Add channel
  • Support
Stay updated with our news!
The best auto-posting service

Do you want the same buttons under the posts?

Channel location and language
ሰላም ለኢትዮጵያ! እንኳን ደና መጡ። የህ ፈጣን መረጃዎችን ከታማኝ ምንጮች ብቻ የምታገኙበት ነው።  @EthiopiaReporter  "ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ" • ጠቆማዎን ይስጡን ➥  @EthiopiaReporterbot  
Show more
70 061-100
~4 623
~7
6.58%
Telegram general rating
Globally
19 522place
of 3 421 135
22place
of 901
In category
154place
of 2 507

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

1
0
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ውስኪ ማምረት ጀመረ! ብሔራዊ አልኮልና አረቄፋብሪካ፣ ብሔራዊ ብላክ ዲር ውስኪ (National Black Deer Whisky) የተሰኘ አዲስ ምርት ከነሐሴ ወር 2013 ጀምሮ ማምረት መጀመሩን ለአዲስ ማለዳ አሳውቋል። ብሔራዊ ብላክ ዲር ውስኪ ሌሎች ዓለም ዐቀፍ ታዋቂ የውስኪ ምርቶች የሚያሟሉትን መስፈርት ያሟላ በመሆኑ የአልኮል መጠኑ በተመሳሳይ 40 በመቶ መሆኑ ተገልጿል። @EthiopiaReporter
1
0

file

file

1
0
°በየትኛውም መልኩ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገባን ኀይል ኢትዮጵያ አትታገሰም° አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ76ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በኒዮርክ ንግግር አድርገዋል፡፡ ሀገሬ ከሶስት ዓመታት በፊት ለውጥ በማድረግ ለዴሞክራሲ፣ ለሰው ልማት፣ ሰብዓዊ መብት እና ቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ ለተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ፍላጎቶች ላላቸው ቡድኖች የውይይት እና የአንድነት በር እንዲከፈት አድርጋለች ብለዋል፡፡ በዚህም አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል ያሉት አቶ ደመቀ መኮንን ሪፎርሙ ያለፈተና አልተከናወነም ሲሉ ለጉባዔተኛው አብራርተዋል፡፡ በዚህ ሂደት ጥቅሜ ተነካብኝ ያለው ወንጀለኛው ቡድን የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን ከጀርባው ካጠቃው እና በርካታ ጥፋት ካጠፋ በኋል መንግስት ህግን ለማስከበር እና ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ እርምጃ ወስዷል፡፡ መንግስት የሰብአዊ ድጋፍ ሲያደረግ ቡድኑ ድጋፉ እንዲደናቀፍ እና የዜጎች ስቃይ እንዲበረታ አደርጓል፡፡ በውሸት ፕሮፖጋንዳ የተካነው ቡድን በርካታ አፍራሽ ተግባራትን ፈጽሟል፡፡ የውሸት ክስተቶችን አስተጋብቷል፤ ቀድሞ በተዘጋጅ ስም የመጣፋት ዝንባሌ ከፍተኛ ዘመቻ አድርጓል፡፡ ሕዝባችን ካለበት ችግር አንጻር በቂ ነው ባይባለም መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ መንግስታዊ ግዴታውን ለመወጣት በመስራት እና የተፈጸሙ ወንጀሎች እንዲመረመሩ እንዲሁም እርምጃዎች እንዲወሰዱ አደርጓል ብለዋል አቶ ደመቀ መኮንን፡፡ የጥፋት ቡድኑ በሚከፍላቸው የፕሮፖጋንዳ ሚዲያዎች አማክኝነት እና በተሳሳተ የፖሊሲ አተያይ የውጭ ፖሊሲ መርህ ሲጣስ ተስተውሏል ያሉት አቶ ደመቀ መርሆች መከበርም አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል። ተጨማሪ፦ telegra.ph/NewYork-09-26-2 @EthiopiaReporter
Show more ...
927
0
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ለአሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን አሳወቀ፡፡ በዚህም መሰረት፦ •ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤ •ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ፤ • ከቦሌ መድሃኒያለም፤ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ፤ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ፤ • ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት አካባቢ፤ • ከፒያሣ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ በቸርችር ጎዳና ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፤ • ከተክለ ሃይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤ • ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤ • ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኢምግሬሽን የኋላ በር መግቢያ፤ • ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤ • ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደፉል ውኋ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት አካባቢ ፤ • ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የመወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ፤ • ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ፤ • ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለጦር አካባቢ የሚዘጉ መንገዶች ሲሆኑ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ መሆኑን አሳዉቋል፡፡ ደመራው ከሚደመርበት መስቀል አደባባይ እና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ስታዲዬም እንዲሁም ከሃራምቤ ሆቴል ወደ ሴንጅ ዮሴፍ የሚያቋርጠው መስቀለኛ መንገዱ ለበዓሉ በሚደረገው ዝግጅት ምክንያት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ ተደርጓል፡፡ ከሳሪስ እና ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ከባድ ተሸከርካሪዎች መንገዱ አጎና ሲኒማ ጋር የሚዘጋ ይሆናል። @EthiopiaReporter
Show more ...
267
0
1
0
1
0
መሰከረም 16/2014 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በዓል ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ ከዚህ በታች የተገለፁትን መንገዶች ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ከአ/አ ፖሊስ ማሳሰቢያ ተላፍሏል። የሚዘጉት መንገዶች፦ • ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤ • ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ፤ • ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፤ • ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችር ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ፤ • ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤ • ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤ • ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኢምግሬሽን የኋላ በር መግቢያ፤ • ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤ • ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደፉል ውኋ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት ፤ • ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የመወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ • ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ • ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ ናቸው። ስንት ሰዓት ነው የሚዘጋው? ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ሁሉ ዝግ ነው። #ሌላው፦ ደመራው የሚደመርበት መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ስታዲዬም እንዲሁም ከሃራምቤ ሆቴል ወደ ሴንጅ ዮሴፍ የሚያቋርጠው መስቀለኛ መንገዱ ለበዓሉ በሚደረገው ዝግጅት ምክንያት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ የሚደረግ ይሆናል። በተጨማሪም ከሳሪስ እና ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ከባድ ተሸከርካሪዎች መንገዱ አጎና ሲኒማ ጋር የሚዘጋ ይሆናል፡፡ #ሼር ያድርጉት ! @EthiopiaReporter
Show more ...
1
0
አቶ ደመቀ ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ! ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ። ውይይቱ በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ባለው ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንደነበር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያግዙ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እንዲሁም ለተጎጂዎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ይበልጥ እንዲመቻች ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በህዳሴ ግድብ ዙሪያም በአፍሪካ ሕብረት ማዕቀፍ የተጀመረው ድርድር በመግባባት መንፈስ እንዲቀጥል ጠይቀው በዚህ ረገድ ተመድ የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡ @EthiopiaReporter
160
0
3 006
4
የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ዛሬ አርብ ይፋ ሆኗል። የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ከነሀሴ 10 - 14/2013 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከዛሬ መስከረም 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ አሳውቋል። በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላቸው ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ፦ - በስልክ ቁጥር (011) 827-5936/37 በመደወል ወይም - በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማሩበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል። በሌላ በኩል ጤና ሚኒስቴር የቀጣዩ ፈተና ምዝገባ በቅርብ ቀናት የሚካሄድ መሆኑን አሳውቋል። ምዝገባው ለአዲስም ሆነ ነባር ተመዛኞች ሙሉ ለሙሉ online የሚካሄድ ሲሆን ተመዛኞች ይህንን አውቀው ዝግጅት እንዲያደርጉም አሳስቧል። የግል የትምህርት ተቋማት ተመዛኞች ለፈተናው ለመመዝገብ የትምህርት ማስረጃዎቻቸው ህጋዊነቱን ማረጋገጥ (Authenticate) ማስደረግ ይጠበቅባቸዋል የተባለ ሲሆን ከምዝገባው በፊት በዚህ መልክ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፋል። @EthiopiaReporter
Show more ...
3 037
2
ሀገራችን ኢትዮጵያ ተጨማሪ 40 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 40 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,468 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,352 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 813 ሰዎች በፅኑ ታመዋል። @EthiopiaReporter
2 609
2
የኦሮሚያ ክልል አዲስ መንግስት ነገ ይመሰረታል። ነገ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤውን የሚያካሄድ ሲሆን አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይመሰረታል። በነገው ጉባኤ ነባር የጨፌው አባላት ይሸናሉ፤ አዲሶቹ ደግሞ ይተካሉ ፤ አዲሱ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ጨምሮ አዲስ የካቢኔ አባላት ይሰየማሉ። በሌሎች ክልሎች አዲስ መንግስት መች ይመሰረታል? • የደቡብ ክልል መንግስት ምስረታ - መስከረም 19 ቀን 2014 ዓ/ም • የአማራ ክልል መንግስት ምስረታ - መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ/ም • የጋምቤላ ክልል መንግስት ምስረታ - መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ/ም • የሲዳማ ክልል መንግስት ምስረታ - መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ/ም • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታ - መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ/ም • የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታ - መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ/ም ይከናወናል። @EthiopiaReporter
Show more ...
2 568
4
" የዚህ ዓመት የሥራ ፈጠራ ወቅታዊ ሁኔታን በማገናዘብ ለየት ባለ ሁኔታ ይካሄዳል " - የኢፌዲሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የኢፌዲሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የዚህ ዓመት የሥራ ፈጠራ ወቅታዊ ሁኔታን በማገናዘብ ለየት ባለ ሁኔታ ይካሄዳል አለ። ይህን ያለው ለሁለት ቀናት በተካሄደ የፌዴራልና የክልል ሥራ ዕድል ፈጠራ አካላት የጋራ መድረክ የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ መድረክ ላይ ነው። የኢፌዲሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ባለፈው ዓመት የታቀደውን 3 ሚሊዮን የሥራ ዕድል የመፍጠር ዕቅድ ማሳካት መቻሉን አስታውሰዋል፡፡ አቶ ንጉሱ ቀጣዩ ሥራ ከዓመታዊ ዕቅድ ለ3 ሚሊዮን ዜጎች ሥራ ዕድል ከማመቻቸት ባሻገር በጦርነት እና በግጭት ምክንያት የወደሙ ኢንተርፕራይዞችን ከመደገፍ አኳያ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ከ43 ሺህ በላይ ዜጎች የተመለሱ በመሆኑ ዕቅዱን በመከለስ በድጋሚ መታቀዱን አሳውቀዋል። በዚሁ መድረክ በአማራ ክልል ምክትል ር/ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ ፥ በተለያዩ ግጭቶች ከ18 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች በመውደማቸው በዚህ ዓምት የሚሰራው የሥራ ፈጠራ ሥራ ከሌላው ጊዜ ይለያል ሲሉ ገልፀዋል። https://telegra.ph/Job-Creation-Commission-09-24 @EthiopiaReporter
Show more ...
