ኢየሱስ ያለው የዘላለም ሕይወት
አለው።
ይህ በአዲስ ኪዳን በብዛት የተጠቀሰው ህይወት. በግሪኩ.
#ZOE #
Greek: ζωή
Transliteration: zōḗ የመለኮት ሕይወት , የዘላለም ሕይወት ማለት ነው።
የመለኮት ሕይወት በክርስቶስ ለሚያምኑት ሁሉ በፀጋው የተሰጠ እና የሚበዛ ነው ዮሐ 10፡10
ስለዚህ በብዙ ሐይማኖቶች እንደሚታመነው
👉የዘላለም ሕይወት ማለት ዝም ብሎ ያለማቋረጥ መኖር፥መኖር፥መኖር .....ማለት አይደለም።
👉የዘላለም ሕይወት ወደፊት የሚመጣ ወይም ወደ ፊት የምናገኘው ነገር አይደለም።
👉 የዘላለም ሕይወት ማንነት ነው።እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደዚህ የሚል ቃል እናገኛለን።
" ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት
#ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።"
(የዮሐንስ ወንጌል 14:6)
ኢየሱስ እርሱ ራሱ ሕይወት እንደሆነ ተናግሯል።የዘላለም ሕይወት ፍለጋ ወደ ሐይማኖት ቦታ መሔድ የለብንም። የዘላለም ሕይወት የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ነው እርሱም ራሱ ኢየሱስ ነው። ሮሜ 6:23
የዘላለም ሕይወት የዛሬ 2000 አመት በዚች ምድር ላይ 33 አመት የኖረ ነው። የዘላለም ሕይወት የሆነው ኢየሱስም ታይቷል፥ ሲናገር ተሰምቷል፥ ተዳሷል።
" ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው
#የነበረውንና #የሰማነውን በዓይኖቻችንም
#ያየነውን #የተመለከትነውንም እጆቻችንም
#የዳሰሱትን እናወራለን፤"
(1ዮሐ 1:1)
እግዚአብሔር የዘላለም ሕይወትን በነፃ ሰጥቶናል።ይህ ሕይወት ያለው ደግሞ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ወስጥ ነው።እኛ ደግሞ ኢየሱስ ስላለን የዘላለም ሕይወት አለን ማለት ነው።
እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
Show more ...