cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethio Scholars Info

Scholarships, call for papers, grants, projects, job vacancies, etc For any comment @ethiolbot

Show more
Advertising posts
4 056Subscribers
No data24 hours
-87 days
-4630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 18 መምህራኑ እንደጠፉበት አስታወቀ ጠፉ የተባሉት መምህራን የሶስተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን በመማር ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል:: ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ላይ ለነበሩ መምህራን ያላግባብ ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር እንደከፈለ እና ተመላሽ እንዳላደረገ ተገልጿል:: አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 18 መምህራኑ ደብዛቸው እንደጠፉበት አስታወቀ፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኦዲት ግኝት ሪፖርት ላይ መክሯል፡፡ የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር  እና የዩኒቨርሲቲው አመራር አባላት በጋራ ባደረጉት ውይይት ላይ እንደተገለጸው ለሶስተኛ ድግሪ በሚል ለትምህርት የተላኩ እና የጠፉ የዩንቨርሲቲው መምህራን ጉዳይ ዋነኛው ነው፡፡ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ እና የፌደራል ዋና ኦዲተር አመራሮች ዩኒቨርሲቲው ለሶስተኛ ድግሪ ትምህርት ብሎ ስፖንሰር ሆኖ የላካቸው መምህራን በወቅቱ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዳልተመለሱ፣ ዩንቨርሲቲውም ለነዚህ መምህራን የከፈለውን ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር ገንዘብ ለምን ተመላሽ አላደረክም? በሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ 18 መምህራን ትምህርታቸውን በተቀመጠላቸው ጊዜ አጠናቀው እንዳልተመለሱ፣ የመመለሻ ጊዜያቸውም እንዳለፈ መናገራቸውን በምክር ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ በተላለፈው ላይ የቀጥታ ስርጭት ላይ ሲናገሩ ተደምጧል፡፡ በዩንቨርሲቲው ህግ መሰረት አንድ የዶክትሬት ወይም የሶስተኛ ድግሪ ትምህርትን ለማጠናቀቅ አራት ዓመት በቂ ሲሆን በተለያዩ አስቸጋሪ ምክንያቶች ትምህርቱን ማጠናቀቅ ላልቻሉ ደግሞ ሁለት ዓመት እንዲጨመርላቸው ይፈቅዳል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል፡፡ ይሁንና እነዚህ የዶክትሬት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተላኩ መምህራን መካከል ትምህርታቸውን በስድስት ዓመታት ውስጥ አጠናቀው ባለመምጣታቸው ከስራ መባረራቸው ተገልጿል፡፡ እነዚህ የቀድሞ የዩንቨርሲቲው መምህራን ከስራ በመባረራቸው ምክንያት ለትምህርት ስፖንሰር፣ ደመወዝ እና ትራንስፖርት ወጪ የወሰዱትን ገንዘብ ማስመለስ አለመቻሉን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ከ18ቱ ውስጥ አምስቱ ከሀገር ውጪ መሆናቸውን በማረጋገጣችን ዋሶቻቸው ላይ ክስ መስርተን ውሳኔው ለእኛ ተወስኖልናል ማስመለስ እንጀምራለን ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም 15ቱ ቀሪ የቀድሞ መምህራን ግን በሀገር ውስጥ እንዳሉ እና የትኛውም ተቋም እንዳልተቀጠሩ አረጋግጠናል ነገር ግን ከደመወዛቸው እና ስራቸው ስላገድናቸው ገንዘቡን ተመላሽ ማድረግ አልቻልንም ሲሉ ለጥያቄው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ #አልአይን @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
👍 4😁 1
አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ 18 መምህራኑ እንደጠፉበት አስታወቀ ጠፉ የተባሉት መምህራን የሶስተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን በመማር ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል:: ዩንቨርሲቲው በትምህርት ላይ ለነበሩ መምህራን ያላግባብ ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር እንደከፈለ እና ተመላሽ እንዳላደረገ ተገልጿል:: አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ 18 መምህራኑ ደብዛቸው እንደጠፉበት አስታወቀ፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኦዲት ግኝት ሪፖርት ላይ መክሯል፡፡ የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር  እና የዩንቨርሲቲው አመራር አባላት በጋራ ባደረጉት ውይይት ላይ እንደተገለጸው ለሶስተኛ ድግሪ በሚል ለትምህርት የተላኩ እና የጠፉ የዩንቨርሲቲው መምህራን ጉዳይ ዋነኛው ነው፡፡ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ እና የፌደራል ዋና ኦዲተር አመራሮች ዩንቨርሲቲው ለሶስተኛ ድግሪ ትምህርት ብሎ ስፖንሰር ሆኖ የላካቸው መምህራን በወቅቱ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዳልተመለሱ፣ ዩንቨርሲቲውም ለነዚህ መምህራን የከፈለውን ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር ገንዘብ ለምን ተመላሽ አላደረክም? በሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ 18 መምህራን ትምህርታቸውን በተቀመጠላቸው ጊዜ አጠናቀው እንዳልተመለሱ፣ የመመለሻ ጊዜያቸውም እንዳለፈ መናገራቸውን በምክር ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ በተላለፈው ላይ የቀጥታ ስርጭት ላይ ሲናገሩ ተደምጧል፡፡ በዩንቨርሲቲው ህግ መሰረት አንድ የዶክትሬት ወይም የሶስተኛ ድግሪ ትምህርትን ለማጠናቀቅ አራት ዓመት በቂ ሲሆን በተለያዩ አስቸጋሪ ምክንያቶች ትምህርቱን ማጠናቀቅ ላልቻሉ ደግሞ ሁለት ዓመት እንዲጨመርላቸው ይፈቅዳል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል፡፡ ይሁንና እነዚህ የዶክትሬት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በተለያዩ ዩንቨርሲቲዎች ከተላኩ መምህራን መካከል ትምህርታቸውን በስድስት ዓመታት ውስጥ አጠናቀው ባለመምጣታቸው ከስራ መባረራቸው ተገልጿል፡፡ እነዚህ የቀድሞ የዩንቨርሲቲው መምህራን ከስራ በመባረራቸው ምክንያት ለትምህርት ስፖንሰር፣ ደመወዝ እና ትራንስፖርት ወጪ የወሰዱትን ገንዘብ ማስመለስ አለመቻሉን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ከ18ቱ ውስጥ አምስቱ ከሀገር ውጪ መሆናቸውን በማረጋገጣችን ዋሶቻቸው ላይ ክስ መስርተን ውሳኔው ለእኛ ተወስኖልናል ማስመለስ እንጀምራለን ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም 15ቱ ቀሪ የቀድሞ መምህራን ግን በሀገር ውስጥ እንዳሉ እና የትኛውም ተቋም እንዳልተቀጠሩ አረጋግጠናል ነገር ግን ከደመወዛቸው እና ስራቸው ስላገድናቸው ገንዘቡን ተመላሽ ማድረግ አልቻልንም ሲሉ ለጥያቄው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ #አልአይን @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
#BahirDarUniversity ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለዘጠኝ ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል። የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ምሁራኑ በየመስኳቸው የነበራቸውን ልዩ አበርክቶ በመገምገም የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷቸዋል። የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ምሁራን፦ 1. ሙሉጌታ አድማሱ ደለለ (Bio Systems Engineering) 2. ታምራት ተስፋዬ ይመር (Biorefinery Engineering) 3. አስማማው ጣሰው ወልዴ (Animal Production) 4. መላኩ አለማየሁ ወርቄ (Horticulture) 5. የሻምበል መኩሪያው ቸከኮል (Animal Nutrition) 6. አቻምየለህ ጋሹ አዳም (Land Governance) 7. ምርኩዝ አበራ አድማሱ (Plant Pathology) 8. ታደሠ መለሠ መራዊ (Curriculum and Instruction) 9. አስራት ዳኘው ከልካይ (Curriculum and Instruction) ቦርዱ የምሁራኑን የማስተማር ሥራ፣ የምርምር ተሳትፎ፣ የማህበረሰብ አገልግሎት እና በተቋማዊ ጉዳይ ያላቸውን አስተዋፆ በመገምገም የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማፅደቁን ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያሳያል።
Show all...