2 867
1
ኢሰመኮ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ የሚገኙ ሲቪል ሰዎች ለደህንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው የሚሳስብ ነው ብሏል። በዚሁ ወረዳ ቦቃ ቀበሌ መስከረም 7 እና 8 /2014 ዓ/ም በደረሱ ሶስት ተያያዥ ጥቃቶች በአጠቃላይ 18 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። መስከረም 8 ቀን 2014 ደግሞ በውልማይ ቀበሌ በተፈፀመ ሌላ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ከነዋሪዎች ሪፖርት እንደደረሰው አሳውቋል። በኪራሙ ወረዳ ባለው አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች ተፈናቅለው በኖሌ ቀበሌ ፣ በሀሮ እና ኪራሙ ከተሞች ተጠልለው የሚገኙ ከ40 ሺ በላይ ነዋሪዎች ለወራት አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታና ሌሎች ድጋፎች ባለማግኘታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ነዋሪዎቹ እንሰገለፁለት ኢሰመኮ አሳውቋል። በአሁን ወቅት ኪራሙ ወረዳን ከቡሬና ነቀምቴ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ዋና ዋና መንገዶች ለተሸከርካሪ እንቅስቃሴ ተዘግተው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ አረጋግጫለሁ ብሏል። ኢሰመኮ የፌዴራል እና የክልሉ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በኪራሙ ወረዳ ላለው የፀጥታ ስጋት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እና በነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱ ኃይሎችን ከህግ ፊት ለማቅረብ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳስቧል። በተጨማሪም በግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ወደቀያቸው መመለሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ተፈናቃዮች ለከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ከመጋለጣቸው በፊት በአፋጣኝ ወረዳውን ከሌሎች አካባቢዎች የሚያገናኙ መንገዶችን እንዲከፈቱና አስፈላጊው ሰብዓዊ እርዳታ መድረሱን እንዲያረጋግጡ ኢስመኮ በጥብቅ አሳስቧል። @EthiopiaReporter
Show more ...
3 273
1
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን እሁድ በሚካሄደው የበርሊን ማራቶን ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም በበርሊን ማራቶን የፈጸምኩትን ሰህተት አልደግምም አለ። አትሌት ቀነኒሳ ከሁለት ዓመት በፊት እአአ 2019 ላይ በጀርመን መዲና በተካሄደው የማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን ለመሻሻል ሁለት ሰኮንዶች ብቻ ቀርተዉት ውድድሩን ማሸነፉ ይታወሳል። "ከውድድሩ በፊት ክብረ ወሰን ለማሻሻል አእምሮዬን አላዘጋጀሁም ነበር። ክብረ ወሰኑን ለመሻሻል አእምሮዬን ባዘጋጅ ኖሮ፤ ክብረ ወሰኑ የዚያን ዕለት ይሰበር ነበር" ሲል ቀነኒሳ ኢንስታግራም ገጹ ላይ ባጋራው ቪዲዮ ተናግሯል። ቀነኒሳ በ2019ኙ የበርሊን ማራቶን ሁለት ሰከንዶች ብቻ ቀርተውት ክብረ ወሰን ሳያሻሽል መቅረቱ "ብዙ ጊዜ ያስደነግጠኛል" ያለ ሲሆን፤ እሁድ በሚደረገው ውድድር በኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተያዘውን ሪኮርድ ለማሻሻል እቅድ እንዳለው ገልጿል። ቀነኒሳ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ በማራቶን ይሳተፋል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ኢትዮጵያን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ በተደረገው ማጣሪያ ላይ ባለመሳተፉ ከቡድኑ ውጪ መሆኑ ይታወቃል። #BBC @EthiopiaReporter
Show more ...
2 868
1
በመስቀል በዓልም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል! ከዚህ ቀደም ፖሊስ ያስተላለፈውን መልዕክት በመተላለፍ ርችት የተኮሱ ግለሰቦች ተይዘው በፍርድ ቤት በዋስ መለቀቃቸውን ፖሊስ ገልጿል። በበዓላት ወቅት የሚተኮሱ ርችቶችን ሽፋን በማድረግ ሰላምን የማደፍረስ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች በሕገ-ወጥ መንገድ የገዙትን የጦር መሣሪያ እንደሚፈትሹ እና የተለያዩ የፀጥታ ስጋቶችን እንደሚፈጥሩ ፖሊስ ገልጿል። የሕገ-ወጦቹን ድርጊት ለመከላከል እንዲቻል መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ.ም በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓልም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ርችቶችን መተኮስ እንደማይችል ኅብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግም መልዕክቱን አስተላልፏል። ጳጉሜ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ለመስከረም 1 ቀን 2014 አጥቢያ ከለሊቱ 11 ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ሦስት ግለሰቦች የ2014 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ርችት ሲተኩሱ ተይዘው ምርመራ ተጣርቶባቸው እያንዳንዳቸው በ4 ሺህ ብር ዋስ ተለቀው በፍርድ ቤት በመታየት ላይ የሚገኝ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውሷል። በተመሳሳይ በቦሌ፣ በቂርቆስ እና በየካ ክፍለ ከተሞች ርችት ሲተኩሱ የተገኙ ግለሰቦች ጉዳይም በምርመራ ሂደት ላይ እንደሚኝም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል። @EthiopiaReporter
Show more ...
2 618
0
"ማንኛውም ት/ቤት ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ ሀገራዊም ሆነ የዜግነት ግዴታ አለበት" - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለሁሉም የዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለ3ቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት/መምሪያዎች በላከው ደብዳቤ ት/ቤቶች ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎችን እንዲያስተናግዱ በጥብቅ አሳስቧል። ትምህርት ቢሮው፥ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት በክልሉ በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከሰ/ወሎ፣ ከዋግኽምራ እና ሰ/ጎንደር ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎች የ2014 ትምህርት ገብተው ለመማር በተለያዩ ት/ቤቶች ጥያቄ እያቀረቡ ነው ብሏል። ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ ባለመያዛቸው ምክንያት ለከፍተኛ እንግልትና የትምህርት እድል እንዳያገኙ እያደረጋቸው መሆኑንም ቢሮው ገልጿል። ይህን ችግር ሁሉም አካል ርብርብ አድርጎ መፍትሄ መስጠት እንዳለበት ና ከትምህርት ገበታቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉ ተማሪዎችን እንዲማሩ በማድረግ ሊደረስላቸው እንደሚገባ አስገንዝቧል። ማንኛውም ትምህርት ቤት የተለያዩ ምክንያቶችን (የክፍል ጥበት አለብኝ፣ መምህር የለኝም ወዘተ) በመደርደር ተፈናቃይ ተማሪዎችን አለመቀበል ፈፅሞ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጿል። በመሆኑንም የዞን አመረር፣ የወረዳ ት/ፅቤት አመራር እና የት/ቤት ርዕሰ መምህራን በጋራ ተመካክረው ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። ትምህርት ቢሮው፥ማንኛውም ት/ቤት ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ ሀገራዊም ሆነ የዜግነት ግዴታ አለበት ያለ ሲሆን መረጃ ማቅረብ የማይችሉ ተማሪዎች ካሉ ተማሪው ደርሸበታለሁ ባለው የክፍል ደረጃ በማመልከቻ ት/ቤቱ በሚያዘጋጀው ፎርም ላይ በማስሞላት እና በማስፈረም እንዲገቡ እንዲደረግ በጥብቅ አሳስቧል። @EthiopiaReporter
Show more ...
3 121
1
አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ዋና አስተዳዳሪ አሺም ስታይነር ጋር በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ ተወያዩ! ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ዋና አስተዳዳሪ አሺም ስታይነር ጋር በልማት፣ በሰላም ግንባታና በሌሎች የትብብር መስኮች መወያየታቸው ተገለጸ። በተመሳሳይ አቶ ደመቀ መኮንን ከዴኒማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ ጋር በልማት ትብብር ላይ መክረዋል። በኒውዮርክ የስራ ቆይታ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም #UNDP ዋና አስተዳዳሪ አሺም ስታይነር ጋር በልማት፣ በሰላም ግንባታ እና በልዩ ልዩ የትብብር መስኮች ዙሪያ ውይይት አካሄደዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ የስራ ከዴኒማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ ጋር ተገናኝተው በልማት ትብብር እና በሰብዓዊ አገልግሎት ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። @EthiopiaReporter
Show more ...
3 615
2
ሀገራችን ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ሳቢያ ተጨማሪ 37 ዜጎችን አጥታለች። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 37 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,481 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,544 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 799 ሰዎች በፅኑ ታመዋል። @EthiopiaReporter
3 248
0
ለተፈናቃዮች ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችና ግብዓቶች መሠራጨታቸው ተገለጸ! በአማራና በአፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ተፈናቃዮችና በግጭቱ አካባቢ ለሚኖሩ ማኅበረሰቦች አገልግሎት የሚውሉ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ልዩ ልዩ ዓይነት መድኃኒቶችና ግብዓቶች እየተሠራጩ መሆኑን፣ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስትሯ (ዶ/ር) ሊያ ታደሰ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፣ በአሸባሪነት በተፈረጀው ሕወሓት ምክንያት ከ1.9 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለጤና አገልግሎት ችግር ተዳርገዋል፡፡ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረውን የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ክፍተት ለመሙላት፣ በአማራ ክልል ከ186 ሚሊዮን ብር በላይ፣ በአፋር ክልል ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የመድኃኒትና የሕክምና ልዩ ልዩ ግብዓቶች እየተሠራጩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተጨማሪ መድኃኒቶችንና ግብዓቶችን ከአገር ውስጥ ከውጭ ግዥ ለመፈጸም እየተሠራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ከመድኃኒትና ከግብዓት ድጋፍ በተጨማሪ ለድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት እንዲውል ለአማራ ጤና ቢሮ 23 ሚሊዮን ብር፣ ለአፋር ጤና ቢሮ 3.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡ ለተፈናቃይ እናቶችና ሕፃናት የሥርዓተ ምግብና አልሚ ምግቦችን ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊው ጥረት፣ እንዲሁም ለሁሉም ተፈናቃዮች በተጠለሉባቸው አካባቢዎች በጤና ባለሙያዎች የጤና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ሚኒስትሩ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ @EthiopiaReporter
Show more ...
3 308
1
አሜሪካ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘውን 453ሺህ 600 የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓ ተገለጸ። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጌታ ፓሲ ለጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ድጋፉም በዛሬው ዕለት በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ አስረክበዋል። የአሜሪካ ኤምባሲ መረጃ እንደሚያመለክተው በዛሬው ዕለት ድጋፍ የተደረገው የኮሮና መከላከያ ክትባት 453 ሺህ 600 የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘው ክትባት ነው። በተጨማሪም 504ሺ ክትባቶች በቀጣይ ድጋፍ እንደሚደረግ ኤምባሲው አስታውቋል። አሁን የተደረገውን ድጋፍ ጨምሮ አሜሪካ እስካሁን ለኢትዮጵያ 2.6 ሚሊዮን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶችን ድጋፍ ማድረጓ ታውቋል። @EthiopiaReporter
3 251
2
#PMOEthiopia: የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 100ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። 1. የፌዴራል የገቢ ግብር ደንብ፣ 2. የመንግሥት ሠራተኞች እና የግሉ ዘርፍ ሠራተኞች ጡረታ ለመደንገግ በቀረቡት ረቂቅ ዐዋጆች ላይ፣ 3. የማዕድን ስምምነቶች፣ 4. የተሐድሶ ሕክምና አገልግሎት ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው። @EthiopiaReporter
3 540
1
በ134 ቀናት ውስጥ 1.14 ቢሊዮን ብር በቴሌብር አማካኝነት ማዘዋወር ተችሏል! ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም በይፋ ለደንበኞች የተዋወቀው ቴሌ-ብር ከቻይናው ሑዋዌ ኩባንያ በመተባበር ሥራ ላይ የዋለ ነው። ስራው ከስምንት ባንኮች ጋር በመተባበር እየተሰራበት ይገኛል። ቴሌብር ባለፉት 127 አመታት የገነባንውን የቴሌኮም መሠረተ-ልማት በኢንፎርሜሽን የበለጸገ ማሕበረሰብ ከመገንባት ባለፈ ለፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ ያልሆነውን ማሕበረሰባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ የተወለደ አገልግሎት ነው ሲሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል። በ134 ቀናት 1.14 ቢሊዮን በቴሌቤብር አማካኝነት ገንዘብ ማዘዋወር ተችሏል። በሌላ በኩል በዓለም ዙሪያ በቴሌኮም ዘርፉ ከተሰማሩ 778 ኩባንያዎች ፤ ኢትዮ ቴሌኮም 28ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 58 ሚሊዮን ደንበኞች ያሉት ኩባንያው ፤ እዚህ ደረጃ በደንበኞች ብዛት ስለመቀመጡ የቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል። ከአፍሪካ ከMTN በመቀጠልም በሁለተኛው ደረጃ ላይ ይገኛል። በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ከ40 እስከ 50 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ግብይት በቴሌብር አማካኝነት ለማድረግ ይቻል ዘንድ እቅድ ስለመያዙ ከኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት መስማማታቸውን ጠቅሶ ብስራት ራዲዮ ዘግቧል። @EthiopiaReporter
Show more ...
