
0

sticker.webp

170
0

sticker.webp

155
0
" አንዲት ነገር " ... 🤔 ✈️ እግዚአብሔርን ብዙ ነገር ጠይቀን እናውቃለን ስለ ብዙ ነገር አስበንም 🤔 እንደምናውቅ እሙን ነው .... 🤔🤔ነገር ግን ምን ይሆን ከጥያቄዎቻችን ሁሉ ነጥሮ የወጣው ጥያቄ .. ?? 🏃 ዳዊት ጌታን እልፍ ጥያቄዎች የጠየቀ ቢሆንም አንዱ ጥያቄ ከሁሉ ይልቅ እየተደጋገመና የሁልጊዜው ነበር ይህም " ክብርህን አይ ዘንድ ፣ ህልውናህ ... መንፈስህን ... " የሚል ነበር ... “እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።” መዝሙር 27፥4 😇 ጌታን በተደጋጋሚ የምንጠይቀው እርሱ ነገር ሌላውን ሁሉ አስቀርቶ አንድ ነገርን ብቻ እንደጠየቅን ይቆጠራልና የህይወታችንን አቅጣጫ የሚወስን ይሆናል.. 😳😳😳😳😳😳😳😳😳😳 ከፀሎታችን ሁሉ የሚደጋገመው አንዱ ፀሎት ... እርሱ " አንዲት ነገር " ነው ። 💡እግዚአብሔር ደስ 😁 የሚያሰኘው ነገር እርሱ ራሱን የሁልጊዜ ጥያቄ ስናደርገው ነው። ይህን መጠየቅም ጌታ ከጥያቄዎች ሁሉ ደስ የሚያሰኘው ጥያቄ ነውና ሌሎች ያልጠየቅናቸውንና ያልፈለግንልቸውን በረከቶች ያስገኝልናል ። ❤️ሰናይና ብሩክ ቀን❤️ @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd @Hesedd
Show more ...
494
5
ብታምኑም ባታምኑም.. .. ብታምኑ ካሁኑ በነገ ድል ምስጋናና ደስታን ትሞላላቹ ባታምኑ ደግሞ በነገው ሰርፕራይዝ ከድንጋጤ ጋር ደስታን ብትሞሉም ትናንት በእምነት አለመደሰታቹና አለማመስገናቹ ይቆጫችኃል... የእምነት ትሩፏት ይለዋል ይሄ ነው... ነገሩ እንደዚ ነው... የጠላት ሴራ የእግዚአብሔርን ስራ እንዲገለጥ ከማድረግ ውጪ ሌላ ስራ የለውም... ስለዚህ ሴራ ሲበዛባቹ ምስጋናን አብዙ ብዙ የእግዚአብሔር ስራ ከፊታችን ነውና... @Hesedd @Hesedd @Hesedd
547
4
ይቅርታ ማለት በሁለት አካላት መካከል ጥል የፈጠረን የጥል መዝገብ በመዝጋት አዲስ የፍቅርና የተስፋን መዝገብ በፍቃዳችን መክፈት ነው። ከሁለቱ አንደኛው ቢጎድል ይቅርታው ጎዶሎ ፍሬውም ጎምዛዛ ይሆናል።
628
8

mp4.mp4

323
2
ምን ያህሎቻችን ዘመንን የምንመረምር ወቅትንም ጠንቅቀን የምናውቅ ይሆን ?? 🤔 ወቅትን ማወቅ ዘርፈ ብዙ ጥቅምን የሚያስገኝ የከበረ ሀብት - እድሜ በከንቱ እንዳይበላ ብርቱ መጠበቂያ - ገንዘብን በትክክል ለመዋሉ መለኪያ ቱንቢ - የህይወትን አላማ ጠንቅቆ ለማየት የሚጠቅም አጉሊ መነፅር ነው። " እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።"(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 12:32) @Hesedd @Hesedd @Hesedd
