cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኦርቶዶክስ ትምህርቶች

ጥያቄ ወይም አስተያየት ካለ 👇 @allemaT21

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
197Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ግንቦት 12 ❖ እንኳን ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል አደረሳችሁ ❖ +++++ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? ✝ ነገዱ ከሶርያ ሲሆን የተወለደው ደግሞ በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ነው። አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል:: ✝ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለመናፍቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው:: ✝ ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት ውበት ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበረሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት:: +ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጓሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት መልዕክታትና ትርጓሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ ማዕርጉም ዲቁና ነበር:: ✝ ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ✝ ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንድ ቀን እመቤታችን በሕዝብ መካከል "አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል:: ✝ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: ✝ አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ (ግብዣ አዘጋጀ):: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ:: ✝ ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንዲገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ:: ✝በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ መሳፍንቱ ጳጳሳቱ ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው:: ✝ "ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር:: ✝ "ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር:: ✝ 'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም:: ✝ አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች:: ✝ ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና [መቅድመ ተአምረ ማርያም] ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል:: ✝ ሊቁ ባረፈ በ35ኛ ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኳል። ✔ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:- *ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ *አፈ በረከት *አፈ መዐር (ማር) *አፈ ሶከር (ስኳር) *አፈ አፈው (ሽቱ) *ልሳነ ወርቅ *የዓለም ሁሉ መምሕር *ርዕሰ ሊቃውንት *ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ) *ሐዲስ ዳንኤል *ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው) *መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ *ጥዑመ ቃል - - - ++++++ አምላካችን እግዚአብሔር ከሊቁ በረከት ያሳትፈን!!! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