3 333
1
ራሚስ ባንክ በቂ ሃብት በማሰባሰቡ ወደ ምስረታ ተሸጋገረ። በምስረታ ሂደት ሁለት አመታትን ያስቆጠረው ራሚስ ባንክ ብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ ባገናዘበ መልኩ ወደ ምስረታ ሂደት መሸጋገሩን አስታወቀ። ባለፈው ሚያዝያ ብሄራዊ ባንክ ባስተላለፈው ትእዛዝ በምስረታ ላይ የሚገኙ ባንኮች 500 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል ይዘው እና የመስራች ጉባኤ አድርገው እስከ ጥቅምት 2 ለፈቃድ እንዲያመለክቱ ቀነ ገደብ ማስቀመጡ ይታወሳል። በዚህም ራሚስ 724 ሚሊየን ብር በመሰብሰብ እውን ለመሆን ተቃርቧል። ራሚስ መስከረም 22 የመስራች ጉባኤ ያደርጋል። #Capital @EthiopiaReporter
3 166
0
ቻይና አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጣልኩ ያለችውን ማዕቀብ ተቃወመች! በኢትዮጵያ ተፈጽሟል ካለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ አሜሪካ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል መወሰኗን ቻይና ተቃወመች። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊጂያን ዣኦ አሜሪካ ጠንቃቃ እና አርቆ አሳቢ ከመሆንም በላይ ገንቢ ሚናን እንደምትጫወት ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል። የሚመለከታቸው አካላት ልዩነቱን በወጉ ለመፍታት፣ ብሔራዊ እርቅ ለማምጣት እና ወደ ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ የሚችሉበት ብልሃትና ችሎታ እንዳላቸው እናምናለንም ነው ቃል አቀባዩ ያሉት። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኢትዮጵያ ተፈጽሟል ከሚሉት የሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ማእቀብ መጣል እንዲቻል የቀረበላቸውን የውሳኔ ሃሳብ ባሳለፍነው አርብ መስከረም 7 ቀን 2014 ዓ/ም በፊርማቸው ማጽደቃቸው የሚታወስ ነው። #AlAin @EthiopiaReporter
Show more ...
3 749
0
በኮቪድ-19 ሳቢያ በአንድ ቀን የ47 ዜጎች ህይወት አለፈ። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 47 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,379 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,489 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 835 ሰዎች በፅኑ ታመዋል። @EthiopiaReporter
3 917
3
በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ደሎ መና ወረዳ የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡ የችኩንጉኒያ ወረርሽኝም በድሬደዋ ሱማሌ እንዲሁም በአፋር ክልሎች ሊከሰት እንደሚችል የኢንስቲትዩቱ የበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል። የአየር ጠባይን ተከትሎ የሚከሰት ወረርሽኝ ሊኖር ስለሚችል ህብረተስቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል። ከመሀል አዲስ አበባ በስተቀር በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በደቡብ ክልሎች የአየር ጠባይን ተከትሎ የወባ ወረርሽኝ ሊከሰት ስለሚችል ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን እና አካባቢዎች በማጽዳት ህብረተስቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል። ከጤና ሚኒስቴር እና ከክልሎች ጤና ቢሮ ጋር በመነጋገር ስጋት ያለባቸውን ቦታዎች የመለየት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቅሰው ፥ ወረርሽኙ ቢከስት አስፋላጊው ግብዓቶችን ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። #FBC @EthiopiaReporter
Show more ...
4 130
2
ኢትዮጵያ የአንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት ከሁሉም ተጎራባቾቿ ጋር እንዲኖር አቅዳለች! የሞያሌ አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎትን የሚያሳልጥ ስምንነት በኢትዮጵያ እና ኬንያ የጉምሩክ ሃላፊዎች መፈረሙን ተከትሎ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ እንደተናገሩት መሰል መሰረተ ልማቶች ከሁሉም ጎረቤት አገራት ጋር እንዲኖር መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡ በጅቡቲ በደዋሌ እና ጋላፊ አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎትን ለማስጀመር እየተሰራ ነው ያሉት ከሚሽነሩ፤ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች በደዋሌ ድንበር ተጠናቋል ከደጋፊ አካላት ጋር ሆነን ወደ ስራ እናስገባለን ብለዋል፡፡ በኤርትራ በኩል አሰብን የሚያገኛኝ የአንድ አለቅ ለመመስረት እንቅስቃሴ መኖሩን አስታውሰው፤ በሱማሌ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን መሰል እንቅስቃሴዎች የመንግስት ውሳኔን በመከተል የሚቀጥል ይሆናል በማለት አክለዋል፡፡ #Capital @EthiopiaReporter
Show more ...
3 901
1
ኢትዮጵያ ያቀረበችው የብድር ይራዘምልኝ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ ማግኘቱ ተገለፀ! ኢትዮጵያ በቡድን 20 የጋራ የብድር ማዕቀፍ ስር ያሉባትን ብድሮች እንዲራዘሙላት ያቀረበችው ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ ማግኘቱ ተገለፀ። ኢትዮጵያ ባሳለፍነው አመት የካቲት ወር ያቀረበችውን ጥያቄ አስመልክቶ የብድር ሰጪ ሃገራት ኮሚቴ መስከረም 06፣ 2014 ዓ.ም ለመጀመርያ ጊዜ ስብሰባ በመቀመጥ እንደተወያዮበትና ምላሻቸው በጎ የሚባል እንደሆነ ነው የገንዘብ ሚኒስቴር የገለፀው። ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ዛሬ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በፈረንሳይ እና በቻይና የተመራው ስብሰባ ኢትዮጵያ በኮቪድ እና በሀገሪቱ ባለው ግጭት ሳቢያ ያለችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባቱ ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን የመጨረሻ ውሳኔውን እና ቀጣይ ሁኔታዎችን ኮሚቴው በቀጣይ ሳምንታት እንደሚያሳውቅም ገልጿል። ኢትዮጵያ ለአበዳሪ ሀገራቱ ያቀረበችውን ጥያቄ በማስመልከት የአለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ (አይ ኤም ኤፍ) ቃል አቀባይ ጌሪ ራይስ ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጡት መግለጫ ኮሚቴው መልስ እንዲሰጥበት ማሳሰባቸው ይታወሳል። @EthiopiaReporter
Show more ...
3 727
1
የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በልዩ ልዩ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። ውይይት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል የሀገራችን ወቅታዊ የጸጥታና የደኅንነት ሁኔታ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች፣ እንዲሁም ጂኦፖለቲካዊ ለውጦችን የተመለከቱ አጀንዳዎች እንደሚገኙበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስታውቀዋል። የሚታዩ ክፍተቶችን፣ ለውጥ የሚያስፈልጋቸው እና መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ገምግሞ በቀጣይ እንደ ሀገር መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራት አቅጣጫዎችን እምዳስቀመጠም ገልጸዋል። @EthiopiaReport
3 656
1
በኢትዮጵያ አዲሱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዝርያ (የዴልታ ቫይረስ) በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው! የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ (የዴልታ ቫይረስ) ስርጭት እየተስፋፋ በመምጣቱ በዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚያገኝ ተናግረዋል። በአገራችን የቫይረሱ ስርጭት መስፋፋት በቫይረሱ የሚያዙ፣ በፅኑ የሚታመሙና ህይወታቸው የሚያጡ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን ነው ሚኒስትሯ የገለፁት። ለአዲሱ ቫይረስ መስፋፋት ቫይረሱን ለመከላከል የሚተገበሩ "የጥንቃቄ እርምጃዎች መቀዛቀዝ ምክንያት አንዱ ነው" ብለዋል። ህዝባዊ ጥንቃቄ የጎደላቸው መሰባሰቦች መብዛታቸውና የህብረተሰቡ በሚፈለገው መጠን ክትባት አለመከተብም ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸውን አመልክተዋል። በትናንትናው ዕለት 43 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ከ800 በላይ ሰዎች ደግሞ በፅኑ መታመማቸውም ነው የገለፁት። ባለፋት ሶስት ቀናት 108 ዜጎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን እንዳለፈ ተናግረዋል። እስከ አሁን ድረስ በቫይረሱ የሞቱ ዜጎች ቁጥር ከ5 ሺህ በላይ መሆኑን ገልፀዋል። የጥንቃቄው አተገባበር መዘናጋት በዚሁ ከቀጠለ ጉዳቱ የከፋ ሊሆን እንደሚችልም ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት። @EthiopiaReport
Show more ...
3 620
0
ወደሰላማዊ ትግል መመለስ እንፈልጋለን የሚሉ የ 'ሸኔ' ታጣቂዎችን በይቅርታ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት ቃል፥ "በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ፍላጎት ያላቸውን የሸኔ ታጣቂዎችን መንግሥት በይቅርታ ለመቀበል ዝግጁ ነው" ብለዋል። አቶ ጌታቸው ባልቻ ፥ ከዚህ በፊት ጫካ ለገቡ ለሸኔ ታጣቂዎች ጥሪ ሲያደግ መቆየቱን ያስታወሱ ሲሆን በተለይም የዛሬ 3 ወር ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ለሸኔ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥሪ መደረጉንና የኦሮሞ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚመለስ የተረዱ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ትግል መመለሳቸውን ገልፀዋል። ኃላፊው፥ "አሁንም ቢሆን ምንም እንኳን ሸኔ በህ/ተ/ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀ ቡድን ቢሆንም አውቀውም ይሁን ባለማወቅ የሽብር ተግባር ተሳታፊ የነበሩ ታጣቂዎችና መሪዎች ወደ ሰላማዊ ትግል የመመለስ ፍላጎት ካላቸው መንግሥት ለአገር ሰላም ሲባል በይቅርታ ይቀበላቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል። ከሰሞኑ ‘ጃል ጎልቻ' የተባሉ የሸኔ አመራር ወደሰላማዊ ትግል መመለሳቸውን የኦሮሚያ ክልል የገለፀ ሲሆን አቶ ጌታቸው ፥ " ጃል ጎልቻ ጫካ የገባው የኦሮሞን መብት እና ጥቅምን ለማስከበር እንጂ የኦሮሞ ጠላት፣ ተዋጊ እና የኦሮሞን የማዋጋት ወይንም ሌላው ኦሮሞን እንዲዋጋ አልሞ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል። አክለው ፥ "ጃል ጎልቻ መጀመሪያውኑ የኦሮሞ ጥያቄ ለመመለስ ጫካ ቢገባም በመሬት ላይ ያለው ሁኔታ የተለየ በመሆኑ ከኦሮሞ ጥቅም ተቃራኒ የሆነውን ጥያቄ አልቀበልም በማለት ወደ ሰላማዊ ትግል ተመልሷል" ሲሉ ገልፀዋል። " ሸኔ" ከወራት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ሽብርተኛ ተብሎ መፈሩጁ ይታወሰል። @EthiopiaReport
Show more ...
