cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የክርስቶስ ፍቅር ❤️❤️ christ of love ..

@በዚህ ቻናላችን እግዚአብሔርንና እግዚአብሔርን ብቻ የምናመልክበት እሱን የምናወድስበት ይሆናል ። 👍 በቻናላችን የእግዚአብሔርን ቃል የምናካፍልበት 👍አዳዲስ መዝሙሮችን የምንለቅበት 👍ወዘተ መንፈሳዊ መሠል ነገሮችን የምናደርስበት ነው ይቀላቀሉን።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
174Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
#ሙላኝ_ተቆጣጠረኝ 🎤#እንዳለ_ወልደጊዮርጊስ ጠልቄ መሄድ እፈልጋለሁ የእኔ እርካታ የአንተው ክብር ነው ላይ ላዩን ማለት ይቅርብኝና ይስጠም ሕይወቴ (በአንተ) በህልውናሀ l(2x) መንፈስ ቅዱስ (3X) ሙላኝ ተቆጣጠረኝ ሌላ ሕይወት አይኑረኝ (4X) ላንብብ ቃልህን ልስማ ሕግህን ላድርግ ስራዬ ደስ የሚልህን መቅደስነቴ ለአንተ ብቻ ነው የለኝም በአንተ ላይ ደባል የማደርገው ከምር ነው ከልብ ነው የአንተ መሆን ምፈልገው ማንከስ ይቅር በሃሳቤ ልከተልህ ቆርጦ ልቤ ሙላኝ ተቆጣጠረኝ ሌላ ሕይወት አይኑረኝ (4x) እኔ ግን (እኔ )እኔ ግን (4x) በጽድቅህ ፊትህን አያለሁ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ/ኝ (2x) ቁርጭምጭሚት ጋር ባለው ህይወቴ በቃኝ አልበልህ በዚህ ረክቼ ጉልበቴንና ወገቤን አልፈህ ተቆጣጠረኝ ከሁሉ ልቀህ በአንተ ተይዞ ሁሉ ነገሬ ቢያልቅ ይሻላል ቀሪ ዘመኔ ጠልቄ መሄድ እፈልጋለሁ የእኔ እርካታ የአንተው ክብር ነው ላይ ላዩን ማለት ይቅርብኝና ይስጠም ሕይወቴ (በአንተ) በህልውናሀ (2x) መንፈስ ቅዱስ (3X) ሙላኝ ተቆጣጠረኝ ሌላ ሕይወት አይኑረኝ (4X) 🎼#ሙላኝ_ተቆጣጠረኝ
Show all...
19ኢየሱስም፣ “ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰዎችን አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው። 20 ወዲያው መረባቸውን ትተው ተከተሉት። ማቴዎስ 4 : 19 19 And he said unto them, Follow me, and I will make you fishers of men. 20 And they straightway left their nets, and followed him. Matthew 4 : 19
Show all...
Coming soon. የምንወደው ወንድማችን ዘማሪ ሳሙኤል ተስፋ ሚካኤል አሁን ላይ አዲስ አልበም እየሰራ ይገኛል ። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ህዝቡ የሚያደርስ ይሆናል ይህን የተወደደ አልበም
Show all...
ገብታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ ።
Show all...
“ወንድሞቼ ሆይ፤ ነጻ እንድትሆኑ ተጠርታችኋል፤ ነጻነታችሁን ግን ሥጋዊ ምኞታችሁን መፈጸሚያ አታድርጉት፤ ይልቁንም አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል።” — ገላትያ 5፥13 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
Coming soon . Coming soon 😇😇😇
Show all...
