cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Show more
Advertising posts
41 987Subscribers
No data24 hours
+1017 days
-42530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ተማሪ መመገብ ያልቻሉ ዩኒቨርስቲዎች እየበዙ ነው🤔 ዲላ ዩኒቨርስቲም የምግብ በጀት እጥረት እንደገጠመው ገልቷል፡፡ ቀደም ሲል የወላይታ ድቻ ዩኒቨርስቲ ተመሳሳይ እጣፈንታ እንደገጠመው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ አብዛሃኛዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለመመገብ ችግር እንደገጠማቸው በዚህ ዘገባችን ስር ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ችለናል፡፡ ለማሳያነትም ድላ፣ ሀዋሳ እና አምቦ ዩኒቨርስቲ በበጀት እጥረትና በምግብ ግብኣት ችግር ተማሪዎቻቸውን መመገብ እንዳልቻሉ ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ችለናል፡፡ ድላ ዩኒቨርስቲው በለጠፈው ማስታወቂያ እንደ ሀገር ባጋጠመን የምግብ በጀት እጥረትና የምግብ ዋጋ መጨመር ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት አስቆጥሯል ብሏል፡፡ ተማሪዎቼ ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ አትክልት እንድመገቡ እያደረኩ ነው ብሏል፡፡ በአስቸኳይ የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ አቅርቦ እንዲሟላልን ጠይቂያለሁ ያለው የድላ ዩኒቨርስቲ የአቅርቦት ሁኔታው እስከሚስተካከል በትዕግስት ጠብቁ ሲል አስታውቋል፡፡ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት @NATIONALEXAMSRESULT
Show all...
👍 24😭 16👎 1🔥 1
ተማሪ መመገብ ያልቻሉ ዩኒቨርስቲዎች እየበዙ ነው🤔 ዲላ ዩኒቨርስቲም የምግብ በጀት እጥረት እንደገጠመው ገልቷል፡፡ ቀደም ሲል የወላይታ ድቻ ዩኒቨርስቲ ተመሳሳይ እጣፈንታ እንደገጠመው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ አብዛሃኛዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለመመገብ ችግር እንደገጠማቸው በዚህ ዘገባችን ስር ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ችለናል፡፡ ለማሳያነትም ድላ፣ ሀዋሳ እና አምቦ ዩኒቨርስቲ በበጀት እጥረትና በምግብ ግብኣት ችግር ተማሪዎቻቸውን መመገብ እንዳልቻሉ ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ችለናል፡፡ ድላ ዩኒቨርስቲው በለጠፈው ማስታወቂያ እንደ ሀገር ባጋጠመን የምግብ በጀት እጥረትና የምግብ ዋጋ መጨመር ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት አስቆጥሯል ብሏል፡፡ ተማሪዎቼ ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ አትክልት እንድመገቡ እያደረኩ ነው ብሏል፡፡ በአስቸኳይ የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ አቅርቦ እንዲሟላልን ጠይቂያለሁ ያለው የድላ ዩኒቨርስቲ የአቅርቦት ሁኔታው እስከሚስተካከል በትዕግስት ጠብቁ ሲል አስታውቋል፡፡
Show all...
Bank Jobs - የባንክ ስራዎች

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚወጡ የትኛውንም የባንክ ስራዎች በፍጥነት እና በአንድ ቦታ ያግኙ!

በመጪው ሰኔ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የአገልግሎት 500 ብር የመክፈል እና ደረሰኝ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በደብዳቤ ማሳወቁን ተመልክቻለሁ። አዩዘሀበሻ 👉ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 http://t.me/ayuzehabeshaofficial http://t.me/ayuzehabeshaofficial
Show all...
#Update የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል? ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ በማሰባሰብ በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በኩል አረጋግጠው ባሳለፍነው ሳምንት ለትምህርት ሚኒስቴር መላካቸውን ያገኘነው መረጃ ያሳያል። 👉https://t.me/hugadssachannel
Show all...
