cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Deleted channel

WeCare is Ethiopia’s digital healthcare platform where treatment seekers can discover practitioners to directly book appointments for online consultation or in clinic visits. [email protected] https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

Show more
Advertising posts
5 069Subscribers
No data24 hours
-17 days
-130 days
Posts Archive
👩‍⚕️👨‍⚕️ Consult our doctors from the comfort of your home !!                                          🔔 በተለያዮ የሕክምና ዘርፎች የጤና ባለሙያዎችን ማማከር ቢያስፈልጎ የ wecare ET መተግበሪያን በመጠቀም ከመረጡት ሐኪም ጋር በኦንላይን ካሉበት ቦታ ሆነው  መወያየት ይችላሉ። መተግበሪያውን ለመጫን ማስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ። 👇👇👇👇👇👇👇               https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient 🗣 Join our social media and lets be a family 📌 Facebook https://www.facebook.com/WeCareET/ 📌YouTube: https://tinyurl.com/rv4zjmwk 📌Instagram: https://www.instagram.com/wecareet 📌 Tiktok: https://vm.tiktok.com/ZMLbbyTXr 📌Website: wecare.et #selamdoctor #wecareet #digitalhealth #ethiopian #🇪🇹
Show all...
ከታች በተያያዙት የትዊተር እና የፌስቡክ ገጾች የእኔ ናቸው መልካም ቀን ! ትዊተር https://twitter.com/YohannesMekon ፌስቡክ https://www.facebook.com/archtyohannes?mibextid=ZbWKwL
Show all...
ጤና ይስጥልኝ በዚህ የቴሌግራም ገጽ ላይ 8,000 ያህል ከሚሆኑ ወዳጆቼ ጋር ልዩ ልዩ ሀሳቦች መለዋወጫ መድረክ አድርገን ስንጠቀምበት ቆይተናል። በቀጣዩ አንድ ሳምንት ውስጥ ይህንን ገጽ ስለምዘጋው ከታች በተያያዙት የትዊተር እና የፌስቡክ ገጾች ላይ በወዳጅነት እንድንቀጥል እጋብዛለሁ። መልካም ቀን ! ትዊተር https://twitter.com/YohannesMekon ፌስቡክ https://www.facebook.com/archtyohannes?mibextid=ZbWKwL
Show all...
Dear Professor, You might recall that I didn't present a defense for my dissertation proposal. Simply put, I was looking for a field and subject matter that would be pertinent to both my academic and personal futures. But, looking here and there for potential area and topic distracted me from my studies and absorbed too much of my time. So far, I have been reading Heritage and environment related issues as well as Rural Urban linkage and how it relates to environmental concerns in the interim. In order to research the implications of climate change on rural-urban linkage concerns, I have now made the decision to do so. Along with working at home in the evenings, I also spend three full days in our library. Before diving too deeply into the subject, I just want to hear your thoughts and suggestions for the next steps. I sincerely appreciate your usual advice.
Show all...
ጤና ይስጥልኝ ወዳጆቼ። በዚህ የቴሌግራም ገጽ ላይ 8,000 ያህል ከሚሆኑ ወዳጆቼ ጋር ልዩ ልዩ ሀሳቦች መለዋወጫ መድረክ አድርገን ስንጠቀምበት ቆይተናል። በቀጣዩ አንድ ሳምንት ውስጥ ይህንን ገጽ ስለምዘጋው ከታች በተያያዙት የትዊተር እና የፌስቡክ ገጾች ላይ በወዳጅነት እንድግቀጥል እጋብዛለሁ። መልካም ቀን ! ትዊተር https://twitter.com/YohannesMekon ፌስቡክ https://www.facebook.com/architectyohannesmekonnen?mibextid=ZbWKwL ወይም https://www.facebook.com/archtyohannes?mibextid=ZbWKwL
Show all...
ነባር ሀገራዊ ተቋማትን ማፍረስ ሀገርን ማፍረስ ነው !!! ---------------------------- (የግል አስተያየት) ደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን ሶዶ ዳጬ ወረዳ (ከወሊሶ ከተማ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት) በምትገኘው ሀሮ በዓለወልድ ቤተክርስቲያን "ኦሮሚያ ቤተክህነት" አቀንቃኞች በቋንቋ እና በብሔር ማንነታቸው ብቻ "ለተመረጡ" 25 "ኤጲስ ጳጳሳት" ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና ባፈነገጠ መንገድ ተሹመዋል። ከአካባቢው እንደተሰማው ምእመናን ይህንን የቀኖና ጥሰት እና ተቋም የማፍረስ አካሄድ ለማስቆም ሲሄዱ ሿሚና ተሿሚዎቹ ታጣቂዎችን አሰልፈው እንደተገኙ እና ጦርነት ለመክፈት ዝግጁ እንደነበሩ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም ለሁለት ተከፍሎ የነበረውን ቅዱስ ሲኖዶስ በእርቅ ወደ አንድነት ለማምጣት ጠቅላይ ሚንስትሩ የሠሩትን በጎ ሥራ እንዳመሠገንነው ሁሉ ዛሬ ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱን ለሁለት ሰንጥቆ (ያውም በብሔር አቧድኖ) እንደተቋም ለማፍረስ የተኬደበትን ርቀት በዝምታ ማየቱ፣ የተረከቡትን መንግሥታዊ ሥልጣን ተጠቅመው ከጀርባ ያደራጁ ኃይሎችን አደብ ለማስገዛት ፍላጎት ማጣቱ (ምናልባትም ግፉበት ማለቱ) አሳዛኝም አሳፋሪም ነው። የኢትዮጵያዊ መልክ እና ሥሪት ያላቸው፣ ከዘር እና ከቋንቋ ማንነት ተሻግረው ዜጎችን አሰባሳቢ እና አስተባባሪ የሆኑ የሃይማኖት ተቋማት መሰንጠቅ፣ ማኮሰስ እና ምእመኖቻቸውን ማዋረድ ዳፋው ለሀገር እንደሚተርፍ ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት አይገባም። ከሕገመንግሥታዊ ሥርዓት ውጪ "የሽግግር መንግሥት መሥርተናል" የሚሉ ዜጎች በሥውር ካቢኔ ሲያቋቁሙ ቢሰማ መንግሥት ተኝቶ ያድር ነበር? እንደ ሀገር ከምንላቁጥበት የብሔር ፖለቲካ አረንቋ ለመውጣት በምንፍጨረጨርበት ወቅት ሃይማኖትን ያህል ትልቅ ሀገራዊ ተቋም ጎትቶ የብሔር ንትርክ ውስጥ መጨመር አእምሮ ቢስነት ነው። ይህንን የመሰለ ነውር እና ጋጠወጥነትን ለማረም እና ሕገወጦችን ተጠያቂ ለማድረግ ቀዳሚው ኃላፊነት የሕዝብን ሰላም እና አንድነት የማስከበር እና የመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው መንግሥት ነው።
Show all...
