cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✝ የያሬድ ዜማ ለነፍሴ✝

አዘጋጅ:ኤፍሬም ነጋሽ እና ህይወት ጌታቸው!!! ✍🎧 ይህ ቻናል የተመሰረተበት ዓላማ 1.የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቆየት ያሉ መዝሙራት ለማቅረብ። 2.በቤተክርስቲያን ለአገልግሎት የሚውሉ ዜማዎችን። 3.መንፈሳዊ የዜማ ትምህርቶችን ለማስተላለፍ ነው። ✝የተደረገልንን እንናገር የተዋህዶን ክብሯን እናንጸባር✝

Show more
Advertising posts
538Subscribers
No data24 hours
-27 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

+++የልቤን በልቤ ይዤ+++ ================== የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜያለሁ የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜያለሁ ካለኝ ነገር ሁሉ አንቺን መርጫለሁ እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጂኝ እላለሁ አዝ--- ግራ ቀኝ ሕይወቴ በሾህ ታጥሮብኛል ከፊት ከኋላዬ መሠናክል በዝቷል እኔስ ያለምርኩዝ ጉዞዬ ከብዶኛል እመአምላክ ደግፊኝ እጄ ተዘርግቷል(2) አዝ--- ቆሜ ሥራመድ ጤነኛ መሥላለሁ የውሥጤን ጎዶሎ እኔ አውቃለሁ ድንግል ሆይ ቅረቢኝ አይዞህ ልጄ በይኝ የጭንቀቴን ካባ አውልቀሽ ጣይልኝ(2) አዝ--- እናት ያለው ሰው ፋፁም አይተክዝም አንድ ቀን ይሥቃል አልቅሶም አይቀረም ሀዘኔን በደሥታ ለውጭው እናቴ በሀሴት ልዘምር በቀረው ሕይወቴ በደሥታ ልዘምር በቀረው ሕይወቴ አዝ--- አሁንም ጎዶሎ በውሥጤ አለና ድንግል ሆይ ቅረቢኝ ዛሬም እንደገና ለዚህች ለትንሿ ለጥቂቷ ዕድሜ እንደከፋኝ አልኑር ቀና አርጊኝ እናቴ(2)
Show all...
#ልቅረብ_ከፊትህ🙏 (ወቅቱ የምህላ ነው ይህንን መዝሙር ተጋበዙልን) 🎙 ዘማሪ ታዲዎስ ልቅረብ ከፊትህ ቸርነትህ ይርዳኝ ዳን በለኝ ጌታ በእጆችህ ዳሰኝ(2) °°°° ከአልጋየ ተኝቼ ዘመናት አለፉ የህመሜ እንቆቅልሽ ይፈታልኝ ቁልፉ መፅጉዕን ያሰብከው ዘመድ አልባውን እኔንም አስበኝ ጌታ ባሪያህን °°° አምናለሁ ጌታየ እኔን አትረሳኝም ትመጣለህ አንተ ጥቂት ብትዘገይም ትፈውሰኛለህ እኔስ ተስፋ አልቆርጥም ቃልህን እንደሰው አትለዋውጥም °°°° ያለመድኃኒት መፈወስ ታውቃለህ የአልጋ ቁራኛን ድነሃል ትላለህ ለደካማው ብርታት ለእውሩ ብርሃን ለበሽተኞች ፈውስ መድሐኒታችን ቤተሰብ ይሁኑ @orthodoxzema
Show all...
ሰላም እለኪ እያለ ሰላም እለኪ እያለ/2/ ሐርና ወርቁን ስታስማማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ ተሰማ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ ተሰማ የገብርኤል ድምጽ ተሰማ ውሃ ስትቀጂ ክንፉን እያማታ ሊያበስርሽ የመጣው በታላቅ ደስታ ከሞገስሽ ብዛት /2/ ሲታጠቅ ሲፈታ አቅርቦልሽ ነበር የክብር ሰላምታ አዝ ====== የምሥራቹን ቃል ምስጢር ተሸክሞ ገብርኤል ተላከ ሊያረጋጋት ደግሞ እርጋታ ተሞልታ/2/ነገሩን መርምራ የመልአኩን ብሥራት ሰማችው በተራ አዝ ===== ይደሰታል እንጂ መንፈሴ በአምላኬ በምስጋና ሳድር ዘወትር ተንበርክኬ ሃሳቤ ለቅፅበት/2/ሌላ መች ያስባል ለእኔ ልጅን መውለድ እንዴት ይቻለኛል አዝ ====== ከአንቺ የሚወለደው ልዑል ነው ክቡር የተመስገነ በሰማይ በምድር ምስጢሩ ኃያል ነው /2/ይረቃል ይሰፋል ከአንቺ በቀር ይኼን ማን ይሸከመዋል አዝ ===== እጹብ ነው ድንቅ ነው አንቺን የፈጠረ አንቺን በመውደዱ ሰውን አከበረ ዓለም ይባረካል /2/በማሕፀንሽ ፍሬ ክብርሽን አልዘልቅም ዘርዝሬ ዘርዝሬ
