cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኑ በጌታ ደስ ይበለን!🎧🎤..🎸.🎵..

እዚህ ቻናል ላይ :- 👉አዳዲስና ዘመን የማይሽራቸዉ ዝማሬዎች 👉አምልኮዎችን(Live Songs) 👉 ስብከቶች፣ የመ.ቅ ጥቅሶችን 👉ልዩ መልዕክት ያላቸውን ፒክቸሮችን ያገኛሉ! ይ🀄️ላ🀄️ሉን 👉ለ አስታያየት አና ማገልገል ለምትፈልጉ @Wendi4th @bibi_son

Show more
Advertising posts
188Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
የዕለቱ ቃል🗞 “በወንጌል #እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን #ኢየሱስ ክርስቶስን #አስብ፤” — 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥8
Show all...
ኢየሱስ ክርስቶስ ብሉይ ኪዳን ባመስጥሮ ,ሀዲሱ ኪዳን ደግሞ በገሀድ የሚተርኩት የቅዱሱ ቃል አማናዊ ግልጠት ነው!!! .... በዘመን መጨረሻ እግዚአብሔር የተናገረበት እንከን የለሽ ንፁህ መስዋዕት !!! በሞቱ ሞታችን ሞቷልና, በህይወቱ ህይወታችን ኖሯልና , በደስታ ስብሐት እንለዋለን ❤ @Nigaaat https://t.me/wengel1
Show all...
፦የአባቴ ብሩካን ✨ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከእየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ፦ያህ በአሰላ የሚገኝ ኤሎሄ የተሀድሶ መንፈሳዊ ግሩፕ ሲሆን ፦በእዚህ ገፅ ፦የስብከታችን ዋና እና የአምልኳችን ዋና የሆነውን ክርስቶስ እየሱስን መግለጥ፣ መስበክ ፦እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ ፦ጥዑመ ያሬዳዊ ዝማሬዎችን ያገኛሉ ይ🀄️ላ🀄️ሉን https://t.me/ELI_ADONAI https://t.me/ELI_ADONAI
Show all...
“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።” — መዝሙር 65፥11 ✨ጻድቅ አባት ያለፈውን አሮጌ ያህን አዲሱን አዲስ ብለን እንድንልና እንድንቀበል ስላደረከን ክበር ተመስገን!!! አሜን😍😍🙏🙏
Show all...
“የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም እኮ የሚሻለውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእርሷ አይወሰድም።”” — ሉቃስ 10፥42 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
“ነገር ግን እግዚአብሔር በሚፈሩት፣ በምሕረቱ በሚታመኑትም ይደሰታል።” — መዝሙር 147፥11 (አዲሱ መ.ት) ✨ጻድቅ አባት ሆይ ስለዚህ ማለዳ ተመስገን!!!
Show all...
“But seek first the kingdom of God and His righteousness, and all these things shall be added to you.” — Mat 6:33 (ABC)
Show all...
“በርታ ሰውም ሁን፤ የምታደርገውንና የምትሄድበትን ሁሉ ታከናውን ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ ሥርዓቱንና ትእዛዛቱን ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ፥ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ።” — 1ኛ ነገሥት 2፥3 ✨ጻድቅ አባት ሆይ ስለ ሁሉ ተመስገን!!
Show all...
“ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ጌታ ሆይ፤ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤” — ዮሐንስ 6፥68 (አዲሱ መ.ት) ✨እድሜያችን ላይ ይህን ቀን የጨመርክልን ጻድቅ አባት ሆይ ተመስገን!!
Show all...
“ለሚጠፋ እንጀራ አትሥሩ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር ምግብ ሥሩ፤ ለዚህም እግዚአብሔር አብ ማረጋገጫ ማኅተሙን በእርሱ ላይ አትሞአልና።”” — ዮሐንስ 6፥27 (አዲሱ መ.ት) ✨በእድሜያችን ላይ ይህን ቀን የጨመርክልን ጻድቅ አባት ሆይ ተመስገን!!