“የኢትዮጵያ” ሕገመንግሥት !!! ኢትዮጵያውያን በተጻፈ የሕገመንግሥት ሰነድ መተዳደር ከጀመርን 92 ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ የአራት ትውልድ እድሜ ጉዞ አራት የተለያዩ ሕገመንግሥታት በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር በሥራ ላይ ቢውሉም አንዳቸውም “የኢትዮጵያ” ተብለው ለመጠራት የሞራል ልዕልና አልነበራቸውም። የቀደሙት ሁለቱ "የንጉሡ"፣ ሦስተኛው "የደርግ" አራተኛው "የሕወሓት" ሕገመንግሥት በመባል ይታወቃሉ። ለማስታወስ ያህል፦ 1) የመጀመሪያው ሕገመንግሥት በ1923 ዓ.ም ከጣልያን ወረራ አስቀድሞ በንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለሥላሴ በሥራ ላይ እንዲውል ተደረገ። 2) ሁለተኛው ሕገ-መንግሥት ኢትዮጵያ ከጣሊያን ወረራ ነፃ ከወጣች በኋላ የ1923ቱን ሕገ- መንግሥት በማሻሻል በ1948 ዓ.ም ጸደቀ፡፡ 3) ሦስተኛውና አጭር እድሜ የነበረው ሕገ-መንግሥት በ1979 ዓ.ም. የወታደራዊው ደርግ የፀደቀው ነው፡፡ ይህ ሕገ-መንግሥት በ1983 ዓ.ም የደርግ አገዛዝ ሲወድቅ ተሻረ፡፡ 4) አራተኛው እና አሁን በሥራ ላይ ያለው የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት በ1987 ዓ.ም በህወኃት መራሹ ኢህአዴግ የፀደቀው ነው፡፡ በንጉሡ ጊዜ የነበሩት ሁለቱ የሕገ መንግሥት ሠነዶች ንጉሡ እንደ ሙሴ ከፈጣሪ ተቀብለው ለኢትዮጵያውያን እንዳበረከቱ ተደርገው የሚትርኩ ነበሩ። (በዘመኑ ይሳሉ የነበሩ ሥዕሎችም ሆኑ የመጽሐፉ ሽፋን የሚያሳዩት በንጉሡ ዘመን የተጻፉት ሕገመንግሥታት በዜጎች ስምምነት የተጻፈ ሳይሆን ምልኮታዊ ሰጦታ ተደርጎ ነበር) የደርግ መንግሥት በበኩሉ ተምኔታዊውን “የወዝአደሩን መብት” ለማስከበር የተጻፈ ሲሆን አሁን በሥራ ላይ ያለው አራተኛው የህወሓት ሕገመንግሥት ደግሞ ብሔረሰቦችን እንደ ጭራቅ ከተተረከላቸው "የብሔር ጭቆና" ነጻ ለማውጣት በሕወኃት ተጠንስሶ በአጋፋሪዎቿ ጭብጨባ በኢትዮጵያውያን ላይ ተጫነ። እንደ ሀገር ለዘመናት ከምንታመስበትና ከማያባራው የእርስ በእርስ ጦርነት እንድናርፍ፣ በዓለም ሕዝብ ፊት አንገታችንን ከሚያስደፋን፤ አዋራጅ ከሆነው ችግር እና ችጋር እንድንወጣ፣ ዜጎች በነጻነት እና በክብር የሚኖሩበት ሥርዓተ መንግሥት ግንባታ (State Building) በትብብር እና በጋራ መሥራት የጠይቃል፡፡ ኢትዮጵያውያን በአሸናፊዎች ጠመንጃ አፈሙዝ የተጻፉ ሕገመንግሥታት ሳይሆኑ ዜጎቸ በየደረጃው ተሳትፈውበት፣ ለኂቃን እና የፖልቲካ ኃይሎች በሰከነ እና በሠለጠነ ውይይት ተገናዝበው የሚጽፉት (የሚያሻሽሉት) "የኢትዮጵያ" የምንለው ሕገመንግሥት ያስፈልገናል። ይህንን እንደምን ማሳካት ይቻል ይሆን? ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች እና ሌሎች ሀገራዊ ተዋንያን በጠረጴዛ ዙሪያ የሚያሰባስብ እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር ማድረግ ከቻልን በቻ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ የልዩነት እና የግጭት መንስኤ የሆኑ የሕገ መንግሥቱ አንቀጾችን ማረም ስንችል፣ የኢትዮጵያውያንን የዘመናት ምጥ የሆነውን “የኢትዮጵያ” የሚባል ሕገመንግሥት ማዋለድ ይቻላል። ሕገ መንግሥቱ ሲሻሻል ዜጎች ያለምንም ስጋት በሀገሪቱ ሉዓላዊ ግዛት እንደልብ የመንቀሳቀስ፣ ሀብት የማፍራት፣ የመኖር መበታችው ይከበርላቸዋል፡፡ ሀብት፣ ጉልበት እና ዕውቀትን በማስተባበር ልሚሊዮኖች የሥራ ዕድል መፍጠር እንችላለን፡፡ ባለሀብቶች በፖለቲካ ወገንተኝነት፣ በሚናግሩት ቋነቋ ወይንም በብሔረሰባዊ ማነንታችው ሳይሆን ለሀገር እድገት እና ለወገን ፍቅር ባላቸው ሀቀኛ ተግባር የማይቋረጥ ድጋፍ የተትረፈረፈ ምርት የማምረት እድል ያገኛሉ፡፡ ከሀገራዊ ፈጆታ የሚተርፈን ምርት ለፋብሪካዎቻቸን ጥሬ ዕቃ እና የወጭ ምንዛሪ ምንጭ ይሆነናል፡፡ ይህ እንዲሳካ መሥራት፣ መወትወት እና በሚችሉት ሁሉ ማገዝ ሀገርን ከሚወዱ ዜጎች ሁሉ የሚጠበቅ የዚህ ትውልድ ዓይነተኛ ኃላፊነት ነው።
Show all...
የዓመት ሰው ይበለን! #ጥምቀት #ጃንሜዳ #ኢትዮጵያ
Show all...
በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሁሉ እንኳን ለከተራ እና ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ የጥምቀት አደረሳችሁ! መልካም በዓል !
Show all...
ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንኳን ለከተራ እና የእየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ! #የዜግነት_ፖለቲካ #ማኅበራዊ_ፍትህ #ኢዜማ
Show all...
1) ከነችግሩም ቢሆን ተቀብለነው እየተዳደርንበት ያለነው የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት ቀአንቀጽ 90 ቁ2 እንዲህ ይደነግጋል፤ "ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተፅእኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መካሔድ አለበት፡" ትምህርት ቤቶቻችን እና ተማሪዎቻችን ላይ የፖለቲካ እና የባህል ቋጥኝ በጉልበት የምንጭንባቸው ከሆነ ልጆቹ ሳይንሱን ምንጊዜ ይማሩት ? 2) ሀገራችን ኢትዮጵያ ተቀብላ በፊርማዋ ያጸደቀችው ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ (Universal Declaration of Human Right ) በአንቀጽ 26 ቁጥር 3 ስለ ሥርዓተ ትምህርት እንዲህ ይደነግጋል። Parents have a prior right to choose the kind of education that shall be given to their children. [ ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሰጠውን የትምህርት ዓይነት የመምረጥ የቅድሚያ መብት አላቸው ] ቋንቋን ጨምሮ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት፣ በኤክስፐርቶች ወይንም በኮሚቴ ተቀርጾ ተማሪዎች ላይ ከመጫኑ በፊት በሕጉ መሠረት የተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ፍላጎት ተጠይቋል? በጎ ነገር እንኳን ቢሆን በፍላጎት እና በሕዝብ ፈቃድ የሚተገበር እስካልሆነ ድረስ ሕጻናቱን በግድ እንደመጋት፣ ወላጆችም ላይ በጉልበት እንደመጫን ይቆጠራል። ውይይት ይቅደም ! ምክክር ይቅደም ! መግባባት ይቅደም !
Show all...
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ታህሳስ 20/2015 ዓ.ም. "በመንግስት ጫና የጎበጡ የመገናኛ ብዙሃን ነፃ ይሁኑ!" ሲል መግለጫ አውጥቷል። መግለጫውን ተከትሎ EBC/ETV ታህሳስ 22/2015 ዓ.ም ከኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ጋር ቃለመጠይቅ ያደረገ ቢሆንም እስከዛሬው ዕለት ጥር 04/2015 ዓ.ም. ድረስ ፕሮግራሙ ለአድማጭ እና ተመልካቾች አልተላለፈም። ፓርቲያችን አሁንም የመገናኛ ብዙሃን አሰራር ሚዛናዊ ሊሆን ይገባል ብሎ ስለሚያምን እና ማህበረሰቡም ተገቢውን መረጃ እንዲያገኝ በማሰብ በዕለቱ የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ፕሮዳክሽን ክፍል በጎንዮሽ ቀረፃ ያስቀረውን ቅጂ አቅርቧል። በጥሞና እንድትከታተሉት ይጋብዛል። #ማኅበራዊፍትህ #የዜግነትፓለቲካ #ኢዜማ
Show all...
መንግሥት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሊከውናቸው የሚገባቸውን መሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ተላልፎ ብቻውን መወሰኑን በአስቸኳይ የማያቆም ከሆነ የሀገራዊ ምክክሩን ፋይዳ ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል። If the government doesn't quickly stop making decisions about fundamental national issues that the National Dialogue Commission should take into consideration, it will start to doubt the value of the Dialogue.
Show all...
