cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የግዕዝ ቋንቋ መማሪያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን። የግዕዝ ትምህርቶችንና የተለያዩ ትምህርቶችን እንመማር

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
1 362Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

መለብው።። አስተዋቂ አስረጅ ሙሱን።። ጥፉ መጥፎ ብልሹ ሐለከ።። ወደረ ሰነከለ ቀየደ ሸነከፈ የከብት ሡሩር።። የተመሠረተ የተፈጠረ የተሠራ ሡጠት።። መመለስ አመላለስ ቀለንቶን።። መባቻ የወር መዠመርያ ሠርቀ ወርኅ ቀፈዋት።። ቀፎዎች ኤርግ።። ቀፎ ቅርጫት ቃል።። ፍሬ ነገር ድምጥ ቡአት።። ሙግት አበባት በሀነ።። በነነ ቡን አለ ያመድ ትቢያ ተለቅሀ።። ተለቃ ተበደረ ወሰደ የገንዘብ የትምርት የመመ።። መላ ፈጸመ ቈረጠ ገደበ #sher_sher @yegeez_memariya
Show all...
ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ። በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው። ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን! #መጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ_ገብረ_ኪዳን
Show all...
ኤሎሄ==አምላኪዬ ፈጣሪዬ ሀርድቦ==አረበደ ቸኰለ ሀዑቢም==ወፍራሞች ደንዳኖች ተሀልመ==ታለመ በህልም ታየ ሐሰየ==ዐሸ መልታሕት==ጒንጭ ፊት ሠረዝ==የቅኔ መንገድ ስም ሁለት አርዕስት ንባቡም ስምጢሩም በዋዌ እየተጫፈረ የሚሄድ ረዚም ሞት==ቀጺብ መጥቀስ በዓይን ማመልከት ረጊዕ ዖት==መርጋት መጽናት ሰብዐ ቤት==ቤተሰብ ዘመድ ወገን ቊልዝ==ቁጥቋጦ መመንጠር ደንን መጨፍጨፍ ቊር==በቁሙ ብርድ ኰሳኩስ==ዥንጉርጉር ኰሳኩስ #ለዮም_ያክለነ_ሠናይ ሶቤ
Show all...
[ፈጥኖ የሚረዳን የቅዱስ ሚካኤል ክብር በሊቁ በቅዱስ ያሬድ ድጓ] ✍ [በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] ❖♥ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፡- ╬ “ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ” (የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል፡- ❖♥ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕ 8፡2 ላይ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ ያሬድ፡- ╬ ♥ “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ” (የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ ይወጣልና) ይላል፨ ╬ ♥“አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት ለሚካኤል ሊቀ መላእክት ዘይስእል በእንተ ምሕረት መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት” (የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት ይጠቅሰዋል፡፡ ❖♥ የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡ ❖♥ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ ╬ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ” (የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድም፡- ╬ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ መልአኮሙ ሥዩሞሙ የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ” (ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል ❖♥ በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር። ❖♥ ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡- ╬ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ሊቅ” (መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ ዐመልማሎ ነው) ❖♥ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡- ╬ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ ከመ ሠርቀ ፀሓይ ሥነ ጸዳሉ” (የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ ❖♥ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡- ╬ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ” (ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው መሪያቸው ነው) ይላል፡፡ ❖♥ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡- ╬ በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ በመንክር ትሕትናከ አስተምህር ለነ ሰአልናከ” (በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ) ╬ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ” (ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡ ╬ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ” (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) አለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፨ ❤ ቅዱሳን መላእክት ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ቅድመ እግዚአብሔር በማድረስ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው በማምጣት ሰውን ከአምላካቸው ጋር በማማለድ ጸንተው ያሉ እንደኾኑ በብዙ ሥፍራ ላይ ተዘርዝሯል፡- ✍️ ለምሳሌ ያኽል ዘፍ 48፥15፤ ዘጸ 23፥20፤ መሳ 6፥11፤ ኢዮ 33፥23፤ መዝ 33፥7፤ 88፥6፤ 90፥11፤ 1ነገ 19፥5፤ 2ነገ 6፥15፤ ዳን 3፥17፤ 4፥13፤ 8፥15-19፤ ዘካ 1፥12፤ ማቴ 18፥10፤ ሉቃ 1፥19፤ 13፥6-9፤ 15፥7፤ ዮሐ 20፥11፤ የሐዋ 12፥6፤ ዕብ 1፥14፤ ራእ 8፥3-4ን ይመልከቱ)፡፡ የቅዱስ ሚካኤል በረከት ይደርብን።
Show all...