👍 7
Do you enjoy reading this channel? Perhaps you have thought about placing ads on it? To do this, follow three simple steps: 1) Sign up: https://telega.io/c/ethio_lecturers 2) Top up the balance in a convenient way 3) Create an advertising post If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.
Show all...
Advertising in the Telegram channel «Ethio Scholars Info» from 3.60 - Telega.io

Advertising in the telegram channel Ethio Scholars Info with a guarantee of placement! Telegram channel «@ethio_lecturers». Category: Education. Subscribers: 4075. Cost of advertising publication: $3.60.

የሚዘርፉን ሰዎች እንደ አራዳ መቁጠርና ማድነቅ እየተለመደ ነው ንግድ ባንክ በሌቦች ተጭበርብሮ፥ ወይም የኦንላይን ቅጽሩ ተሰብሮ ከሆነ ብዙ አይገርምም፤ እጅግ ታላላቅ የሚባሉ የአለም ተቋማት ሳይቀር እንዲህ አይነት አደጋ አጋጥሟቸው ያውቃል፤ እዚህ ሰፈር፥ ንቁ ዘበኛ ቢኖሮ እዚያ ማዶ ደግሞ የበለጠ ንቁ ሌባ ይኖራል፤ እያንዳንዱ ጽኑ በር ፥ ብርቱ መስበርያ አለው፤” ብርቅ አይደለም፤ ወደፊት በሌሎች ባንኮች ላይ ተመሳሳይ ነገር መፈጸሙ አይቀርም፤ በግሌ ያስገረመኝ ሌላ ነገር ነው፤ ስለዝርፍያው የተሰጠው ማህበራዊ ምላሽ እጅን ባፍ ብቻ ሳይሆን በጆሮም ያስጭናል፤ አብዛኛው ማህበራዊ ሚድያ ላይ ያለው መንፈስ ፥በቀልድም ቢሆን ሌቦችን የሚደግፍ ነው፤ ጨዋታ ቢሆንም የጨዋታው አቅጣጫ ያሳስባል፤ የሆነ ማህበራዊ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፤ የበሽታው መነሾ ምን ይሆን? የኔ ግምቶች እኒህ ናቸው፤ ሀ) “ ሰርቶ መብላት” የሚባለው ነገር ለብዙ ሰው ፥ለብዙ ሰው የትም የማያደርስ የዳገት መንገድ ሆኖበታል፤ ድሮ ‘ ያልሰራ አይብላ” የሚባል መፈክር ነበር፤ አሁን የሰራም የማይበላበት የኢኮኖሚ ጣቢያ ላይ ደርሰናል ፤ ለመኖር መስረቅ፥ ማጭበርበር ፥ መቆመር ወይም የሎተሪ እድለኛ መሆን ብቻ ነው የሚያዋጣው ‘ የሚል መንፈስ ነግሷል፤ ስለዚህ ውስጥ ውስጡን ፥ የሚዘርፉ ሰዎች እንደ አራዳ መቁጠር፥ ማድነቅ እየተለመደ ነው፤ ለ) ገዥዎችን እና ሀገረ መንግስትቱን ለያይቶ ማየት አለመቻል ሌላው ችግር ይመስለኛል ፤ ዋና ዋና የሀገር ተቋማትን እንደ ራስ መቁጠር እየቀረ ነው፤ ብዙዎቻችን፥ እኒህ ትልልቅ ተቋማት ቢወድሙ ወይም ቢዳከሙ ፥ የማታ የማታ፥ ጦሱ ለሁላችንም እንደሚተርፍ አናውቅም፤ ወይም ለማወቅ አንፈልግም፤ ሐ) የሕግ ተቋማት እና የጸጥታ ተቋማት ፥ የመንግስትን መዋቅር ተጠግተው የሚዘርፉ ሰዎችን ለመቅጣት ያላቸው ቸልተኝነት ወይም አቅመቢስነት ያሳስባል፤ መንግስት የሚደራጀው በዋናነት የዜጎችን ሕይወት እና በላባቸው ያፈሩትን ንብረት ለመጠበቅ ነው፤ አሁን አሁን፥ ኢትዮጵያ ፥ ትልልቅ ቀማኞች፥ እንኳን ቅጣት ግልምጫ ሳያገኛቸው፥ እንደ ልብ እየፋነኑ እሚኖሩባት አገር ሆናለች፤ ሕገ-ወጥነት አትራፊ ከሆነ ሁሉም የሕገ-ወጥነት ተቋዳሽ ለመሆን መጣሩ አይቀርም:: በእውቀቱ ስዩም @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
👍 1