Show all...
ኢሳይያስ 55 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ ምድርን በማራስ፣ እንድታበቅልና እንድታፈራ ለዘሪው ዘር፣ ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣ ¹¹ ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣ በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤ የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል። ✨በእድሜያችን ላይ ይህን ቀን የጨመርክልን እግዚአብሔር ተመስገን !!
Show all...
“እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥19 (አዲሱ መ.ት) ✨ስለሰጠኀን ስለዛሬዋ ማለዳ ጻድቅ አባት ሆይ ተመስገን!!
Show all...
“እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤ በእውነትህም እሄዳለሁ፤ ስምህን እፈራ ዘንድ፣ ያልተከፋፈለ ልብ ስጠኝ።” — መዝሙር 86፥11 (አዲሱ መ.ት) ✨ስለሰጠኀን ስለዛሬዋ ማለዳ ጻድቅ አባት ሆይ ተመስገን!!
Show all...
“ለራሳችሁ ጽድቅን ዝሩ፤ የጽኑ ፍቅርን ፍሬ ዕጨዱ፤ ዕዳሪውንም መሬት ዕረሱ፤ እርሱም መጥቶ፣ ጽድቅን በላያችሁ እስኪያዘንብ ድረስ፣ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና።” — ሆሴዕ 10፥12 (አዲሱ መ.ት) ✨ስለዚህ ማለዳህ አባት ሆይ ተመስገን!!
Show all...
“ዝማሬ በማቀርብልህ ጊዜ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ፤ አንተ የተቤዠሃትም ነፍሴ እልል ትላለች።” — መዝሙር 71፥23 (አዲሱ መ.ት) ✨ስለዚህ ማለዳ እግዚአብሔር ይመስገን!!
Show all...
“በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእርሱ የተነሣ ነው፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፣ ጽድቃችንና ቅድስናችን፣ ቤዛችንም ሆኖአል።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥30 (አዲሱ መ.ት) ✨ስለዚህ ማለዳ እግዚአብሔር ይመስገን!!!
Show all...
✨የተወደዳችሁ የአባቴ ብሩካን የጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ✨አብርሃም አንድያ እና ውድ ልጁ ይስሐቅን ሊሰዋ በማለዳ እግዚአብሔር ወደ አሳየው ተራራ ይስሐቅን ሊሰዋ ሔደ ...... 👉ይስሐቅ ለአብርሃም ፦አንድያ ልጁ ፦ዘሩን የሚያበዛለት ብቸኛ ልጁ ፦በሽምግልና ያገኘው ፦የሀብቱ ወራሽ ፦የአምላኩ እግዚአብሔር ቃል......ብቻ ይስሐቅ ለአብርሃም እንደ አይኑ ብሌን ነበር ግን ይህ ሁሉ ይስሐቅ ለአብርሃም ቢሆንም አብርሃም ግን አንድ ነገር ያቃል ይስሐቅ ቃል ከሆነው ከእግዚአብሔር እንደማይበልጥ ያውቃል ፤ቀዳሚ ከሆነዉ እግዚአብሔር እንደማይበልጥ ያውቃል ቅድሚያም ለእግዚአብሔር ይላል.....አብርሃም እንዲህ ነበር። ....እኛስ ግን እንዴት ነን🤔???? ዘፍጥረት 22 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን ፈተነው፤ “አብርሃም!” አለው። እርሱም “አቤቱ አለሁ” አለ። ² እግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ “የምትወደውን አንዱን ልጅህን፣ ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው። ³ በማግስቱ ጠዋት አብርሃም ማልዶ ተነሣ፤ አህያውን ጭኖ፣ ሁለት አገልጋዮቹንና ልጁን ይስሐቅን ይዞ፣ ለመሥዋዕት የሚበቃውን ዕንጨት ከቈረጠ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞውን ጀመረ፤
Show all...
“ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤ በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።” — ኢሳይያስ 50፥4 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
✨የተወደዳችሁ የአባቴ ብሩካን የጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ✨ልጅ ሳለው ወደ እናቴ እቅፍ መግባትን እጓጓ ነበር እናቴም እራሴን በእጆችዋ እየዳበሰች ወደ ማላቀው ግን ልወጣ እና ልነቃ ወደ ማልፈልግበት ያኔ በትንሿ አይምሮዬ ወደ ማቃት ሰላም ታስገባኝ ነበራ "እናቴ😍" እናቴን ጌታ አብዝቶ ይባርክልኝ!!! ✨ወደ እግዚአብሔር እቅፍ መገባትን እንጓጓ ያኔ እግዚአብሔር ወደ እጆቹ እቅፍ ያስገባናል፣ በሰላሙም ያሳርፈናል ብቻ እኛ የእርሱን መገኘት እንናፍቅ ህልውናውን እንሻ መገኘቱ ወዳለበት እናቅና ያኔ እርሱን እግዚአብሔርን ማግኘት ይሆንልናል።
Show all...
“ሌሎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትሕትና ቊጠሩ እንጂ፣ በራስ ወዳድነት ምኞት ወይም ከንቱ ውዳሴ ለማግኘት አንዳች አታድርጉ።” — ፊልጵስዩስ 2፥3 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
ላንተ ከተባለ 😍❤️ ለአንተ ነዉ ልባል እንጂ ለእየሱስ ነዉ ልባል እንጂ
Show all...
2ኛ ቆሮንቶስ 12 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ መመካት ብፈልግ እንኳ እንደ ሞኝ መቈጠር የለብኝም፤ ምክንያቱም የምናገረው እውነት ነው። ነገር ግን ማንም ስለ እኔ ከሚያየውና ከሚሰማው በላይ እንዳይገምተኝ ከመመካት እቈጠባለሁ። ⁷ ከዚህ ታላቅ መገለጥ የተነሣ እንዳልታ በይ የሥጋዬ መውጊያ፣ እርሱም የሚያሠቃየኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ። ⁸ ይህ ነገር ከእኔ እንዲወገድልኝ፣ ጌታን ሦስት ጊዜ ለመንሁት፤ ⁹ እርሱ ግን፣ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ ፍጹም የሚሆነው በድካም ጊዜ ነውና” አለኝ። ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ያድር ዘንድ፣ ይበልጥ ደስ እያለኝ በድካሜ እመካለሁ። ¹⁰ ስለ ክርስቶስ በድካም፣ በስድብ፣ በመከራ፣ በስደትና በጭንቀት ደስ የምሰኘው ለዚህ ነው፤ ስደክም ያን ጊዜ ብርቱ ነኝና።
Show all...
🎙️ እኔ ምናፍቅህ 😭 አሁን ያለውበትን መንፈሳዊ ርሀብ የገለፀልኝ ድንቅ መዝሙር በጌታ ስሙት
Show all...