3 444
1
ታሊባን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ ንግግር ለማድረግ ይፈቀድልኝ ሲል ጥያቄ አቀረበ! በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓመታዊ ጉባኤ በተያዘው ሳምንት በኒው ዮርክ ከተማ መጀመሩን ተከትሎ ታሊባን መልዕክቱን ለዓለም አቀፍ መሪዎች ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ጠይቋል። ታሊባን ጥያቄውን በደብዳቤ ያቀረበ ሲሆን የመንግስታቱ ድርጅት ኮሚቴ ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። በዶሃ የቡድኑ ቃል አቀባይ የሆኑት ሱሃሊ ሻኢን በአፍጋኒስታን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አምባሳደር ተደርገው መሾማቸው ይታወሳል። አፍጋኒስታንን የተቆጣጠረው ታሊባን የቀድሞ አስተዳደር ተቀባይነት እንደሌለው አሳውቋል። ታሊባን በመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ መልዕክቴን ላስተላልፍ ማለቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኮሚቴ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል። ዘጠኝ አባላት ባለው ኮሚቴ ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይና እና ራሺያ አሉበት። #AlAin @EthiopiaReporter
Show more ...
3 838
1
በኮቪድ-19 ሳቢያ በአንድ ቀን የ43 ዜጎች ህይወት አልፏል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 43 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 10,463 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,575 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። የማታው ሪፖርት እንደሚያሳየን 835 ሰዎች በፅኑ ታመዋል። @EthiopiaReporter
3 745
0
ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ በኒውዮርክ የተመድን ጠቅላላ ስብሰባ እየተካፈሉ ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአሜሪካ ኒውዮርክ እየተካሄደ ያለውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ስብሰባ በመካፈል ላይ ናቸው። በስብባው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኢትዮጵያና የመን ጨምሮ በተለያዩ የአለም ሀገራት ያሉ የጸጥታ ችግሮች ዜጎችን ለረሀብ እየደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ @EthiopiaReporter
4 146
1
በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ448 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር አዋለ! ዳሽን ቢራ በመጫን መነሻውን ከአማራ ክልል ደብረብርሃን ከተማ ያደረገው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-26981 ኢት. ተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ አዲስ አበባ ከተማ ከደረሰ በኋላ ወደ ሀረር ከተማ በማቅናት ላይ እያለ ቃሊቲ ኬላ ላይ በተደረገበት ፍተሻ አሽከርካሪውን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያጓጉዘው ከነበረ 448 ሺህ 550 የአሜሪካ ዶላር ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረው ዶላር ሊያዝ የቻለው ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ ባደረገው ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ ሲሆን አሽከርካሪው ዶላሩን በቢራ ሳጥን ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር ነው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬከቶሬት ከፀረ-ኮንትሮባንድ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ያዋለው።በወንጀሉ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለው አሽከርካሪ ከነዶላሩ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተላልፎ ጉዳዩ በምርመራ ላይ መሆኑም ታውቋል። @EthiopiaReporter
Show more ...
4 285
2
የማlኤርትራ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግሥታት ባለሥልጣናት ላይ እንዲጣል ትዕዛዝ የሰጡበትን የማዕቀብ ውሳኔ ተቃወመች! በአሜሪካ እና አውሮፓ አገራት የሚተላለፉ ሚዛን የሳቱ ውሳኔዎችንና የሚወሰዱ እርምጃዎችን የተቃወመው የኤርትራ መንግሥት አገራዊ ሕጎችን፣ የአገራትን ነፃነት እና ሉኣላዊነትን የሚጥሱ ስለመሆኑ በማሳወቅ ኮንኗል። በማስፈራራት የሚመጣ ለውጥ አለመኖሩን አክሎም መሰል የአሜሪካ አካሄድ በርትዕ እና በሕግ ፊት ተቀባይነት የለውም ሲል የማዕቀብ ውሳኔውን እንደማይቀበል ማስታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል። በተያያዘ ዜና አሸባሪው ሕወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመው ጥቃት በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ወንጀል መሆኑን የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ገልፀዋል፡፡ ሆኖም ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ አሸባሪው ሕወሓት የፈፀማቸውን ወንጀሎች እና የጦርነቱን ዋነኛ መነሻ ለመሸፋፈን የሐሰት ትርክቶችና ፕሮፖጋንዳዎችን አጠናክሮ መቀጠሉን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ @EthiopiaReporter
Show more ...
4 224
0
የፖስፖርት አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹን ወደ አስራ ሁለት ማሳደጉን የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ሁነት ኤጀንሲ አስታወቀ! ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጅብ ጀማል ይህን የተናገሩት ለውጭ ጉዳይ ለዋናው መ/ቤት ሰራተኞች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ተጠሪ ተቋማት፣ ከመከላከያ ሚኒስቴር እና ከተለያዩ ተጠሪ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ኤጀንሲው እየሰራ ስላለው የኦን ላይን አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ሲሰጡ ነው። ከመደበኛው አሰራር በተጨማሪ አሁን ላይ የኦን ላይን አገልግሎት ላይ ልዩ ትኩረቶ ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ያስታወቁት አቶ ሙጅብ ባለፈው ዓመት ከ145ሺህ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች የኦን ላይን አገልግሎት ኤጀንሲው መስጠቱን ተናግረዋል። በሆሳእና፣ በጋምቤላ እና አሶሳ አዳዲስ ቅርንጫፎች በመክፈት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ቁጥር ወደ 12 ማድረሱን ለሰልጣኞች አብራርተዋል። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከኤጀንሲው የሚፈልጉትን አገልግሎትን ለማግኘት የኦን ላይን አማራጩን በስፋት መጠቀም እንዳለባቸው መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። @EthiopiaReporter
Show more ...
3 865
0
የዲያቆን ዳንኤል ንግግር 'አደገኛ ትርክት' ነው ስትል አሜሪካ ማውገዟ ተገለጸ ከሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የትግራይ ኃይሎችን በተመለከተ በአንድ ስብሰባ ላይ የሰጡትን አስተያት አሜሪካ ማውገዟን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ። "እንደዚህ ያለ የጥላቻ ትርክት አደገኛ እና ተቀባይነት የለውም" በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በትናንትናው ዕለት መተቸተቻውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዘግቧል። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባልም ናቸው። ከዚህ ቀደም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘር ጭፍጨፋ አማካሪ እንዲሁም የአሜሪካ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) ኃላፊ ሰማንታ ፓወር በዚህ ጦርነት ሰብዓዊነትን ዝቅ የሚያደርጉ ጥላቻን የሚሰብኩ ትርክቶችና ቃላቶች መጠቀማቸው ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል። ነገር ግን የዲያቆን ዳንኤል ክብረት አስተያየት በአሜሪካ መንግሥት ትኩረት አግኝቶ ትችት ሲቀርብበት የመጀመሪያው ነው ተብሏል። የአማራ ከልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት አንድ ዝግጅት ላይ ዲያቆን ዳንኤል "እነሱ" ብለው የጠሯቸውን አካላት "ከምድረ ገጽ ብቻ ሳይሆን ከሰዎች ህሊናም እንዲጠፉ" ሲናገሩ ተሰምተዋል። በኤኤፍፒ ዲያቆን ዳንኤል አስተያየታቸውን እንዲያብራሩ የተጠየቁ ሲሆን በመልዕክት በሰጡት ምላሽም "እነሱ የሚለው የሚያመለክተው ህወሓት የሚለው አሸባሪ ቡድኑን ነው" ሲሉ አስተባብለዋል። ግሎባል ሴንተር ፎር ዘ ሪስፖንሲብሊቲ ቱ ፕሮቴክት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሲሞን አዳምስ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት የዲያቆን ዳንኤል ንግግር "በእውነት የሚረብሽ እና ጥንቃቄ የጎደለው ነው" ብለዋል። አክለውም "በኢትዮጵያ ውስጥ በብሔር የሚከሰቱ ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ መበራከታቸውን ከማየት አንፃር ዳንኤል በአጠቃላይ ከትግራይ ተወላጆች ይልቅ ስለ ህወሓት ብቻ ነው የሚናገረው የሚለውን ለመገመት ከባድ ነው" ብለዋል። ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የፌደራል መንግሥት ባለስልጣን ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት ዳንኤል "የግል ስሜታቸውን ነው" በማለት የተናገሩ ሲሆን ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ሊጠፉ ይገባል አላሉም በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል። በጥቅምት መጨረሻ በትግራይ ከልል የተከሰተው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አፈናቅሏል እንዲሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም በረሃብ አፋፍ ላይ ናቸው። ጦርነቱ ወደ አጎራባቾቹ አማራና አፋር ክልልም ተዛምቶም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቅሏል። በትግራይ ክልል በከፋው ረሃብ ምክንያት ሰዎች አረንጓዴ ቅጠሎችን ለመብላት መገደዳቸውን ኤሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት በአንድ የጤና ማዕከል አንዲት እናትና 0.77 ግራም የምትመዝን ጨቅላ በረሃብ ሞተዋል። አንድ የእርዳታ ቡድን በሚሰራበት ከ20 በላይ በሆኑ ወረዳዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በረሃብ መሞታቸው ተዘግቧል። #BBC#APD @EthiopiaReporter
Show more ...
3 789
6
የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በጎረቤት ሱዳን! የሱዳን መንግስት መገናኛ ብዙሃን በሀገሪቱ "ያልተሳካ" የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉን አሳውቁ። የአገሪቱ ገዥ ምክር ቤት አባል ሁኔታው ​​በቁጥጥር ስር መዋሉን ለሮይተርስ ተናግረዋል። ~ የከሸፈዉን የሱዳን መፈንቅለ መንግስትን ሙከራ ተከትሎ በሜጀር ጄኔራል አብደል-ባቂ ባክራዊ የሚመራ በርካታ የጦር መኮንኖች የሱዳን ጦር እንደተቆጣጠሩ የወታደራዊ ምንጮች ለአል-አረቢያ ተናግረዋል። ~ አል-አረብያ የአረብኛ ቋንቋ እንደዘገበዉ ከሆነ የጦር ታንኮች ከሠራዊቱ የሕክምና ክፍል በማንቀሳቀስ እና በአካባቢው ከፍተኛ ወታደራዊ ኃይል በማሰማራት በሱዳን ፓርላማ አቅራቢያ ወደ አሮጌው የኦምዱርማን ድልድይ የሚወስደውን መንገድ ዘግተዋል፡፡ ~ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት አባል እና የምክር ቤቱ ይፋዊ ቃል አቀባይ መሐመድ አል ፋቂ ሱለይማን መላዉ የሱዳን ህዝብ ሀገሪቱን እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል። በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸዉ ላይ በሰጡት አስተያየት ሀገርን ለመከላከል እና ሽግግሩን ለመጠበቅ ተሯሯጡ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ~ አልጀዚራ ከካርቱም እንደዘገበው የሱዳን ሠራዊቱ የጦር መሣሪያ መጋዘኑ የሚገኝበትን ቦታ አሁንም እንደያዘ እና አንዳንድ የጦር መኮንኖችም እዚያ ውስጥ እንደነበሩ አስነብቧል፡፡ የጦር መኮንኖቹ መሣሪያዎቻቸውን አስረክበው እንዲወጡ እየተደራደሩ ይገኛል ብለዋል፡፡ ~ የሱዳን መፈንቅለ መንግስትን ሙከራ ቢከሽፍም የሱዳን የፀጥታ ኃይሎች ግን ካርቱም ከመንትያ ከተማዋ ኦምዱርማን ጋር የሚያገናኘውን ትልቁን ድልድይ እንደዘጉት ይገኛል፡፡ @EthiopiaReporter
Show more ...