ኢየሱስ በመስቀል ሞቱ፣ በሥጋው፣ የመቅደሱን መጋረጃ ቀዶልን ወደ እግዚአብሔር ፊት አቅርቦን ሳለ፣ ዛሬ ቤተ ክርስቲያንን «የሰው መጋረጃ» ጋርዷት፥ የተሰቀለውን-ክርስቶስ ሰዎች እንዳያዩት እንዳያደርግ፣ ምን ያህል ስለተግዳሮታችን ልንጠነቀቅ ያስፈልግ ይሆን? በተለይ ምስባክ ላይ የምንቆም ሰዎች? የቡድን ፎቶግራፍ እንኳ ስንወስድ፣ ከኋላችን የቆሙትን እንዳንሸፍን ብርክክ እንላለን፡፡ በተለይ «ዘለግ» ያለ ቁመና ያለን፡፡ በቤቱ ውስጥ፡ ሥጋዊ-መጋረጃዎች ሆነን ከመገኘት ከእያንዳንዳችን የመንፈስ ቅዱስ ግሳጼ አይለየን፡፡ ሁላችን በርከክ እንበል፣ 'ዘለግ ያልን ጎንበስ፣ ማራኪ 'መንፈሳዊ ደም-ግባት' ያለን ሙሴያዊያንና ኤልያስያውያን፣ ከአንገታችን ሰበር፤ 'አይን- ያዠ' ሥጦታ ያለን 'ግርማ ሞገሳሞች' ሰዎች ክርስቶስን በጸጋችን ውስጥ ማየት ስለሚፈልጉ፡ ዝቅ እንበል፡፡ ኢየሱስ ይታይበት፡፡ አብ ዛሬም «የምወደው ልጄ እርሱ ነው፡ እርሱን ስሙት» የሚለው ድምጹ አልተለወጠም፡፡ ጌታ ይርዳን፡፡ ሳምሶን ጥላሁን
Show all...
Watch "Oh Nefse (ኦ ነፍሴ) - Oh My Soul by Dawit Getachew - Bless & affectionately praise the Lord, O my soul!" on YouTube https://youtu.be/mTrnpfDZ2bI
Show all...
Watch "#ፓስተር_ተከስተ_ጌትነት#ልበልህ_መልካም_ነህ"pastor Tekeste Getenet“LEBELEHMELKAM NEH”new Protestant mezmur2021/2014" on YouTube https://youtu.be/aSSz15TPTsA
Show all...
✍ ኢየሱስ ሽልማት ወይስ ስጦታ ************************* ✍ ሽልማት የተሸላሚውን የጥረት ውጤት ስጦታ ደሞ የሰጭውን ለጋስነት ወይም ወዳጅነት ያሳያል፡፡ 📌 ሽልማት ሰርተን የምንቀበለው ስጦታ ደሞ ሳንለፋ የምናገኘው ነው፡፡ ✍ ሽልማት የሚገባን ነገር ሲሆን ስጦታ ግን የማይገባን ነገር ነው፡፡ 📌 ክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን እንጂ አልተሸለምነውም፡፡ ✍ ኢየሱስ ሕይወት እንዲሆነን በስጦታ እንጂ በሽልማት አልተቀበልነውም፡፡ 📌 እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሸልም ድረስ ሳይሆን እስኪሰጥ ድረስ አለምን እንዲሁ ወዷልና ኢየሱስ ሽልማታችን አይደለም!! ✍ ለተወደደ በሙሉ ስጦታ ይሰጥ ይሆናል የተወደደ ሁሉ ግን አይሸለምም፡፡ 📌 ኢየሱስ ሽልማት ቢሆን ኑሮ አንዳችንም አይገባንም ነበርና የዘላለም ሕይወት ባላገኘን ነበር፡፡ ነገር ግን ስጦታ ነውና እንዲሁ ተወደን ተቀበልነው፡፡ ✍ ለመዳን ካልሰራን ፣ ለመፅደቅ ካልለፋን ፣ በፀጋ ድነናል ካልን ፣ የራሳችን ጥረት የለበትም ካልን ፣ ስጦታው ራሱ የተሰጠን ባልነበርንበት ነው ካልን ፣ ኢየሱስ የሚባል አዳኝ እንዳለ እንኳን የማናውቅ ከነበርን ፣ ለተስፋው ቃል እንግዶች ከነበርን እውነት ህይወት መንገድ የሆነው ኢየሱስ ስጦታችን እንጂ ሽልማታችን አይደለም፡፡ 📌 እንዲሁ በፀጋ የሆነ #ነፃ_ስጦታ እንጂ እንዲሁ በፀጋ የሆነ #ነፃ_ሽልማት የለም፡፡ ✍ ሽልማት በራስህ ሲያስመካህ ስጦታ ደሞ በሰጭህ ያስመካሀል!! 📌 ሽልማት የጥረት ውጤት ስጦታ የፍቅር ውጤት ነው!! ✍ ሽልማት ያለ ውድድር የለም.....ስጦታ ደሞ በውድድር የለም!! 📌 በሽልማት ጭብጨባው ለተሸላሚው ነው በስጦታ ጭብጨባው ለሰጪው ነው!! ✍ ሽልማት ለአሸናፊ ነው....ስጦታ ግን ለተወዳጅ ነው!! 📌 ኢየሱስን እንዲሁ በነጻ ተሰጠን ብለን ስናበቃ ሽልማቴ ነህ ማለት እርስ በእርሱ ይታኮሳል!! ኢየሱስ ስጦታችን እንጂ ሽልማታችን አይደለም!! በስጦታው ተደሰቱ!! #ሄኖክ_አሸብር http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD
Show all...