“መኖሪያችን የሆነው ምድራዊ ድንኳን ቢፈርስም፣ በሰው እጅ ያልተሠራ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሆነ ዘላለማዊ ቤት በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።” — 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥1 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
መዝሙር 104 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ ክብርንና ግርማን ለብሰሃል። ² ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል፤ ሰማያትንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፤ ³ የእልፍኝህን አግዳሚ በውሆች ላይ አኖርህ፤ ደመናትን ሠረገላህ አደረግህ፤ በነፋስ ክንፍ ትሄዳለህ። ⁴ መላእክትህን መንፈስ፣ አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ። ⁵ ለዘላለም እንዳትናወጥ፣ ምድርን በመሠረቷ ላይ አጸናሃት። ⁶ በጥልቁ እንደ ልብስ ሸፈንሃት፤ ውሆችም ከተራሮች በላይ ቆሙ። ⁷ በገሠጽሃቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ፤ የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ። ⁸ በተራሮች ላይ ፈሰሱ፤ ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ፣ ወደ ሸለቆዎች ወረዱ። ⁹ ተመልሰው ምድርን እንዳይሸፍኑ፣ አልፈውም እንዳይመጡ ድንበር አበጀህላቸው። ¹⁰ ምንጮችን በሸለቆ ውስጥ እንዲሄዱ አደረግህ፤ በተራሮችም መካከል ይፈሳሉ፤ ¹¹ የዱር እንስሳትም ከዚያ ይጠጣሉ፤ የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ይቈርጣሉ። ¹² የሰማይ ወፎች ጎጇቸውን በወንዞቹ ዳር ይሠራሉ፤ በቅርንጫፎችም መካከል ይዘምራሉ። ¹³ ከላይ ከእልፍኝህ ተራሮችህን ታጠጣለህ፤ ምድርም በሥራህ ፍሬ ትረካለች። ¹⁴ ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤ ¹⁵ የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣ ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣ ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል። ¹⁶ ደግሞም የእግዚአብሔር ዛፎች፣ እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች ጠጥተው ይረካሉ፤ ¹⁷ ወፎች ጎጆአቸውን በዚያ ይሠራሉ፤ ሽመላ በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ታገኛለች። ¹⁸ ረጃጅሙ ተራራ የዋልያ መኖሪያ፣ የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው። ¹⁹ ጨረቃን የወቅቶች መለያ አደረግሃት፤ ፀሓይም የምትጠልቅበትን ጊዜ ታውቃለች። ²⁰ ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤ የዱር አራዊትም ሁሉ በዚህ ጊዜ ወጥተው ይራወጣሉ። ²¹ የአንበሳ ግልገሎች ምግብ ፍለጋ ይጮኻሉ፤ የሚበሉትንም ከእግዚአብሔር ይሻሉ። ²² ፀሓይ በወጣች ጊዜም ይመለሳሉ፤ በየጐሬአቸውም ገብተው ይተኛሉ። ²³ ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል፤ እስኪመሽም በተግባሩ ላይ ይሰማራል። ²⁴ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች። ²⁵ ይህች ባሕር ሰፊና የተንጣለለች ናት፤ ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣ ስፍር ቍጥር የሌላቸውም ነፍሳት በውስጧ አሉ። ²⁶ መርከቦች በላይዋ ይመላለሳሉ፤ አንተ የፈጠርኸውም ሌዋታን በውስጧ ይፈነጫል። ²⁷ ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸው ዘንድ፣ እነዚህ ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ። ²⁸ በሰጠሃቸውም ጊዜ፣ አንድ ላይ ያከማቻሉ፤ እጅህንም ስትዘረጋ፣ በመልካም ነገር ይጠግባሉ። ²⁹ ፊትህን ስትሰውር፣ በድንጋጤ ይሞላሉ፤ እስትንፋሳቸውንም ስትወስድባቸው ይሞታሉ፤ ወደ ዐፈራቸውም ይመለሳሉ። ³⁰ መንፈስህን ስትልክ፣ እነርሱ ይፈጠራሉ፤ የምድርንም ገጽ ታድሳለህ። ³¹ የእግዚአብሔር ክብር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ እግዚአብሔር በሥራው ደስ ይበለው፤ ³² እርሱ ምድርን ሲመለከት፣ ትንቀጠቀጣለች፤ ተራሮችም እርሱ ሲዳስሳቸው ይጤሳሉ። ³³ በሕይወት ሳለሁ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ቆሜ እስከ ሄድሁ ድረስም አምላኬን እወድሳለሁ። ³⁴ እኔ በእግዚአብሔር ደስ እንደሚለኝ፣ የልቤ ሐሳብ እርሱን ደስ ያሰኘው። ³⁵ ኀጥአን ከምድር ገጽ ይጥፉ፤ ዐመፀኞች ከእንግዲህ አይገኙ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ ሃሌ ሉያ።
Show all...