“የሚሰማኝ ግን በተስፋ ይኖራል፤ ከክፉም ሁሉ ያለድንጋጤ ያርፋል” (ምሳ.፩፥፴፫) ዲያቆን ዐቢይ ሙሉቀን ክፍል ሁለት የተከበራችሁ አንባብያን የዚህን ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ማቅረባችን ይታወቃል። ቀጣዩን ደግሞ እንደሚከተለው አቅርበናል። እግዚአብሔር አምላካችን መቼም ቢሆን ተስፋችንን አያሳጣንም፡፡ ነገር ግን ተስፋ የምናደርገው ነገር ለእኛ የሚያስፈልገን መሆን አለበት፤ የሚጎዳንን አይሰጠንምና፡፡ ‹‹በእርሱም አማካኝነት ወደቆምንበት ወደ ጸጋው በእምነት ተመራን፤ በእግዚአብሔርም ክብር ተስፋ እንመካለን፡፡ የምንመካ በእርሷ ብቻ አይደለም፤ በመከራችን ደግሞ እንመካለን እንጂ፤ መከራ በእኛ ላይ ትዕግሥትን እንደሚያመጣ እናውቃለንና፡፡ ትዕግሥትም መከራ ነው፤ በመከራ ተስፋ ይገኛል፡፡ ተስፋም አያሳፍርም፤ በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን መልቷልና›› በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ምእመናን በላከው መልእክቱ ይነግረናል፡፡ (ሮሜ.፭፥፪-፭) ተስፋ የሚታየውን በማይታየው ይቀይራል፡፡ አብርሃም በሽምግልና ዘመኑ ያገኘውን አንድ ልጁን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በዐይነ ሥጋ ሳይሆን በዐይነ ኅሊና የሚታይ የተሻለ ጥቅም ስለነበረው ነው፡፡ በመጽሐፍ ‹‹አብርሃምም እግዚአብሔር በፈተነው ጊዜ ልጁን ይስሐቅን ይሠዋው ዘንድ በእምነት ወሰደው፡፡ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ብሎ ተስፋ ያደረገለትን አንድ ልጁን አቀረበው፡፡ እግዚአብሔር ከሙታን ለይቶ ሊያስነሣው እንደሚችል አምኗልና፤ ስለዚህም ያው የተሰጠው መታሰቢያ ሆነለት›› ተብሎ የተነገረው ለዚህ ነው፡፡ አብርሃም የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ በተስፋም ከሚያውቀው ሀገር፣ ከሚያውቀው ሕዝብ ወጥቶ ወደማያውቀው ሀገር፣ ወደማያውቀው ሕዝብ ሄደ። (ዕብ.፲፩፥፲፯-፲፱፤ ዘፍ.፲፪፥፩) በሰው ሰውኛው ሲታይ አብርሃም የፈጸመው ትክክል አይደለም ሊባል ይችላል፡፡ ምክንያቱም ‹‹በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል›› እየተባለ ያንኑ የዘሩ መጠሪያ የሆነውን ሠዋው ሲባል ‹እሺ› ብሎ መሄድ ምን ያህል እምነትና ጽኑዕ ተስፋ እንዳለ የሚያስረዳ ነው፡፡ አብርሃም አንድ ልጁን ለእግዚአብሔር አልከለከለውም፤ እንዲሁ እግዚአብሔርም አንድያ ልጁን ለአብርሃም አልከለከለውም፡፡ እንኳን ለአብርሃም በእምነት ለታዘዘው ለጠላቶቹ እንኳን አልከለከላቸውም፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት በእንደዚህ ያለ ጽኑዕ ተስፋ ያኖራል፤ በተስፋ መኖር ብቻም ሳይሆን ከክፉ ሁሉ ያለ ድንጋጤ ያሳርፋል። ከክፉ ማረፍ:-የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማው አዳም ልጅነትን አጣ፤ ከገነት ወጣ፤ ከገዢነት ወደተገዢነት ወረደ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማው ቃየልም እንዲሁ ተቅበዝባዥ ሆነ። በአምላኩ በእግዚአብሔር ቃል እየተጠራ የንስሓ ጊዜ ቢሰጠው ይህን እድል አልጠቀምም፤ የሕይወትን ቃል አልሰማም ያለው ቃየል የሚቅበቀዘበዝ፣ ሰላሙን የተነጠቀ ፈሪ ሆነ። የእግዚአብሔርን ቃል ቢሰማ ግን ከእንደዚህ ያለው ክፉ ሕይወት ይድን ነበር። የእግዚአብሔርን ቃል የሰማው ነቢዩ ዳዊት ምንም እንኳን የጎልማሳ ሚስት ቢቀማም ጎልማሳ ቢያስገድልም በንስሓ መመለሱ ዛሬም የንስሓ ሕይወቱ ለእኛ በአብነት ሲጠቀስ ይኖራል። የእግዚአብሔርን ቃል ባልሰማበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቶ ነበር። የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰማና በንስሓ ሲመለስ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቀ፤ ኃጢያቱን ይቅር ተባለ፤ ሀብተ ጸጋው ሁሉ ተመለሰለት። ነቢዩ ኢሳይያስ የእግዚአብሔርን ቃል ባልሰማበት ወቅት ሀብተ ትንቢቱ ተነሳው፤ ለምጽ ወጣበት፤ የእግዚአብሔርን ቃል በሰማ ጊዜ ግን ሀብተ ትንቢቱ ተመለሰለት፤ ኃጢያቱ ይቅር ተባለለት፤ ከለምጹም ነጻ። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት በተስፋ እንድንኖር ያደርገናል፤ ከክፉም እንድናለን። በሐዲስ ኪዳንም የእግዚአብሔርን ቃል የሰሙት ሐዋርያት እሳቱን እና ስለቱን ታግሠው ለበለጠ ክብር በቅተዋል። ከመካከላቸው የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማው ይሁዳ ግን ተለይቷል፤ አልሰማም ማለት በእዝነ ሥጋው አልሰማም ማለት አይደለም፤ በእዝነ ልቡናው ግን በእርግጥም አልሰማም። ስለዚህ ምንም እንኳን ከሐዋርያት ጋር ቢቆጠርም፣ ትምህርቱ፣ ተአምራቱ ባይነፈገውም ክብር ግን አላገኘም። የእግዚአብሔርን ቃል በአግባቡ አልሰማምና። (ኢሳ.፮፥፩-፲) በዘመናችንም ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ስለማይሰማ ሥጋዊ መፍትሔው ብቻ ይታየዋል። በእርግጥ ያም የሚገኘው በእግዚአብሔር ነው። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የሥጋም የነፍስም ድኅነት እንደሆነ አለመቀበል በብዙኃኑ ዘንድ ይስተዋላል። ይህ የሆነው ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ካለመስማት ነው። ሥጋዊ ዕውቀትን ብቻ ተምሮ ያደገ ሰው ሁሌም የሚታየው ሥጋዊ ድሎት ነው፤ ‹‹በቃልህ እዘዝ፤ ልጄ ይድናል›› ያለው የመቶ አለቃው ቃል ትዝም አይለው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማቱም በመጨነቅ፣ በመሸበር፣ ለውጥ የማያመጣ መፍትሔ ሲያፈላልግ ዘመኑን በከንቱ ይጨርሳል። (ማቴ. ፰፥፰) የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ቃሉን በትክክል ሰምቶ በተግባር ላይ ማዋል በመሆኑ ሐዋርያው ያዕቆብ ‹‹ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። ቃሉን ሰምቶ የማያደርገው ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስታዋት እንደሚያይ ሰው ይመስላል። ራሱንም ተረድቶ ይሄዳል፤ ወዲያውም እንዴት እንደሆነ ይረሳል›› በማለት እንደነገረን ቃሉን ሰምቶ በሕይወት መተርጎም ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ ሕይወት ነው፤ በተስፋ ያኖራል፤ ከክፉም ያለምንም ድንጋጤ ያድናል። ከእግዚአብሔር ቃል የራቀ ሁሌም የሚታየው ሥጋዊ መፍትሔ ስለሆነ ይህ ደግሞ ዘላቂ ባለመሆኑ ሁሌም በመጨነቅ፣ በመሸበር ዘመኑን ያሳልፋል። የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ ግን በተስፋ ይኖራል፤ ከክፉም ይድናል። የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተን፣ በጽኑዕ ተስፋ ተሞልተን፣ የተረጋጋ ኑሮን ኖረን ከክፉ እንድንድን እግዚአብሔር ይርዳን፤አሜን። (ያዕ. ፩፥፳፪-፳፬)
Show all...