910
2
⏩⏩ SPIRITUAL MATURITY⏪⏪ 🔥መንፈስ ቅዱስና መንፈሳዊ ብስለት🔥 ✅ በህይወት ለመኖሩ የሚያስፈልገውን የሚያውቅ ሰው " አዋቂ" ወይም የበሰለ ነው ተብሎ እንደሚጠራ በመንፈሳዊው ህይወትም ለመኖር በእጅጉ የሚያስፈልገውን የሚያውቅ ሰው የበሰለ ነው ተብሎ ይጠራል። ይህም ሰው የሚያስፈልገውን የሚያውቅና ይህንም ለማግኘት የቱንም አይነት ዋጋ ለመክፈል የቆረጠ ነው። ይህ ለአማኙ በህይወት መኖር እጅግ የሚያስፈልገውና መገኘቱም ደግሞ ለምንኖረው ኑሮ ዋነኛ የሆነው እርሱ "መንፈስ ቅዱስ" ነው። እርሱ እንደሚያስፈልገን ማወቅ የብስለት መጀመሪያ ሲሆን እለት እለት በእርሱ መሞላት ደግሞ የብስለት መንገድ ነው። ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ አስፈላጊነትን ያልተረዳና የእርሱን ሙላት በህይወቱ የማይፈልግ ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ህይወቱ የሚያስፈልገውን ዩማያውቅ በክርስቶስም ህፃን የሆነ ሰው ነው። ይህ ሰው ትልቅ ስም ያለው ፣ ታዋቂ አገልጋይ ፣ የቤተክርስቲያን መሪም ሊሆን ይችላል ። ነገር ግን ይህን ሁሉ መሆኑ የመንፈስ ቅዱስን ቦታ አይተካለትምና ህፃንነቱ ከእርሱ አይሻርም። " መንፈስ ቅዱስን እንጠማለን!! " 👉👉👉👉 Biblical Teachings Join Us on➡️➡️➡️ @Hesedd
Show more ...
828
5
ቅንነት.. .. ቅንነት .. ስለ እግዚአብሔር.. . ስለ ሰውና ስለ ራሳችን ትክክለኛ የሆነ ( መፅሀፍ ቅዱሳዊ የሆነን እውቀት ከመያዛችን የተነሳ የሚኖረን የከበረ ማንነት ሲሆን ቅንነት የክርስቶስ ልብና እግዚአብሔር ሁሉን የሚያይበት አይኑ ነው። ይህ ቅንነት ባለበት ሰው ጠላቶቹ የሚያደርጉትን አያውቁም ለማለት.... ሲያሳድዱት ለመፀለይ... ሲረግሙት ለመመረቅ ቀላል ይሆንለታል... ስለ ጠላቶቹ ሰዎች የሚያውቀው እውቀት ይህን እንዲያደርግ ብቻ ይፈቅድለታልና... ዛሬ ነገሮችን በክርስቶስ ልብ ለምን ማስተናገድ አቃተን.. .. ለክፉ ... ክፉ .. ለመልካም መልካም አንዳንዴም ለመልካም ሳይቀር ክፉ መመለሳችን ለምን ይሆን... ውስጣችን የክርስቶስ ልብ እንዳይገለጥ ያደረገው ይህ ቅን ያልሆነ ጠማማ ወይም ክርስቶሳዊ ያልሆነ እውቀት ነው። ይህን ካልኩኝ ዘንዳ ነገርን ሁሉ በክርስቶስ ( በተለይ ሰውን ) ብቻ ማወቅ ለመራራትም ሆነ በእግዚአብሔራዊው እውቀት ለመራመድ ወሳኝ ነውና የእውቀታችን ሚዛን ክርስቶስ ይሁን እያልኩ መልካም ቀን እመኛለሁ 😊😊 ከወደዱት ያጋሩት ይቀላቀሉን @Hesedd @Hesedd
Show more ...