4 222
4
በሀገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች መያዛቸው ተገለጸ። በሀገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ያልተፈቀዱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የቴሌኮም ማጭበርበሪያ /ፍራዉድ/ መሳሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዙን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገልጿል። በዚህም በሀገር ደረጃ ሊያደርስ የነበረዉን ከ19.3 ሚሊዮን ብር በላይ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ኪሳራ ማዳን መቻሉን በኤጀንሲዉ የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂዎች ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊዉ አቶ እሸቱ ቡሬሳ ጠቅሰዋል። በተጠናቀቀዉ በጀት አመት የደህንነት ስጋታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ በ14 ድርጅቶች ስም የመጡ 49 ድሮኖችና የስለላ ካሜራዎች ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገቡ መከልከላከል መቻልንም ኃላፊው አንስተዋል። በአሁኑ ሰዓት ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገቡ ክልከላ ከተደረገባቸዉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ምንድን ናቸው? - የቴሌኮም ፍራዉድ መፈጸም የሚያስችል (sim box) ፣ - ስፓይ ካሜራ፣ - ሳተላይት ስልክ፣ - ድሮን ፣ - የመገናኛ ሬዲዮ፣ - ወታደራዊ ባይነኩላር እና የቅኝት መሳሪያዎች፣ - ለሰቪላዊና ወታደራዊ አገልግሎት የሚዉሉ ጂፒኤሶች፣ - ድብቅ የድምፅ መቅጃ ማይክራፎኖች፣ - ዱዋል ባንድ ራዉተር፣ Transmitters (fm) - vsat የተባሉት እንደሚገኙበት ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያሳያል። ኢንፎርሜሽን መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡና ከሀገር ውጪ የሚወጡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎች፣ የመረጃ ማነፍነፊያዎችና የጥቃት መፈጸሚያ ቴክኖሎጂዎች በሀገር ደህንነት ላይ አደጋ እንዳያስከትሉ የመከላከል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የመቆጣጠር ኃላፊነት ተሰጥቶታል። @EthiopiaReporter
Show more ...
4 646
3
በመላው ዓለም የኮሮና ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ ከጎርጎርሳውያኑ 2019 ወዲህ የዓለም መሪዎች ለመጀመርያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው ሊመክሩ ነው። ልዉጡ የኮሮና ተሐዋሲን ጨምሮ ወረርሽኙ አሁንም በመላው ዓለም ስጋት እየሆነ ባለበት ሰዓት ወረርሽኙ ብርቱ ጉዳት ያደረሰባት የኒው ዮርክ ከተማ በዚህ ሳምንት ከ100 በላይ የዓለማችን መሪዎችን መቀበል ጀምራለች። መሪዎቹ በስብሰባቸው በበርካታ ዓለማቀፍ ፈታኝ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ቢጠበቅም የአየር ንብረት ለውጥ፣ ፍትኃዊ የኮሮና ክትባት ተደራሽነት፣ በታሊባን አስተዳደር ስር የወደቀችው የአፍጋኒስታን መጻኢ ዕድል፣ እንዲሁም በማይናማር እና በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ጋር በተያያዘው አስከፊው ቀውስ ጉዳይ ላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚችሉ አሶሽየትድ ፕረስ በዘገባው አመልክቷል። የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የስብሰባውን መቃረብ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ «ዓለም በተዘበራረቀ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች» ብለዋል። «በሃገራት የደህንነት ዋስትና አለመኖር፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የድህነት መጨመር እና ረሃብ፣ ገደብ የለሽ የቴክኖሎጂ ዕድገት፣ የኒኩልየር ጦር መሳርያ ስጋት እና እየተባባሰ የመጣው የሰብአዊ አድልዎ እና ኢፍትኃዊነት እየነገሱ በሌላ በኩል ሴራ እና ውሸት ነዳጅ ሆነው በማሕበረሰቡ ውስጥ ታላቅ መከፋፈልን እየፈጠሩ» ዓለም ሚዛኗን እንድትስት እያደረጋት ነው በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። የዓለም መሪዎችም ፤ «ፊታቸውን ወደ አረንጓዴ ልማት ማዞር እና ዋስትናዋ የተጠበቀላት ዓለም እንድትኖር» ጥሪ ያቀረቡት ጉተሬስ የኮሮና ወረርሽን በምድር ላይ የፈጠረውን ቀውስ ለመታደግ በጎርጎርሳውያኑ 2022 የመጀመርያ አጋማሽ የዓለማችን 70 በመቶ የሕዝብ ቁጥር እንዲከተብ የተቀናጀ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል። @EthiopiaReporter
Show more ...
4 522
1
ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታትን ጨምሮ ከትግራይ ጀምሮ ወደ አጎራባች ክልሎች በተስፋፋው ጦርነት ውስጥ ተሳትፎ ባላቸው አካላት ላይ ማዕቀብ መጣል የሚያስችል ውሳኔ ከሰሞኑ ወስናለች። በውሳኔው በኢትዮጵያ ግጭት እንዲራዘም፣ ሰብአዊ ርዳታ እንዳይደርስ እና ተኩስ አቁም እንዳይደረግ መሰናክል በመሆን ተጠያቂ ናቸው ያሏቸው አካላት ላይ የገንዘብ ዝውውር እና የጉዞ ማዕቀብ እንዲጣል የሚያስችል ነው። ውሳኔውን ተከትሎ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ዩናይትድ ስቴትስ «በሽብርተኛው ሕወሓት ትርክት ላይ ከተመሰረቱ» ቁልፍ የፖሊስ አውጪዎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ቡድኖች ሀሳብ አመንጭነት ከሚሰጡ ውሳኔዎች ልትወጣ ይገባል ሲሉ ባለፈው ሳምንት ለፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ግልጽ ደብዳቤ ልከዋል። የሕወሓት ኃይሎች በበኩላቸው የዩናይትድ ስቴትን ርምጃ አወድሰዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንኒስቴር በበኩሉ በግጭቱ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ወገኖች በድርድር ላይ ወደ ተመሰረተ ውይይት የሚመጡ ከሆነ ማዕቀቡ ሊዘገይ የሚችልበት ዕድል እንዳለ አመልክተዋል። #DW @EthiopiaReporter
Show more ...
3 867
0
21 ሆስፒታሎች በአማራ እና በአፋር ክልሎች ጉዳት እንደረሰባቸው ተገለፀ! በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አሸባሪ በተባለው ህወሓት ተይዘው በነበሩ የአማራ እና የአፋር ክሎች አካባቢዎች በሚገኙ 21 ሆስፒታሎች፣ 287 የጤና ጣቢያዎች እና ከአንድ ሺህ አንድ መቶ በላይ የጤና ኬላዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የጤና ሚኒስቴር በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። በአማራ ክልል በሚገኙ አምስት ዞኖች ውስጥ ባሉ 20 ሆስፒታሎች፣ 277 የጤና ጣቢያዎች ከአንድ ሺህ በላይ የጤና ኬላዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሯ አክለውም በተመሳሳይ በአፋር ክልል በሚገኝ አንድ ዞን ውስጥ 1 ሆስፒታል፣ 10 የጤና ጣቢያዎች፣ 38 የጤና ኬላዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል፡፡ ጉዳቶቹ በጤና ተቋማት ብቻ ሳይሆን በተቋማቱ በስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ላይ መሆኑን በመግለፅ ከስራ ቦታቸው እንዲፈናቀሉ ቡድኑ አድርጓል ሲሉ ገልፀዋል። በተመሳሳይ ቁጥራቸው በውል ያልተገለፁ አንቡላንሶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል ሲል ብስራት ራዲዮ ዘግቧል። @EthiopiaReporter
Show more ...
3 581
1
ጎረቤት ሀገር ሱዳን የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ላይ ውዝግብን ለመፍታት #ቱርክ ያቀረበችውን የማደራደር ጥያቄ መቀበሏ ታውቋል። የቱርክን የማደራደር ጥያቄ ሱዳን መቀበሏን ያሳወቁት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማሪያም አል-ሳዲቅ አል-መሃዲ ናቸው። ይህንንም ጉዳይ የቱርክ የዜና ወኪል የሆነው አናዱሉ እና የሱዳን መንግሥት የዜና ወኪል ሱና ዘግበውታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ፥ "የሱዳን የሉዓላዊ ም/ ቤት ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታህ አል-ቡርሐን ባለፈው ወር ወደ ቱርክ በተጓዙ ወቅት ፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረውን የድንበር አለመግባባት ለመፍታት ከቱርክ ባለሥልጣናት የቀረበውን የማደራደር ጥያቄ ተቀብለዋል" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በኩል በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤቱ ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታህ አል-ቡርሐን አብዱል ራህማን ሰኔ ወር ላይ ወደ ቱርክ መጓዛቸው ይታወሳል። አል-ቡርሐን በአንካራ ቆይታቸው ከፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋር ተገናኝተው በርካታ ምጣኔ ሀብታዊ ስምምነቶችን ተፈራርመው ነበር። በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የኢትዮጵያው ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ቱርክ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ የተለያዩ የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ስምምነት ተፈራርመው እንደነበር ይታወሳል። #BBC @EthiopiaReporter
Show more ...
4 470
3
በርካታ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው እለት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ከ30,192 በላይ ተማሪዎች ተመርቀዋል። የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ደግሞ ለአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ለጃፓናዊ ፕሮፌሰር አሱሺ ሱኔካዋ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል። ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም በሲዳምኛ ሙዚቃ እና ሌሎች ስራዎች ላበረከተው አስተዋጽኦ ለአርቲስት አዱኛ ዱሞ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል። @EthiopiaReporter
5 403
4
ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ከአብዬ ግዛት መውጣታቸውን እንደማትቀበል አስታወቀች። የደቡብ ሱዳን መንግስት በአብዬ ግዛት በሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲወጡ ሱዳን ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አደረጓል። የተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ረዳት ሚኒስትር ዣን ፒዬር ላክሮይክስ ባለፈው ሳምንት ደቡብ ሱዳንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ መግለጫ ሰተዋል። የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ልዑክ እና በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት፣ በአብዬ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል እንደ ሱዳን ፖስት ዘገባ። የደቡብ ሱዳን መንግስት መግለጫው በተጨማሪ በአወዛጋቢው ክልል ውስጥ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይልን ለመተካት ሱዳን ያቀረበችውን ጥሪ ውድቅ ማድረጎን አስታውቋል። “በዚህ ሁኔታ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ይህ ኃይሉ የተሰጠውን ተልዕኮ በሙያ እና በገለልተኝነት እያከናወነ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ ጦር እንዲወጣ በሚደረገው ጥሪ እንደማይስማማ ለመግለፅ እንወዳለን” ብሏል መግለጫው። የደቡብ ሱዳን መንግሥት የአብዬን ግዛት ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኝ ፓለቲካዊ ሂደት እንዲጀመር ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል ሲል አክሏል። @EthiopiaReporter
Show more ...
