cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

GOD WITH US

የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ ውድ የጣቢያችን አባላት በሙሉ ይህ የቴሌግራም ጣቢያ ቃለ-እግዚአብሔር የምንካፈልበት መጽሐፍ-ቅዱሳዊ እውቀት ምንጨብጥበት የወንጌል ጣቢያ ነው፡፡ "ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።" —ማቴዎስ 1:23—

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ናፍቀናል ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና፤ አንተ የሌለ እስኪመስል ቤት ወና። የሆነ ይመስላል የሰው ክፋት፤ በሰው ልብ ሰንቅሮ ገብቶዓል ጥፋት። እባክህ ናና ወደ አንተ ውሰደን፤ ወደ ዘላለሙ እረፍት ወደ ፅዬን፤ አስገባን አስገባን ንጠቀን። እዛ ሄደን ለአንተ እንስገድ እንዘምር፤ ይብቃን ሰልችቶናል የምድር ነገር። ሀያ አራት ሰዓት ሽር ጉድ እንበል፤ በብርሃን አለም በደስታ እያልን እልል። በፊትህ እናሸብሽብ እንውደቅ ለአንተ፤ እኛን ለአዳንከው ሞታችንን ሞተ። ስለዚህ እንድህ ብለንሀል፤ ውሰደን ወደአንተ ልናይህ #ናፍቀናል። #አጥናፉ ✒ናፋቂው❤❤❤💞💞💞
Show all...
ነጭ ቬሎ ለብሳ ያጌጠች ሙሽሪት ጭቃ ውስጥ ገብታ ብትገኝ። ከጭቃው እንድትወጣ ከተፈለገ በትክክል ማወቅ ያለባት ነገር ምንድን ነው? 👉ጭቃ ውስጥ እንዳለች? 👉ጭቃው በጣም አስቀያሚ እንደሆነ? በእርግጥ እነዚህን ነገሮች ብታውቅ ይጠቅማት ይሆናል። ቢሆንም ግን ከጭቅው እንድትወጣ ማወቅ ያለባት ዋናው ነገር- 👉የለበሰችው ንፁህ፣ ነጭ፣ ውድ እና ጭቃ #የማይመጥነው ልብስ መሆኑን ነው። የልብሱን ንፅህና እና ዋጋ ስትረዳ የት መዋል እንዳለባት ይገባታል። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ከሐጢአት ልምምድ ለመውጣት መፍትሄው በየቀኑ ስለሰራሀው ኃጢአት ዝርዝር ቁጭ ብለህ ማሰብ ሳይሆን አንተ ያለህን #ክብር ማወቅ ነው። #የንጉስ ልጅ መሆኑን ያልተረዳ የንጉስ ልጅ ቆሻሻ ሰፈር ቢውል፣ ለምኖ ቢበላ አይገርምም❗ በየመድረኩ አሁን ያለንበት አዘቅት ይነገረናል። ግን ምን እንደለበስን አይነገረንም። አቤት! በክርስቶስ የለበስነውን ክብር ብናውቅ! ..እንኳን ኃጢአት፡ የምድር ክብሯ እራሱ አይመጥነንም እኮ! 🙏ጌታ አይኖቻችንን ይክፈትልን🙏 🙏Share share share share🙏 ⛓️ @berbantefeta       ⛓️ ⛓️ @berbantefeta_bot⛓️
Show all...
Repost from GOD WITH US
Show all...