Watch "ፓስተር #እንዳለ_ወልደጊዮርጊስ "አልከሰርኩም" Pastor Endale Woldegiorgis “ALKESERKUM”new Protestant Mezmur 2021/2014" on YouTube https://youtu.be/ELGpyfKj7xg
Show all...
ሌላ ነገር ሁሉ ከኛ ላይ ይርገፉና እሱን መፈለግ መጠማት በክርስቶስ ስም ይሁንልን ።🙏🙏
Show all...
የክርስቶስ ፍቅር ❤️❤️ @በዚህ ቻናላችን እግዚአብሔርንና እግዚአብሔርን ብቻ የምናመልክበት እሱን የምናወድስበት ይሆናል ። 👍 በቻናላችን የእግዚአብሔርን ቃል የምናካፍልበት 👍አዳዲስ መዝሙሮችን የምንለቅበት 👍ወዘተ መንፈሳዊ መሠል ነገሮችን የምናደርስበት ነው ይቀላቀሉን። https://t.me/christloved
Show all...
ተሐድሶውና ማርቲን ሉተር በቤተ ክርስቲያን የተሐድሶ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የነበረው ጀርመናዊው ማርቲን ሉተር (Nov.10, 1483 - Feb.18, 1546)፣ "ጻድቅ በእምነት ይኖራል" (ሮሜ 1፡17) የሚለውን ቃል መሠረት በማድረግ፣ በወቅቱ የነበረውን የሮም ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፣ በተለይም በድነት፣ በአማኝና በቤተ ክርስቲያን ማንነት ዙሪያ ፊት ለፊት በመቃወም የጀመረው ታላቅ የተሐድሶ ንቅናቄ በቅርቡ አምስት መቶ ዓመት አልፎታል። ይህን ታሪካዊ ቀን ለማስታወስ በዓለም ዙሪያ፣ በተለይም በትውልድ ሀገሩ በጀርመን ዝግጅት ተደረጎ ነበር። ሉተር የወቅቷን የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ስሁት አስተምህሮና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በቀጥታ የሚጋጭ ተልኳዊ የራስ-ግንዛቤ የተቃወመበት 95 ጭብጥ ሀሳብ የያዘ ጽሑፍ "thesis" በቪተንበርግ ከተማ ቤተ ክርስቲያን (Wittenberg Castle Church) በር ላይ የለጠፈው ጥቅምት 31፣ 1517 ነበር። ይህቺ ቀን፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፍታለች፤ የታሪክም መገንጠያ ሆና ትታሰባለች። ሉተር ማንም ሊደፍረው የማይችለውን የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንን የተሳሳተ መሠረት፣ በነፍሱ በመወራርድ አናውጧል። April 18, 1521 በንጉሥ ቻርልስ አምስተኛ (የስፔንና የሮማ ካቶሊካዊ ግዛት ንጉሥ) በተሰየመው የቤተ ክህነት ፍርድ ቤት፣ አስተምህሮውን እንዲሽር (recant) በተጠየቀ ጊዜ፡- በታሪክ "እነሆ እዚህ ቆሜለሁ" (Here I stand) በመባል በሚታወሰው የሙግት ንግግሩ እንዲህ ብሎ ነበር፦ "የተከበሩትን ፓፓ ጨምሮ፣ ማንም ግለሰብ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማስረጃነት በመጥቀስ ስህተቴን ካሳየኝ፣ ጽሁፌን በአደባባይ አቃጥላለሁ። ሆኖም ኅሊናዬ የቅዱሳት መጻሕፍት እውነት እስረኛ ሆኗል፤ ስለዚህ ከበራልኝ የእውነት ብርሃን ፈቀቅ ለማለት ኅሊናዬ አይፈቅድም፤ አያዋጣኝምም!" May 8, 1521፣ ፍርድ ቤቱ "ኑፋቄ" በማለት ከቤተ ክርስቲያን አባልነት በሞት ፍርድ አገደው። ሥራዎቹም ታገዱ፤ ማንበብም ሆነ ማሰራጨት ሕገ ወጥ ድርጊት መሆኑ ታወጀ። ይሁን እንጂ፣ ሉተር እስከሞተበት ጊዜ ድረስ በታማኝት፣ በሞት ጥላ ውስጥ እያለፈ አገልግሏል። ሉተር በብዙ መከራ ውስጥም እያለፈ፣ ውሎው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር፣ ልቡም በመንግሥቱ ንጹህ የወንጌል ሥራ ላይ ያተኮረ ነበር። ትጉህ፣ የማይለጉም፣ ለጠራው እግዚአብሔርና ለበራለት እውነት ታማኝ ነበር። በዓመት ሁለት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ከጥግ እስከ ጥግ ያነብ ነበር። በሙሉ ጊዜ ፕሮፌሰርነት እያገለገለ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በጀርመንኛ ተርጉሞ፣ ለገዛ ሕዝቡ የማይጠፋ ርስት አድርጎ አውርሷል። የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ሕይወቱ እስትንፋስ አድርጎ ነበር የሚይስበው። የዘወትር የውስጥ ጩኸቱም;፟ "ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ።" (መዝ 119፡18) የሚል ነበር። እንዲህም ብሎ ጽፏል፦ "መጽሐፍ ቅዱስ ዛፍ፣ በውስጡም የተጻፉት ቃላት ቅርንጫፎች ቢሆኑ፣ እያንዳንዱን ቅርንጫፍ ደጋግሜ ወጥቼ ወርጄበታለሁ።" (What Luther Says: An Anthology, Vol. 1, p. 83)። ይኽም ለቃሉ የነበርው ረሃብ ያሳየናል። ከርስቶስን ያማከለ ታላቅ የቃሉም ሰባኪ ነበር። ከ1510-1546 ሦስት ሺህ ጊዜ ያህል ሰብኳል። ያም ማለት በአንድ ቀን ተኩል፣ አንድ የወንጌል ስብከት ማለት ነው። ምንም እንኳን፣ የቀድሞ አባቶችን ሥራዎች ጠንቅቆ ቢያጠናም፣ የስብከቱ ዋና ምንጭ ቅዱስ ቃሉ ነበር። የጸሎት ሰው ነበር - ከልቡ! ከከንቱ ኀይማኖተኝነት የመነጫ ሙት ልምምድ ሳይሆን፣ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል የተደገፈና ሕያውነት የተሞላ ጸሎት ነበር። የተሃድሶውም ጩኸት መሠርቱ፣ የእግዚብሔር ቃልና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ነበር። የእኛስ የስብከታች መካከለኛ ምን ይሆን? መዝሙር 46 ብዙ አጽናንቶታል። ልጅ ሞቶበታል፤ ከስሜት መርበሽ ጋር ታግሏል። እድሜውን በሙሉ በሞት ዐዋጅ ጥላ ውስጥ ነበር የኖረው። ማንም ሰው ቢያገኘው፣ እንዲገድለው ሕጋዊ ፈቃድ የሰጠው የቻርልስ አምስተኛ የሞት ዐዋጅ እንዲህ ይል ነበር፡-"ሥጋዬ፣ ነፍሴ፣ ደሜ፣ በመንግሥቴ ግዛት ያለ አስተዳደርና ዜጋ ሁሉ ሉተርን ከምድር ገጽ እንዲያጠፋው አዝዣለሁ" (Heiko A. Oberman, Luther: Man Between God and the Devil, 29.)። በኩላሊት ህመምና የራስ ምታት (ማይግሬን)፤ በሆድ ድርቀት፤ በጆሮ ቁስልና የትኩሳት ንዳድ ይሰቃይ ነበር። በአጋንት መንፈስ ነው የሚመራው፤ ሀሰተኛ ነብይም ተብሏል። August 2, 1527 የጻፈው ማስታወሻ እንዲህ ይላል፦ "ከሳምንት በላይ በሞትና በሲዖል ጥላ ውስጥ ተመላልሻለሁ። በክርስቶስ ላይ ያለኘ መታመን እስኪፈተን ድረስ መላው አካሌና መጋጣጠሚያዎቼ ሁሉ ታመዋል። የመከራ ጎርፍና ማዕበል ተባብረው፣ እምነትን የሚፈትን ድቅድቅ የቀን ጨለማ ውስጥ ከተውኛል። ተስፋ መቁረጥ ልቤን አድክሞታል። ይሁን እንጂ በቅዱሳን ምልጃ ተርፈኩኝ፤ እግዚአብሔርም በምህረቱ አሰበኝ፤ ከመከራዬም አሳረፈኝ። " (Man Between God and the Devil, 323.) እናም ከዳዊት ጋር፦ "አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን፣ በሚደርስብን መከራ ሁሉ የቅርብ ረዳታችን ነው። ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ እንኳ፣ ተራሮችም ወደ ባሕር ጥልቅ ቢሰምጡ አንፈራም። ውሆች ቢያስገመግሙ፣ ዐረፋ ቢደፍቁም፣ ተራሮችም ከውሆቹ ሙላት የተነሣ ቢንቀጠቀጡም አንደናገጥም።" (መዝ 46:1-3) በማለት ዘምሮ፣ በጸጋው ለትውልድ የሚተርፍ ሥራ ሠርቶ አለፈ። ጌታ ተሃድሶውን ይስደድልን፣ ዘመንን መረዳት እንደአባቶች ይለግሰን! አሜን! (በዶ/ር Girma Bekele ) #ተሐድሶው #ማርቲን_ሉተር @christ of loved❤️❤️ @christ of loved ❤️❤️
