cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኬብሮን

በዚህ ቻናላችን፦- የቤተ ክርስቲያን ትውፊት፣የእለት ተዕለት በአላት፣ መዝሙራት፣የቅዱሳን ታሪክ፣ውዳሴ ማርያም የግዕዝ ጥናት ይማራሉ። -ኬብሮን ማለት ሕብረት ማለት ነው፡፡ -ለማንኛውም አሰተያየትና ጥያቄ @yetewahidoligoch_bot ይጠቀሙ፡፡

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
190Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

 በዓለ ደብረ ቁስቋም በዓለ ደብረ ቁስቋም እንኳን አደረሰን ዲያቆን ዘካርያስ ነገደ ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡ ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭) የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡ ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡ እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም፤ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡›› ‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡ አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ  ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ (ድርሳነ ማርያም) ኅዳር ፮ ቀንን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡፡ ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም መጽሐፍ ትርጉም በመምህር ተስፋ ሚካኤል፤ ፳፻፫ ዓ. ም ‹‹እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም›› (ዘዳ. ፴፫፥፳፮)
Show all...
#ሱላማጢስ_ተመለሽ (መሐልይ ፯፦፩) +. ጠቢቡ ሰሎሞን ስለቅድስት ድንግል ማሪያም መካነ-ልደቷ ፤ዘላለማዊ ድንግልናዋን ፤ቅድስናዋን፤ የአምላክ እናትነቷን ተገልጾለት እንደተናገረ ሁሉ፤ ፍቅር አንድነት የተሰጣት፤ ፍቅር አንድነትን በቃል ኪዳኗ የምታሰጥ ፍጽምት በመሆኗ ምክንያት ሱላማጢስ የተባለች የቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታ ጋር ወደ ግብፅ የመሰደዷን ነገር በመንፈሰ-እግዚአብሔር ተገልጾለት ተናገሯል፡፡ ‹‹ ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጡስ፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤/ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ እናይሽ ዘነድ ተመለሽ/ በማለት ፍቅር አንድነት የተሰጣት ፤ፍቅር አንድነት የምታሰጥ ፍጽምት ቅድስት ድንግል ማርያም ተመለሽ ተመለሽ ባንቺ የተደረገውን ተድላ ደስታ እንይ ሲልአብራርቷል፡፡ +. ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ-ሐንታ በማህሌተ-ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ በበረሃ እንደምትኖረው ዋኖስ ሱላማጢስ የተባለች እመቤታችንም በግብፅ በርሃ መኖሯን እንዲህ እይላሉ፦ ‹‹ኦ ሰላመ-ሰጣዊት እንተ-ትሔውጺ እምርኁቅ ወትትርአዪ ለኩሉ በደብረ-ምጥማቅ ተፈሥሒ ድንግል ዘገዳመ-ጽጌ ማዕነቅ እስመ-ሰምዐ በምድርነ ቃለ-ተአምርኪ ጽድቅ ለአድኅኖ-ዓለም ዘይበቁዕ እምብሩር ወወርቅ›› ; /ፍቅር አንድነት የተሰጠሸ ፍቅር አንድነት የምታሰጭ ፍጽምት ሱላማጢስ ድንግል ከሩቅ የምትጎበኚ ነሽ ፤በደብረ ምጥማቅ ለሁሉ የምትታዪ የበረሃ አበባ ዋኖስ ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ፤ከብርና ከወርቅ ይልቅ በደለኛን ለማዳን እውነት ያለበት የታምርሽ ቃል በምድራችን ተሰምቷልና ደስ ይበልሽ/ በማለት የሰሎሞንን መሐልይ መነሻ በማድረግ ተርጉመውታል፡፡ +. ጠቢቡ ሰሎሞን በመቀጠልም እንዲህ ይላል፦ ‹‹ከርሥኪ ሥውጠ ሥርናይ ወሕጹር በጽጌ››/ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር በአበባ የታጠረ ነው/ በማለት የእመቤታችን ማሕፀኗ ሥጋውን በአምሳለ ኅብስት የሰጠን የወልደ እግዚአብሔር ማደሪያና ፤በጸጋ መንፈስ ቅዱስ የታጠረ የተከበበ መሆኑን ተናግሯል፡፡ አባ ጽጌ-ድንግልና አባ-ገብረ ማርያም በማሕሌተ-ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ የሰሎሞንን ቃል ሲተረጉሙ፦ ‹‹ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከነፍርኪ ጽጌ ሥውጠ ሥርናይ ከርሥኪ ወሕጹር በጽጌ ትእምርተ ሕይወትየ ድንግል ወዘጉንደ መንግሥት በጽጌ በማሕሌተ ጽጌ እዌድሰኪ ለጽጌ ተቀጺልየ ዘንጽሕኪ ጽጌ››/ከንፈሮችሽ ፍሕሶ እንደሚባል ቀይ ልም ሐር ናቸው፤ሆድሽ ስንዴን የተመላ በአበባ የተከበበ ድንግል ሆይ የድኅነቴ ምልክትና የመንግሥት ሥር መሠረት አነቺ ነሽና የንጽሕናሽን ዘውድ ተቀዳጅቸ አበባ (አነቺን) በማሕሌት አመሰግንሻለሁ በማለት የመንግሥት ሥር የሆኑ እነ ዳዊት እነ ሰሎሞን ባመሰገኑበት ቃል እነርሱም አመስግነዋል፡፡ +. ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮረጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖ ድርሰቱ ላይ ሰሎሞን ተናገረውን እንዲህ በማለት ይገልጸዋል፦ ‹‹ኦ እግዝእትየ መርዓት እምግበበ አናብስት ዘወጻእኪ፤ ወእምአድባረ አናምርት ወእምታእካ ዘነገሥት ዘቆምኪ ይመስል በቀልተ ወክሳድኪ ከመ አርማስቆስ ግብረ እደ ኬኒያ አዕይንትኪ ከመ ኮከበ ጽባሕ ወመላትሕኪ ቀይሕ ከመ ጽጌረዳ ዘሐይቀ ኢያሪኮ ወአስናንኪ ጸዐድዒድ ኅጹባት በሐሊብ ወጣዕመ ቃልኪ እምአስካለ ወይን፤ መዐዛ አፉኪ ከመ ርሔ አፈው ወጼና አልባስኪ ከመ ሠርጸ ጢስ ዘስኂን ኩለንታኪ ሠናይት ኦ መርዓት አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ወመዐድም ሥንኪ ወአጥባትኪ ከመ ሄላ፤ ወይሕውዝ እምኔሆን ሐሊብ ድንግልናዊ በዘቦቱ ተሐፅነ መሴሰየ ኩሉ ዘሥጋ›› /ከነገሥታት እልፍኝ ከአናምርት ተራሮችና ከአናብስት ጉድጓድ የወጣሽ ቁመናሽ የሰሌን ዛፍ የሚመስል ሙሽራዪቱ እመቤቴ ሆይ አንገትሽ ብልኽ አንጥረኛ እንደሠራው የወርቅ ዘንግ ነው፤ ዓይኖችሽም እንደ አጥቢያ ኮከብ ነቸው፤ ጉንጮችሽ በኢያሪኮ ባሕር ወደብ ላይ እንዳለ ጽጌረዳ አበባ ናቸው፤ጥርሶችሽም በወተት የታጠቡ ነጫጮች ናቸው፤ የአነጋገርሽ ጣዕም ከወይን ፍሬ ወገን ነው፤የአፍሽም መዐዛ እንደ አፈው ሽታ ነው፤ የልብሶችሽም መዓዛ የዕጣን ወገን እንደሚሆን ቅታሬ ጢስ ነው፤ሙሽራዪት ሆይ ሁለንተናሽ ያማረ ነውና ምንም ምን ነውር የለብሽም፤ ደምግባትሽ ያማረ ነው፤ጡቶችሽ እንደ ምንጭ ናቸው፤ከነርሱም የድንግልና ወተት ይፈሳል ፤ሥጋ የለበሰውን ሁሉ የሚመግብ ጌታ ባደገበት ገነዘብ/ በማለት በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ የቅድስት ድንግል ማርምን ዘላለማዊ ድንግልንዋን፤መካነ ልደቷን ፤ ንጽሕንዋን ፤ቅድስንዋን፤የአምላክ እናትነቷንና የመልኳን ደም ግባት በስፋትና በጥልቀት ተንትኖ ተናግሯል። በመመለሷ ሀገራችንን ወደቀደመ ክብሯ፣ አንድነቷ ትመልስልን፤ ሕዝባችንንም በበረከቷ ትጎብኝልን፤ በስደት ያሉትንም በሰላም ትጠብቅልን። #ለዓለመ_ዓለም_አሜን!!! የእመብርሃን ምልጀዋ ሁሌም አይለየን!!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
Show all...
+ ተማሪዎች ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ይህን ይጸልዩ + የግብፅ ቤተክርስቲያን በቅርቡ ማዕረገ ቅድስና የሠጠቻቸው ቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡ ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡ +++ ጸሎት +++ ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ! አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡ ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡ ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!" ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጥቅምት 2014 ዓ.ም.
Show all...
የእምነት አባቶቻችን የጌታ ደቀመዛሙርት ህይወታቸው እንዴት አለፈ? ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥ 💥 ማርቆስ እስኪሞት ድረስ በአሌክሳንድርያ ግብፅ ጎዳናዎች በፈረስ ታስሮ እየተጎተተ ህይወቱ አልፋለች:: 💥 ሉቃስ በግሪክ ሰቅለውት ህይወቱ አልፋለች:: 💥 ማቴዎስ በቆንጨራ ተቆርጦ ሞቷል:: 💥 ዮሐንስ በፈላ ዘይት ውስጥ ተቀቅሎ ህይወት አለፏል:: 💥 ጴጥሮስ ተዘቅዝቆ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቷል:: 💥 ቶማስ በህንድ በጦር ተወግቶ መስዋእት ሆኗል:: 💥 ጳውሎስ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገርፎ አንገቱ ተቆርጦ ህይወቱ አልፏል:: 💥 ስምዖን ግማሽ ለግማሽ ተቆርጦ ነው የሞተው:: 💥 ማትያስ በድንጋይ ተወግሮና አንገቱ ተቆርጦ:: 💥 እንድርያስ በስቅላት ህይወቱ አልፏል። 💥 ያዕቆብ በእየሩሳሎም አደባባይ አንገቱ ተቆርጦ ነው የሞተው:: 💥 በርተለሚዎስ በግርፋት ህይወቱ አልፏል:: . ሁሉም መልካሙን ገድል ተጋደሉ ክርስቶስን ካዱ ሲባል አይሆንም ብለው አንገታቸውን ለካራ ሰውነታቸውን በዘይት ለመቀቀል ለግርፋት ለስቅላት አሷልፈው ሰጡ። . በረከታቸው ይደርብን🙏
Show all...
Watch "መዝሙር #shorts" on YouTube https://youtube.com/shorts/CgnETOokeI8?feature=share
Show all...
Watch "ዜማ ዘመለክአ ማርያም [ #Murade_Zema_Tube ]" on YouTube https://youtu.be/kyriZCvf9ZA
Show all...
ዜማ ዘመለክአ ማርያም [ #Murade_Zema_Tube ]

