የቀጠለ_በእውኑ ግን ይሄ ቃል ስለጥምቀት ያወራልን! እግዚአብሔር ለሙሴ ተናገር ብሎ የነገረው ስለ ህጻናት ጥምቀት ነው? ለምትወልደው ሴት የተፃፈውን ቀን ወስዶ ለሚወለደው ልጅ ማድረግስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው? አይገባኝም፡፡ቃሉ ሲጀመር ከላይ እስከ ታች ስለ ጥምቀት አያወራም፡፡ስለመርከስ እንጂ፡፡ታድያ በምን ሒሳብ ይሄ ሊሆን የቻለው!?
◻️
ሁለተኛው ደግሞ እንዲህ ይላል፡ ሴት ብታረግዝና ሴት ልጅም ብትወልድ እንደ መርገምዋ ወራት ሁለት ሳምንት ያህል የረከሰች ናት፤ ከደምዋም እስክትነጻ ድረስ ስድሳ ስድስት ቀን ትቀመጥ።ይሄ ደግሞ ወንድ ልጅ ከምትወልደው ቀን በሁሉም በለጥ ይላል፡፡ከወለድ በኃላ በመርከስ በአንድ ሳምንት ይሄኛው ይበልጣል፡፡ከቤት ባለመውጣትና ቤተ መቅደስ ባለመግባትም ወንድ ልጅ ከወለደቺው ሁለት እጥፍ ቀን ይበልጣል፡፡
◻️
ሴት ልጅ ብትወልድ ሁለት ሳምንት ትቀመጥ ማን? የወለደቺው ሴት፡፡ቀኑን ያዙት፡፡ከደምዋም እስክትነጻ ስድሳ ስድስት ቀን ትቀመጥ ይላል፡፡ሁለት ሳምንት 14 ቀን ነው፡፡14+66=80 ቀን፡፡እንግዲህ ይሄንን ቀን ሴት ልጅ ስትወለድ በሰማንያ ቀንዋ መጠመቅ አለባት የሚል አንድምታ አለውን? ስለ ውሃ ጥምቀትስ ያወራልን? አያወራም፡፡እንኳን ስለ ጥምቀት ስለሚወለዱት ህጻን እራሱ አያወራም፡፡ስለምትወልደው እንጂ፡፡በብሉይ ኪዳን ያለ ቃል ነው፡፡
◻️
እሺ አይቻልም ግን እንደምንም ልክ አንዳንድ ሃይማኖቶች እንዳደረጉት ቀኑን ለልጆቹ ሰጥተን የሌለውን ያልተፃፈውን በዛን ቀን ነው በውሃ መጠመቅ ያለባቸው ብንል፡፡አዲስ ኪዳን ላይ ያለውን ቃል እናፈርሳለን፡፡ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ማቴ 16፥16 እምነት ከመጠመቅ ቀዳሚ ነው፡፡ሰው ሳያምን ቢጠመቅ ጥምቀቱ በዛው ውሃ ይበለዋል እንጂ ትርጉም የለውም፡፡ያመነ ካለ ለመጠመቅ ማመን ግድ ነው፡፡ተጠምቆ ማመን አይቻልም፡፡
◻️
ምን አምነህ ትጠመቃለህ! ለመጠመቅ ማመን ከቀደመ ለማመንስ ምን ይቀድማል? ሮሜ 10፥17 እምነት ከመስማት ነው፥ መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ለማመን ቃሉን ምስማትና ማንበብ ወንጌልን መስማት ያስፈልጋል፡፡በአጭሩ ስለ አዳኙ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መስማት ነው፡፡
◻️
ታድያ ፈጣሪ አላየንም ብለን ለወለደቺው ሴት የተፃፈውን ቀን አዙረን ለተወለዱት ብንሰጥና ብናጠምቅ ስለምን ሳያምኑ ይጠመቃሉ? ከመጠመቅ በፊት እኮ ማመን ይቀድማል፡፡ህጻናቱ በዛን ሰዕት ወንጌል ሰምተው ነውን? በነዛ ቀናት ኢየሱስ አዳኝ ነው ብለው አምነው ነውን? አይደለም፡፡ስለዚህ የቃሉን እውነት ወደ ተፃፈለት ቦታ ብንመልሰው ይሻላል፡፡
S h a r e '
✳️✳️
@Yezelalemhiywet✳️✳️
✳️✳️
@Yezelalemhiywet✳️✳️
✳️✳️
@Yezelalemhiywet✳️✳️
Show more ...