cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

@የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
672Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
. 🚨ኢየሱስ ፊትህ ይርበኛል!😭 ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ 🚨የዚህ አለም ነገር ቶሎ ቶሎ ይሰለቸኛል ነብሴ አንተን አንተን ትላለች! 🚨በምን አይነት ፍቅር እንደነካኸኝ እንጃ! መለወጥ የምትፈልጉ ሁሉ አሁኑኑ ስሙት!😭😭😭😭👆👆👆👆 🚨ይድረስ ለአማኞች ሁሉ! 🚨ድንቅ የፀሎት ጊዜ! 🚨ከአገልጋይ መልካሙ ሙሉጌታ ጋር! ……………………………………………………… በ youtube ቻናሌም ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቴን በስፋት ይከፋፈሉ 👇 https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ Holy Tube Ethiopia ........................………………………… #ራስዎን_በቤት_ይገንቡ ............▪️•°○.......................... ✔️ አስተያየት ካላችሁ 👇👇👇በዚ አናግሩኝ @melke1211_bot 🚨ሼር ይደረግ #Share #Share🚨 ቻናሉን ይቀላቀሉ ✨ @HolyTubeEthiopia✨ ✨ @HolyTubeEthiopia
Show all...
1ኛ ዮሐንስ 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁸ ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና። ⁹ ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም። ¹⁰ የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። ¹¹ ከመጀመሪያ የሰማችኋት መልእክት፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ የምትል ይህች ናትና፤ ¹² ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው። ¹³ ወንድሞች ሆይ፥ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ። ¹⁴ እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል። ¹⁵ ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ። ¹⁶ እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል። ¹⁷ ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል? ¹⁸ ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።
Show all...
Repost from Tesfa
የእግዚአብሔርን ፊት ስትፈልግ ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት መተዋወቅን ትለምዳለህ: የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማትን ትለምዳለህ: ትፀናለህ:: ይህም ከአምላክህ: ከአባትህ ጋር ጥልቅ መቀራረብ ያለበት ስፍራ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግ ፣ ፊቱን መፈለግ ትፋልጋለህ? ልንረዳህ በዚህ አለን:: #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube
Show all...
Repost from Tesfa
ልመና እግዚአብሄር ፊት ቀርበን የሚያስፈልገንን ነገር እንደቃሉ ተረድተን ፈቃዱን አውቀን የምንጠይቅበት መንገድ ነው:: ይህ አይነቱን ፀሎት በእግዚአብሐር ፊት በእምነት ስንፀልይ ደጋግምን የምንፀልይበት ሳይሆን አንዴ ልመናችንን ካስታወቅን በኋላ እግዚአብሄር እንደሰማን በማመን ውጤቱን መጠበቅ ነው፡፡ በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል: ይሰጠናል:: አንተስ? ፀሎትን: ልመናን ወደሚሰማ፤ ሰምቶም ወደሚመልስ አምላክ እንዴት መቅረብ እንዳለብህ ፣ እንዴት መፀለይ እንዳለብህ፤ ማን ይነግርኝ ይሆን ብለሀል? ልንረዳህ፤ ልናስተምርህ በዚህ አለን:: #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtub
Show all...
#አንተ_ግን_ስትጸልይ_ወደ_እልፍኝህ_ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ። 8፤ ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና።
Show all...
ቶሎ የሚከበንን ኃጢአት ማስወገድ ~~~~ ኢየሱስ ከዮሐንስ እጅ በተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመናችን ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ ነፃ ወጥተናል። የባሪነት ቀንበራችን ተሰብሯል። ዓለም በባሪነት ውስጥ ቢኖርም፣ እኛ ግን በነፃነት ለመኖር ነፃ ወጥተናል። ክብር ለአዳኛችን ይሁን! ከኃጢአት ነፃ ወጥተናል ማለት የኃጢአት ፈተና የለብንም ማለት አይደለም። ከኃጢአት ነፃ ብንወጣም፣ አሁንም የኃጢአት ፈተና አለብን። ከኃጢአት ጋር ውጊያ አለብን። ኃጢአት ይከበናል። የዓለም ፍቅር ይከበናል። ሥጋዊ አስተሳሰብ ይከበናል። የገንዘብ ፍቅር ይከበናል። የባለጠግነት አሳብ ይከበናል። የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል እንዳንመሰክር ይተበትቡናል። ለእግዚአብሔር መንግስት እንዳንኖር ይጎትቱናል። በሚያታልል ምኞት ይስቡናል። ጳውሎስም ተከቧል። ግን በእምነትና ለእግዚአብሔር መንግስት በመኖር ድል አድርጓል። ሥጋውን ጎሰመ። ምድራዊ ብልቶቹን ገደለ። ነፍሱ በእርሱ ዘንድ እንዳትከበር እንደ ከንቱ ነገር ቆጠረ (ሐዋርያት 20:24)። ነፍሱን ለወንጌል ሥራ አሳልፎ ሰጠ። ጳውሎስ በኃጢአት ቢከበብም፣ የከበበውን ኃጢአት በእምነት በማስወገድ መንፈሳዊ ሩጫውን በድል አጠናቋል። 