" ከቀን ወደ ቀን እየተበባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ለጤና ባለሙያዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል " - የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ፕሬዚዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ያነሰ ትኩረት ምክንያት ብዙዎች የሚወዱትን የሙያ ዘርፍ በመልቀቅ፣ በመቀየር እንዲሁም አገር ጥለው በመውጣት ላይ ይገኛሉ " ብለዋል። እንዲህ የሆኑት ምን ያህል የጤና ባለሙያዎች ናቸው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ዮናታን፣ " በቁጥር ይህ ነው ብዬ ባልገልጽም በonline apply እያደረጉ ብዙ ጤና ባለሙያዎች፦ - ነርሶች፣ - ሀኪሞች፣ - ሚድዋይፎች፣ - ጤና መኮነኖች በተለያዩ መንገዶች አገር ጥለው እየወጡ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። " ወደ ፊላንድ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳ በህጋዊም በህገ ወጥም መንገድ ብዙ ጤና ባለሙያዎች ከአገር እየለቀቁ ነው። ብዙ የጤና ባለሙያዎች የህክምና ሙያቸውን ጥለው ወደ ንግድ እንዲሁም ወደ ተለያዩ ዘርፎች እየቀየሩ እንደሆነ ብዙ ተጨባጭ መረጃዎች አሉን። በየቀኑ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ቅሬታዎችን የምንቀበልበት አካሄድ አለን " ሲሉ አክለዋል። “ ጤና ባለሙያዎች ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ወደ ዩንቨርስቲ የሚቀላቀሉ ቢሆኑም በተቃራኒው ግን በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች ሆነው ይገኛሉ " ነው ያሉት አቶ ዮናታን።   በሥራ ላይ ያሉትም፣ " ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ የመብት ጥያቄዎችን ለመንግሥት ቢያቀርቡም እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ አለመሰጠቱ በባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል " ያሉት የማኀበሩ ፕሬዚዳንት፣ ቅሬታዎቹን እንዲጠቅሱ ሲጠየቁም፣ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ የጤና ባለሙያዎች ለመንግሥት ያቀረቧቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች፦ * የደሞዝ ማሸሻያ፣  * የነፃ ህክምና፣ * የHouse allowance፣ * የRisk /ተጋለሠጭነት / * የቤት፣ * የትርፍ ስሃት ክፍያ ጥያቄዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ " በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ የመብት ጥያቄዎችን ማቅረብ እንደ ነውር ሊታይ አይገባም። የሰላማዊ ድምፆች ሊደመጡ ይገባል " ብለዋል። " ከቀን ወደ ቀን እየተበባሰ የሚገኘዉ የኑሮ ውድነት  ለጤና ባለሙያዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል" ብለው፣" መንግሥት በጤና ስርዓቱ ላይ የሚከተለውን ፓሊስ ቆም ብሎ ሊመረምረው ይገባል። የቱንም ያክል የዘመነ እና የረቀቀ የጤና ፓሊሲ ቢኖር ጤና ባለሙያዎችን መሠረት ያላደረገ ፓሊሲ ምንም ያክል እርቀት አይሄድም፣ የታቀደውንም ውጤት አያመጣም " ሲሉ አስገንዝበዋል። “ መሠረታዊ ፍላጎቱን ማሟላት የማይችል ጤና ባለሙያ ለታካሚዎች ተገቢዉን ህክምና ይሰጣል ብሎ ማሰብ በፍፁም አይቻልም። መንግስት በጤና ባለሙያዎች ላይ እየደረሱ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እና የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችን ችላ ከማለት ወጥቶ በአገር ላይ የከፋ ችግር ከማስከተላቸው በፊት መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ ጥሪን አቀርባለሁ ” በማለት አሳስበዋል። በሌላ በኩል ፤ " የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ችግሮች አሉ። የእኛም ማኀበር ይህን በተመለከተ በመግለጫ ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ ጠይቋል። ችግሩ ግን መፍትሄ አላገኘም አሁንም ብዙ ቅሬታዎች አሉ " ብለዋል። መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው። tikvah
Show all...