5 168
1
የመስከረም 20 ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር #ኦብነግ ከምርጫ እራሴን አግልያለሁ ብሏል። ግንባሩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባና ሌሎች ችግሮችን በተመለከተ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ መፍትሄ ባለማግኘቱ እንደሆነ አመልክቷል። የኦብነግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጅግጅጋ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ነው ከምርጫው እራሱን ማግለሉ ያሳለፈበት ውሳኔ ላይ የደረሰው። ፓርቲው ከምርጫው ወጥቻለሁ ካለባቸው ምክንያቶች መካከል፦ 👉 ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ በመቅረቱ። 👉 ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ ችግሮች ስላሉ። 👉 የምርጫ ካርድ የተሰራጨው ለሕዝቡ ሳይሆን ለገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ደጋፊዎች እንዲሁም ገዥው ፓርቲ ለራሳቸው ወገኖች ነው። 👉 የመራጮች የምዝገባ ሂደት ማጭበርበር የተሞላበት በመሆኑ። 👉 የዕጩዎች ምዝገባን ማገድ፣ ዕጩዎችን እና አባላትን ማጥቃትና ማዋከብ እንዲሁም ትክክለኛ የመራጮች ምዝገባ ማደናቀፍ ስለነበረ። 👉 በሶማሌ ክልል በበለጠ የፖለቲካ ምህዳሩ ጠባብ በመሆኑ የሚሉት ይጠቀሳሉ። #ONLF ፥ ምርጫውን ለ3 ወራት በማራዘም የተፈጠረው የሕዝብ ተስፋ፣ ምርጫ ቦርድ የተበላሸውን አሰራር ባለማስቆሙ ሂደቱ ጠልሽቷል ብሏል። ኦብነግ ከምርጫ ለመውጣት በመወሰኑ ማዘኑንና በቀላሉም እዚህ ላይ እንዳልደረሰ ገልጿል። ኦብነግ ትጥቅ ትግሉን ለማቆም ዋናው ምክንያት የሶማሌ ክልል ሕዝብ መብቶችን በሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማስከበር በመሆኑ ነው ቢልም ከምርጫው ተገዶ መውጣቱን ገልጿል። #BBC @EthiopiaReporter
Show more ...
4 679
2
የመላው የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ ፃፈ። ✅ድርጅቱ የፃፈው ደብዳቤ ከላይ ተያይዘዋል። @EthiopiaReporter
3 982
4
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው! የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 6793 ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ነው፡፡ ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ዲግሪ በመደበኛ እና ተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡ በዛሬው መርሐ-ግብርም ለአርቲስት አዱኛ ዱሞ የክብር ዶክቶሬት ይበረከትለታል ተብሏል፡፡ በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በሰባት ካምፓስ ከ40 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝም ነው በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገለፀው፡፡ @EthiopiaReporter
3 748
0
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 298 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው። ከተመራቂዎቹ ሰባቱ በሦሥተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው። 215ቱ በሁለተኛ ዲግሪ እና ቀሪዎቹ 1 ሺህ 76 ተማሪዎች በመጀመረያ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው። #OBN @EthiopiaReporter
3 571
0
የጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 696 ተማሪዎች አሰመርቋል። ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ 450 ወንድ እና 246 ሴት በአጠቃላይ 696 ተማሪዎችን አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ 252 ተማሪዎች በአጠቃላይ ሕክምና እና በጥርስ ሕክምና የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል። ዩኒቨርሲቲው በሶማሊላንድ ሀርጌሳ ካምፓሱ በ'ኒውትሬሽን' የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 19 የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችንም ማስመረቁን የተቋሙ ፕሬዝዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያስመረቃቸው ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛ፣ በማታ እና በርቀት መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው። #ኢፕድ @EthiopiaReporter
3 781
1
ከሳዑዲ አረቢያ 373 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡ በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ፣ ሪያድ 373 ዜጎቻችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። @EthiopiaReporter
4 073
0
የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ኃይሎች ወደ የተኩስ አቁም ስምምነት የሚመጡ ከሆነ ለመጣል ያቀደችውን ማዕቀብ ልታዘገይ እንደምትችል ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች። የኢትዮጵያ መንግስት እና ሕወሓት "በመካሔድ ላይ ያለውን ግጭት አቁመው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአፋጣኝ ድርድር የሚጀምሩ ከሆነ" ማዕቀቡ ሊዘገይ እንደሚችል የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዘግየት ብለው በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ብሊንከን "ሁለቱ ወገኖች በዚህ ረገድ አፋጣኝ እርምጃ የሚወስዱ ከሆነ ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀቡን ለማዘግየት እና የድርድር ሒደቱን ለመደገፍ ዝግጁ ነች" ማለታቸውን ሮይተርስን ዘግቧል። @EthiopiaReporter
4 732
4
1
0
4 133
1
1
0
3 659
1
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ! የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ ተጠያቂ ባደረጓቸው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ላይ እንዲሁም በህወሓት እና በኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ በፈረሙት የስራ አስፈጻሚ አካል ትዕዛዝ (executive order ) የትግራይ ክልል ግጭት እንዲራዘም ፤ ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይቀርብ ያስተጓጎሉ እና የቶክስ አቁም ስምምነት እንዳይደረስ እንቅፋት ሆነዋል ባሏቸው ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ወስነዋል። ማዕቀቡ እንዲጣል ያዘዙትም ከላይ ለተጠቀሱት ጉዳዮች ተጠያቂ ናቸው በተባሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የአማራ ክልል መስተዳደር ባለስልጣናት ላይ፤ እንዲሁም በህወሓትና በኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ እንደሆነ የአሜሪካ መንግስት ያወጣው መግለጫ ያመለክታል። ተጠያቂ ናቸው የተባሉት የመንግስት ባለስልጣናት እና የህወሓት አመራሮች ማንነት ግን ይፋ አልተደረገም። ተጨማሪ ለማንበብ: https://bit.ly/3tMfOK8 @EthiopiaReporter
Show more ...
3 559
3
የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከጦርነት ቢሊየን ዶላሮችን እንደሚያተርፉ ሪፖርት አመላከተ! የአሜሪካ መንግስት ከ2004 አንስቶ ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ባደረገው ስምምነት 43.8 ቢሊየን ዶላር ወጪን አድርጓል። ታላላቅ የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ሀገሪቱ የመስከረም 11ዱን ሽብር ጥቃት ተከትሎ ከመጣውና አሜሪካን ሽብርተኝነትን የመዋጋት (War On Terror) ብላ ከሰየመችው ጦርነት በርካታ ቢሊዮኖን ዶላሮችን ማግኘታቸውን ባሳለፍነው ሳምንት የወጣ ሪፖርት አመላከተ። የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት “ቢግ ቴክ ሴልስ ዋር” የተሰኘ ተቋም ያወጣውን ሪፖርት ዋ አድርጎ ባወጣው መረጃ፤ ከአውሮፓውያኑ 2004 አንስቶ አማዞን፣ ፌስቡክ፣ ጉግል፣ ማይክሮሶፍት እና ትዊተር በዋናነት በጦርነት ላይ ያተኮሩ ትላልቅ ኮንትራቶችን ከመንግስት ወስደው ሲሰሩ እንደነበር ገልጿል። የአሜሪካ ጦር ኃይል እና ስለላ ተቋማት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጉዜ ወደ ዲጂታል እየተለወጠ መምጣቱን ተከትሎ በክላውድ ኮምፒውቲንግ እና ጂፒኤስ ሶፍትዌሮች ረገድ ፍላጎታቸውም እየጨመረ ቆይቷል። #AlAin @EthiopiaReporter
Show more ...
3 466
3
ከአሜሪካ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋራ ፍሬአማ ውይይት ማድረጋቸዉን በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አህጉረ ስብከት የሚመሩ 12 ሊቃነ ጳጳሳት አስታወቁ። ላለፉት ሁለት ቀናት ከተለያዩ የአሜሪካ መንግሥት ኃላፊዎች ጋራ ውይይት ሲያደርጉ የቆዩት ሊቃነ ጳጳሳት፣ ውጤታማ ተልእኮ መፈጸማቸውን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ሕወሓት በጀመረውና አሁንም ወደ አፋር እና አማራ ግዛቶች ባስፋፋው የጥፋት ጦርነት በብዙ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መገደላቸውን፣ መቁሰላቸውን እና መፈናቀላቸውን ለአሜሪካ ባለ ሥልጣናት የገለጹት ብፁዓን አባቶቹ፣ የባይደን መንግሥት ትክክለኛ አቋም በመያዝ ሕወሐትን እንዳያስታምም ጠይቀዋል። "በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት በዋሽንግተን ዲ.ሲ በአካል በመገኘት የኢትዮጵያን ፍትሃዊ አቋም ለአሜሪካ የሕግ አውጪዎች በማስረዳታቸው ከታላቅ አክብሮት ጋር ምስጋናችንን እናቀርባለን" ሲሉ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል። @EthiopiaReporter
Show more ...
3 484
2
በታይም መጽሄት ተጽዕኖ ፈጣሪ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ሳራ መንክር ተካተተች! ታይም መጽሔት በትምህርት፣ በሳይንስ፣ በኢኮኖሚክስ በሌሎች ዘርፎች ጨምሮ በ2021 መስከረም 7/2014 በዓለም ላይ እጅግ ተጽእኖ ፈጣሪ ያላቸዉን የ100 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ሰባት አፍሪካውያንን አካቷል፡፡ በዚህም ኢትዮጲያዊቷ ሥራ ፈጣሪ እና የምግብ ፖሊሲ ባለሙያ ሳራ መንክር ተካታለች፡፡ ሳራ መንከር አርሶ አደሮች እና መንግስታት በግብርናዉ ዘርፍ የተሻለ ውሳኔ መስጠት እንዲችሉ የሚያግዝ ግሮ ኢንተለጀንስን ተቋም በማቋቋም ትመራለች፡፡ በዝርዝሩ ዉስጥ ናይጄሪያዊቷ የዓለም ንግድ ድርጅት ኃላፊ ንጎዚ ኦኮንጆ ኢውያላ ተካተዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት የኮቪድ ምላሽ የሚመሩት የካሜሮን ዜግነት ያላቸዉ ዶ/ር ጆን ኒንጋሶንግ እና የኬንያ የአካባቢ መብት ተሟጋች ፊሊስ ኦሚዶ በዝርዝሩ ከተካተቱት መካከል ናቸው። @EthiopiaReporter
Show more ...