በሀገራዊ ምክክሩ ዜጎች በንቃት እንዲሳተፉ በቂ አትኩሮት ይሰጠው! ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት በሀገራችን ኢትዮጵያ በየዘመኑ የነበሩትን፣ ከፖለቲካው ሥርዓት የሚመነጩ ችግሮችን ለመፍታት እና ወደተሻለ ሀገራዊ ሁኔታ ለመሸጋገር የሚያስችል ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማንበር እቅስቃሴ ማድረግ ከተጀመረ ከሃምሳ ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል። እነዚህ እንቅስቃሴዎች የሥርዓት ለውጥ ከማምጣት ተሻግረው የዴሞክራሲን ፍሬ ከማፍራት ይልቅ ሀገራዊ ችግሮቻችንን በአይነትና በብዛት እየጨመሩ እና እየተወሰሳሰቡ እንዲመጡ በማድረግ ዛሬ ላይ የኢትዮጵያችን ህልውና እና ቀጣይነት ላይ ከፍተኛ አደጋ ለመደቀን በቅተዋል፡፡ ምንም እንኳ ሌሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ቢኖሩም፤ የኢትዮጵያ ህልውና ላይ የተደቀነው አደጋ በዋነኛነት የሚመነጨው፣ ከሀገራዊ የፖለቲካ ሥርዓቱ ነው። ሀገራዊ የፖለቲካ ሥርዓቱ በተለያዩ ፍላጎቶች፣ ጥቅሞች፣ ስሜቶች፣ ተስፋዎች እና ስጋቶች በመወጠሩ፤ እርስ በእርስ አለመተማመን፣ ሰላም ማጣት፣ መፈናቀል፣ አለመረጋጋት . . . ወዘተ ተፈጥሮ መዋቅራዊ ቅራኔ ውስጥ እየዳከርን መገኘታችን የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ ይህ አደገኛ ሀገራዊ ሁኔታ ሳይረፍድ እና ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ከመውጣታቸው በፊት በጋራ አንድ መፍትሔ ካልተበጀለት፤ እርስ በእርሳቸው እየተሳሳቡ ጫፍ እና ጫፍ የቆሙትን የተለያዩ ፍላጎቶች፣ ጥቅሞች፤ ስሜቶች፤ ቡድኖች እና ድርጅቶች በሙሉ ጠራርጎ፣ ማንኛችንም አሸናፊ ወደማንሆንበት ምድራዊ ሲኦል ውስጥ የመግባት እድል እንዳለን መገንዘብ ይኖርብናል። ይህንን ሁላችንም ላይ የተደቀነ ሀገራዊ አደጋ ለማስወገድ፣ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት በተለይ በፖለቲካው ሂደት ውስጥ ከተሞከሩት እንዲሁም ሀገራዊ ሁኔታውን ከማባባስ እና ከማወሳሰብ ይልቅ ምንም አይነት መፍትሔ መስጠት ካልቻሉት የፖለቲካ አካሄዶች ውጭ ባለ ሂደት፣ መፍትሔ የማፈላለጉ ጥረት አማራጭ የሌለው አካሄድ መሆኑን መቀበል ያስፈልጋል። ሀገራዊ ምክክር ያስፈለገውም የሀገራችን አንኳር ችግሮች በመደበኛው የችግር አፈታት ሂደት መፍትሔ ማግኘት በማይቻልበት ደረጃ በመድረሳቸው እና በመቀጠልም፣ የበለጠ እየገዘፉና እየተወሳሰቡ ሄደው ሀገርን የማፍረስ ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት ሀገርን ለማዳን እንዲያስችል ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በፊት ኮሚሽን ተቋቁሞ የተጀመረውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት በተመለከተ አሁን በደረስንበት ደረጃ ዋናው ጉዳይ መሆን ያለበት በሀገራችን ህልውና እና ቀጣይነቷ ላይ ያንዣበበውን አደጋ ለአንዴም ለሁሌም እንዲወገድ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ሊረዳን የሚችል ስምምነት ላይ ለመድረስ ደግሞ በምክክሩ ላይ የሚሳተፉ ባለድርሻ አካላትን በሂደቱ ላይ በቀናነት እንዲሳተፉ የማሳመን ሥራ በስፋት ሊከናወን ይገባል፡፡ የሀገራዊ ምክክሩ ቁልፍና ወሳኝ ባለድርሻዎች ምክክሩን ለመቀበል እና እንዲነቃቁ ለማድረግ፣ በመጀመሪያ መደረግ ያለበት፣ በሀገራዊ ምክክር ምንነትና እና በሀገራችን ሁኔታ ያለውን አስፈላጊነት አስመልክቶ ግልጽ የሆነ አረዳድ እንዲኖር ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የተለያዩ ባለድርሻዎች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ማሳየት ነው። ሀገራዊ ምክክር በመደበኛ አሰራሮች ሊፈቱ የማይችሉ መዋቅራዊና ጊዜያዊ ቅራኔዎችን በሰላማዊ መንገድ ተነጋግሮ ለመፍታት የሚያስችል በመሆኑ፤ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው። ሀገራዊ ምክክር በአግባቡ ከተጠቀምንበት ልዩነቶችን በማስታረቅ ሀገራዊ የፖለቲካ ቀውስን ለማስቀረት፤ ፖለቲካዊ አጣብቂኞችን ሰብሮ ለመውጣት እና ውጥረትን ለማርገብ፤ በትጥቅ የታገዘ አመፅ እንዳይፈጠር አስቀድሞ ለመከላከል ያስችላል፡፡ በተጨማሪም፤ ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር ከዚህ ቀደም ለተፈፀሙ በደሎች እና ወንጀሎች እንዲሁም የፍትህ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ይረዳል፡፡ በውጤቱም ከተፈጠሩ ፖለቲካዊ ቀውሶች ፈጥኖ በማስወጣት በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል መተማመንን ይፈጥራል፡፡ በፖለቲካዊ ሥርዓቱ ላይ ጥያቄ ለሚያነሱ አካላትም በሀገራዊ ምክክር ላይ በመሳተፋቸው በሀገር ጉዳይ ላይ የባለቤትነት ስሜትን በማጎልበት ልዩነቶችን በሰላማዊ ውይይት የመፍታት ባህል በማዳበር እንዲሁም ሀገራዊ ቀጣይነት እና መረጋጋትን በማረጋገጥ፤ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መደላድሎችን ይፈጥራል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከዚህ ቀደም በተለያየ መልኩ ሲገልፅ እንደቆየው፤ ሀገራዊ ምክክሩ በዚህ ወቅት ለአጠቃላይ ማህበረሰባዊ ደህንነታችን የሚኖረው አስተዋፅዖ ከፍተኛ ስለሆነ የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ሀገራዊ አጀንዳ ነው፡፡ ነገር ግን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለዚህ ሀገራዊ ክንውን እየሰጡት ያለው ትኩረት በጣም አነስተኛ መሆኑ ፓርቲያችንን በእጅጉ አሳስቦታል፡፡ ከሁሉም በላይ መንግሥት ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ብዙ እርቀት ተጉዞ አስተዋፅዖ ማድረግ ሲጠበቅበት፤ በምክክሩ ላይ ሊፈቱ የሚገባቸውን ጉዳዮች አስቀድሞ በመወሰን እንዲሁም ግጭቶች እንዲቀንሱ በትጋት ከመስራት ይልቅ በመንግሥታዊ መዋቅሮች ያልተገባ ውሳኔ ምክንያት ተጨማሪ ግጭቶች እየተፈጠሩ መሄዳቸው እንድንሰጋ አድርጎናል፡፡ በኢዜማ እምነት መንግሥት አስተባባሪ እንጂ አፍራሽ፤ ጠቃሚ እንጂ ጎጂ፤ ጠንካራ እንጂ ልፍስፍስ፤ ሕግ አስከባሪ እንጂ ሕግ የሚጥስ ሆኖ መገኘት የለበትም፡፡ በመንግሥት በኩል የሚከናወኑ አፍራሽ አካሄዶች አደጋቸው ለሁላችንም ነውና ሊወገዱ ይገባል፡፡ መንግሥት የሀገራዊ ምክክሩን ሂደት የሚያበላሹ ተግባራትን ማከናወኑ እንዲሁም የምክክሩን ሂደት ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚጠበቅበትን ሚና በአግባቡ እስካሁን አለመወጣቱ ትክክል እንዳልሆነ መረዳት ይጠበቅበታል፡፡ ለአብነትም፤ ኢዜማ ከዚህ ቀደም ባወጣቸው መግለጫዎች ላይ እንደገለፀው መንግሥት መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸውን ሀገራዊ የፖሊሲ ጉዳዮች፤ የሕገ-መንግሥት አንቀፆች፤ አዋጆች እና ሌሎች ውሳኔዎችን ከሀገራዊ ምክክሩ አስቀድሞ መወሰኑ የምክክር ኮሚሽኑን በማቋቋም ያሳየውን በጎ ተስፋ የሚያጨልም ነው፡፡ ከመንግሥት በተጨማሪም የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ ልሂቃን፤ የሙያ ማሕበራት፤ የሲቪክ ማሕበራት፤ መገናኛ ብዙሃን፤ የሃይማኖት ተቋማት እና ሰፊው ሕዝብ እስካሁን ባለው ሂደት ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሚና በአግባቡ አልተወጡም፡፡ ሀገራዊ ምክክር ለተወሰኑ ግለሰቦች ወይም ተቋማት ብቻ የሚተው ሳይሆን የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የነገ ህልውና፤ ደህንነት፤ ሰላም፤ ልማት እና ተጠቃሚነት የሚወስን ጉዳይ መሆኑን አለመገንዘብ ሁላችንንም ለውድቀት የሚዳርግ መሆኑን ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ በሀገር ዕጣፈንታ ላይ የሚወሰንበትን ክንውን ትኩረት አለመስጠት ማኅበራዊ ኪሳራ እንደሆነ እያንዳንዱ ዜጋ ማወቅ አለበት፡፡ ፓርቲያችን ኢዜማ ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ ትኩረት እንድትሰጡት እያሳሰበ የሚከተሉት ምክረ ሃሳቦች ተግባራዊ ሊደረጉ ይገባል ብሎ ያምናል፡፡
Show all...
1. መንግስት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሊሠራ የሚችላቸውን መሠረታዊ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ተላልፎ ምክክሩ ላይ ጫና መፍጠሩን በአስቸካይ እንዲያቆም፤ እንዲሁም ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅበትን መንግሥታዊ ሐላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ፤ 2. ምክክር ኮሚሽኑ ለዜጎች መድረስ ያለባቸው መረጃዎች በአግባቡ መድረሳቸውን እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ ተገቢው ትኩረት እንዲሰጣቸው ማድረግ ላይ በአትኩሮት እንዲሰራ ብሎም ክንውኖቹን፤ እቅዶቹን እና የሀገራዊ ምክክሩን አስፈላጊነት በተመለከተ በመገናኛ ብዙሃን እየቀረበ በአግባቡ መልዕክቶችን ለማኅበረሰቡ ወቅቱን ጠብቆ እንዲያደርስ ራሱን የቻለ የአየር ሰዓት እንዲመደብለት 3. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም እና ምርጫ ቦርድ እንዲሁም ሌሎች የዴሞክራሲ ተቋማት እየሠሩት ያለውን ጅምር በጎ ሥራ ምሳሌ በማድረግ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በተሰጠው ስልጣን ልክ ተግባሩንና ታማኝነቱን ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ እንዲያደርግ፤ በኮሚሽኑ ውስጥ የሚያገለግሉ ግለሰቦችም ታማኝነታቸውን ለህሊናቸው እንዲያደርጉ 4. የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ ልሂቃን፤ የሙያ ማሕበራት፤ የሲቪክ ማሕበራት፤ መገናኛ ብዙሃን፤ የሃይማኖት ተቋማት እና ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሚና በአዎንታዊነት እንዲወጡ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ፡፡ በአጠቃላይ፤ ሀገራዊ ምክክር እንደስሙ ሀገራዊ መሆን አለበት፡፡ ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ያለምንም ተጽዕኖ እንዲሳተፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ሚና መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንደ ሀገር ያሉንን ልዩነቶች ለማስታረቅ ሁላችንም ከልባችን በእውነተኛነት መስራት አለብን፡፡ በጋራ ለአደጋ እንደተጋለጥነው ሁሉ፤ አደጋውንም በጋራ ለመጋፈጥና በጋራ ለመወጣት መትጋት ይጠበቅብናል። በኢዜማ በኩል የሀገራዊ ምክክር አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም አባላትን እንዲሁም ማሕበረሰቡን ለማንቃት የሚችለውን ሁሉ እያከናወነ ሲሆን፤ በቀጣይም ለሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን የበኩሉን ሚና እንደሚወጣ ማረጋገጥ ይወዳል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጥር 02/ 2015 ዓ.ም. https://drive.google.com/file/d/1V40ppZkk8s-H3wt9AFlqwPBHCVG_KON5/view?usp=drivesdk #የዜግነት_ፖለቲካ #ማኅበራዊ_ፍትህ #ኢዜማ
Show all...
እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!! #መልካም_ገና
Show all...
