cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Princess ❤

" መንፈሴ በአንድ መንገድ ፣ስጋዬ ደግሞ በሌላ አቅጣጫ ይመሩኛል ።በሁለቱ ኃይሎች ፍጭት መሐል ነፃነቴ እንደሚወጣ ግን ይሰማኛል ፤ ያ ነፃነት ግን ዘግይቶ እንደሚመጣ ፣በስቃይም እንደሚገኝ አውቃለሁ ..." @Tenswaa

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
167Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ደካማ ሰዎች ይበቀላሉ፣ ጠንካራ ሰዎች ይቅር ይላሉ፣ ብልህ ሰዎች ችላ ይላሉ። @tinswaa
Show all...
🌈⭐️⭐️ ደስታን ላራሳቾችን ስንፈልገው ⭐️ 🌟 አይገኝም ነገርግን ደስታን ለሰው ⭐️ ስንሰጠው ወደ እኛ ተመልሶ ይመጣል፣ ይህ የደስታ ምስጢራዊ አስማት ነው። ስለዚህ ባለን አቅም ሁሉ ደስታን ለሰው እንስጥ የእኛ ደስታ ከምናስበው በላይ እያደገ እያደገ ይመጣል። @tinswaa
Show all...
ደሃው ሞቶ ሞቶ ሀብታም ብቻ ቀረ ሀብታም ኖሮ ኖሮ ደሃ ሆኖ ቀረ እርሱም እንደ ደሃው ለሞት ተቃረበ የሚረዳው አጥቶ ተኝቶ ተራበ የሚያስታምም ጠፍቶ ሞትንም ተመኘ ግን እንደምኞቱ ሞትም አልተገኘ ✍ ታምሀዊ @tinswaa
Show all...
በአንዷ ህይወቴ ሁለት ምርጫ ይዤ ነብሴን እየቀጣሁ ለስጋዬ አግዤ መኖርን መርጬ ከአምላኬ ስጣላ ወደፊት እየሔድኩ ሳላይ ወደኋላ ብርቅርቋ ዓለም ሆና ተገላልጣ ለጊዜያዊ ኑሮ ዘላለሜን ሳጣ ጨረስኩት እድሜዬን መንገዴን እንዳጣው ተስፋባገኝ ብዬ ይኸው ደጅህ መጣው ✍ ታምሀዊ @tinswaa
Show all...
☞.............አእምሮን ለመደምሰስ እንጂ ለመሙላት እንዳልመጣሁ የሚያወሱ አንዳንድ አሉታዊ ነገሮች ብቻ ይነገሩ ይሆናል ፡፡ሆኖም አሮጌዉ አእምሮ ካልተደመሰሰ አዲሱ ሊፈጠር አይችልም ፡፡ፈጠራ ከጥፋት ዉስጥ ያንሠራራል፡፡ህይወትም በሞት ዉስጥ ያብባል፡፡.............. ☞ እዚህ ያሉ ስራወቼ በሙሉ አእምሮን በመደምሰስ ላይ ያተኩራሉ ፡፡ የአእምሮ ስሮችን በጣጥሶ በመጣልም በእያንዳንዱ የህይወት ጊዜያት ነፃነታችሁን ታዉጃላችሁ ፤ እናም ያለ አንዳች ያለፈ ታሪክ መኖር ትችላላችሁ ፡፡ከአለፈ ታሪክ ጋር መኖር በእስር ቤት ተከርችሞብን እንደመኖር ነው ... ባግዋን ኦሾ @tinswaa
Show all...
“የሰዉ ልጅ በጣም የሚገርም ፍጡር ነዉ፡፡ ገንዘብ ለማግኘት ሲል ጤናዉን መስዋእት ያደርጋል፡፡ ከዛ መልሶ ጤናዉን ለማግኘት ያለዉን ገንዘብ በሙሉ ያፈሳል፡፡ ስለነገ በጣም ይጨነቅና ዛሬን መኖር ይረሳል ፣ዉጤቱ ደግሞ ዛሬንም ነገንም እንዳይኖር ያደርገዋል፡፡ ሰዉ አንድም ቀን እንደማይሞት አድርጎ ይመላለሳል ነገር ግን አንድም ቀን ሳይኖር ይሞታል” - -ዳላይ ላማ-- @tinswaa
Show all...
ለራስ የሚነገር መልዕክት ___ መልዕክት 1 እራስክን ከማንማ ጋር አታወዳድር፡፡ ይህን ባደረክ ጊዜ እራስክን በራስህ እንደሰደብክ ቁጠረው፡፡ መልዕክት 2 ቁልፍን ያለመክፈቻ ማንም እንደማይሰራ ሁሉ ፈጣሪም መፍትሄ የሌለው ችግር እንዲገጥምን አይፈቅድም፡፡ መልዕክት 3 ደስታህን ከራስህ ባራቅህ ጊዜ ሕይዎት በአንተ ላይ ትስቃለች፡፡ ደስተኛ በሆንክ ጊዜ ሕይዎት ፈገግታዋን ትለግስሃለች፡፡ ሌሎች እንዲደሰቱ ምክንያት በሆንክ ጊዜ ግን ሕይዎት የከበረ ሠላምታዋን ታቀርብልሃለች፡፡ መልዕክት 4 ማንኛውም ስኬታማ ሰው ከበስተጀርባው አስቸጋሪ ታሪኮች እንዳሉት ሁሉ ማንኛውም የችግር(አስቸጋሪ) ታሪክ መጠናቀቂያው ስኬት ይሆናል፡፡ ስለሆነም ችግሩን ተቀበልና ለስኬት ተዘጋጅ፡፡ መልዕክት 5 የሌሎችን ስህተት ለመተቸት በጣም ቀላል ነው፡፡ ከባዱ ነገር የእራስን ስህተት መረዳቱ ላይ ነው፡፡ መልዕክት 6 የተፈጠረልህ መልካም አጋጣሚ ባመለጠህ ጊዜ እዛው ባለህበት ቁመህ አይንህን በእንባ አትሙላ፡፡ ቀጣዩንና የተሻለውን መልካም አጋጣሚ እንዳታይ ይከልልሃልና፡፡ መልዕክት 7 ለችግር ፊትን ማዞር ችግሩን አይቀይረውም ችግሩን መጋፈጥ እንጅ፡፡ በሌሎች ቅሬታን ከማሰማት እራስን ለውጦ ሠላምን መግዛት፡፡ መልዕክት 8 ስህተት ስህተቱ በተፈጠረበት ወቅት ስሜትን ይጎዳል፡፡ ከዓመታት በኋላ የስህተቶች ድምር የሚፈጥረውና ወደ ስኬት የሚያመራው ከስህተት መማር ተሞክሮ(ልምድ) እንለዋለን፡፡ መልዕክት 9 የቀለጠ ወርቅ ጌጣጌጥ እንደሚሆነው፣ የተጠረበ ድንጋይ ሀውልት እንደሚሆነው ሁሉ፣ አንተም በብዙ ችግር ባለፍክ ቁጥር አንተነትህ እያደገ መሆኑን አትርሳ፡፡ በመሆኑም ስትሸነፍ ጠንካራ ስታሸንፍ የተረጋጋ ሁን፡፡ @tinswaa
Show all...
😍👏👏👏👏
Show all...