4 247
2
ወደ ትግራይ ክልል የሰብኣዊ እርዳታ ጭነው ከተጓዙ 466 ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች 428ቱ እስካሁን አለመመለሳቸው ተገለፀ! የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎች ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም በትግራይ እንዲሁም በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለዓለም ዐቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ኃላፊዋ በመግለጫቸው ወደ ትግራይ የሚደረጉ የአየር እና የየብስ የሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት ጉዞዎች በተባባሩት መንግሥታት የአየር በረራ እንደቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል። የአውሮፓ ኅብረት የሰብኣዊ እርዳታ በረራም ባለፈው ሳምንት መጀመሩን አንስተዋል። እስከ መስከረም 6 ድረስም ከ6 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ የምግብ ነክ ቁሶች፣ ከ6 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶች እንዲሁም 760 ሺሕ ሊትር የሚጠጋ ነዳጅ እና ከ1 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ የግብርና ግብዓት ወደ ትግራይ መጓጓዙን ገልጸዋል። በትግራይ ክልል ያለውን የሰብኣዊ መብት ጥሰት በተመለከተ በኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት ጥምረት የሚካደውን ምርመራ ግኝት እና ምክረ ሃሳቦችን መንግሥት ለማጤን ዝግጁ መሆኑን አክለዋል። ሆኖም ሁለቱ የሰብኣዊ መብት ተቋማት ጥናት በአማራ እንዲሁም በአፋር ክልል በሕወሓት የሽብር ቡድኑ የተፈጸሙ ጥቃቶችን እንዲያካትቱ ጠይቀዋል፡፡ በተያያዘ ዜና የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ ወደ ትግራይ ክልል ገብተው ያልተመለሱ እርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ጉዳይ እንዳሳሰበው አስታውቋል። ተጨማሪ ያንብቡ፦ telegra.ph/PMOfficeEthiopia-09-16 @EthiopiaReporter
Show more ...
4 972
2
ባለፈው ሳምንት ወደ መቐለ ከደረሱት 149 የጭነት መኪናዎች ውስጥ አንዳቸውም እንዳልተመለሱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት #UN ዛሬ ምሽት አስታውቋል። ተመድ ፥ እኤአ ከሐምሌ 12 ጀምሮ ወደ ትግራይ ከገቡ 466 የጭነት መኪኖች የተመለሱት 38 ብቻ መሆናቸውን ጠቁሟል። ድርጅቱ ፥ "በትግራይ ለሚኖሩ ሰዎች ሕይወት አድን እርዳታ ለማድረስ የጭነት መኪናዎች ያስፈልጉናል" ብሏል። ከዚህ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ በፊት ዛሬ ከሰዓት ላይ መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚንስቴር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ከተጓዙ የከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች መካከል 428 ተሽከርካሪዎች እስካሁን ከክልሉ እንዳልወጡ መናገራቸው ይታወሳል። ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://telegra.ph/PMOfficeEthiopia-09-16 @EthiopiaReporter
1
0
በአዲስ አበባ ከደረጃ በታች የሆኑ 11 ትምህርት ቤቶች እውቅና ተሰረዘ! የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ከደረጃ በታች ናቸው ያላቸውን የ11 ትምህርት ቤቶች የእውቅና ፍቃድ መሰረዙን አስታወቀ፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በከተማዋ የሚገኙ 672 ነባር እና 51 አዲስ ትምህርት ቤቶች ተመዝነው ለሚቀጥለው ዓመት ማሻሻያ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው 61 ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ ዋና ስራ አስኪያጇ ባለፈው ዓመት ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው 65 ትምህርት ቤቶች 60ዎቹ በተደረገ ክትትል የደረጃ ማሻሻል በማድረጋቸው የእውቅና ፈቃድ እንደተሰጣቸው አንስተዋል፡፡ ምንም አይነት ማስተካከያና ማሻሻያ ያላደረጉ 5፣ ዘንድሮ በተደረገው ክትትልና ቁጥጥር መስፈርቱን ያላሟሉ 6 ትምህርት ቤቶች የእውቅና ፍቃዳቸው መሰረዙን አስታውቀዋል፡፡ ፍቃዳቸው ከተሰረዘው መካከል በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙት ሱፐር ኪድስ፣ ኢንዱራንስ አዲስ፣ ኤልሻዳይ ወረዳ 12፣ ጵሾን ወረዳ 9፣ ቪካስ እና ሮሆቦት ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሀሞና እና እመሙዝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማም ሁንዴ ጉዲና የመጀመሪያ ደረጃ እና ማይ ፊፍ ቅድመ መደበኛ እንዲሁም ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አዶናይ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት እንደሚገኙበት አብራርተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡ #ENA @EthiopiaReporter
Show more ...
4 660
1
የሞጆ ባቱ የክፍያ ፍጥነት መንገድ መስከረም 10 ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል! -ትራንስፖርት ሚኒስቴር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሚያዚያ ወር 2013 የተመረቀውና፤ የሞጆ-ሀዋሳ የመንገድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የሞጆ ባቱ የክፍያ ፍጥነት መንገድ የተሟላ የክፍያ ማከናወኛ ስርዓት ተሟልቶለት መስከረም 10 ቀን 2014 ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ አስታወቁ። መንገዱ 92 ኪሜ ርዝመት ያለው ሲሆን 5 ደረጃቸውን የጠበቁ የክፍያ ጣቢያዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሆኑ ሚኒስቴር ዴኤታው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል። የክፍያ ጣቢያዎች ሞጆ፣ ቆቃ፣ ቦቴ፣ መቂ እና ባቱ መውጫ ጣቢያዎች ናቸው ብለዋል። ባለፉት 4 ወራት ከተከናወኑት ስራዎች መካከል የ5 ክፍያ ጣቢያዎች የኦፕሬሽን ስራ ማከነወኛ ህንፃዎች እና የስራተኞች ማደሪያ ዶርሚተሪዎች፣ ጋራዦች፣ የተሽከርካሪዎች ደህንነት ማስጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች፣ የክፍያ ማከናወኛ ካኖፒ መጠናቀቃቸውን ካሳሁን ጎፌ ገልፀዋል። @EthiopiaReporter
Show more ...
4 333
1
#Update: ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና #በወረቀት እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገልጿል። የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ የሚከተለውን ነጥብ አንስቶታል፦ • ፈተናው የሚሰጠው በወረቀት ነው፡፡ • የኢኮኖሚክስ የትምህርት አይነት አይኖርም። • የመልቀቂያ ፈተናው ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች ይሰጣል። • በተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው የሚገኙ ተማሪዎች ሁኔታው ተጠንቶ ወደ ፊት አቅጣጫ ይቀመጣል፡፡ @EthiopiaReporter
4 295
9
በኢትዮጵያ በስምንት ወራት ውስጥ የ128 ሰዎች የአይን ብርሃን መመለሱ ተነገረ! በሀገሪቱ በ8 ወራት ውስጥ በተደረገ የአይን ብሌን ንቀል ተከላ 128 ሰዎች የአይን ብርሀናቸው መመለሱ ተገልፆል። ሆኖም ግን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአይን ባንክ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደረገ በመሆኑ ልገሳው ከሌሎች ጊዜያት ጋር ሲነፃፀር አናሳ መሆኑ ተገልፆል፡፡ ባንኩ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ 2,651 የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸው ማየት ችለዋል ሲል በተቋሙ የአይን ባንክ የግንዛቤ ማስጨበጫ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ነጋ ደምሴ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በባንኩ 8 ሀኪሞች ብቻ በመኖራቸው እና የለጋሾ ቁጥር አናሳ መሆኑ እያጋጠሙ ያሉ ከፍተኛ ችግር መሆናቻውብን ገልፀዋል፡፡ በአዲስ አበባ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ጎንደር እና አርባምንጭ የአይን ብሌን ንቀል ተከላ ህክምና እንደሚደረግ ተገልፆል፡፡ ተቋሙ በ2040 ምንም አይነት የአይን ጠባሳ የተከሰተበት ታማሚ እንዳይኖር  ማቀዱን አቶ ነጋ ደምሴ  ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረገ ጥናት ከ300 መቶ ሺህ በላይ የሚገመት መስራት የሚችል ወጣትና ጎልማሳ በአይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት እንደተጓዳ  እና ወረፋ በመጠበቅ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ @EthiopiaReporter
Show more ...
4 222
1
426 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ! በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን እንዲመለሱ እየተደረገ ባለው ጥረት 426 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ፡፡ በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ ሪያድ 158 ህጻናትን ጨምሮ 426 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡ @EthiopiaReporter
4 077
1
ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችላትን፤ የአንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት ስምምነት ከኤርትራ ጋር ለመስማት በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ። ይህ የተባለው ኢትዮጵያና ኬኒያ የሞያሌ አንድ-አለቅ የድንበር አገልግሎት ማዕከልን ወደ ስራ ለማስገባት የመግባቢያ ስምምነት በተፈራረሙበት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው። በሥነ ሥርዓቱ ላይም የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ካቤታ “እኛ የጉምሩክ ፕሮቶኮል አዘጋጅተናል። የኢትዮጵያ መንግሥት አስቀድሞ፤ ለኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስገብቷል። በኢትዮጵያ በኩል እያንዳንዱን ዝግጅት አጠናቀን፤ ከኤርትራ በኩል ምላሾችን በመጠባበቅ ላይ ነን” ሲሉ ተናግረዋል። የአንድ-አለቅ የድንበር አገልግሎት ማዕከል የድንበር ነክ ጉዳዮችን የሚቆጣጠሩ የመንግሥት ተቋማትና ሰራተኞች የተቀናጀ የድንበር አስተዳደር ሥራዎችን በተሳካ መልኩ መተግበር እንዲችሉ የሚያስችል ነው። በተጨማሪም ነጋዴዎች፣ የጭነት አገልግሎት አቅራቢዎች ወይም አጓጓዦችና ሌሎች መንገደኞች ድንበር አቋርጠው ለመሻገር የሚያልፉባቸውን ሂደቶችን ቀላል፣ ፈጣን እና ወጪ ቆጣቢ እንዲሆኑ በማድረግ የድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴዎችን የተቀላጠፉ እንደሚያደርግም ታምኖበታል። ኢትዮጵያ የሞያሌው ስምምነት ከተሳካ በኋላ ተመሳሳይ የድንበር አገልግሎት ማዕከሎችን ከሱዳን፣ ከሶማሊያ እና ከጅቡቲ ጋር ለማቋቋም አቅዳለች። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 90 በመቶ የሚሆነው የውጭ ንግዷን በጅቡቲ በኩል የምታካሄድ ሲሆን በኬንያ፣ በሶማሊያ፣ ሶማሊላንድ፣ ሱዳን እና ኤርትራ የወደብ መዳረሻዎች በኩል የውጭ ንግዷን ማካሄድ ብትችል በጅቡቲ መስመር ያለውን መጨናነቅ ይቀንሰዋል ተብሏል። Via Addis Maleda @EthiopiaReporter
Show more ...