"የትኛውም ብሔር 'አዲስ አበባ የእኔ ናት' ሊል አይችልም። ... አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ ናት። ... የትኛውም ክልል አዲስ አበባ ላይ 'የኔ' የሚለው ጉዳይ የለም። ሊኖርም አይገባም።" (ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ - የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ) https://m.youtube.com/watch?v=3_eRcJumvMw&feature=youtu.be#bottom-sheet
Show all...
ሕግ የማያከብር ሕግ አስከባሪ ? ---------------------- ኢዜማ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አባሉ አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውንና አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው፤ የሕክምና ዕርዳታ የሚያገኙበት መንገድ እንዲመቻች በመጠየቅ ለሚመለከታቸው የፍትሕ አካላት እና ለምርጫ ቦርድ ተደጋጋማ አቤቱታ አቅርቦ ነበር። ቦርዱም ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጠው በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ፖሊስ ምላሽ ባለመስጠቱ፤ ለሦስተኛ ጊዜ ደብዳቤ ለመጻፍ ተገዷል። ፓርቲያችን ያቀረባቸውን ተደጋጋሚ አቤቱታዎችም ሆነ የምርጫ ቦርድ ጥያቄ ከመጤፍ ባለመቁጠር ያለመከሰስ መብት ያላቸውን የሕዝብ ተወካይ በማንአለብኝነት በማሠር ማንገላታት እና መደብደብ ሕገወጥነት ብቻ ሳይሆን ነውረኝነት ነው። ታከስ ከፋይ ዜጎች ሕግን እንዲያስከብርልን ያቋቋምነው ተቋም በማንአለብኝነት ሕግን የማጥስ ከሆነ ዜጎች ፍትሕን ከወዴት ያገኟታል?
Show all...
https://youtu.be/nZFa4vskK0Q የኢዜማ ሴቶች መምሪያ ሐላፊ ቅድስት ግርማ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከ ሃሌታ ሚዲያ ጋር ያደረጉት ቆይታ https://www.facebook.com/100063770933024/videos/1195892667630043/?flite=scwspnss&mibextid=jnPKxsCKaeeGyS9o የ ኢዜማ ዋና ጸሃፊ አበበ አካሉ የፕሪቶሪያውን ስምምነት አስመልክቶ ከ ኤፍ ኤም 97.1 ጋር ያደረጉት ቆይታ https://youtu.be/QnvvgV-oyIw የኢዜማ ሃገራዊ ምክክር ኮሚቴ አባል ብስራት ጌታቸው በፕሪቶሪያው ስምምነት እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ከ የኛቲቪ ጋር ያደረጉት ቆይታ https://youtu.be/K9MWzPnFt0g  የኢዜማ ዋና ጸሃፊ አበበ አካሉ የመንግስት አገልግሎት እና ሙስናን አስመልክቶ በ ፋና ቲቪ ያደረጉት ቆይታ https://www.facebook.com/123960474361367/posts/pfbid0hmLsqub8PPZfjLxALzX8jfRuLTP19YmbDnpXgHJf4HaeMHriPbvtgMPRDkpuaMZrl/?mibextid=Nif5oz የኢዜማ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ የፕሪቶሪያውን ስምምነት አስመልክቶ ከ ፋና ጋር ያደረጉት ቆይታ https://fb.watch/h8nW1kMvdp/ የኢዜማ ምክትል መሪ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን የኢዜማ አባል እና የምክር ቤት አባል ታረቀኝ ደግፌ እስርን አስመልክቶ ከጉራጌ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ያደረጉት ቆይታ https://youtu.be/t8LZ59jfx5c በወለጋ ማንነት መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ኢዜማ በሰጠው መግለጫ ባላገሩ ቲቪ የሰራው ዘገባ https://drive.google.com/file/d/1P4M1_4DzNGfsdPs5sgtoeAsKclSCapr0/view?usp=drivesdk የኢዜማ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ  የኢዜማ አባል እና የምክር ቤት አባል ታረቀኝ ደግፌ እስርን አስመልክቶ ከቢቢሲ ጋር ያደረጉት ቆይታ https://youtu.be/prq2PSNrSzM በአዲስ አበባ ት/ቤቶች የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባንዲራ መሰቀል እና መዝሙር መዘመርን አስመልክቶ ኢዜማ በሰጠው መግለጫ ኢሳት ቴሌቪዥን የሰራው ዘገባ (ከ 8፡20 ጀምሮ) https://drive.google.com/file/d/1P3nuiDQSsb3RZzKZInBaVYOJnaTS1uQj/view?usp=drivesdk የኢዜማ ድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሐላፊ ዋስይሁን ተስፋዬ ከሙስና ጋር በተያያዝ ከአዲስ ቲቪ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ያደረጉት ቆይታ  https://youtu.be/MLf4K1YO0rk የኢዜማ ድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሐላፊ ዋስይሁን ተስፋዬ በአዲስ አበባ ት/ቤቶች የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባንዲራ መሰቀል እና መዝሙር መዘመርን አስመልክቶ  ከአንከር ሚዲያ ጋር ያደረጉት ቆይታ https://youtu.be/5aMrAipAIb4 የኢዜማ ዋና ጸሐፊ አበበ አካሉ በአዲስ አበባ ት/ቤቶች የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባንዲራ መሰቀል እና መዝሙር መዘመርን አስመልክቶ ከ ኤፍኤም 107.8 ጋር ያደረጉት ቆይታ
Show all...
