cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መዝሙረ ስንክሳር

ይህ ቻናል:-🌹🌹🌹🌹🌹 🌹የቸብቸቦ መዝሙሮች 🌹የፆም እና የንስሀ መዝሙሮች 🌹የተለያዩ ስብከቶች 🌹ኦርቶዶክሳዊ ፎቶዎች 🌹መንፈሳዊ መፅሀፍት በ pdf 🌹ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄዎች 🌹መንፈሳዊ መፅሀፍት በ ትረካ.....🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹የሚያገኙበት ቻናል ነው https://t.me/+lGweAO0dfHpjN2I0 ሊንኩን ይጫኑ::

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
257Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

I'm listening to "ያሬድ ፈልፈለ ማሕሌት" by ዝማሬ ዳዊት.
Show all...
👑👑👑👑✝✝✝✝👑👑👑👑🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 አሰርገዋ ለኢትዮጵያ ሰማይ በስብሐት ወበ ሃሌሉያ ያሬድ ካህን ጥዑመ ልሳን ለቤተ ክርስቲያን ፀሓያ ✡✡✡✡✡✡✡✡✡✡✡✡ ቅዱስ ያሬድ ሚያዚያ 5 ቀን 505 ዓ.ም በአክሱም ከተማ አባቱ /አብዩድ/ይስሀቅ ከ እናቱ ከክርስቲና /ታኡክልያ/ ተወለደ። ቅዱስ ያሬድ አባቱ ገና በሰባት አመቱ ሲሞትባት እናቱ በአጎቱ ወስዳ አኖረችው ። ቅዱስ ያሬድ ገና በልጅነቱ ከጓደኞቹ ይልቅ እርሱ ትምሕር አልገባው እያለ ይቸገር ነበር ዳሩ ግን አልገባው ማለቱ የጌታ ታምር ይገለፅ ዘንድ ነው። ምንም ትምሕርት አልገባው ቢለው በእመቤታችን በጌታችን ፍቅር የታሰረ በመሆኑ ዘወትር ይፆማል ይፀልያል። መምህሩ የቀለም ጥያቄ ሲጠይቁት ለመመለስ በመቸገሩ መምህሩ በዱላ ቅጣቱን አፀኑበት በዚህም የተማረረው ቅዱስ ያሬድ ኮብልሎ ወደ ማይኪራሕ የተባለች ስፍራ ዘለቀ በወቅቱም ደክሞት ስለነበር ዛፍ ስር እራሱን ለማሳረፍ ጋደም አለ።በተኛበት ዛፍ ስር አንዲት ትል ከዛፉ ጎጥ ላይ ለመውጣት ስትጥር ትወድቅ ስትነሳ ስድስት ጊዜ ተመላለሰች አልቻለችም በሰባተኛው ስትሞክር እንደምንም ብላ ወጣች። ይህን የተመለከተው ቅዱስ ያሬድ እኔ ከፍ እሷ አልሻልም ወይ ብሎ እራሱን ይጠይቃል ከዚህም በኋላ ቅዱስ ያሬድ ሮጦ ወደ መምህሩ በሐጓዝ ያቋረጠውን ትምሕርት ይቀጥላል በጾም በፀሎት አብዝቶ በትጋት ቀጠለ እግዚአብሔር በድንግል ማርያም ስም የጥበብ ፅዋን አጠጣው ። ቅዱስ ያሬድ አልገባህ ያለው ትምህርት በአጭር ጊዜ ውስጥ ብሉይና አዲስ ኪዳንን ወሰነ በሚስጢር ባህር ውስጥ ጠለቅ ያን ጊዜ በፀሎት ሳለሰማያዊ ዜማ ተድሞርን መጣበት።ሶስት ወፎች በመላዕክት አምሳል መተው አነጋገሩት ወደ ሰማይ ነጥቀው ወሰዱት ከመላዕክቱ ማሕበር አደረሱት።ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክቱ ልዩ የሆነ የምስጋና ዜማ ሚስጢር አዳመጠ።ይህን ዜማ ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙት ይዞት ወደ ምድር እንዲወርድ የተፈቀደለት ግን ቅዱስ ያሬድ ብቻ ነው። ቅዱስ ያሬድ ወደ ምድር ተመልሶ በአክሱም ከተማ ንጉሱ ፌት በታላቅ ተመስጦ አመሰግኗል። በዚህም የከተማው ህዝብና ንጉስም አደነቁት።ቅዱስ ያሬድ በአክሱም ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ከቆየ በኋላ ለእመቤታችን አንቀፀ ብርሀን ደርሶላት ከፍ ሀገሩ ወጥቷል።