ከግብረ አውናን (Masterbation) እንዴት መላቀቅ ይቻላል ? (በቀሲስ ህብረት የሺጥላ ) ሀ. ግብረ አውናን እንደ ማር ጠብታ ነው ። የማር ጠብታ ልብስ ላይ የወደቀ እንደሆነ በፍፁም የሚለቅ አይመስልም ፣ ነገር ግን ትንሽ ለቅለቅ ያደረጉት እንደሆነ ወዲያውኑ ይለቃልይህ ክፋ ልማድም እንደማር በቀላሉ ባይሆንም ከልብ በመፀፀት በጠንካራ መንፈስ ከተነሱ ሊያስወግዱት ይቻላል። በመጀመሪያ የሚያስፈልገው ከዚ ነገር መቼም መላቀቅ አልችልም ብሎ ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ከፍተኛ ትግልና ጥረት ይጠይቃል ስለዚህ ተስፋ መቁረጥ ፈፅሞ አይገባም ለ. ሴጋ ልማድ ነው ። ልማድ ደሞ በሌላ ልማድ ይሸነፋል። ጠንክረህ ከተነሳህ ይህን ተግባር በትዝታ ብቻ የምታስብበት ቀን ሩቅ አይሆንም ነገር ግን ከዚህ ልማድ ጋር ለመዋጋት ከመነሳትህ በፊት "ይህን ክፋ ልማድ ምን ያህል ከልቤ ጠልቼዋለው ? " በማለት ራስህን ጠይቅ ። መላልሰህ የምትሰናከለው ሳትፀፀት ወይም ሴጋን መተው ስላልፈለክ ሳይሆን ጣዕሙ በልቡናህ ስላለና ጎጂነቱ ዘልቆ ወደልብህ ስላልገባ ነው ስለዚህ ይህን ነገር ከልብህ ልትጠላው ይገባል ሐ. ይህን ክፋ ልማድ እንደ እሳት የሚያያይዙት የራስህ ተግባርና በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ናቸው ከዚህ እኩይ ተግባር መላቀቅ ከፈለክ ተዐቅቦ ያስፈልግሀል ተዐቅቦ ማለት መከልከል መቆጠብ ማለት ነው የምትከለከለውም ወደዚህ መጥፎ ሐሳብ ልቡናህን የሚስቡትን ነገሮች ከማየት ፣ ከመስማት፣ ከመንካትና ፣ ከመሳሰሉት ነው ። ስለዚህ የሴቶችን ገላ በፊልምም ፣ በአካልም ቢሆን በምንም መልኩ ከማየት ተቆጠብ። በመዋኛና በመጠመቂያ ቦታዎች ራስህን ጠብቅ የሴት ልጅን መልክና ቅርፅ መርዘህና አተኩረህ አትመልከት ስለ ዝሙት የሚያሳስቡ ሥዕሎችን፣ ፅሁፎችን፣ ወሬዎችን ፣ የሴት ገላ የሚያሳዩ የሙዚቃ ክሊፖችን ፣ የወሲብ ፊልሞችን አጥብቀህ ሽሻቸውስራህ ሁሉ አንተው እያራገብክ ለምን ይቃጠላል ? እንዳይሆንብህ መ. ዘወትር ልቡናህ የሚጠመድበትን ነገር ፈልገህ አድርግ ቦዘኔ አትሁን ትጉህ ሰራተኛ ሁን ።ስራህም አይምሮህን የሚያሰራ ቢዚ የሚያደርግ ይሁን ትርፍ ሰአት አይኑርህ የሚነበብ ወይም ሌላ የሚሰራ ስራ ፈጥረህ ሥራ ሠ. "ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው " የሚለውን የወንጌል ቃል አስብ በዚህ ክፋ ልማድ ተጠምደህ ሳለ ለብቻህ መሆንን አትውደድ ቢቻልህ አኗኗርህና መኝታህ ከምታፍረውና ከምታከብረው ሰው ጋር ይሁን ። ይህም ጓደኛህ ወይም ከቤተሰብህ አንዱ ሊሆን ይችላል በፀሎት ከሚረዱህ መንፈሳውያን መምህራን አባቶች ጋር ጊዜ ማሳለፍን ውደድ ረ. እንቅልፍ የያዘህ ስለ መሰለህ ብቻ ወደ መኝታህ አትሂድ አንዳንዴ ተኝተህ ውለህ እንቅልፍ ያምርሀልና ። ነገር ግን ሰይጣን ሊፈትንህ ከሆነ በምትነኛበት ጊዜ እንቅልፍ ከአይንህ ይርቃል ። ተከትሎም ፈተናው ይመጣና ወደ ዝሙት ህሊናህ ይሳባል ። ከዛ ሴጋ ትፈፅማለህ ስለዚህ ከመተኛትህ በፊት በደንብ መድከምህንና ቶሎ ማሸለብ መቻልህን መርምረህ ተኛ ሰ. ጸሎት ማድረግንም አትርሳ የሚረሳ ነገር አይደለምና ስትተኛም በጀርባህ ወይም በሆድህ አትተኛ ከዚህ ይልቅ በጎንህ ለመተኛት ሞክር አመጋገብህ በልክ ይሁን ፣ ፆምን ፁም ፣ ቅዱሳት መፃህፍትን አንብብ መዝሙርንም አዳምጥ ዘምር ሸ. እንዲህ ያለ ፈተና ሲነሳብህ /አድርግ አድርግ ሲልህ / ከቻልክ ስገድ ወይም የሆነ እንቅስቃሴ /ስፖርት / ስራ ሽንት መሽናትም ጥሩ መፍትሄ ነው አይምሮህ ሽፍት እንዲያደርግ ያደርገዋል በየጊዜው ፀበል መጠመቅን ቸል አትበል የሴት ገላን ሳታይ ቀ. ሰውነትህን አትነካካ ቢበላህ እንኳን አትከከው ስታክና ስትነካካው በዛው አድርግ አድርግ ሊልህ ይችላልና ንፁህ ሁን ፣ ሻወር ውሰድ ፣ ወክ አድርግ ፣ አንብብ ከምንም በላይ አጥብቀህ ፀልይ ። ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን. 💚 @ort_mezmur 💚 💛 @ort_mezmur 💛 ❤️ @ort_mezmur ❤️
Show all...

ድንኳኑን ሥራ እንዴት አድርጎ እንደሚሰራ ለሙሴ ነገረው ሲል ለመጀመርያ ጊዜ ዘመረ።(ዘጸ 25፥8-10) ✝️ይህ የሆነው ኅዳር ስድስት ቀን ነበር። ከሰማይ ተመልሶ ለመጀመርያ ጊዜ ዜማውን ያዜመበት ቦታም ሙራደ ቃል ተብሎ ተጠራ።እስከዛሬም ሙራደ ቃል እየተባለ ይጠራል።ዜማው ከሰማይ የወረደ መሆኑን ለመግለጽ ነው። ✝️የዜማውም ስም አርያም ተብሎ ተጠራ። ምክንያቱም ከሰማይ የተገኘ ልዑል ዜማ ስለሆነ ነው። ✝️ቅ/ያሬድ ዜማውን ከሰማይ የሰማው መሆኑን ሲያረጋግጥ "ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ እመላእክት ቅዱሳን እንዘ ይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉዕ ሰማያተ ወምድረ ውድሳተ ስብሐቲከ/ "ወይ ዜማ! በሰማይ ሳለሁ ከቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ የከበርህ ምስጋናህ ሰማያትንና ምድርን መላ እያሉ የሰማሁት ዜማ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? ሲል ተናግሯል።(ድጓ ዘአርባዕቱ እንስሳ ) ✝️በዝማሬ ድርሰቱም ፦ሰማየ በአብ ወበወልድ አርያመ ወበመንፈስ ቅዱስ ኃበ ዓረጉ ሰማዕኩ እመላእክት ዝማሬ በአድንኖ ወበአትህቶ ቦ ዘያጽሕሱ ወቦ ዘይዜምሩ /"በአብ ወደ ሰማይ ፥በወልድ ወደ አርያም፥ በመንፈስ ቅዱስም በወጣሁ ጊዜ ከመላእክት ዘንድ ራስን ዝቅ በማድረግ በትህትና ዝማሬን (ምስጋናን )ሲያቀርቡ ሰማሁ ፣የሚያሸበሽቡ አሉ የሚዘምሩም አሉ በማለት ተናግሯል። ✝️ቅ/ያሬድ ወደ ሰማይ ተነጥቆ የመላእክትን ዝማሬ ሰምቶ መመለሱ ከቅ/ጳውሎስ ጋር የሚያመሳስል አለው። ቅ/ጳውሎስ፦የተገለጠለትን ሰማያዊ ራእይ ሲናገር ከአስራ ዐራት ዓመት በፊት እስከ ሦሥተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ ወደ ገነት ተነጠቀ ሰውም ሊናገረው የማይገባውንና የማይነገረውን ቃል ሰማ።2ኛ ቆሮ 12፥1-5 ✝️በእግዚአብሔር ዘንድ ለትልቅ ነገር የተመረጡ ሰዎች ወደ ሰማይ እየተነጠቁ መወሰድና በዚያም ልዩ የሆነውን ራእይ ማየት የተለመድ እንደሆነ ከቅ/ጳውሎስ አነጋገር ማረጋገጥ ይቻላል። ✝️ቅ/ጳውሎስ ወደ ሰማያት እንደተነጠቀ ሁሉ ቅ/ያሬድም ወደ ሰማያት ተነጥቆ ዜማውን ወደ ምድር ማውረዱን ልብ ይሏል። ✝️ቅ/ያሬድ ከዕለታት ባንዳቸው ቀን በሙራደ ቃል ሁኖ ድምጹን ከፍ አድርጎ ዜማውን ባዜመ ጊዜ በዘመኑ የነበሩ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ከነሠራዊታቸው፥መሳፍንቱ፥ መኳንንቱ ፥ወይዛዝርቱ፥ሊቃውንቱና ካህናቱ እሱ ወዳለበት ተሰብስበው የሚያዜመውን ዜማ ከጣዕሙ ብዛት የተነሳ እየሰሙ እንደ ዋሉ ይነገራል። ✝️በሌላም ጊዜ ንጉሡ አፄ ገብረ መስቀል የቅ/ያሬድን ዜማ እየሰሙ ሳሉ በተመስጦ ስለነበሩ የያዙት የብረት ዘንግ ከቅዱስ ያሬድ እግር ላይ እንደ ተተከለና ደም እንደፈሰሰበት ይታወቃል። ሁኖም ግን ቅ/ያሬድ በዜማው ተመስጦ ውስጥ ስለ ነበር አልተሰማውም ነበር። ✝️ስለፈሰሰው ደምህ የፈለግኸውን ነገር አደርግልህ ዘንድ ንገረኝ ሲሉት እሱም የምለምንህ አንዲት ነገር ናት እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር በፈቀደልኝ መጠን በዚህ ከተማ ከአንተ ጋር ቆይቻለሁ ብዙ ደቀ መዛሙርትንም ተክቼአለሁ ከእንግዲህ የቀረኝ ዘመን በጸሎትና በብህትውና ማሳለፍ እችል ዘንድ ከከተማው ራቅ ወዳለ ቦታ ሂጄ ፈጣሬን አገለግል ዘንድ ፍቀድልኝ ብሎ እንደለመናቸው ይታወቃል። ✝️ይህን በመስማታቸው ንጉሡ ያዘኑ ቢሆኑም ስለ ገቡለት ቃል ከመፍቀድ ውጭ አማራጭ አልነበራቸውምና ፈቀዱለት። ህዝቡ ሁሉ በኃዘን ተዋጠ ህዝበ ክርስቲያኑ እስከ ተከዜ ወንዝ እንደ ሸኙትም ይነገራል። በዚህ ጊዜ በመጨረሻ ስንብቱ "እንዲህ አለ "ሰላመ ነሣእነ ወሰላመ ኃደግነ ለክሙ እግዚአብሔር ምስለ ኩልክሙ ወሰላመ እግዚአብሔር እንተ ኩሉ ባቲ ተሀሉ ወትረ ምስለ ኩልክሙ/"ሰላምን ተቀበልን ለእናንተም ሰላምን ተውንላችሁ የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን ሰላም የሚገኝባት የእግዚአብሔር ሰላም ሁሉ ጊዜ ከእናንተ ጋር ትሁን ሲል እንደ ተሰናበታቸው ታሪኩ ያስታውሰናል። ✝️ታሪኩ ብዙ ነው ነገር ግን ከብዙ በጥቂቱ ከዚያም በኋላ ገዳም ገብቶ በብህትውና እየኖረ ሳለ እንደ ተሰወረ ይነገራል። ከዚህ በተጨማሪም ወአዕረፈ የሚለውን በመያዝ እንደ ሞተ የሚናገሩ አሉ። ነገር ግን ይህ ሚያሳየው ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ አረፈ እንጂ ሞተ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት ስለዚህ እንደተሰወረ ይነገራል። የዜማ ድርሰቶቹን በአጭሩ ለማየት የቅ/ያሬድ ድርሰቶች 1/ድጓ 2/ጾመ ድጓ 3/ዝማሬ 4/መዋሥዕት 5/ምዕራፍ ናቸው። ✝️የዜማ ዓይነቶች ግዕዝ ዕዝል አራራይ ናቸው። ለእያንዳንዳቸው ትርጓሜ ነበራቸው ግን ከጊዜ አንጻር ትንታኔውን ትቼዋለሁ። ✝️ድጓ ማለት ድግዱገ ጽሕፈት ጽሕፈቱ የከሳ የቀጠነ ደቃቅ ረቂቅ የሆነ ማለት ነው። ✝️ድጓ ማለት የጽሕፈቱን ረቂቅነትና የምልክቱን ብዛት በመመልከት ረቂቅ እስትግቡእ (ስብስብ)ማለት ነው። ✝️ድጓ ማለት በማላላት ሲነበብ የቤተ ክርስቲያን ትጥቋ ነው ብለው የሚተረጉሙ ሊቃውንትም አሉ። ✝️ድጓ ማለት ምዕላድ መድበል ማለት ነው። ድጓ በአራት አበይት ክፍሎች ይከፈላል ፩/ዮሐንስ ፪/አስተምህሮ ፫/ጾመ ድጓ ፬/ፋሲካ ✝️በአራት የተከፈለበት ምስጢርም ለብሉይ ሲሰጥ፦ ፩/ዘመነ አበው ፪/ዘመነ መሳፍንት ፫/ዘመነ ነገሥት ፬/ዘመነ ካህናት ምሳሌ ነው። ለሐዲስ ሲሰጥ ፦ ፩/ዘመነ ክርስቶስ ፪/ዘመነ ሰማዕታት ፫/ዘመነ ሊቃውንት ፬/ዘመነ መነኮሳት። ✝️በሌላም ወንጌል በአራት ክፍል መከፈልዋን(መጻፍዋን) ያሳያል። እንዲሁም በዮሐንስ ተጀምሮ በዮሐንስ ያልቃል ይህ የሆነበት ምክንያትም ዓለም በዮሐንስ ዘመን ተፈጥሮ በዮሐንስ ዘመን ማለፉን ስለሚያሳይ ነው። ፩/ዮሐንስ "ይህ የመጀመርያው የድጓ ክፍል ነው ዮሐንስ ተብሎ ይጠራል። ምክንያቱም መጥምቁ ዮሐንስ የብሉይና የሐዲስ መሸጋገርያ የብሉይ መጨረሻ የሐዲስ መጀመርያ እንደመሆኑ መጠን አራቱ ወንጌላውያንም የዮሐንስን ታላቅነትና መንገድ ጠራጊነትን በመተረክ የጀመሩ ስለሆነ የወንጌላውያኑን አሠር በመከተል የመጀመርያው ክፍል በእርሱ እንዲጠራ ሆነ። በዚህ ክፍልም መጀመርያ የሚገኘው ብፁዕ አንተ ዮሐንስ የሚለው ነው። ፪/አስተምህሮ "ይህ ክፍል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረውን ትምህርት የሰራቸውን ተአምራት የሚያመለክት ሁኖ በመገኘቱ አስተምህሮ ተባለ። አስተምህሮ ማለት ማማለድ ይቅርታ የሚለውን ትርጓሜ ይይዛል። ፫/ጾመ ድጓ "ይህ ሦሥተኛው የድጓ ክፍል ነውይህ ክፍል በአቢይ ጾም ጊዜ በነግህ ፥በሠለስት፥በቀትር፥በሠርክ እንዲሁም በሌሊት የሚዘመር መዝሙር ነው።በውስጡም ያለው ፍሬ ሐሳብ የጾምን፥የጸሎትን፥የምጽዋትን፥የፍቅርን፥የሥነ ምግባርን ትምህርት የያዘ ታላቅ ምስጢር ነው። ፬/ፋሲካ "ይህ አራተኛው የድጓ ክፍል ሲሆን የቃሉም ትርጓሜ በእብራይስጥ ፖሳህ ማለት አለፈ ሄደ ማለት ነው። ይኸውም እስራኤላውያን በግብጽ አገር በግ አርደው ደሙን በመርጨት ቀሳፊ መልአክ የእስራኤልን ቤት እያለፈ ግብጻውያንን እያጠፋ እስራኤላውያን ከመቅሠፍት ስለዳኑ ፖሳህ(ፋሲካ)ተባለ። ይህ ክፍል ምድቡ ከሚያዝያ ወይም ከትንሣኤ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን መጨረሻ ድረስ ነው። እነዚህ ክፍላት በአራቱ ክፍላተ ዘመንም ይመደባሉ 1/ዘመነ መጸው 2/ዘመነ ሐጋይ 3/ዘመነ ጸደይ 4/ዘመነ ክረምት ናቸው እነዚህንና መሰሎቻቸውን ለመዘርዘር ጊዜ ስለሚያጥረን ከዚህ አበቃን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አልቦ እምቅድሜሁ ወአልቦ እምድኅሬሁ ማኅሌታይ ሰብእ ዘከማሁ ያሬድ ካህን ለክርስቶስ ሰበከ ትንሣኤሁ ኢየአዱ እንስሳ ወሰብእ እምነ ሠላስ
Show all...