Show all...
#ስምሽን_ቢጠሩ_የማትጠገቢ 🎙 ዘማሪ ፍቃዱ አማረ ስምሽን ቢጠሩ የማትጠገቢ የመንገድ ስንቄ ነሽ የነፋሴ መጋቢ ምስጋናሽ ይብዛልኝ ወደቤቴ ግቤ °°°° ጻድቃን የወረሱሸወ የእግዚአብሔር ከተማ የመንኩሳን ሰፈር የሞላብሽ ግርማ ቡራኬሽ ይድረሰኝ እናቴ ይህ ፍቅርሽ ነፋሴን በምስጋና ላንቺው ላድርስልሽ °°°° የአለም አርነት ጽህፈት ያለብሽ የህይወት ፊደሌ ጽድቅ የተማርኩብሽ ቢያነቡሽ አታልቂ ሚስጥርሽ የሰፋ ስምሽ ማራኪ ነው ከልብ የማይጠፋ °°°° በሰው አገር ስኖር ሰው ጠፋቶ ከጎኔ ባልጀራ ሆነሽ የለሊት ብርሀኔ ተስፋዬን አብዝተሽ ጥሜን አስታገሽው በብዙ በረከት ህይወቴ ሞላሽው °°°° ፋፁም እሩሩህ ነሽስምሽ ጣህም ያለው አዘኔ ሲበዛ ባንቺ እጽናናለው የአለም እርጋታ የሰላም ውጥን ነሽ ጊዜ ለጣለው ሰው አይጨክንም ልብሽ ✅✅✅✅✅✅✅ ⏸ @orthodoxzema ⏯ ✅✅✅✅✅✅✅
Show all...
#በህይወቴ_በዘመኔ 🙏 በህይወቴ በዘመኔ ደስ የሚለኝ ለእኔ በወንጌል ማመኔ/2/ ህይወቴ ቢመራ ጌታ በቃልህ ጣፋጭ ይሆን ነበር ሲያድሰኝ ፍቅርህ ያንተ ጸጋ ጌታ ስለበዛልኝ ጨለማው ተገፎ ብርሃን መራኝ ወዴት እሄዳለሁ የእጅህ ጥበብ ሆኜ ፍቅርህ እያደሰኝ ሞተህልኝ ድኜ ምን አይነት መውደድ ነው አንተ ለእኔ ያለህ ምን ይከፈልሃል ለፍፁሙ ፍቅርህ ምን አይነት መውደድ ነው አንተ ለእኔ ያለህ ምን ይከፈልሃል ለፍፁሙ ፍቅርህ ደጅህ ላይ ተጥዬ ደጅህ ላይ ልሙት ቃልህን ልፈጽም በፍፁም ፍርሃት @orthodoxzema
Show all...
#የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ #መርገመ_በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡ በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ #አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦ ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡
Show all...
Repost from Addis Admass
የጻድቁ የአቡነ ተክለሃይማኖት ልጆች የሆኑት የወላይታ ሶዶ ሕጻናት እንዲህ "ክርስቶስ ሆይ አሁን አድን " እያሉ በዓለ ሆሳዕናንን እያከበሩ ይገኛሉ።
Show all...
Repost from N/a
ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በነበረው አስቸኳይ ስብሰባ ሕገ ወጡ ቡድን በአምስት ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ይቅርታ እንዲጠይቁ አሳስቧል። ምልአተ ጉባኤው ቤተ ክርስቲያን በሯ ለይቅርታ ክፍት በመሆኗ እስካሁን የተጠበቀው ይቅርታ ተግባራዊ አልሆነም ብሏል። አያይዞም ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ሕገ ወጥ ተሿሚዎቹ በጽሑፍ ይቅርታ እንዲጠይቁ አሳስቧል። መጋቢት 21 የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንዲካሄድም ወስኗል።
Show all...