GOD WITH US

የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ ውድ የጣቢያችን አባላት በሙሉ ይህ የቴሌግራም ጣቢያ ቃለ-እግዚአብሔር የምንካፈልበት መጽሐፍ-ቅዱሳዊ እውቀት ምንጨብጥበት የወንጌል ጣቢያ ነው፡፡ "ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።" —ማቴዎስ 1:23—

. #አእምሮን_ማንቃት 👇 #ክርስቲያናዊ_ጋብቻ ➊➟ አድጌአለሁ ወይ? - በአካል - በአእምሮ - በኢኮኖሚ ❷➟ መፈለግ - እግዚአብሔር መጠየቅ (መጸለይ) - በጊዜው - ትክክለኛውን ሰው ❸➟ መጠየቅ - ቶሎ ብለው እሺ የሚሉ - ልጸልይበት ጊዜ ስጠኝ የሚሉ - እራሳቸውን ከፍ ወይም ዝቅ አድርገው ጥያቄውን ውድቅ የሚያደርጉ ❹➟ መጠበቅ - ምላሽን መጠበቅ - እርሱን/ሷን ብቻ መጠበቅ - በእ/ር ፊት እየቃተቱ መጠበቅ ❺➟ በግልጽ መነጋገር - ትክክለኛ ስሙን/ ቤተሰቡን/ ስራውን/ ደሞዙን/ ራዕዩን/ ዘሩን/ - የጤና ሁኔታን/ ቁመት/ የወገብ ቁጥር - የምትወዱትን/ የምትጠሉትን/ ቀለም/ ባህሪ ❻➟ ለቤተሰብ እና ለቤ/ክ ማስተዋወቅ - ቤተሰብ ይቀበለውም አይቀበለውም - ለቤ/ክ የእጮኛን አጥቢያ ቤ/ክ ማስተዋወቅ - የጋብቻ ቀን ለቤ/ክ እና ለቤተሰብ ማስተዋወቅ ❼➟ የጋብቻ ቀን - በቤ/ክ ቢሮ ውስጥ - በቤ/ክ በአምልኮ ፕሮግራም - በሰርግ በቤ/ክ አዘጋጅተው ወይም በቤተሰብ ✍ #መጋቢ_ጣሰው_ገ/መድህን Group @Covenantsons Channel @christsbelievers
Show all...
በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ #በሞት_ጥላ_አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው። ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል። በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር የአስጨናቂውንም ዘንግ #ሰብረሃል። የሚረግጡ የሰልፈኞች ጫማ ሁሉ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፤ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል። #ሕፃን_ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል። (…ኢሳይያስ 9)
Show all...
"ተወለደ ጌታ" 05:46 | 5.4MB 🎷🎸የገና መዝሙር🎺🥁 🏵መልካም ገና🏵 🎈 @berbantefeta 🎈 🎈 @berbantefeta_bot 🎈
Show all...
👉🏻👉🏻አትቀስር!👈🏽👈🏽 ✍️ ከመንፈሳዊ ዓለም ወደ ሕይወታችን የሚመጣውን ፍሰት እንዲቋረጥ ከሚያደርጉ ትልቅ በሽታዎች መካከል አንዱ ጣትን በሌሎች ላይ መቀሰር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ኢሳይያስ 58፥9 - "የዚያን ጊዜ ትጣራለህ፤ እግዚአብሔርም ይመልስልሃል፤ ለርዳታ ትጮኻለህ፤ እርሱም፣ ‘አለሁልህ’ ይልሃል። “የጭቈና ቀንበር፣ የክፋትን ንግግርና ጣት መቀሰርን ከአንተ ብታርቅ" 👉🏻 ጣትን በመቀሰር ውስጥ የምናጣው ብዙ ነገር ሲኖር ጣትን ባለመቀሰር ውስጥ ደግሞ ትልቅ በረከት አለ። ብዙ ሰው የማያውቀው ጣቱን ሲቀስር አንድ ለሦስት እየተመራ መሆኑን ነው ፣ ማለትም አንዱን ጣት ወደ ምንቀስርበት ሰው ስናደርግ የተቀሩት ሶስቱ ደግሞ ወደኛ የሚጠቁሙ መሆናቸው ነው። በኢሳያስ 58 ውስጥ ጣትን መቀሰር ከተውን በህይወታችን እንዲህ ይሆናል ይላል... 1. ብርሃንህ በጨለማ ያበራል፤ 2. ሌሊትህም እንደ ቀትር ፀሓይ ይሆናል፤ 3. እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ይመራሃል፤ 4. ፀሓይ ባቃጠለው ምድር ፍላጎትህን ያሟላል፤ 5. ዐጥንትህን ያበረታል፤ 6. በውሃ እንደ ረካ የአትክልት ቦታ፣ እንደማይቋርጥም ምንጭ ትሆናለህ። ማቴዎስ 7 1 “እንዳይፈረድባችሁ በማንም ሰው ላይ አትፍረዱ፤ 2በምትፈርዱበትም ዐይነት ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል። #እኛ_ፈራጆች_ሳንሆን_አንድ_ቀን_በክርስቶስ_የፍርድ_ወንበር_ፊት_የምንቀርብ_ነን! በመጨረሻም ሁልጊዜ ማወቅ ያለብን ነገር የምንወስነው ክፍም ይሁን መልካም ውሳኔ አንድ ቀን በእኛ ሕይወት ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ነው ስለዚህ ጣታችንን መቀሰር እንተው። መልካም ቀን
Show all...