📜የወደድከኝ ጊዜ ሰማይ የለም ነበር ፣ ገና አልተዘረጋም ቀን አልተቆጠረም ፣ አልመሸም አልነጋም ጨረቃ የለችም ፣ በምሽት ላይ ደምቃ ጸሐይም አታውቅም ፣ ወጥታና ጠልቃ የወደድከኝ ጊዜ....... የብሱ ተገላልጦ ፣ ምድር አልተባለም ውኃ በአንድ ስፍራ ፣ አልተሰበሰበም ምድር መሽከርከሯን ፣ ገና አልጀመረችም የሜዳን ቡቃያ ፣ አላበቀለችም የወደድከኝ ጊዜ....... ወፎች በሰማይ ላይ ፣ መብረር አልጀመሩም አራዊቱ ሁሉ ፣ በስም አልተጠሩም ምድርን ሊያጠጡ ፣ ወንዞች አልፈሰሱም አሦች በባሕር ውስጥ ፣ አልተንቀሳቀሱም የመረጥከኝ ጊዜ....... እኔ እንኳን ራሴ ፣ ገና አልተፈጠርኩም አንተን አላወ'ኩም ፣ አንተን አልመረጥኩም ያለነቀፌታ ፣ ያለ እንከን አ'ረከኝ ህፀፅ የሌለበት ፣ እድፍ አልባ አ'ረከኝ አለም ሳይፈጠር ፣ ይሄ ሁሉ ሳይሆን በክርስቶስ መረጥከኝ ፣ በፍቅር እንድሆን እናማ እንዲህ አልሁህ....... ሞቴን ልትሞትልኝ ፣ ግድ ያለህ መሞቴ የዘላለም እረፍት ፣ የሁሌ ሰንበቴ የሕይወት ቃል ያለህ ፣ ቃል የታጣልህ ቃል ፍቅር ከሚለው ቃል ፣ ማፍቀርህ ይልቃል ✍ሄኖክ አሸብር ✝ @Excellent_youth ✝ ✝ @Excellent_youth
Show all...
ራእይ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵ እንዲሁም ታማኝ ምስክር፣ ከሙታን በኵርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፣ ⁶ አምላኩንና አባቱን እንድናገለግልም መንግሥትና ካህናት ላደረገን፣ ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁ አሜን። ⁷ እነሆ፤ በደመና ይመጣል፤ የወጉት እንኳ ሳይቀሩ፣ ዐይን ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከእርሱ የተነሣ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎ! ይህ ሁሉ ይሆናል፤ አሜን። ⁸ “ያለውና የነበረው፣ የሚመጣውም፣ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ፣ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ” ይላል።
Show all...
1ኛ ቆሮንቶስ 15 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵⁴ #የሚጠፋው_የማይጠፋውን_የሚሞተውም_የማይሞተውን_በሚለብስበት_ጊዜ፣ “#ሞት_በድል_ተዋጠ” ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል። ⁵⁵ እንዲሁም፣ “ሞት ሆይ፤ ድል መንሣትህ የት አለ? ሞት ሆይ፤ መንደፊያህስ የት አለ?”። ⁵⁶ የሞት መንደፊያ ኀጢአት ነው፤ የኀጢአትም ኀይል ሕግ ነው። ⁵⁷ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድልን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ⁵⁸ ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።
Show all...
“እናንተም በመጨረሻው ዘመን ሊገለጥ የተዘጋጀው ድነት እስኪመጣ ድረስ በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል።” — 1ኛ ጴጥሮስ 1፥5 (አዲሱ መ.ት)
Show all...