4 664
3
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የጀርመን አፍሪቃ ሽልማትን አሸነፉ! የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የጀርመን የአፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ተገለጠ።ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ለሽልማት የበቁት በሕይወት ዘመናቸው ለአሰብአዊ መብቶች መከበር ላደረጉት አስተዋጽዖ መሆኑን የጀርመን የአፍሪቃ ሽልማት አዘጋጆች ባወጡት መግለጫ ዐሳውቀዋል። ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከ30 በላይ እጩዎች መካከል አሸናፊ የኾኑት ከተለያዩ የፖለቲካ እና የመገናኛ አውታሮች በተውጣጡ 24 ገለልተኛ የዳኞች ቡድን ተመርጠው ነው። ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት የጀመሩት ገና በለጋ የወጣትነት እድሜያቸው በ23 ዓመት አዲስ አበባ ውስጥ በጥብቅና ሞያ ከተሰማሩበት ጊዜ አንስቶ እንደሆነ ሸላሚ ድርጅቱ ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ላበረከቱት አስተዋጽዖ የጀርመን የአፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ አድርጓቸዋል። ሽልማቱ ለእርሳቸው ምን ትርጉም እንዳለው ባልደረባችን ማንተጋፍቶት ስለሺ ላቀረበላቸው ጥያቄ «ትልቅ ደስታ ይሰጣል በትልቅ ትህትናም እቀበለዋለሁ። ለእኔ ብቻ የተሰጠ ሽልማት ሳይሆን ለስራ ጓደኞቼ፣ ለቤተሰቦቼ እና ለጓደኞቼም ጭምር ለሁላችን በሰብዓዊ መብት መከበር ለምናደርገው አስተዋጽዖ በእኔ ስም የተሰጠ እውቅና እና ክብር ነው። » ብለዋል። ተሸላሚ ያደረገዎት «የጀርመን አፍሪቃ ተቋም» ፕሬዚደንት ዶ/ር ኡሺ አይድ የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት ማሸነፎን ባስተዋወቁበት ወቅት፦ «ገለልተኛ ዳኞች ድንቅ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች በመምረጡ ተደስቼያለሁ፤ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በሕይወት ዘመናቸው ለሰብአዊ መብቶች ላደረጉት አስተዋጽዖ ሽልማቱ ይገባቸዋል» ብለዋል። #DW @EthiopiaReporter
Show more ...
4 799
2
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 እንደሚሰጥ ተገለጸ! የ2013 ዓመተ ምህረት የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 እንደሚሰጥ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ፡፡ የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በሰጡት መግለጫ ከ6 መቶ ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ አስታውቀዋል ፡፡ @EthiopiaReporter
4 571
6
የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ለጠ/ሚ/ር ዐቢይ ጥሪ ምላሽ ሰጡ! የአፍሪካዊያን አንድነት ወሳኝ ነው ሲሉ የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትብብር ጥሪ ምላሽ ሰጡ። ፕሬዝዳንቱ በቲውተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት አኅጉራችን በርካታ የምጣኔ ሃብት ዕድሎች አሏት ብለዋል። ዕርስ በዕርስ በተሳሰረች ዓለም ውስጥ ጥቅምን ለማስጠበቅ፣ ውሳኔዎችን እየመዘኑና እየመረጡ ለመጓዝ ደግሞ የአፍሪካዊያን አንድነት ወሳኝ ነው ብለዋል። በጋራ ሆነን ይህንን ማሳካት እንችላለንም ነው ያሉት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከቀናት በፊት ባቀረቡት ጥሪ ለአኅጉሪቱ እድገት የተባበረ አፍሪካ መሰረታዊ መሆኑን ጠቅሰው ያለን እምቅ የተፈጥሮና የሰው ኃይል ሃብት ወደታላቅነት ለመጓዝ በቂ ነው ማለታቸው ይታወሳል። ለዚህም በትብብር እንስራ ሲሉ መጠየቃቸው አይዘነጋም። @EthiopiaReporter
Show more ...
4 544
0
የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ከ302 ሺህ ዶዝ በላይ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ አደረገ! የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 302 ሺህ 400 ዶዝ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ ማድረጉን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል። የአሁኑ ድጋፍ ከዚህ ቀደም ከተሰጡት 1.6 ሚሊዮን ዶዝ ተጨማሪ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አሜሪካ ለአፍሪካ ለመስጠት ቃል የገባችው የ25 ሚሊዮን ሕይወት አድን ክትባት አካል ነው ተብሏል። በአፍሪካ ዴልታ የተበላው የኮቪድ-19 ልውጥ ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ቫይረሱን ለመከላከል ክትባት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ሆኑ መገኘቱ ተመልክቷል። የአሜሪካ መንግሥት ከአፍሪካ ኅብረት እና ከአፍሪካ ሲዲሲ ጋር በመቀናጀት ክትባቶቹን የማከፋፈል ሥራውን እንደሚቀጥል ተገልጿል። @EthiopiaReporter
4 618
1
በኢትዮጲያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ5ሺ በላይ ሆነ፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ34 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል❗ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው እለታዊ መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 34 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል። በመላው ሀገሪቱ የቫይረሱ ስርጭት መዛመት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 5,001 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በአሁኑ ወቅት በፅኑ ህሙማን መከታተያ ውስጥ 783 ሰዎች የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። @EthiopiaReporter
4 732
2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ/ም የትምህርት ካላንደርን ይፋ ያደረገ ሲሆን ከጥቅምት 1 ቀን ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ትምህርት እንደሚጀምር ተገልጿል። @EthiopiaReporter
4 760
13
በኢትዮጲያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ5ሺ በላይ ሆነ፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ34 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል❗ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው እለታዊ መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 34 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል። በመላው ሀገሪቱ የቫይረሱ ስርጭት መዛመት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 5,001 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በአሁኑ ወቅት በፅኑ ህሙማን መከታተያ ውስጥ 783 ሰዎች የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። @EthiopiaReporter
1
0
አሜሪካ ለግብፅ ትሰጥ ከነበረው የ 300 ሚሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ የተወሰነውን እንደምትቀንስ ተገለፀ። አዲሱ የባይደን አስተዳደር ይህን ውሳኔ ያሳለፈው በግብፅ ላይ እየተነሳ ባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ክስ አሳሳቢነት ሲሆን ለግብፅ በሚሰጣት ቀሪው ገንዘብ አጠቃቀም ላይ ቁጥጥርና ገደብ እንደሚኖርም ተነግሯል። በውሳኔው ሙሉ በሙሉ እቀባ አለመተላለፉ የተወሰኑ ህግ አውጪዎችንና የመብት ተሟጋቾችን ቅር ቢያሰኝም ቀደም ባሉ አስተዳደሮች ለግብፅ ወታደራዊ ድጋፍ በመስጠት ላይ ከነበራቸው አቋም የአሁኑ ውሳኔ ቢያንስ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን ግምት ውስጥ ማስገባቱ የተሻለ እንደሆነ ተቀምጧል። ግብፅ ታገኝ ከነበረው 300 ሚሊየን ዶላር 170 ሚሊየኑን ብቻ እንድታገኝ እቅድ የተያዘ ሲሆን፣ የግብፅ መንግስት የሰብአዊ መብት ጥበቃን በተመለከተ የተቀመጠለትን ቅድመ ሁኔታዎች እስኪያሟላ ድረስ ቀሪው 130 ሚሊየን ዶላር ላይ እቀባ የሚደረግበት ይሆናል። ፕሬዝዳንት ባይደንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ብሊንከን እንደ ግብፅ ባሉና በአል ሲሲ አይነት አምባገነን መሪዎች በሚተዳደሩ አጋር ሃገራት እንኳን የሰብአዊ መብት ጥበቃን ለማስከበር ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለፃቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት አያሌ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዲሞክራቲክ ህግ አውጪዎች እቀባው በከፊል ሳይሆን ሙሉ በሙሉ እንዲደረግና ጠቅላላው የ 300 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንዲታገድ ጫና እያደረጉ እንደሆነ ተገልጿል። #አዲስዘይቤ @EthiopiaReporter
Show more ...
4 687
5
የኢሬቻ በዓል ለኮሮናቫይረስ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግና የተሳታፊው ቁጥር ሳይገደብ እንዲከበር የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ወሰነ! በዓሉ መስከረም 22 በአዲስ አበባ እንዲሁም መስከረም 23 በቢሾፍቱ እንዲከበር ኅብረቱ ወስኗል። የዘንድሮው በዓል እንዴት መከበር እንዳለበት የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት በአዳማ ምክክር ካደረገ በኋላ ባሳለፈው ውሳኔ ላይ መግለጫ ሰጥቷል። የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ጸሐፊ እና የቱለማ ኦሮሞ አባገዳ ጎበና ሆላ የኢሬቻ በዓል የምስጋና፣ ይቅርታ እና የፍቅር በዓል ነው በማለት ኢሬቻ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። አንዳንድ አካላት በዓሉን ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ለማዋል ፋላጎት አላቸው ያሉም ሲሆን የኢሬቻን ባህላዊ እሴት የሚፃረር በመሆኑ እነዚህን አካላት ሕብረተሰቡ ሊታገላቸው ይገባል ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። @EthiopiaReporter
Show more ...
4 633
1
4 514
0
በኢትዮጵያ የዴልታ ቫይረስ ዝርያ መኖሩ ከተረጋገጠ ወዲህ 9 ሺህ 164 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ! በአንድ ሳምንት ውስጥ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ 17 ነጥብ 7 በመቶ መድረሱን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፣ ይህም ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር ዴልታ የመሰራጨት መጠኑ ከፍተኛ መሆኑን የሚያመላክት መሆኑ ተመላክቷል። ቫይረሱ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለመግታትና ለመቆጣጠር የተሳሳቱ ግንዛቤዎችን ማስወገድ እንዲሁም የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ ተገቢነት እንዳለው ተነስቷል። በኢትዮጵያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ9 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። በአንድ ሳምንት ውስጥም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ውስጥ 737 ያህሉ ወደ ጽኑ ህክምና ክፍል የገቡ ሲሆን፤ 158 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል። @EthiopiaReporter
4 282
2
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የስፖርት ውርርድ ሎተሪ ድርጀቶች #Betting አስተዳደር እና ፍቃድ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የተሻሻለ መመሪያ ይፋ አደረገ። አዲስ በተሻሻለው መመሪያ የስፖርት ውርርድ ሎተሪ ድርጀቶች ፍቃድ ለማደስ ይከፍሉት ከነበረው 200 ብር ወደ 100,000 ብር ያደገ ሲሆን አዲስ ፍቃድ ለሚያወጡ ድርጅቶች ደግሞ 500,000 ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል ድርጅቶች 1.5 ሚሊዮን ብር የባንክ ዋስትና ማቅአብ ይጠበቅባቸዋል። የስፖርት ውርርድ ሎተሪ ድርጀቶች የሚሰጡት ከፍተኛ የሽልማት ጣሪያ 1 ሚሊዮን ብር እንዲሆን የሚያስገድድ ሲሆን በተጨማሪም ተጫዋች ደንበኞች ከ21 አመት በላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል። አዲስ የተሻሻለው 172/2013 መመሪያ የተለያዩ የተሻሻሉ ህጎችን ያካተተ ሲሆን መመሪያውን የማያሟሉ ድርጅቶች ላይ የመዝጋት እርምጃዎች እንደሚወስድ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታውቋል። አሁን ላይ ህጋዊ 42 የስፖርት ውርርድ ሎተሪ ድርጀቶች ሲኖሩ በቀጣይ ፍቃድ የመስጠት ሂደቱ ይቀጥላል ተብሏል። #Capital @EthiopiaReporter
Show more ...
4 750
11
በኢትዮጲያ ባለፉት 24 ሰዓታት 38 ዜጎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው እለታዊ መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 38 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል። በመላው ሀገሪቱ የቫይረሱ ስርጭት መዛመት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 4,967 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በአሁኑ ወቅት በፅኑ ህሙማን መከታተያ ውስጥ 751 ሰዎች የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። @EthiopiaReporter
4 891
5
Privacy Policy