#ዋጋ_ከፋዩ_ደም ደም ለሥጋዊ ሕይወታችን ከሚያስፈልጉት ዋና ዋና መሠረታዊ ነገሮች አንደኛው ነው፡፡ በሰዎችና በአብዛኞቹ ባለብዙ ሴል እንስሶች የደም ሥር ውስጥ እየተዘዋወረ ምግብና ኦክስጅን ለሰውነት ክፍሎች የሚያደርስ ቆሻሻን ከሰውነት ውስጥ የሚያስወግድ ሰውነትን ከበሽታ በመከላከል ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት አስደናቂ ፈሳሽ ነው። ደም ከሕይወት ጋር በጣም የተያያዘ ስለሆነ የደም ዝውውር ሲቆም የሥጋ ሕይወት ይቆማል፡፡ ደም ሰውነታችን ጸንቶ ሕይወታችን እንዲቀጥል የሚያደርግ ከልብ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚረጭ በደም ሥሮች አማካኝነት ተዘዋውሮ እየተዳረሰ ሰውነትን የሚዋጅና ከምግብ የሚገኝ የሰውነታችን አንደኛው ፈሳሽ አካል ነው፡፡ የደም ዝውውር ከቆመ የሰው እንቅስቃሴ ይገታል፡፡ ሥጋ በሕይወት የሚቆየው በውስጡ ባለው ደም ነው፡፡ ሰውነታችን በቂ ደም ይፈልጋል፡፡ ይህንም ደም ከተለያዩ ምግቦች ያከማቻል፡፡ ደም በውስጡ የተለያየ ቅርጽና ዓይነት ያላቸው ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ ሴሎች አሉት፡፡ ነጭ የደም ሴል በሽታን ሲከላከል ቀይ የደም ሴል አየርና ምግብን ያጓጉዛል፡፡ ከሕይወት ጋር በጣም የተያያዘ ስለሆነ የደም ዝውውር ሲቆም የሥጋ ሕይወት ይቆማል፡፡ በሃይማኖታዊውም ሥርዓት ደም ሁለቱም ኪዳናት የጸኑበት ማኅተም ነው፡፡ ፊተኛው ኪዳን በእንስሳት ደም ሐዲሱ ኪዳን ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ደም ጸንተዋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ደም ሞትና ሕይወትን ያመለክታል፡፡ ዘኁ. 25:19 ነገ. 2፡22-23፡፡ በሰውነት ውስጥ የሚገኘው ደም የሚወክለው ሕይወትን በመሆኑ የፈሰሰ ደም የጠፋ ሕይወትን (ሞትን) ይወክላል፡፡ የብሉይ ኪዳን የሥርየት ሥርዓት በእንስሶች ደም ነበር፡፡ በደምና በሕይወት መካከል የጸና ትስስር ስላለ እግዚአብሔር የእንስሶችን ደም ለኃጢአት ሥርየት እንዲውል አደረገ፡፡ በብሉይ ኪዳን አንድ ሰው እግዚአብሔር ካዘዘው ትእዛዝ ወጥተው ሊሠራ የማይገባውን ኃጢአት ቢሰራ ከሠራውም በሆላ ተፀፅቶ ንስሐ ቢገባ ለኃጢአቱ ቀንዱ ያልከረከረውን ጥፍሩ ያልዘረዘውን ፀጉሩ ያላረረውን ነውር ነቀፋ የሌለበትን በግ ወደ ደብተራ ኦሪት መሥዋዕት ያቀርባል፡፡ ከሰው ተመርጦ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው በእስራኤል ከተማ የተሾሙ ካህናትም ተንሳኢው ለኃጢአት መሥዋዕት በቀረበው ጠቦት