የውሃ ጥም ሲይዘን ቦዶ የነበረውን ብርጭቆ በውሃ እንደምንሞላ ከዛም ጥማችንን እንደምናረካ፤ #የብጭቆው በውሃ መሞላት የአንተ የውሃ ጥም ነው። #የመርካትህም ምስጢር መጠማትህ ነው። 👉ለጥምህና ለራብህ እርካታ የሚዮንህ አንተ የተጠማሀውና የተራብከው እራሱ ነው ነገር ነው ሚሆነው፤ ከዛውጭ ከሆነ ማስታገሻ ቢሆን እንጂ መቼም እርካታ አይሆንም። #ትረካ ዘንድ እንደምትጠማ እንዲሁ እግዚአብሔርን የመፈለግ ጥማትና ረሀብ ሲኖረን እንረካ ዘንድ እግዚአብሔር እራሱን ይገልጥልናል፤ የሚያረካህ የተጠማሀው ነገር እንደሆነ እንዲሁ እግዚአብሔርን እርሱን ተጠምተሀልና ጌታ እግዚአብሔር #ለጥምህ_እርካታ_ሊሆን_እራሱን_ይገልጣል። #ጥማትህ_እግዚአብሔር፤ 😍እርካታህ_እራሱ_እግዚአብሔር። በሰማያት ላይ የተቀመጥከው ልቤን ማደሪያ ዙፋንህ ያረከው እንዳተ ሚሆን ሚያክልህ የለም ያውና ሕያው ለዘለዓለም ያውና ሕያው ለዘለዓለም
Show all...
😍“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።” 😍“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።” 😍“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።” 😍“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።” 😍“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።” 😍“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።” — ፊልጵስዩስ 4፥4 (አዲሱ መ.ት) 😍😍😍😍😍😍😊 https://t.me/Nubegetadesyibelen https://t.me/Nubegetadesyibelen
Show all...
የሚያድነዉን እውነት መውደድ፤ ማክበርና መታዘዝ ይሁንልን! Join 👇 @Nubegetadesyibelen
Show all...
#የኢየሱስ_ቅድምና ( #2 ) 🗣በአገልጋይ ብርሃኑ ታምራት 👉ጌታ ኢየሱስ በሥጋ የተገለጠው ከጊዜ በኋላ ከድንግል ማርያም ነው።ይሄ ግን ለመገለጥ ሥጋን መዋሃድን እንጂ ጅማሬን አያሳይም።ኢየሱስ አልፋ ነው። #የመጣውም_ከአለበት_ወደ_አለበት_እንጂ_ከአለበት_ወዳልነበረበት_አይደለም።እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦ 📖ዮሐንስ 1 ¯¯¯¯¯¯⁹ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን #ወደ_ዓለም_ይመጣ_ነበር። ¹⁰ #በዓለም_ነበረ፥ #ዓለሙም_በእርሱ_ሆነ፥ #ዓለሙም_አላወቀውም። 👉 #ወደ_ዓለም_በሥጋ_የመጣው_ኢየሱስ_በዓለም_ውስጥ_የነበረው_ነው። #የነበረው_መጣ።ያልታየው በሥጋ ተገለጠ።ዓለምን የፈጠረውም እርሱ ነው።በዓለምም ነበረ።ዓለም እንዲያየውና የማዳን ሥራውን ለመፈፀምም በሥጋ ተገለጠ። 👉በሥጋ ተገልጦ መመላለሱን፤ከሴት ተወልዶ የሰው ልጅ መባሉን ያዩ ሕልውናውን በሥጋ ከተገለጠበት ጊዜ ጀምረው እንዳይቆጥሩት "በመጀመሪያው ቃል ነበር…ቃልም ሥጋ ሆነ" በማለት የኢየሱስ ክርስቶስን ቅድምና አሰምቶ ዮሐንስ ተናገረ። 👉ያመንበት ኢየሱስ አልፋ ነው።ለፍጥረት መጀመሪያን የሰጠ መጀመሪያ የለሽ ቀዳማዊ እርሱ ነው።መጨረሻ የሌለው ዖሜጋም እርሱ ነው።ለፍጥረት ፍፃሜን ይሰጣል።እርሱ ግን ፍፃሜ የለውም። 👉በለበሰው ሥጋ ዘመን ቢቆጠርለትም በመለኮታዊ ማንነቱ መጀመሪያም መጨረሻም የለውም። 👉እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦ 📖ዮሐንስ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵⁷ አይሁድም፦ ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ⁵⁸ #ኢየሱስም፦ #እውነት_እውነት_እላችኋለሁ፥ #አብርሃም_ሳይወለድ_እኔ_አለሁ አላቸው። 👉ደግሞም ባለ ራእዩ ዮሐንስን እንዲህ አለው፦ 📖ራእይ 1 ¯¯¯¯¯¯¹⁷ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ #ፊተኛውና_መጨረሻው_ሕያውም_እኔ_ነኝ፥ ¹⁸ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ። 👉የኢየሱስ ሕልውና(መኖር) ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ በኋላ ሳይሆን ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር ነው። 🙏ዓለም ሳይፈጠር ለኖረ፤ዓለምንና በዓለምን ያለውን ለራሱ ለፈጠረ ለጌታ ኢየሱስ ክብር ይሁን።አሜን።። 🗓16/09/2014 የጌታ ዓመት✍
Show all...