ገብረ ላልቶ ይነበባል ። 🔻 ግሱ ሲገሰስ • ገብረ ➜ ሠራ ፣ አደረገ • ገብር ➜ ያሠራል • ግበር ➜ ይሠራ ዘንድ • ግበር ➜ ይሥራ • ገቢር /ገቢሮት/ ➜ መሥራት • ገባሪ ➜ የሠራ • ገባርያን ➜ የሠሩ ለወንዶች • ገባሪት ➜ የሠራች • ገባርያት ➜ የሠሩ ለሴቶች • ግቡር ➜ የተሠራ • ግብር ➜ ሥራ • ግብረት ➜ አሠራር /አደራረግ/ • ምግባር ➜ በጎ ሥራ • ተግባር ➜ ሥራ
Show all...
#መልካም_አእምሮ_ያስፈልገናል " የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፤ የኃጥኣን ምክር ግን ተንኰል ነው። (መ.ምሳሌ12:5) ✝ይ🀄️ላ🀄️ሉን👇 @yegeez_memariya አእምሮዎ ለእርስዎ መልካም ወይም ለእርስዎ ጥፋት ሊሠራ ይችላል ፡፡ #ለእርስዎ_መልካም በሚሰራበት ጊዜ ቀና ሆነው እንዲቆዩ ፣ ግቦችዎ ላይ መድረስ እና በየቀኑ እንዲደሰቱ ይረዳዎታል ፡፡ ግን መጥፎ ሲሰራ አሉታዊ እና ተስፋ መቁረጥ ሊያደርግብዎት ፣ ወደኋላ ሊልዎት እና እራስን ማጉደል የሚያስከትሉ ሀሳቦችን እንዲያስቡ ያደርግዎታል ፡፡ ስለዚህ ከመጥፎ ይልቅ አእምሮዎን መልካም እንዲሠራ ያስተምሩ ፡፡ ይህንን ለማድረግ በጣም አስፈላጊው መንገድ በእምነት ማሰብ ነዉ ውሳኔ ማድረግ ነው ፡፡ አሁን አንጎልዎ ይህንን አዲስ ሚና በአንድ ሌሊት ማከናወን አልቻለም። ሥር ነቀል ለውጥ እንዲደረግ እየጠየቁት ሊሆን ይችላል ፣ እና ያ ጊዜ ይወስዳል። ነገር ግን ያንን በትጋት እና #በእግዚአብሔር_እርዳታ ፣ በእርስዎ ላይ ከመሰራት ይልቅ አንጎልዎ ለእርስዎ ይሰራል እናም በህይወትዎ ውስጥ አዎንታዊ ኃይል ይሆናል ፡፡ የእውቀት (ኮግኒቲቭ) የነርቭ-ሳይንቲስት ምሁር የሆኑት ዶክተር ካሮሊን ሊፍ እንዳሉት አንጎል ለማደግ አሥራ ስምንት ዓመት እና ዕድሜው እስከ ብስለት ድረስ ይወስዳል ፡፡ ይህ ነጥብ እንዳያመልጥዎት! በተወለዱበት ጊዜ እና ሰውነትዎ እያደገ ሲሄድ ሰውነትዎ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ የአካል ክፍል ሙሉ በሙሉ የተገነባ ሲሆን አንጎሉ ለማደግ በእውነቱ አሥራ ስምንት ዓመታት ይወስዳል ፡፡ እና አንዴ ከተሰራ በኋላ #እስከሚሞቱበት_ቀን ድረስ ማደግ ይቀጥላል። ያ ማለት ምንም ያህል እድሜ ቢኖራችሁ ፣ አንጎልዎ #አሁንም_እያደገ ነው ፡፡ ይህ በጣም ጥሩ ዜና ነው ፣ ምክንያቱም በድሮ ወይም የተሳሳቱ አስተሳሰብ ስርዓቶች ውስጥ ተጣብቀው መቆየት የለብዎትም ማለት ነው። አንጎላችን አሁንም እያደገ ነው ፣ ይህ ማለት በአስተሳሰባችሁ ውስጥ አሁንም ማሻሻል ይችላሉ ማለት ነው ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው "የጻድቅ አሳብ ቅን ነው።" ✝ይ🀄️ላ🀄️ሉን👇 @yegeez_memariya
Show all...
