cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኪነ - ወንጌል

ወንጌልን በስነፅሁፍ ✔መጣጥፎች እና ወጎች * ትዝታ ዘመጽሔት ✔ከመጽሔት የተገኙ ምሥክርነቶችና ተረኮች * ከመጽሐፍት ዓለም ✔ምርጥ የመፅሐፍ ገጽ ምርጥ መጽሐፍ ጥቆማ https://t.me/joinchat/AAAAAFRIVkV_Mr8zvnJDcA እነሆ በዚህ ቻናል የማንዳስሰው ርዕሰ ጉዳይ አይኖርም 🙋🙋🙋🙋🙋

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
167Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

“ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤” — ዕብራውያን 12፥28
Show all...
ይድረስ ለደረጄ ከበደ ።.....።።።።።....... ፬ ፨ይበቅላል፨ እንኳን የተዘራው ያልተዘራውም ይበቅላል እኳን ያቦካኽው ያቦኩልህም ኩፍ ይላል እንኳን የቆሰቆ ከው የከሰመውም ይነዳል አመድነው ብለህ የናቅከው ፍሙ አገር ምድሩን ይሞቃል ያሰብከው ብቻ መቼ ! ያለሙልህም ይፈታል ተኝተህ ብቻ እማይደል ተኝተውልህም ታያለህ ጠጥተህ ብቻ አይደለም ጠጥተውልህም ትሠክራለህ በዚች ከንቱ አለም ምን ይሄ ይገርምሃል እንኳን የዘራኽው ያልዘራኽውም ገና ይበቅላል ለ አገርህ ውድቀት ለትውልድህ ክሽፈት ምክንያት የፈለከው እንዴት ይሄ ይጠፋሃል ? "ይሰፍር ለክሙ ወይሰፍር ለክሙ " ለተርጉመው መሰል ወይስ ያልኩት ገብቶሃል ? ...... እንዲህ ነው...... በቁና ሰፍረህ ከነበር በሥልቻ ይከፍሉሃል ለምታጭደው ለምን ለምትዘራው ነው መጨነቅ ሞኝነት እንዳይሆንብህ በቆሎ ዘርቶ ስንዴ መጠበቅ የማሱልህ ብቻ ሣይሆን ቅልጥምህን የሚሰበረው ሌት በጨረቃ ውጋገን ለጠላቴ ብለህ የማሥከው የራሥህ ከርሥ ነው የሚደፋህ እገረ ሰባራ የሚያረግህ ዛሬ በአባትህ ላይ የወረወርከው ድንጋይ ነገ ልጅህን ሲፈነክተው ባ'ደባባይ ከየት መጣ አትበል ዲቃላ ዘርህን ሥታየው ከያት ወለድሽው አትበላት ሰማኒያ ማህተም የነበራት በጨረቃ ውጋገን ሰርቀህ የተኛህባት ሰርቃ የወለደችልህ የጨረቃ ሚስትህ ናት አይ ! የዘንድሮ ልጅ ! አትበል የዘንድሮ አባት አምና ዘርተህ ነው ዘንድሮ እኔን ያጨድከው ከወንድምህ ትንሽ ጉድፍ' ይልቅ ነውና ያንት' ምሦሶ ትልቅ ማነው የጋረደኝ አትበል ደርሦ እቅፋት አትፈልግ እሥኪ ያየ ይመሥክር ከጉድፍና ከግንድ ማንኛው በደንብ ይከልል የትኛውሥ ቅንነት ያሥጥል ትናት ከጅህ አምልጣ ከመሬት የወደቀችው ክረምት ዝናብ ሢነካት ለምዷን ያወለቀችውት ያች ቅንጣት የዘረኝነት ዘር እልፍ ሆና የበቀለችው ቀድማ በልብህ ነበር እሸት ፍሬ ያወጣችው አምና አንተዉስጥ ነበር ጽጌዋን ያኮረተችው አንተስ የኖህ ልጅ የያፌት ወንድም መሳለቅ ቀልሎ የታየህ ለአባትህ ልብስ ከማገልደም የጥንቱን ስህተት በድን አጥም ምትቆፍር በአያትህ ግዳይ ምትፎክር ከየት ይመጣል ቅርጫፍ ከሌለ ግንዱ የትናንት እሣት ነበረ የዛሬ አመዱ የገረጣውን የአባትህን ፊት አትናቀው የአንተ ወዝ ነው እንዲህ አድርጎ የመጠጠው የሚብረከረው ጉልበቱ ዛሬ አቅም ያጠረው ጢሻ ናጫካ እሜኬላ መንገድህን ሲመነጥር ነው እናም በአባትህ ው ስጥ የምትዘራው አባዬ ብሎ የሚጠራህ የነገው ልጅህን ነው ።
