cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

kingdom first youth ministry

ይህ ግሩፕ የተመሠረተው የእግዚአብሔር ቃል ምንማማርበት ነው የመሠረትኩትም እንድንሰራራበት ነው ጥላሁን ነኝ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
198Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ማቴዎስ 7 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ “በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ¹⁴ ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው።
Show all...
ለተኛ ጋቢውን ፣ ለሮጠ ፈረሱን ይሰጠዋል። ኢትዮጵያዊያን ሁሉን ተሸክማ የምትኖር ዓለም ከሰነፍ በስተቀር የሚከብዳት የለም። ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ልህቀት ላይብረሪ ኑኑኑኑኑኑ እናንብብ!!
Show all...
ይሁዳ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁰ እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፤ እጅግ ቅዱስ በሆነው እምነታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ ትጉ፤ በመንፈስ ቅዱስም ጸልዩ። ²¹ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚያደርሳችሁን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ ሳለ፣ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
Show all...
[19/05, 06:11] Tilahun Mamo: 1ኛ ዮሐንስ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵ ከእርሱ የሰማነው ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት፣ እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም፤ የሚል ነው። ⁶ በጨለማ እየተመላለስን ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል እንዋሻለን፤ እውነትንም አንኖረውም። [19/05, 06:12] Tilahun Mamo: 1ኛ ዮሐንስ 2 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ማናቸውንም ነገር አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድ፣ የአብ ፍቅር በእርሱ ዘንድ የለም፤ ¹⁶ ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም። ¹⁷ ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል።
Show all...
“ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤” — 1ኛ ጴጥሮስ 3፥15 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
1ኛ ጴጥሮስ 2 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ² በድነታችሁ እንድታድጉ፣ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹሑን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤ … ¹⁵ ምክንያቱም፣ መልካም በማድረግ የአላዋቂዎችን ከንቱ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። … ²¹ የተጠራችሁትም ለዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የእርሱን ፈለግ እንድትከተሉ ምሳሌን ሊተውላችሁ ነው።
Show all...
ሰላም ወዳጆቼ ዛሬ አንድ ዝግጅት ልጋብዛችሁ ነው። በልህቀት የተዘጋጀ እንጦጦን የንባብ ቦታው በጋራ ለመጎብኘት አስበናል ቀኑም ግንቦት 16 እሁድ ጠዋት ሲሆን የቲሸርት ሁለት መቶ (200) ብር ብቻ በመክፈል አብረውን መጓዝና በንባብ ዙሪያ አብረውን መምከር ይችላሉ። ለመመዝገብና ሌላ መረጃ ከፈለጉ +251929287386 ፍሬ +251915632382 መቅደስ +251925869996 በምነት ብለው በመደወል በቶሎ ይመዝገብ ያለን ቦታ ውስን ነው።
Show all...
ከእንቅልፋችን ዛሬ እንንቃ መለወጥ ባለብን ጊዜ እንለወጥ ለማደግና ፍፁም ለመሆን መተው ያለብን እንተው ማስጣል ያለብንን እናስጥል መጋት ማቆም የማደጋችንና ለታላቅ የአገልግሎት ግብዣ የምንጠራበት መንገድ ነው ነው ዕብ 5 13፤ ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ 14፤ ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው። ኢየሱሰ ክርስቶስን ለመምሰል ታላቅ ለሆነ ማንነት ተጠርተናል ዘፍ 21 8፤ ሕፃኑም አደገ፥ ጡትንም ከመጥባት ተቋረጠ፤ አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣን አደረገ። ሰለዚህ እኛ ዘሬ በተሰጠን አጭር ጊዜ ሞተንና ሸተን በጨለማውስጥ የነበርን ጌታ ደርሶ በህይወት ለዘላለም ኑሩ የተባልን እኛ ዛሬ አታላይ የሆነውን አለም ጥለን በክርስቶስ ፍቅር ውስጣችን ተቃጥሎ በሱ ፍቅር ዝለን እሰክንወድቅ ድረስ ክርስቶስን በመናፈቅና መንፈስቅዱስን ቀነንና ሌሊት በመጠማት ወደ እግዚአብሄር ማደግ ግድ ይለናል በመሰቀሉ ላይ የተከፈልን ዋጋ እጅግ ውድ ከውድም በላይ ውድ ነው ወደ ኤፌሶን 1 18-19፤ ተባረኩ።
Show all...
ሰው ወደ ራሱ ውስጣዊ ማንነት ለመመለስ #የኋላ_ማርሽ ያስፈልገዋል! ሄነሪ ፎርድ የመጀመሪያውን መኪና ሲሰራ መኪናው የኋላ ማርሽ አልነበረውም ። ወደ ቤቱ ተመልሶ ለመምጣትም አስቸጋሪና ዙርያ ጥምጥም መሄድ ብሎም ረጅም መንገድ መጓዝ የግድ ነበር ። ከመኪና ጋራዡ ጥቂት እርምጃዋችን ድንገት አልፎ ከሄደ ወደ ጋራዡ ለመመለስ አዳጋች እንደሆነ ከተረዳ በኃላ ነበር ፎርድ የኋላ ማርሽን የሰራው ። ከዚህ ተማሩ ... #የኋላ_ማርሽ የሌለው ህይወት የምትኖሩ ከሆነ ወደ እናንተነታችሁ ማእከል ተመልሳችሁ መምጣት አትችሉም ። በሕዝብነት ተራ ትርምስ ውስጥ ጠፍታችሁ ትቀራላችሁ ። በተመስጦ ማሰላሰል ወደራሳችሁ የምትመለሱበት የሕይወት የኋላ ማርሽ መሆኑን ተገንዘቡ ። ሌሎችን መከተል ብቻውን ወደ ትርምስና ወደ በራስ አለመተማመን የሚወስድ ነውና ..
Show all...
2ኛ ጴጥሮስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²-³ የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ⁴ ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!