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ በአበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልልን አርማ መሰቀልና መዝሙር መዘመርን አስመልክቶ ህዳር 29/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በግልፅ እንዳስቀመጠው ይህ ህገ ወጥ ተግባር በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ብሎ እንደሚያምን አጽንኦት ሰጥቶ አሳስቧል የሚመለከተው አካልም ለከተማው ነዋሪዎች ግልፅ የሆነ መረጃ እንዲሰጥ ጥሪውን አቅርቦ ነበር፡፡ አሁንም በትምህርት ቤቶች እየተነሳ ያለው ሁከት ቀጥሎ መዝሙሩም ይዘመራል አርማውንም እንሰቅላለን የሚለው ግብ ግብ እንደቀጠለ ነው፡፡ ኢዜማ ይህን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለው ሲሆን ለሚመለከታቸው አካላትም በጉዳዩ ላይ ማብራርያ እንዲሰጡን እና ይህ ሕገወጥ ተግባር እንዲቆም የሚጠይቅ  ደብዳቤዎችን አስገብቷል፤ ሆኖም ግን የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ሁለት ጊዜ የላክነውን ደብዳቤ አልቀበልም በማለት ለህግ እንደማይገዛና በማናለብኝነት አንደሚንቀሳቀስ በገሀድ አስመስክሯል፡፡ ለሚመለከታቸው አካላት ያስገባነውን ደብዳቤ ከዚህ በታች ያያዝን ሲሆን አሁንም በድጋሚ ብጥብጡን እየፈጠረው ያለውን አርማ የመስቀልና መዝሙር ዘምሩ የማለት ግዳጅ እንዲቆም እየጠየቅን በቀጣይነትም ጉዳዩን ወደ ህግ አግባብ ወስደን እልባት እንዲያገኝ ከማድረግ ወደኃላ እንደማንል ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡ #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Show all...
ግልጽ ለማድረግ ያህል ! - በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር ማንም ለማንም የማይሰጠው ወይንም የማይነፍገው ሊከበር የሚገባ ሰብአዊ መብት ነው። - በፍላጎት ላይ ተመሥርቶ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ ተጨማሪ ቋንቋን መማር ቢበረታታ ይጠቅማል። - ሕዝቡ "እፈልጋለሁ" እስካለ ድረስ 83ቱም ብሔሮች ቋንቋቸውን ለማስተማር እኩል መብት አላቸው። - በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር የክልል መዝሙርን ከመዘመርም ሆነ የክልል አርማን ከመስቀል ጋር የሚያገናኘው አንዳች ጉዳይ የለም። - በግድ "ቋንቋዬን ተማሩ፣ መዝሙሬን ዘምሩ፣ አርማዬን ስቀሉ" ማለት ግን የለየለት አምባገነንነት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ማይምነት ነው። - በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማርን ሰበብ አድርጎ የከተማ ንጥቂያም ሆነ የፖለቲካ ሽሚያ የሚመኙ ካሉ ምኞታቸው አይሳካም።
Show all...
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ አባልና የሴቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ቅድስት ግርማ እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ማዕረጉ ግርማ የሀገር አቀፍ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ምክር ቤት ሰብሳቢ እንዲሁም የሀገር አቀፍ ፓርቲዎች የአካል ጉዳተኛ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሆናችሁ በመመረጣችሁ ፓርቲያችሁ የተሰማውን ደስታ እየገለጸ፤ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲሰፍን ዴምክራሲያዊ አሰራር እንዲዳብር የተሰጣችሁን አደራ በሃላፊነት እንደምትወጡ ልበ ሙሉ መሆናችንን እየገለፅን ፍሬያማ የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ አንመኛለን፡፡ #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Show all...
ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ሆነ የፌደራል መንግስቱ ኃላፊዎች በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የሕዝብ ተመራጮች ለመረጣቸው ህዝብ ድምፅ ሆነው አስፈላጊውን ማስተካከያ እንዲደረግ ጫና ካልፈጠሩ እና ሁኔታውን የማያረጋጉ ከሆነ፣ ሂደቱ ወደ አላስፈላጊ ብጥብጥና አለመረጋጋት ከተሸጋገሩ የመጀመሪያ ተጠያቂዎች መሆናቸውን አበክረው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ህዳር 29/2015 ዓ.ም
Show all...
የአዲስ አበባን ሕዝብ መብትና ፍላጎት በጉልበት ለመጨፍለቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ይቁም! ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ /ኢዜማ/ የተሰጠ መግለጫ፤ ባለፈው ዓመት ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቂሊንጦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጀምሮ እስከ ትናንትናው ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በበርካታ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ፣ የክልል መለያ አርማና መዝሙርን መነሻ በማድረግ አላስፈላጊ ውጥረትና ግጭት እንዲቀሰቀስ እና የትምህርት ሂደቱ እንዲስተጓጎል ተደርጓል፤ ሁኔታውም እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶችም አሉ። ሰንደቅ ዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር የሀገርን ትርጉም የሰነቁ ትዕምሮቶች ናቸው። ጀግኖች አባቶቻችን ቀኝ ገዢ ወራሪዎችን የተፋለሙት የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ አንግበው፤ ብሔራዊ መዝሙሯንም በሕብረት እየዘመሩ ስለመሆኑ ታረክ በደማቁ መዝግቦታል። አትሌቶቻችን ድል ባደረጉባቸው የዓለም አደባባዮች ሁሉ በድል ከፍ አድርገው ያውለበለቡት የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ነው። በስሜት እንባቸውን አፍስሰው የዘመሩትም ብሔራዊ መዝሙራችንን ነው። በአሸባሪዎች የተከፈተብንን ጦርነት የመከትነውም በሀገራችን ሰንደቅዓላማ ስር ተሰባስበን ነው። ይህ ሁሉ የሚያመለክተው ሰንደቅዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር የሀገር መገለጫ ክቡር ጌጦች መሆናቸውን ነው። ከዚህ መሠረታዊ ግንዛቤ፣ መርህ እና ሕጋዊ አሠራር ባፈነገጠ መልኩ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚደረገው ሕገወጥ የሆነ የአንድን ክልል መዝሙር እና መለያ አርማ ከሀገር ሰንደቅ ዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር እኩል ወይም በላይ ተማሪዎች ላይ ለመጫን መሞከር ግጭትና ሁከትን ወደ ከተማዋ ማስረግ መታሰቡን ማሳያ ነው፡፡ ኢዜማን ግርታ የፈጠረበት ጉዳይ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ የአዲስ አበባ አስተዳደር እና የፌደራል መንግስት ሀላፊዎች በጉዳዩ ላይ ያላቸው አረዳድ ትክክለኛ ባለመሆኑ መሬት ላይ እየፈጠሩት ያለውን ችግር ልብ ብለን ስናየው ችግር ካልተፈጠረ በሥልጣን ላይ መቆየት የማይችሉ እስከሚመስል የተደረሰበት ሁኔታ ነው። አንድን አመለካካት ብቻ በበላይነት ለመጫን የተቀረፀው ሕገ መንግስት እንኳን በሁኔታው ላይ ከሚሰጠው አረዳድ ውጭ በአዲስ አበባ ከተማና በኦሮሚያ ክልል መሀከል ያለውን የግንኙነት መስመርና የአሰራር መርህ የጣሰ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከተለያዩ ምንጮች ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ሕገወጥ ተግባር በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በተከታታይ ተስተውሏል። ለአብነትም፤  አርብ ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቂሊንጦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ረቡዕ ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብሔራዊ አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ረቡዕ ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ረቡዕ ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በሚያዝያ 23 የአጸደ ህጻናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ሐሙስ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፈለገ ዮርዳኖስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ማክሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጠመንጃ ያዥ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ሐሙስ ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ አምባ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  አርብ ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ድል በትግል እና አዲስ ተስፋ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፤  ማክሰኞ ህዳር 27/2015 ዓ.ም ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሙሉ ብርሃን (አዲስ ብረሃን) ትምህርት ቤት፤  ማክሰኞ ህዳር 27/2015 ዓ.ም ጉለሌ ክ/ከተማ ቀጨኔ ደብረሰላም ትምህርት ቤት፤  ማክሰኞ ህዳር 27/2015 ዓ.ም የካ ክ/ከተማ ከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ረቡዕ ህዳር 28/ 2015ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አዲስ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልልን አርማ ለመስቀል እና የክልሉን መዝሙር ለማስዘመር በተደረጉ ሕገወጥ ተግባራት ረብሻዎች፣ ግጭቶች እና የትምህርት ክፍለጊዜ መስተጓጎሎች ከመከሰታቸውም ባለፈ ድርጊቱን የተቃወሙ ተማሪዎች እና መምህራንም ታስረዋል፤ ተደብድበዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች አንድም በከተማው አስተዳደር ወይም በፌደራል መንግስቱ ሥር ያሉ ናቸው። የአዲስ አበባን መስተዳደር ም/ቤትን የመረጠው የአዲስ አበባ ሕዝብ እንጂ የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ አይደለም፤ የፌደራል መንግስቱም የተመረጠው፣ የአዲስ አበባን ሕዝብ ጨምሮ፣ በሁሉም ክልሎች በሚኖረው ሕዝብ በመሆኑ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ወይም በፌደራል መንግስት ሥር የሚገኙ ት/ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎችን የኦሮሚያ ክልል መዝሙር ዘምሩ፣ የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ አውለብልቡ ተብለው የሚታመሱበት ጉዳይ ፍጹም አግባብነት የለውም፡፡ እንደ ኢዜማ አረዳድ ይህ አካሄድ በየትኛውም መመዘኛ ሕጋዊ መሠረት የሌለው ሲሆን ከአዲስ አበባ ት/ት ቢሮም ሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካላት በጽሑፍ የሰፈረ መመሪያና ትዕዛዝ ወደ ት/ቤቶች መተላለፍ አለመተላለፉን ለአዲስ አበባ ሕዝብ በግልጽ እንዲያሳውቁ አበክረን እንጠይቃለን፡፡ የነገው አገር ተረካቢ ትውልድ በዘር ፖለቲካ ትርክት ተፅዕኖ ሥር ወድቆ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር መቆርቆሩን የሀገር ተስፋ መሆኑን ማሳያ ምልክት ነው። ታዳጊ ተማሪዎች የሀገር ትርጉም ገብቷቸው ለኢትዮጵያ ሲሟገቱላት፤ በዕድሜ ታላላቆቻቸው ደግሞ በሀገር ቋሚ ምልክቶች ላይ ሲቀልዱ መመልከት በእጅጉ ያሳፍራል። መጪው ትውልድ ሀገሩን የበለጠ እንዲወድ ማድረግ በሚገባቸው ትምህርት ቤቶች ከፋፋይ ትርክቶችን ማስተጋባት በሀገር ዕጣ ፈንታ ላይ መቀለድ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። ለትምህርት ከቤታቸው የወጡ ተማሪዎችን ለግጭት መጋበዝም ኢ-ሞራላዊነት መሆኑም አፅንዖት ሊሰጠው ይገባል። በዚህ አጋጣሚም ተማሪዎች ለግጭት የሚጋብዟቸውን ድርጊቶች በትዕግስት፣ በሰላማዊ እና ስርዓት ባለው መንገድ በማስተናገድ ራሳቸውን ከጉዳት እንዲጠብቁ መልዕክት ማስተላለፍ እንወዳለን። የፀጥታ አካላትም ተማሪዎችን ከጉዳት መጠበቅ እንጂ የሀይል አካሄድን በፍጹም መጠቀም እንደማይገባቸው እያሳሰብን የስርዓት ሳይሆን የህዝብ ጠባቂ መሆናቸውንም ለአፍታም ቢሆን እንዳይዘነጉት መልዕክታችንን እናስተላልፋለን። ምንም እንኳን መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር በሰንደቅ አላማችን መደብ ላይ በሚያርፈው አርማ ሙሉ ለሙሉ መግባባት ላይ ባይደረስም፤ ሕጋዊ ዕውቅና ያለውን የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር ማጉደፍ ግን በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሰሞኑን በአዲስ አበባ ት/ቤቶች በተነሱ ግጭቶች የተነሳ ጉዳት ለደረሰባቸው ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለእስር የተዳረጉት ተማሪዎች እና መምህራን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ይጠይቃል።
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!