#የኢየሱስ_ቅድምና 🗣በአገልጋይ ብርሃኑ ታምራት 👉የኢየሱስ ሕልውና የጀመረው በድንግል ማርያም ማኅፀን አይደለም። #ኢየሱስ_መጀመሪያ_ነው_እንጂ_መጀመሪያ_የለውም።ጊዜን የፈጠረ እርሱ ነውና ዘመን አይቆጠርለትም። 👉ዮሐንስ ወንጌሉን ሲጀምር የሚሰብከው ኢየሱስ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እንደነበር በመናገር ይጀምራል። 👉"በመጀመሪያው ቃል ነበር" በማለት በመጀመሪያ ያለው ጊዜ የመለኮትን ቅድምና ለመናገር ነው።በሥጋ መገለጥ ከዘመን ኋላ የተከናወነ ሲሆን የኢየሱስ ሕልውና ግን ከዘመን ዘመናት በፊት ዘመን የሚባል ቆጠራ ሳይኖር፤ዓለማት ገና ሳይፈጠሩ ነው። #ኢየሱስ #ቃል_የተባለው_በሁለት_ምክንያት_ነው። #አንደኛ፦ የመሆን(የኲነት) ስሙ ነው።ማለትም ለአብ ቃሉ ነው።አብ የሚናገረው በኢየሱስ ቃልነት አማካኝነት ነው።በአጭሩ ኢየሱስ የአብ ቋንቋው ነው።የሰው ሁሉ ቃል ዝርው(በአየር ተጭኖ ወደ ጆሮ የሚደርስ ከዛም የሚበተን) ሲሆን ኢየሱስ ግን ለአብ አካል ያለው ቃሉ ነው።እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦ “በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ #ስሙም #የእግዚአብሔር_ቃል ተብሎአል።” — ራእይ 19፥13 #ሁለተኛው፦ ቃል የተባለው የአብ መገለጥ ስለሆነ ነው።አብን ያየው ማንም የለም።ኢየሱስ ግን አብን ገለጠው፥ተረከው፥አብራራው።ስለዚህ በልብ ያለ ሀሳብ በቃል ሲነገር እንደሚገለጥ እንዲሁ ኢየሱስ የአብ መገለጥ ነው።ኢየሱስ የአብ መልክ፥የባሕርዩና የክብሩም መንፀባረቅ ነው።እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦ 📖ዕብራውያን 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥² ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት #በልጁ_በዚህ_ዘመን_መጨረሻ_ለእኛ_ተናገረን፤³ #እርሱም #የክብሩ_መንጸባረቅና #የባሕርዩ_ምሳሌ_ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤ 👉ስለዚህ ኢየሱስ የአብ ቃሉ ነው።አንድም አብ የሚናገርበት፥አንድም አብ የተገለጠበት ነውና። ይቀጥላል……… 🗓15/09/2014 የጌታ ዓመት✍
Show all...