👍 10😁 1
የጅማ ዩኒቨርስቲ መምህሩ የ 2 ሚሊዮን ብር እድለኛ ሆኑ የጅማ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አብዮት ታከለ በቆረጡት 20ኛው ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ2ኛው ዕጣ የ2,000,000 ብር ዕድለኛ መሆናቸዉን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ መምህር አብዮት የረዥም ጊዜ የሎተሪ ደንበኛ ሲሆኑ ደግመው ደጋግመው በላኩት ቴክስት በ2ኛው እጣ የ2 ሚሊዮን ብር እድለኛ አድርጓቸዋል፡፡ መምህሩ በደረሳቸውም ገንዘብ የቢዝነስ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ እንደሚሰማሩ ገልጸዋል፡፡ @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
👍 5👏 2
የስራ ባህላችን ሲፈተሽ አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር እንደነገረኝ ከሆነ ከ7 አመት በፊት ተጨማሪ ተጓዳኝ ስራ ልጀምር ብዬ ዲሽ መግጠም ጀመርኩ አለ። ታዲያ በሰዓቱ የገጠመኝ ነገር ይገርማል አለኝ። ምን መሰለህ የስራ ባህላችን እጅግ መቀየር አለበት! የስራ ባልደረቦቼ ሳይቀሩ አንተ እኮ ይህን ስራ መስራት የለብህም ምን ሆነህ ነው ይሉኝ ነበር። ለአንተ ይሄ አይመጥንህም ተው አታሰድበን እስከ ማለት ደርሰውም ነበር። አንድ ቀን ደግሞ እንዲሁ ተደውሎልኝ ስሄድ የተማሪዎቼ ቤት ኖሯል ከዚያማ ከላይ ወጥቼ እየሰራሁ ቲቹ ነው እኮ እየሰራ ያለው ደሞዙ አንሶት ነው አሁን ይህን የሚሰራ ሲሉ ሰማዋቸው። ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰፈር የሚያውቀኝ ሰው አንተ መምህርም አይደለህ ለምንድን ነው ከአቧራ ጋር የምትታገለው አሁን የመምህር ደሞዝ አልበቃህ ብሎህ ነው ሲል የዲሽ ጥገናውን እንዳቆም አሳስቦኝ ነበር። ብቻ ምን መሰለህ ትንሽ ስራ ስትጀምር የሚተችህ መብዛቱ አለኝ! እና አሁን የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ከፍቼ ጥሩ የሚባል ስራ እየሰራሁ እገኛለሁ በመምህርነቱም እየሰራሁ ነው ።  ያው እንደምታውቀው ቅርብ ጊዜ ኑሮው እጅግ በመናሩ ብዙ መምህራን ጓደኞቼ ሲቸገሩ አያለሁ እኔ ግን ብዙ ጫና ቻል አድርጌ በመስራቴ ኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም ችያለሁ ። ሳጠቃልልህ የስራ ባህላችን በጣም መስተካከል አለበት። የሚሰራን ሰው ለማደናቀፍ  የሚደረጉ ብዙ ጥረቶች አሉ። ቢቻል ብናበረታታው ካልተቻለ ደግሞ ዝም ብን ሲል GA ሃሳቡን አጠቃሏል ። እናንተስ ምን ትላላችሁ? @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
👏 11😁 1
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!