782
8
🙏🙏የእግዚዘብሔር ደስታና ሀዘን🙏🙏 የክርስቶስ ልብ ❤️ ልብ የሀሳብ ምንጭ የነገሮች ሁሉ መጀመሪያና የህይወትም ማዕከል ናት ። በመፅሀፍ ቅዱስ ብዙ አይነት ልቦችን ተገልጠው እናያለን ። ጠቅለል ባለ ሁኔታ ስናየው በምድር ላይ ሁለት አይነት ልቦችን እናገኛለን። እነርሱም የክርስቶስና የዲያብሎስ ልብ ናቸው። እንደየቅደም ተከተላቸው በአዲሱ ሰውና በአሮጌው ሰው ወይም በእውነተኛው መንፈሳዊው ሰውና እንደዛ ባልሆነው ሰው እነዚህን ልቦች እናገኛቸዋለን ። እግዚአብሔር ምንጊዜም አይኖቹ ወደ ሰው ልጆች ልብ ይመለከታሉ ስለሆነም ይህን ተከትሎ እለት ተእለት የሚያየውን ልብ ተከትሎ ሁለት ነገሮችን ምንጊዜም ልቡ እንደሚያስተናግድ ለማወቅ የሚያከብድ አይሆንም ። ይህም የልጁን ልብ በማየቱ የሆነ ታላቅ ደስታና ምንም እርሱ ሰውን ቢፈጥር እንኳን በውስጡ በሚያየው የእርሱ ባልሆነ የዲያብሎስ ልብ ምክንያቱ የሚያስተናግደው መሪር ሀዘን ናቸው። እግዚአብሔር አምላክ የልጁ ለሆነው መልካም ልብ የወሰነው ታላቅ ክብርና በረከትን ሲሆን እንዲህ ላልሆነውና እርሱን ለሚቃወመው ልብ ሁሉ ግን ቁጣው ታላቅና ፍርዱም አስፈሪ ነው ይህም የዘላለም እሳትና ጥፋት ነው። የክርስቶስ ልብ በብሉይ ኪዳን ዘመን በነበሩ የተለዩ ቅዱሳኖች ተገልጦ ታይቷል ይህም መንፈስ ቅዱስ በህይወታቸው ላይ ከመገኘቱና የፅድቅን የህይወት መንገድ ከመምራቱ የተነሳ የሆነ ነው። መንፈስ ቅዱስ በምድር በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ እንደ ፍቃደኝነታቸው የክርስቶስን ልብ ያስተምራቸዋል ። ይህ ልብ ትምህርቱ ሲሆን አስተማሪውም መንፈስ ቅዱስ ነው። በትክክል ይህን ልብ የተማሩ ( ክርስቶስን ማለቱም ልቡን የተማሩ ) እርሱን ይመስላሉ። እግዚአብሔር ክርስቶስ ወይም እርሱን( ኢየሱስን ) የሚመስሉ ሁሉ እንደ ልቡ ናቸው። አይኖቹ ወደ እነርሱ ጆሮዎቹ ወደ ጩከታቸው የፀሎታቸውም መልስ የሚቸኩል ነው። ኢየሱስ ጌታ ነው !! 😃መልካም ቀን😃 @Hesedd ።።። @Hesedd @Hesedd ።።። @Hesedd
Show more ...
818
6
🙏🙏የእግዚዘብሔር ደስታና ሀዘን🙏🙏 የክርስቶስ ልብ ❤️ ልብ የሀሳብ ምንጭ የነገሮች ሁሉ መጀመሪያና የህይወትም ማዕከል ናት ። በመፅሀፍ ቅዱስ ብዙ አይነት ልቦችን ተገልጠው እናያለን ። ጠቅለል ባለ ሁኔታ ስናየው በምድር ላይ ሁለት አይነት ልቦችን እናገኛለን። እነርሱም የክርስቶስና የዲያብሎስ ልብ ናቸው። እንደየቅደም ተከተላቸው በአዲሱ ሰውና በአሮጌው ሰው ወይም በእውነተኛው መንፈሳዊው ሰውና እንደዛ ባልሆነው ሰው እነዚህን ልቦች እናገኛቸዋለን ። እግዚአብሔር ምንጊዜም አይኖቹ ወደ ሰው ልጆች ልብ ይመለከታሉ ስለሆነም ይህን ተከትሎ እለት ተእለት የሚያየውን ልብ ተከትሎ ሁለት ነገሮችን ምንጊዜም ልቡ እንደሚያስተናግድ ለማወቅ የሚያከብድ አይሆንም ። ይህም የልጁን ልብ በማየቱ የሆነ ታላቅ ደስታና ምንም እርሱ ሰውን ቢፈጥር እንኳን በውስጡ በሚያየው የእርሱ ባልሆነ የዲያብሎስ ልብ ምክንያቱ የሚያስተናግደው መሪር ሀዘን ናቸው። እግዚአብሔር አምላክ የልጁ ለሆነው መልካም ልብ የወሰነው ታላቅ ክብርና በረከትን ሲሆን እንዲህ ላልሆነውና እርሱን ለሚቃወመው ልብ ሁሉ ግን ቁጣው ታላቅና ፍርዱም አስፈሪ ነው ይህም የዘላለም እሳትና ጥፋት ነው። የክርስቶስ ልብ በብሉይ ኪዳን ዘመን በነበሩ የተለዩ ቅዱሳኖች ተገልጦ ታይቷል ይህም