👍 19😭 4 3
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የፃፈው ደብዳቤ ፡ ጉዳዩ፦ ያለአግባብ ገንዘብ ከባንክ ወጭ ያደረጉ ተማሪዎችን ይመለከታል፤ እንደሚታወቀው ባንካችን መጋቢት 06/2016ዓ.ም የሲስተም ማዘመን ስራ እየተሰራ በተፈጠረው የሲስተም ችግር ምክንያት ደንበኞች ያለአግባብ ገንዘብ ሳይኖራቸው ከሂሳባቸው ወጭ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ባንካችን ከአ/ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር በተሰራው የማስመለስ ስራ አብዛኛው ደንበኞች ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ መመለስ ችለዋል፡፡ ነገር ግን ጥቂት የሚባሉ ደንበኞች ዕዳቸውን ከፍለው በሚፈለገው ፍጥነት ሊመልሱ አልቻሉም፡፤ በመሆኑም ዩኒቨርስቲው ይህንን የሀገር ሃብት ለማስመለስ እስካሁን ድረስ ለሠራው ሥራ ምስጋናችንን እያቀረብን፣ የቀረውን ገንዘብ ማስመለስ ይቻል ዘንድ ከዚህ ደብዳቤ ጋር ባያያዝነው ሠንጠረዥ ላይ በተመለከተው ዝርዝር መሠረት ልክ እንደዚህ ቀደሙ በተቋሙ ለሚገኙ ተማሪዎች ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ #በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተመላሽ እንዲደረግ ልዩ የሆነ መመሪያ እንዲሰጣቸው በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ [የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ] ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
👍 30😁 19 5😭 3👏 1
ዒድ ሙባረክ ! መጻህፍት ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445 ዓ/ሂ የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል። በዓሉ የሰላም፣የመተሳሰብ እና የፍቅር ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልጻል። ዒድ ሙባረክ
Show all...
👍 21 4
Show all...
አዲስ_ዓለም(belayzgetnet) is LIVE | TikTok

ስለ ኦቲዝም እንወያይ ከዶ/ር ስመኝ ጋር. Check out አዲስ_ዓለም(belayzgetnet) LIVE videos on TikTok! Watch, follow, and discover the latest content from አዲስ_ዓለም(belayzgetnet).

7👌 4🥰 1
የ8ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን... የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ሰኔ 4 - 5/2016 እንዲሰጥ ተወስኗል። ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት @NATIONALEXAMSRESULT
Show all...
👍 25 3👎 1🥰 1
አዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት ዛሬ ማለትም ቅዳሜ ከምሽቱ2:30 ጀምሮ በtiktok አካውንቷ ብቅ ብላ ስለ ኦቲዝም ምንነት  ትተነትናለች። በፕሮግራሙ ዶ/ር ስመኝ ተስፋዬ ስለ ኦቲዝም ምንነት ያዘጋጀችውን ካጋራችን በኋላ የውይይት ጊዜ ይኖረናል። ዶ/ር ስመኝ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ መምህርት ስትሆን፣ በማህበራዊ ገጿም ጤና ነክ ጉዳዮችን ለማህበረሰቡ በመልቀቅ ከሚመጡ ችግሮች ቀድመው ይጠነቀቁ ዘንድ ማህበራዊ ግዴታዋንም እየተወጣች ያለች እህታችን ናት። በዚህም በኦቲዝም ዙሪያ ትኩረት አድርጋ ለመስራት የምትሻ በመሆኗ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከኦቲዝም ጋር በተያያዘ ተሳትፎ ታደርጋለች። ዛሬ ምሽት የአዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት ታድማ ስለ ኦቲዝም  ከቃረመችው ብሎም ለእናንተ የእውቀት ምንጭ የሚሆን መረጃ ይዛ ስለምትቀርብ በፕሮግራሙ በመታደም ብዙ ታተርፋላችሁ። ወንድምና እህቶቼ ምናልባት እርስዎ በማጋራትዎት አንድ ሰው ሊጠቅሙ ይችላሉና ሳይሰስቱ የሚመለከታቸው ሰዎች ላይ ይደርስ ዘንድ ያጋሩ ፕሮግራም ዛሬ ቅዳሜ ምሽት 2:30 ፕሮግራሙ የሚተላለፍባት ገጽ 👉http://tiktok.com/@belayzgetnet 👉http://tiktok.com/@simegn.tenachin
Show all...