⚔🔫 ከባዱ ጦርነት ተጀምሯል ኢትዮጵያ ሆይ እግዚአብሔር ይጋረድልሽ።😥 ለማንም የማይበጀው ጦርነት ተጀምሯል። በልቶ ማደር ላቃተው ዜጋ ጦርነት አይገባውም። ስንት የሰላም አማራጮች ባለበት ሁኔታ ወላፈኑ የማይነካቸው የመሰላቸው አለቆች መፈታተሹን መርጠውታል። በዚህ ጦርነት #ሀገር_ትጎሰቁላለች #ህጻናት_አረጋውያን_እና_እናቶች_ስቃያቸውን_ይጠብሳሉ #ዜጎች_የጦርነት_ማገዶ_ይሆናሉ #ቤተክርስቲያን_በብዙ #ትጎዳለች #የሚያተርፈው_ማን_ይሆን🙏 ለሰላም እንጂ ለጦርነት የሚሰንፍ በሌለባት ምድር ጦር አውርድ ወሬዎቻችን እዚህ አደረሱን። ⛪️ጸልዩ በእንተ ሀገሪትነ ኢትዮጵያ 🇪🇹 እግዚኦ መሀርነ ክርስቶስ
Show all...
ፈያት ---- ወንበዴዎች ፈድለ ---- በዛ ከልክ አለፈ ዔረግ ---- ወጥመድ የአውሬ መያዣ ዔር ---- ጠባቂ መላክ ዋየየ ---- አስተዛዘነ አጫወተ ቁማስ ---- መዳ ጠቃ የልብስ ነዶ ቢሕ ---- ጉማሬ የወንዝ አውሬ ሻሮም ---- ሀለይት መዘምራን ቆቅሀ ---- እንሰት ቆቅ ርሙም ---- ዝም ያለ ዝምተኛ ርሱዕ ---- የተረሳ የተዘነጋ ባሕቱ ---- ብቻ እንጂ ግን ነገር ግን ዘራዊ ---- በታኝ አጥፊ አባካኝ ዘርከደ ---- ሰደበ አዋረደ ሐሰሰ ---- ፈለገ
Show all...
ሰውም የሚዘራውን ያጭዳል በሥጋም የሚዘራ ሞትን ያጭዳል በመንፈስ የሚዘራ የዘለዓለም ሕይወትን ያጭዳል በጎ ሥራ መሥራትን ቸል አንበል በጊዜው እናገኘዋለንና እንግዲህ ጊዜ ሳለን ሁሉ መልካም ሥራ እናድርግ ይልቁንም ለሃይማኖት ሰዎች ገላ 6:1-11
Show all...
ድራር↔እራት ፍልፍል↔በርበሬ ከዊነ↔መሆን ክህለ↔ቻለ ሴሰየ↔መገበ ተንበለ↔ለመነ ጽርሕት↔ድስት፣ምንቸት አፈ ክብ ማብሰያ ጽልእ↔ጥል ጠብ ቂም ፈላሲ ፈሰስ↔የሚፈስ ፈሳሽ ወራጅ ፒርልዩ↔ቀንጣፋ ዛፍ አሾኃማ ገላሜዎስ↔ኅሥሥት ዛተ↔ይችን ይችኛይቱን 🌹መልካም.ቀን🌹
Show all...