መንፈስ ቅዱስ በህይወታቸው ላይ ከመገኘቱና የፅድቅን የህይወት መንገድ ከመምራቱ የተነሳ የሆነ ነው። መንፈስ ቅዱስ በምድር በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ እንደ ፍቃደኝነታቸው የክርስቶስን ልብ ያስተምራቸዋል ። ይህ ልብ ትምህርቱ ሲሆን አስተማሪውም መንፈስ ቅዱስ ነው። በትክክል ይህን ልብ የተማሩ ( ክርስቶስን ማለቱም ልቡን የተማሩ ) እርሱን ይመስላሉ። እግዚአብሔር ክርስቶስ ወይም እርሱን( ኢየሱስን ) የሚመስሉ ሁሉ እንደ ልቡ ናቸው። አይኖቹ ወደ እነርሱ ጆሮዎቹ ወደ ጩከታቸው የፀሎታቸውም መልስ የሚቸኩል ነው። ኢየሱስ ጌታ ነው !! 😃መልካም ቀን😃 @Hesedd ።።። @Hesedd @Hesedd ።።። @Hesedd
Show more ...
1
0
🤔እግዚአብሔርን መምሰል ይቻላል?😳 እንዴት ?? " የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።ውን(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:2-3) ♦️ እግዚአብሔርን መምሰል ይቻላል። ➡️ ይህም ደግሞ እርሱን ለመምሰል የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ስለሰጠን ነው ። ይህም እግዚአብሔር ሳይዘራ እንደሚያጭደው ሳይበትን እንደሚሰበስበው ሰው ክፉ ስላልሆነ ነው። እግዚአብሔር ምንም ነገርን እንደ ፍሬ ከመጠየቁ በፊት ቀድሞ እንደ ዘር ሰጥቶናልና ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን መምሰል ይቻላል ብዬ ደፍሬ መናገር እችላለው። ባይቻል ኖሮ ቀድሞ በተናገረን ነበር ነገር ግን እውነት የሆነው ቃል ይህ ይቻላልና መምሰል ትችላላችሁ ለዛም ይሆን ዘንድ የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶናል ይላል ስለዚህ የተሰጠንን የከበረ ነገር በመገለጥ እውቀት እያወቅን በህይወታችን የልጁ የኢየሱስ መልክ በህይወታችን ይገለጥ ስል ሀሳቤን በዚህ እቋጫለው። “የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።” 2ኛ ጴጥሮስ 1፥2-3 🙏 🌝 መልካም ቀን 🌝 🙏 ➡️➡️ ከወደደዱት ለሌሎች ያጋሩ ⬅️⬅️ " Biblical Teachings " @Hesedd @Hesedd @Hesedd
Show more ...
317
2
ከበጉ ( ከክርስቶስ ) የሆነ ማፅናናት እንደማያቆስል ( ደስታን እንደሚሰጥ ) ሁሉ ከበጉ የሆነ መግረዝ ያደማል ያቆስልላል ( ያሳዝናል ) ነገር ግን ይህ ወደ ህይወት ይመራል ... ከበጉ ያልሆነ ማፅናናትም ( ደስታ ያለው የሚመስል) ሆነ መግረዝ ( ህይወትን ማጥፋት) ግን መጨረሻው ወደ ሞት ነው... ለምን ይሆን ግን መፅናናትን ከኢየሱስ ይልቅ ከሌላው የምንከጅለው ለምንስ ይሆን በጌታ እጅ ለመገረዝ አሻፈረኝ የምንለው.. .... አስተዋይ መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል !!! @Hesedd @Hesedd @Hesedd
462
2
302
0
የእግዚአብሔር ቃል በህይወታችን ላይ ብንዘራው ምርጥ ዘር ፤ ከሄድንበት መልካም መንገድ ፤ ብናበላው የተመረጠ ማዕድ ፤ ብንጠጣው አርኪና ጥም ቆራጭ ነው። ቃሉ ከማር ወለላ ይልቅ ይጣፍጣል @Hesedd @Hesedd @Hesedd
502
2
571
1
Last updated: 27.11.21
Privacy Policy