በግ ላይ እጁን ጭኖ የሥራውን ኃጢአት ይናዘዛል አስታራቂው ሊቀ ካህናት [መሥዋዕት አቅራቢው] ለመታረቂያ የመጣውን ጠቦት በግ አርዶ አወራርዶ ከበጉ ደም ወደ ደብተራ ኦሪት አስገብቶ ከደሙ በጣቱ ነክሮ የድንኳኑን መጋረጃ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል በዕጣኑም ቀንድ መሠዊያ ይቀባዋል፡፡ በኃጢአተኛው ምትክ የእንስሳት ደም ፈሶ ሞት ለሚገባው ኃጢአተኛ ሥርየት ይሆናል፡፡ ይህ የበግ ደም ከጊዜያዊ መቅሰፍት አድኖ በረከተ ሥጋ ያሰጠናል እንጂ በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት በባሕርያችን ዘልቆ የገባውን ርግምና እና ሞት ያጣናትን ልጅነት ሊያስጠን አልቻለም፡፡ የእንስሶቹ ደመ ነፍስ ናቸውና መሥዕዋቱንም የሚያቀርቡት ካህናት በእርግማና ውስጥ ናቸውና ሕያው ለሆነ የሰው ልጆች የዘላለም ካሳ መሆን አልቻሉም፡፡ ከፍጡራን መካከል የመርገም ቆጥኝን አንከባሎ የተዘጋብንን ገነት መክፍት የሚችል ዋጋ ከፋይ ደም አልተገኘም፡፡ ከአዳም ጀምሮ በብዙ ስቃይ ደረታቸውን ለጣር ደርታቸውን ለግርፋት አንገታቸውን ለሰይፍ በመስጠት ደማቸውን የፈሰሱ በርካታ ቅዱሳን ነበሩ ደማቸው ሰለፈሰሰ ግን የቀድሞ ልጅነታች ወደ ዱሮው መኖሪያችን ልንመለስ አልቻልም ደሙ በራሱ አቅም አልነበረውም እና፡፡ በአዳም ምክንያት የመጣው ዕዳ በደል በፍጥረታዊ ሰው መናሳት የማይችል ጽኑ ነበር፡፡ ነቢያቱ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ተቆጥሮ ሕዝቡንም ራሳቸውንም ከሞተ መስመለጥ አቆቷቸው { እነሆ እነተ ተቈጣህ እኛም ኃጢአት ሠራን ስለዚህም ተሳሳትን። ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።} ኢሳ 64:5 እያሉ ልያድናቸው ወደ ሚቸለው ጌታ በብርቱ ጮሁ፡፡ ምክንያቱም በአዳም አለመታዘዝ ወደ ዓለም የገባዌን ኃጢአትና የሞት ዕዳ ማጥፋት የሚቻለውና ለሰው ልጅ ሕይወትን የሚሰጠው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑ በሚገባ ተረድተዋል፡፡ እግዚአብሔር የአዳም ዕዳ ለመክፈል ለሰው ልጆች ሥርየተ ኃጢአትን ለመስጠት ደም ሳይፈር ሥርየት የለምና እግዚአብሔርነቱን ሳይተው ከሰው ልጆች መካከል እንደ አንዱ ሆነ ዳግማዊ አዳም በመባልም ተጠራ ከኃጢአት በቀር ፍጹም እኛን መሰለ፡፡ በሰይጣን ሐሳብ የተሰናከለውን የተሰነፈውን የሰው ልጅን ባሕርይ አጽንቶ አምላክነትን ሰጥቶ አሸናፊ ያደርገው ዘንድ ቃል በተዋሕዶ ሥጋና ደምን ተካፈለ {ፍጹም ሰው ሆነ}፡፡ እግዚአብሔርንም በበደልን ጊዜ የፈረደብን እግዚአብሔር በእኛና በእርሱ መካከል