#Murade_Zema_Tube #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #መ/ር #አበበ #ቤተማርያም ዝግጅቱን ስለተከታተሉ እናመሰግናለን፡፡ Subscribe በማድረግ ቤተሰቡን ይቀላቀሉ፡፡

#ድንግል_ሆይ_ከሚያስብ_ሁሉን_ከማይዘነጋ_ከልጅሽ_ዘንድ_አሳስቢ ◦◦◦ #ድንግል_ሆይ በቤተልሔም ካንቺ የተወለደውን መወለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስን ያሟሟቁትንም #አሳስቢ ◦◦◦ #ድንግል_ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ከሀገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ካንቺ ጋራ መሰደዱን #አሳስቢ ◦◦◦ #ድንግል_ሆይ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ #አሳስቢ ◦◦◦ #ድንግል_ሆይ ረኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኃዘኑን ከእርሱ ጋራ የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ #አሳስቢ ◦◦◦ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ መዓትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ ◦◦◦
Show all...
"...፥ እኔም ትውልድ ነኝ...፥"
Show all...
+++ " ጌታዬ ሆይ ኃጢአት የሚያስተሠርይ ዕንባ የለኝም፡፡ የዚህን ዓለም ሥራ በማሰብ ልቡናዬ ደከመ፡፡ ተቈርቍሮ ወደ አንተ ያለቅስ ዘንድ አይቻለውም እነሆ በኃጢያት ብዛት ልቡናዬ ተባረደ። አንተን ወዶ በሚፈስሰው ዕንባ መናደድ አይቻለውም፡፡ የሀብታት የምሥጢራት መገኛ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አንተ ግን ራርተህ ፈጽሞ መመለስን ስጠኝ። ካንተ በመራቅ ካንተ በመለየት ተሰጥቶኝ የነበረውን ክብር አጣዋለሁ " +++ #ወዳሴ_አምላክ (ዘዘወትር)
Show all...