👍 10👌 2 1
በኢትዮጵያ ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ ምክንያቱ ‹‹ከፍተኛ የሙቀት መጠን ነዉ›› ሲል  የዓለም ባንክ ገለጸ🤔 የዓለም ባንክ አደረግኩት ባለዉ ጥናት በኢትዮጵያ ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ ምክንያቱ ከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመር ነዉ ብሏል፡፡ ከፈረንጆቹ 2003-2019 በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የወሰዱ ወደ 2.5 ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎችን ዳታ ሰብስቦ ያገኘዉ ዉጤት መሆኑን ነዉ ይፋ ያደረገዉ፡፡ በትምህርት ዓመቱ ለከፍተኛ ሙቀት የተዳረጉ በተለይ ደግሞ በፈተና ወቅት ከባድ ሙቀት የሚያገኛቸዉ ተማሪዎች ፤ቀዝቃዛ አየር ባለባቸዉ ስፍራዎች ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር ሲወዳደር ዉጤታቸዉ በእጅጉ ቀንሶ ተገኝቷል ነዉ ያለዉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ተጽዕኖ በተለይ በሰብ-ሰሃራ አፍሪካ አገራት ላይ የበረታ ነዉ የተባለ ሲሆን፤ የአየር ንብረት ለዉጡን ለመቋቋም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች በስፋት አለመኖራቸዉ ሁኔታዉን እንደሚያባብሰዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡ የጥናቱ መሰረታዊ ግኝት የሆነዉ በትምህርት ዘመኑ ከፍተኛ ሙቀት የሚስተናገድባቸዉ ቀናት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸዉ እንዲቀሩ የሚያደርግ መሆኑን ነዉ፡፡ ይህም በኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎች ላይ ወደ 2.28 በመቶ ዝቅ ያለ ዉጤት እንዲመዘገብ እንደሚያደርግ ነዉ፡፡ በጥናቱ ይፋ እንደሆነዉ ግልጽ የሆነ ምክንያት ባይቀመጥለትም ወንዶች ከሴቶች በበለጠ በሙቀት መጨመሩ ምክንያት የፈተና ዉጤታቸዉ ዝቅ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከወንዶች ጋር ሲነጻጸሩም ሴቶች በተሻለ መልኩ በትምህርት ገበታቸዉ ላይ የሚገኙ እና ለትምህርታቸዉም ከፍተኛ ቦታ ያላቸዉ ሆነዉ ተገኝተዋል፡፡ አሁን ላይ በተለያዩ የአለማችን አገራት ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ የሙቀት መጨመር ምክንያት መሆኑን ማስረጃ አለን ሲሉ በዓለም ባንክ የሪሰርቸሮች ግሩፕ ዋና ተመራማሪ ፓትሪክ ቤህረር ተናግረዋል፡፡ ፓትሪክ ጨምረዉም ከፍተኛ ሙቀት ከተማሪዎቹ በተጨማሪ በመምህራን የስራ እንቅስቃሴ ላይም የራሱ ተጽዕኖ ይኖረዋል ነዉ ያሉት፡፡ ፖሊሲ አዉጪዎች ይህንን ጉዳይ በደንብ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ያሉት ተመራማሪዉ ፤በመማሪያ ክፍሎች ዉስጥ ያለዉን የሙቀት መጠን በማስተካከል ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ስፍራን መፍጠር አለባቸዉ ብለዋል፡፡ የተሻለዉ አማራጭ እንደየአከባቢዉ የሚለያይ ቢሆንም ግን አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሲሉ የሚጨምሩት ተመራማሪዉ ፤ይህም ተማሪዎች ለከፍተኛ ሙቀት ያልተጋለጡ አከባቢዎች ላይ እጅግ በተሻለ ሁኔታ መማር እንደሚችሉ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በ2022 ዘ ጋርዲያን ይዞት በወጣዉ አንድ ጽሁፍ ከፍተኛ የሙቀት መጨመር በጥራት እንዳናስብ በማድረግ ፣ የማሰላሰል እና የማመዛዘን ችሎታችን ላይ ተጽዕኖ ስለሚኖረዉ ስህተት የመስራት ዕድላችንን ከፍ ያደርገዋል ሲል አስታዉቆ ነበር፡፡ @NATIONALEXAMSRESULT
Show all...
😁 75👍 36🤣 17👎 4 4💯 2👏 1