የቆመን የጥል ግድግዳ በደሙ የሚያፈርስልንን አንድያ ልጁን ሰጠን፡፡ ዋጋ ከፋዩ የክርስቶስ ደም ከላይ እንዳየነው በአዳምና በሔዋን የእግዚአብሔር ሕግ ሽረው የደረሰባቸው መርገመ ሥጋንና መርገመ ነፍስን የቀደሙት ነቢያትና ካህናት በጸለዩት ጸሎት በሚያቀርቡት የእንስሳና የአዕዋፍ ደም ሊያርቁት አልቻሉም ይልቁኑ እነርሱም በጥንተ መርገም ፍዳ ተይዘው ወደ ሲኦል መውረድ አልቀረላቸውም፡፡ የሚሠውዋቸው እንስሳት ፍጡራን በመሆናቸው የደማቸው መፍሰስ ምንም የሰጠን ጥቅም አልነበረም፡፡ የናዝረቱ ኢየሱስ { የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ } ዮሐ 1:29 ሁኖ በቀራኒዮ ላይ ሲታረድ ሐዲስ ኪዳን ተመሰረተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተመሰረተች ዘላለማዊ ድኅነት ተሰጠን በባሕርያችን የነገሰውን ሞት በደሙ ጠርቆ ከመንገዳችን አስወገደው ከእግዚአብሔር ቁጣ አመለጥን { ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።} ሮሜ 5:9 ቤተክርስቲያን ተቀድሳ የተመሠረተችው በክርስቶስ ደም ነው፡፡ ኤፌ. 5:26፡፡ የክርስቶስ ደም ባለሥልጣን ነው፡፡ የሞትን ደጅ ይሰብራል፡፡ በደሙ ማኅተም የታተምን ሁሉ የዘለዓለማዊ ሕይወትን ደጅ የማንኳኳት ሥልጣን አለን፡፡ የመልአኩን ሰይፍ አልፎ ገነትን የወረሰው በደሙ ማኅተም ነው፡፡ ሰማዕታት ዲያብሎስን ድል የነሡት በበጉ (ከኢየሱስ) ደም ነው፡፡ ራእ. 12:11፡፡ ታላቁን መከራ ያለፉት ብፁዓን በደሙ ኃይል ነው፡፡ ራእ. 7:14፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ኃይል በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የጠብ ግድግዳ ሰባብሮአል መጋረጃውን ሰንጥቆ ለሁለት በመክፈል መጋርጃውን ገፎታል የዲያብሎስን ዝናር አስጥሎአል ሐዲስ ኪዳን የጸናው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው፡፡ ማቴ.26÷26፡፡ ይህ ደም የምሕረት ደም ነው፡፡ የአቤልና ሰማዕታት ደም በግፍ ፈሶ ለፍርድ የሚጮህ ደም ነው የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ግን በግፍ ቢፈስም ምሕረትን ይናገራል፡፡ ራእ. 6÷10፡፡ ከዘላለማዊ ርግምን የዋጀን የክርስቶስ ኢየሱስ ደም! #ELDAAH-KNOWLEGE OF GOD JOIN US 👇👇👇👇👇 @God_with_us_Emmanuel @God_with_us_Emmanuel @God_with_us_Emmanuel @God_with_us_Emmanuel ይ🀄️ላ🀄️ሉን
Show all...