📌“ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።” (ሐዋርያት 20፥24) ከጳውሎስ አጋር ሰራተኛ የሆነው ደማስም በዓለም ተከቧል። ከበባውን ግን በእምነት ድል ማድረግ አልቻለም። ተሸነፈ። የከበበውን ኃጢአት በእምነት ማስወገድ አልቻለም። ንጉሱ ሰሎሞንም በኃጢአት ተከቦ ነበር። በዓለም ፍቅር ተከቦ ነበር ነገር ግን ድል ማድረግ አልቻለም። የከበበውን ኃጢአት በእምነት ማስወገድ አልቻለም። ተሸነፈ። በመጨረሻም ለጣኦት በመስገድ እግዚአብሔር እጅግ የሚጸየፈውን ኃጢአት ፈጸመ። እስራኤልውያን ከግብጽ ባሪነት ከወጡ በኋላ፣ በኃጢአት ተከበው ነበር። በሥጋ ምኞት ተከበው ነበር። ከመና ይልቅ የግብጽን ዱባና ዓሳ እንዲሁም ሥጋ ተመኝተው ነበር። የከበባቸውን ኃጢአት በእምነት ማስወገድ አልቻሉም። ብዙዎቻቸው በምድረ በዳ ወደቁ። እግዚአብሔርንም አስቆጡት። ከግብጽ ቢወጡም ወደ ተስፋይቱ ምድር ከናዓን አልገቡም። በኃጢአት ተሸነፉ። ጌታችን ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በውኃውና በደሙ ካስወገደ በኋላ የኃጢአት ስርየት ብቻ አይደለም የሰጠን። ተልዕኮም ስጥቶናል (ማቴዎስ 28:18-20)። ያም ተልእኮ ወደ ዓለም ሁሉ እንድንሄድ፣ የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል እንድንመሰክር፣ ነፍሳትን እንድናድን፣ የእሱን ትምህርት እያስተማርናቸው ደቀ መዛሙርት እንድናደርጋቸው ነው። ሆኖም ግን ይህን የጌታን ተልዕኮ እንዳንፈጽም ኃጢአት ይከበናል። የዓለም ፍቅር ይከበናል። የገንዘብ ፍቅር ይከበናል። የሥጋ መሻት ይከበናል። ግን ማሸነፍ እንችላለን። ማስወገድ እንችላለን። ማሸነፍ የምንችለው በአንድ ነገር ብቻ ነው። እርሱም በእምነት ነው። በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ በእምነት መሳተፍና እስከ መጨረሻ ራስን ለእግዚአብሔር መንግስት ሥራ አሳልፎ መስጠት ያስፈልጋል። እጃችንን አጣጥፈን በመቀመጥ የሚከበንን ኃጢአት ማስወገድ አንችልም። 📌የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፦ “...እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” (ዕብራውያን 12፥1-2)
Show all...
(ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 8) ---------- 14፤ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። 15፤ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። 16፤ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። 17፤ ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን። 18፤ ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ። 19፤ የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
Show all...
ፓስተር ተስፋ ጋቢሶ፡ ግሩም አባት ነህ አዝ፡ ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ ባንተ ድኜአለው ነፃ ወጥቼአለው ተመስገን ኢየሱስ እልሀለው ቀርቦ የሚያፅናና በጠፋበት መከራው ገዝፎ ባየንበት ጌታዬ ነበርክ በዛ ስፍራ እያፅናናኸኝ እንዳልፈራ አዝ፡ ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ ባንተ ድኜአለው ነፃ ወጥቼአለው ተመስገን ኢየሱስ እልሀለው በሌለበት የሚያረካ ነገር በዚያ በረሀ ደረቅ ምድር የህይወት ተስፋ ሆነኸልኝ ከአለት ውሃ ፈለቅልኝ አዝ፡ ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ ባንተ ድኜአለው ነፃ ወጥቼአለው ተመስገን ኢየሱስ እልሀለው አውሎ ንፋስም እየነፈሰ ማዕበሉም እያተራመሰ ወደኔ የደረሰ ሲመስለኝ ለህየወቴ ስሰጋ ሳለውኝ አዝ፡ ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ ባንተ ድኜአለው ነፃ ወጥቼአለው ተመስገን ኢየሱስ እልሀለው ግራ ቀኜን ባይ ዙሪያው አጥር ሆኖብኘ ነበር ኑሮ በምድር መውጪያ ከሌለው ከዝግ ቦታ አንተ አወጣኸኝ የእኔ ጌታ አዝ፡ ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ ባንተ ድኜአለው ነፃ ወጥቼአለው ተመስገን ኢየሱስ እልሀለው ላስጨናቂዎች ሳልገዛ ስለበዛልኝ ያንተ እገዛ ወጥቼአለው ቅጥሩ ፈርሶ የወሰንከውም ጊዜው ደርሶ አዝ፡ ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ ባንተ ድኜአለው ነፃ ወጥቼአለው ተመስገን ኢየሱስ እልሀለው ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ ባንተ ድኜአለው ነፃ ወጥቼአለው ተመስገን ኢየሱስ እልሀለው...❤❤❤
Show all...
መዝሙር 91 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል። ² እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ። … ⁴ በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። … ⁶ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም። ⁷ በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። ⁸ በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ። ⁹ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ። ¹⁰ ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። ¹¹ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ … ¹³ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። ¹⁴ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። ¹⁵ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ። ¹⁶ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
Show all...