Show all...
"ዘርሽ የት ነው? "አሉኝ እነ ዘር ፑልፒቱ ፣ እነዘር ሥብከቱ ፣ ደጋግመው ጠየቁኝ ። የት ነበረ..ዘሬ ? ማን ነበር ....አባቴ ? የአቶ እከሌ ልጅ ! ብዬ እማወራላት የሚሆነኝ ትምክህት ? ከየት ነው የበቀልሁ እንዴትሥ አድርጌ እዚህ የተገኘሁ ? በደሜ ውስጥ ያለው የአባቴ ዘረመል የእንቶኔ ? የአያእከሌ..? ያነማነው ይባል ? "ይሰባካል እና ዛሬም በኔ ቀዬ ንገረኝ ዘርህን ?" ብሎ አፋጠጠኝ ቦርጫሙ አለቃዬ የት ነኝ ልበላቸው ይገድሉኝ ይሆን እንዴ..? ዝም ልበላቸው ይሾሙኝ ይሆን እንዴ..? አንድ ሆኖ ዘሬ ከ ዘራቸው... ደግሞስ ካልገጠመ ደሜ ከደማቸው..? ካልሆነስ ምን አልባት ፣ የኔ ወላጅ አባት፣ የእነሱ አባታቸው ? ። እስኪ ምን ልመልስ የማነህ ለሚል ክስ ዘሬን ያወቃችሁ ይህንን አንብባችሁ ንገሩኝ አባቴን ልወቅ የማን'ነቴን ....
Show all...
እየዞርኩ ነው አይልም መዞሩንም ልብ አይልም እየሄደ ማስሎት ወደፊት አለ እኮ ብዙ ቀራንዮን ትቶ ቁልቁል ቁልቁሉን የሚንከራተት
Show all...
“በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤” — ገላትያ 1፥6 የሚገርመኝ ሰው ከክርስቶስ ዘወር ካለ በኋላ እንጂ እየዞረ እያለ አይታወቀውም ! ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደምንሰማ መጠንቀቅ እንዳለብን የሚመክረን “አላቸውም፦ ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል ለእናንተም ይጨመርላችኋል።” — ማርቆስ 4፥24 * ሰሞኑን የዶ/ር ደረጄ አወዛጋቢ ንግግር ብዙዎቻችንን እረብሾናል አሳዝኖናል :: የእግዚአብሔር ቃል ምን ይመክረናል “እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤” — ኤፌሶን 5፥15 * በጥንቃቄ መጠበቅ ያለብን ፦ ከራሳችን ፦ ከምናደንቃቸው ፦ ከማናደንቃቸው ፦ ከምንከተላቸው..... * በእግዚአብሔር ቤት እነዚህ እንዳሉ እንደሚኖሩም ማወቅ ይጠቅመናል “ከውሾች ተጠበቁ፥ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ፥ ከሐሰተኛም መገረዝ ተጠበቁ።” — ፊልጵስዩስ 3፥2 * ውሻ እንዳለ እንጂ ማን መቼ ውሻ ሆኖ እንደሚነክሰን አናውቅምና በጥበብና በጥንቃቄ እንመላለስ ፡፡ ቸር ሰንብቱ አሳባችሁን እጠባበቃለሁ @kinewngell
Show all...
መልሰኝ
Show all...
የት ለመድረስ እየሮጥን ነው, መቼ ለመድረስ እየሮጥን ነው?
Show all...
ምን እየናፈቅን ይሆን ? ምን እየተጠባበቅን ነው ? ምን እያሠላሠልን ነው ? ምን እየተራብን ነው ? ምን ለማግኘት እየተስገበገብን ነው? ምን ለመቀበል እየተንቀዠቅዥን ነው?
Show all...