✍ርዕስ:- አቀባበል [ሉቃስ ፲ ÷ ፴፰ - ፵፪] የትምህርቱ አላማ:~ ወደ ህይወታችን የመጣው ጌታ ከእኛ ምን እንደሚፈልግ ማሳየት ክፍል-፩ ➦ማርታና ማርያም ቢታንያ በተባለች መንደር ይኖሩ የነበሩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ያስነሳው የአልዓዛር እህቶች ነበሩ። ይህ ቤተሰብ በጌታ የተወደደ ቤተሰብ እንደነበረ ቅዱሱ መጽሐፍ ያስረዳናል። ከላይ ርዕሱ አጠገብ በተጠቀሰው ጥቅስ መሠረት በዚህ የትምህርት ክፍል በአንድ ቤት ውስጥ የተስተዋለውን ሁለት የአቀባበል አይነት ከፍለን እንመለከታለን... ሁለት እህትማማቾች ልዩ እንግዳ በመቀበል ስራ ተይዘዋል። •|ማርታ ምግብ አዘጋጅታ ለማቅረብ ደፋ ቀና ስትል ማርያም ግን ቁጭ ብላ ይስተዋላል። የነገሩ ፍፃሜ እንዲህ ነው:- ማርያም መልካም እድል መርጣለች❕የማርታንና የማርያምን አቀባበል በሦስት ንፅፅረ-ርዕስ የምንዳስስ ይሆናል መልካም ንባብ.... ከአቀማመጥ አንጻር ➥ማርታን የቤት አገልግሎት ብዛት ከጌታ ድምፅ አርቋት ነበር። ለዚያም ነው ጌታን ማናገር በፈለገች ጊዜ "#ቀርባም" (ቁ.40) የሚለው... #መቼስ_የራቀ_ሲጠጋ_ነው_ቀረበ_የሚባለው.... ማርታ ታደርግ የነበረው ሁሉ ለጌታዋ ቢሆንም ወደ ድምፁ የሚያስጠጋት ሆኖ አልተገኘም። የጌታን ቃሎች የመስማት ጥልቅ ፍላጎት ቢኖራትም የአገልግሎቱ ብዛት እድል አልፈጠረላትም። ምንም ያህል ጌታ የመጣው ወደ ማርታ ቤት ቢሆንም ወደ ቤቷ ለቀረባት ጌታ በቤቷ ርቃ ነበር። ማርታን የተጠመደችበት ክፉ ሳይሆን መልካም ስራ ከጌታ ድምፅ አራቃት። ስለዚህ ማርታን የተጠመደችበት አገልግሎት ክቺን (ኩሽና) አስቀምጧታል። ➦መጽሐፍ ማርያም ተቀምጣ የነበረችበትን ቦታ ሲነግረን:- "...እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች::" ይላል |• ማርያም ግን የማርታ እንደሆነ እንጂ የማርያም እንደሆነ በማላውቀው ቤት ውስጥ አቀማመጧን ከድምፁ አንፃር አድርጋለች። የውሎ ቦታ ምርጫ (Settlement selection) ያደረገችው ከጌታ ድምፅ አንፃር ነበር። የተኘችበት ስፍራ ድምፁን ለመስማት ምቹ በሆነ የቦታ ክልል ውስጥ ነበር። [#ለጌታ_ድምፅ_ምቹ_ድባብ_ፈጣሪዎች_እኛ_ነን_እያልኩ_አይደለም] ማርያም ቅርበቷ ድምፁን ለመስማት ካላት ጥልቅ መሻት እንደነበረ የሚንረዳው እግሩ አጠገብ ያስቀመጣት ጉዳይ ቃሉን መስማት እንደነበረ ስናጠና ነው። ➥አንዳንዶቻችንን አገልግሎት አምላክ ሆኖብን ከጌታ ድምፅ አርቆናል። በበዛ መድረክ ለመስማት የፈዘዘ (የደከመ) አልያም ለቅርቡ ጌታ የራቀ ጆሮ ሆኖብናል። አቀማመጥህ/ሽ በአገልግሎትሽ ወይስ ከአገልግሎትህ/ሽ ጌታ አንፃር❓ ጸጋ ይብዛላችሁ‼
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!