1ኛ ቆሮንቶስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁶ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ²⁷ ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ ²⁸ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ @Nubegetadesyibelen
Show all...
ማቴዎስ 7 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። ⁸ የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።
Show all...
የሚናፈቅ እየሱስ አለ❤️❤️❤️ሲጠራ ሁሉ የሚያረካ.... አምላኬ አምላኬ ወዳንተ እገሠግሣለው ፤ነፍሴ አንተን ተጠማች ሥጋዬ አንተን ናፈቀች እንጨት እና ውሃ በሌለበት በምድረበዳ ሀይልህን እና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስህ ውስጥ ተመለከትኩክ ምህረትህ ከህይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሀል እንዲሁ በህይወቴ ዘመን አመሰግንሀለው። በአንተም ስም እጆቼን አነሳለው ነፍስም በቅቤ እና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች....ከንፈሮቼም ስምህን ያመሰግናሉ በመኝታዬም አስብሀለው በማለዳም እናገርልሀለው ረዳቴ ሆነህኛል እና በክንፎችህም ጥላ ደስ ይለኛልና ነፍሴ በሆላህ ተከታተለችህ። እኔም ቀኝህ ተቀበለችኝ..............መዝ፡63.. እየሱስን ምንናፍቀው በምቾታችን ሰአት ብቻ ሳይሆን የሚቀድም ሌላ እንዳላ ብዙዋች በሚያስቡበት ሰአት የስጋችንን የምቾት ጥያቄ አልፈን የነብስ እርካታ የሆነውን መናፈቅም ጭምር ነው እርሱ እውነተኛ መሻት ነውና...... እርሱ ህልውናችን እና የመኖራችን ዋና ነውና............እውነተኛ ጥምን የሚያረካ....ምድር ላይ ያሉ ብዙ ነገሮችን ነብሳችንን ብንመግባት ደግማ ትራባለች ልትረካም አትችልም ምክንያቱም ነብሳችን ውስጥ ያለው የእርካታ ጥያቄ ጉድጋድ ልኩ የእግ/ር ልጅ እየሱስ ብቻ ነው ሌላው አይሞላውም.....የልባችን ዙፋን ብቻውን ይገባዎል...... ነብሳችን የምትወድክ እየሱስ ሁሉም ይቅርና አንተ ከቤታችን ግባ....ና እና ልባችንን አርካው እየሱስ🙏🙏🙏
Show all...
1ኛ ቆሮንቶስ 16 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ። ¹⁴ በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን።
Show all...
📚ነገ ሌላ ቀን ነው ለጠላቶችህ ደስታ ብለህ ሳይሆን መሸነፍህ ለሚያስከፋቸው ሰዎች ብለህ ጠንካራ ሁን ዛሬ ውስጥህ ሰላም አጥቶ መኖር አስጠልቶሀል? ተስፋ እንዳትቆርጥ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ሰዎች ከሰው ክብር ዝቅ አርገውክ በሚጠሉህ ሰዎች ተከበሀል? የሚወዱህ ይመጣሉ፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ስንት የደከምክበት ቢዝነስ ብልሽትሽቱ ወጥቷል? ቀና በልና አማራጮችን ተመልከት፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ በትምህርትህ የተዘጋጀከውንና የደከምክበትን ያህል ውጤት አላመጣህም? ትምህርት በቃኝ እንዳትል፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። የተሸነፍከው የወደክ፣ የተሰበርክ ቀን አይደለም። የተሸነፍከው በወደክበት ለመቅረት አምነህ የተቀመጥክና ዳግም መሞከር ያቆምክ ዕለት ነው ። በል ተነስ ፤ ይህቺ ምድር ለተሸናፊ ቦታ የላትምና "ለችግሮችህ በሙሉ ትልቅ ችግር ሁንባቸው ።" ✝ Excellent_youth ✝ ✝ Excellent_youth ✝
Show all...