ቅዱስ ያሬድ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በመዘዋወር ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል። ቅዱስ ያሬድ አምስት የዜማ አይነቶች ደርሷል:: እነሱም ድጓ, ፆመ ድጓ, ዝማሬ, መስዋዕት,እና ምዕራፍ ሲሆኑ አስራ አንድ የዜማ ምልክቶችን ሰርቷል ለቤተክርስቲያን ሰርቷል። ቅዱስ ያሬድ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከራስ ጠጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ሙሉ አካሏ ነው። በዚህም ሊቃውንቱ በብዙ ስያሜዎች ይጠሩታል ጥዑም ልሳን ንህብ ማህሌታይ ካህን ሊቀ ሊቃውንት የሱራፌል አምሳል የቤተክርስቲያን እንዚራ መዘምር ወበድርሳን ልዑለ ስብከት በማለት ይጠሩታል።ቅዱስ ያሬድ በ 571 አመቱ በተወለደ በ 71 አመቱ ተሰውሯል ። የቅዱስ ያሬድ ፀጋ እረድኤቱና በረከቱ በሁላችን ላይ ይደርብን🙏 መልካም በዓል🙏 አሜን🙏 ⛳⛳⛳⛳🌴 💫💫💫💫💫💫💫💫
Show all...
ፍጡራንን ነን ግን?🤔 📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢 "እየጠላን የምናደርገው" 💭💭💭💭💭💭🍃🍃❖❖❖ ብዙ ሰው ‹‹እኔ ሐሜት አልወድም፡፡ ግን ማማት የሚወዱ ጓደኞች አሉኝ›› ይላል፡፡ አሁን እርሱ ምን እያደረገ ነው? ‹‹ወዳጆቼ ሐሜተኞች ናቸው›› ሲል እያማቸው አይደለምን? ወይስ ለእርሱ ሲሆን ሐሜቱ ተለውጦ የመረጃ ቅብብል ይሆናል?! በነገራችን ላይ ይህ የዚህ ጽሑፍ መግቢያ ራሱ ሐሜት ነው። የማንወደው ነገር ግን እየጠላንም ቢሆን የምናደርገው ኃጢአት ሐሜት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሜተኛ ሆኖ የተጠቀሰው በእባብ ያደረው ሰይጣን ነው፡፡ በመጀመሪያ የታማው ደግሞ እግዚአብሔር ሲሆን፣ ሐሜቱን ሰምታ ሳትመረምር የተቀበለችውና ለስሕተት የቸኮለችው ሴት ሔዋን ነበረች፡፡(ዘፍ 3፥1-5) የሰይጣን ሐሜት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አንደኛ "አትሞቱም፤ እንደ እርሱ እንዳትሆኑ ነው የከለከላችሁ" በሚለው ንግግሩ "እግዚአብሔር ዋሽቷችኋል" እያለ ፍቅሩን እንድትጠራጠር እያደረገ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ከዛፉ ብትበሉ እንደ እርሱ ትሆናላችሁ በማለት የእግዚአብሔር አምላክነት "የዛፍ ፍሬ" በመብላት የተገኘ መሆኑንና እርሱም እንደ እነርሱ የነበረበት ጊዜ እንዳለ እንድታስብ እየገፋፋት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስም ማጥፋት (Character assassination) ከየት ሊገኝ ይችላል? ሰይጣን በነገር ሁሉ ፍጹም የሆነን አምላክ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሐሰት ፈጥሮ ለማማት ወደ ኋላ ካላለ፣ አንዳች ጉድለት የማያጣብን እኛማ ከሐሜቱ ጅራፍ ልናመልጥ እንደማንችል ሊታወቅ ይገባል፡፡ በተለይ በአሁን ጊዜ ሐሜት በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሥሩን ሰድዷል። እንደውም ባልንጀራን ማማት እንደ ምግብ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን በዚህች ደሃ አገር ከመጠን በላይ ወፍረን እንቸገር ነበር። ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን የሐሜት አውድማዎች ሆነዋል። በየገጾቻችን ከሽነን የምናቀርባቸው ጽሑፎች ጠረናቸው የሰው ሥጋ የሰው ሥጋ ይላሉ። ፊታችን በሐሜት ወይቦ ሁለት መልክ ካወጣን ቆየን። ይኸው ሳንባችን በማማት አየር ተመርዞ ሳሉ ከበረታብን ሰነባብተናል። ወዳጃችንን የማናማበት ብቸኛው ጊዜ ከእርሱ ጋር የምንሆንበት ሰዓት ነው። ያውም ደግሞ ያንኑ ጊዜ ሌላኛውን ሰው ለማማት ካልተጠቀምንበት ማለቴ ነው። ሊቁ ዮሐንስ ካዝያን እንደሚናገረው ሰው ከሚጠቅመው ቃለ እግዚአብሔር ይልቅ የማይጠቅመው ሐሜት ያጓጓዋል። የአምላክ ቃል ሲነገር እንቅልፍ እንቅልፍ የሚለው ሁሉ፣ የሐሜት ነገር ሲሆን ግን እንደ እርሱ ንቁ የሚሆን የለም። በጥፍሩ ቆሞ ይሰማል። ሌሊቱን ሁሉ ሳይተኛ ቢያድር ደስ ይለዋል። ለመሆኑ ባልንጀራችንን ስለ ምን በቀስታ እናማዋለን? የወዳጃችንንስ ውድቀት በማውራት በእኛ ላይ የምንጨምረው ምን በጎ ነገር አለ? በሰው ፊት መልካም እየመሰልን ከኋላው ግን ስለ እርሱ ውድቀት በማውራት የራሳችንን ደረጃ ከፍ ማድረግ አይቻልም። ስለ ሌሎች በማውራት የምናጠፋውን ሰዓት ራሳችንን ለማሳደግ ብንጠቀምበት ኖሮ "መኖራችንን ትርጉም እንዲኖረው" ማድረግ ይቻለን ነበር። "ንጹሕ ወዳጅነት" ሐሜትና ማሾክሾክ የሌለባት የታማኞች ጌጥ ናት። የሐሜት ስለታቸውን ያልጣሉ ሰዎች "እውነተኛ ባልንጀርነት"ን አያውቋትም። አንተ በፍቅር ወዳጅ አድርገህ ከፊትህ ስታቀርባቸው እነርሱ ከኋላህ ሆነው የሚያሙህን አትጥላቸው፤ አትጣላቸው። ነገር ግን የሐሜቱ እርሾ እንዳያገኝህ ቶሎ ተለያቸው። ከፊትህም አድርገህ አታሰቃያቸው። የእነርሱ ቦታ ከኋላህ መሆን ነው። ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል። ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም። "ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" ገላ 5፥15 ይቆየን💧🙏 ⛳⛳⛳⛳⛳ ✤🕯ሰናይ ሌሊት ይሁንልን 🙏🕯✤ 🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
Show all...
እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፦ ፩ኛ. ትዕቢተኛ ዓይን፥ ፪ኛ. ሐሰተኛ ምላስ፥ ፫ኛ. ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ ፬ኛ. ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ፭ኛ. ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ ፮ኛ. በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር ፯ኛ. በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ። ምሳሌ 6÷16-19
Show all...
H
Show all...
H
Show all...
H
Show all...
Show all...
መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች❔

💠 እንኳን ደና መጡ ! 💠 ጥያቄዎች ➱ @Orthodox_question መዝሙር ➱ @Orthodox_mezemur መፅሐፍ ➱ @Orthodox_book መፅሀፍ ➱ @EOTC_books ግጥም ➱ @Orthodox_poem በአላት ➱ @Orthodox_bealat ፊልም ➱ @Orthodox_film ብራና ➱ @EOTC_library 💠 @EOTC_library_bot 💠 ለአስተያየት ➱ @Orthodox2_bot