Show all...
#ምስክርነት ሴት አገልጋይ ነኝ ከ10 ዓመት በላይ #ፖርኖግራፊ እና #እራስን_በራስ_ማርካት (masturbation) ውስጥ ነበርኩ Selam ena L ebalalew set negn be #porn ena be #masterbation lememed wuset yegabahut gena lej hogne nw #10_amet yalefegnal endet ena mecha endegemrkut balwekem lej hogne gn yemadergew sekfagn ena sw seyanadedegn nber eyadekugn semta gn porn mayet jemerku agote 5 kefl gena segba selk setagn eza laye game dawload lemaderg sefelg nber xxx video mayet yejemrkut tv layem ye #dance mnamn leloch becha semet keskash tarikochen be selka aneb nber lemakome kal gebcha selyem nber gn gefa bel and sament wyem hulet sament bekoye nw degma emelsalwe agelagye negn zemare agelglote mnm fera alenberwem beze meknyat endhonem algebagnem nber bezu selote selyalew bezu agelglotoch tekafeye endetlwetku amegne nber gn melsha erasen ezew magegneta mecham yemalelawet meslogn nber gn le geta yemsanew nger yelm be eshetu alefo endelwete redagn ahun 2 wer lehongn nw semetu enkwan besamagn rasen megzat cheyalew Eshetun geta yebarkew betam ken sw nw Wendmoche ena ehetoche ene yememekrachu nger be nore andegna nger selkachu laye kalu channeloch leave maderg yalbachun leyu agelglote legezaw makome albachu ena negrun be fisum le eraschu becha atyazut sw councils leyeragchu yegbal ena le sw tenagerut keze befit leloch tenagre ignore tedergeyalew gn eshetu endeza aldergem selzi Anbibachu enantem leloch share adrgu enlalen. @Christ fo loved ❤️❤️ @christ of loved❤️❤️
Show all...
Watch "ሲረዳኝ አየሁ !!! ድንቅ የአምልኮ ጊዜ ከዘማሪ ጵንኤል ጋር.... || Prophet Suraphel Demissie || PRESENCE #GospelMission" on YouTube https://youtu.be/Frbcvsb1__g
Show all...
Watch "ENDASHAW TEKA ||በምህረትህ || New Ethiopian Protestant Mezmur 2020" on YouTube https://youtu.be/ij4_6NXcRF8
Show all...
Watch "Surafel Hailemariyam አመሰግንሃለሁ [ Amesegenhalew ] [ New Ethiopian Gospel Song 2021 ]" on YouTube https://youtu.be/nwkX8rjEJjU
Show all...
👉👉መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ጥሩ ውጤታማ ሆነው የሚሰሩበት እግዚአብሔርም እንዲረዳቸው ለመሪዎቻችን አጥብቃችሁ እንድትፀልዩላቸው በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።🙏🙏🙏 የክርስቶስ ፍቅር ❤️❤️
Show all...
ሰበርዜና! የኢዜማ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የትምህርት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን #የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል:: የኦነግ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ቀጀላ መርዳሳ ለባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። ሹመታቸው የፀደቀው ሚንስትሮች ስም ዝርዝር 1. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር አቶ ደመቀ መኮንን 2. ግብርና ሚኒስትር--- አቶ ዑመር ሑሴን 3. ኢንዱሰትሪ ሚኒስትር--- አቶ መላኩ አለበል 4. የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር-- አቶ ገብረመስቀል ጫላ 5. የማዕድን ሚኒስትር ---ኢንጂነር ታከለ ኡማ 6. የቱሪዝም ሚኒስትር ---አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ 7. የሥራና ክህሎት ሚኒስትር--- ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል 8. የገንዘብ ሚኒስትር--- አቶ አሕመድ ሽዴ 9. ገቢዎች ሚኒስትር---አቶ ላቀ አያሌው 10. የፕላንና ልማት ሚኒስትር--- ዶክተር ፍጹም አሰፋ 11. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ---አቶ በለጠ ሞላ 12. የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር-- ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ 13. የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ---ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ኢብራሂም 14. የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢነጂነር ሃብታሙ ኢተፋ 15. የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ 16. የትምህርት ሚኒስትር-- ዶክተር ብርሃኑ ነጋ 17. የጤና ሚኒስትር --ዶክተር ሊያ ታደሰ 18. የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ 19. የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ 20. የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ 21. የፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ 22. የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም
Show all...
Watch "በህልውና በመንፈስ ቅዱስ መረስረስ... ዘማሪ ጵንኤል || Prophet Suraphel Demissie || PRESENCE #GospelMission" on YouTube https://youtu.be/SeRgukjpu6A
Show all...
Watch "Surafel Hailemariyam @Kingdom Sound Worship Night, Menfes Kidus- Original Song By Aster Abebe" on YouTube https://youtu.be/o8eFuC9RA0A
Show all...
ድጋፍ ለወንድማችን ! አብዛኛው ሰው በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ያውቀዋል ወንጌል ሰባኪው ወንድማችን ኤፍሬም። ወንድማችን ኤፍሬም በአሁኑ ሰዓት እንደወትሮ ወንጌል በከተማው በገጠሩ በእግሩ እየኳተነ እየሰበከ አይገኝም። አሁኑ ሰዓት ይልቁንም በሆስፒታል ይገኛል ኤፊ ኩላሊቱን የታመመ ሲሆን የህክምና ባለሞያዎች እንዳሉት ከሆን የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልገው እና ለንቅለ ተከላውም እጅግ ብዙ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ አሳውቀዋል። ይሄንንም ወጪ በመሸፈን ወንድማችንን ኤፍሬም ከገባባተ አሰቃቂ ሁኔታ እንዲወጣ በር ከፋች ነገር ተቀንሷል። ለወንድማችን ኤፍሬም ገቢ ማሰበሰቢያ የተዘጋጀ የአምልኮ ምሽት የፊታችን እሁድ በዘፀአት ቤተክርስቲያን ተዘጋጅቷል። የተለያዩ የእግዚአብሔር ሰዎች የሚያገለግሉ ሲሆኑ ወንድማችንን ለማደን እንትባበራለን። @christ_zene @christanzenabot
Show all...
ዘኍልቁ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²² እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ²³ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦ ²⁴ እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤ ²⁵ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤ ²⁶ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።
Show all...
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊 🌻🌻 መልካም 🌻🌻️ 🌻🌻 አዲስ 🌻🌻 🌻🌻 ዓመት 🌻🌻️ 🌻️🌹⁣🌾🌻💐🌷🌻 🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊 🌻🌻💐💐💐🌻🌻 🌻🌺 እንኳን 🌺🌻 🌻🌹አደረሳችሁ🌹🌻 🌻🌻🌾🌾🌾🌻🌻
Show all...