#ግንቦት_፲፩ ✝️ከሰማያዊ ውቅያኖስ ሰማያዊ ዜማን ቀድቶ ከኢትዮጵያ ባሻገር ዓለምን ያረካ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ማን ነው? ✝️ከውቅያኖሱ መሀል በጭልፋ እንደመጨለፍ ያህል እንጂ ታሪኩ እጅግ ሰፊና ጥልቅ እንደመሆኑ መጠን በዚህ ተነግሮ ያልቃል ማለት አይደለም። "ከሰማይ ሰማያዊ ዜማን ቀድቶ ኢትዮጵያን አርክቶ ዓለምን ያረካ ማን ነው ?" ሲባል መልሳችን ቅዱስ #ያሬድ ማለት እንጂ ሌላ አማራጭ የለንም። ቅዱስ ያሬድ ማን ነው? ቅዱስ ያሬድ ሐረገ ትውልዱ ከካህናተ አክሱም ሆኖ አባቱ ይስሐቅ(አብድዩ) እናቱ ታውክልያ(ክርስቲና) ይባላሉ። ✝️ቅ/ያሬድ በ505 ዓ/ም በሚያዝያ ወር በአክሱም ከተማ ተወለደ። የስሙ ትርጓሜም ያሬድ ማለትም ወሪድ፥ መውረድ ማለት ነው። ✝️ይህን ስያሜ በቀዳማዊ ያሬድ ጊዜ ደቂቀ ሴት ከደብር ቅዱስ "ደቂቀ ቃኤል ወዳሉበት ወደ ምድረ ፋይድ ስለወረዱ ያንን ለማስታወስ አባቱ መላልኤል "ያሬድ" ብሎ ሰይሞታል። "ወጸውዓ ስሞ ያሬድሃ እስመ በመዋዕሊሁ ወረዱ መላእክተ እግዚአብሔር ውስተ ምድር እለ ተሰምዩ ትጉሃነ"በእርሱ ዘመን ትጉሃን ተብለው የሚጠሩ የእግዚአብሔር መላእክት የተባሉት ደቂቀ ሴት ከደብር ቅዱስ ወደ ምድረ ፋይድ ወርደዋልና። (ኩፋ 5፥21) ✝️ኢትዮጵያዊ ቅዱስ ያሬድም በስድስተኛ መቶ ክፍለ ዘመን ተነስቶ ሰማያዊውን ጣዕመ ዜማ ወደ ምድር የሚያወርድ ስለሆነ አባቱና እናቱ ይህን ተገልጾላቸው ያሬድ ብለው ሰይመውታል። ዘመኑ በደረሰ ጊዜ ደግሞ ከሰማይ ሰማያዊ ዜማን ወደ ምድር ያወረደ ብቸኛ ነው። ✝️በቀዳማዊ ያሬድ ደቂቀ ሴት ከደብር ቅዱስ ወደ ምድረ ፋይድ እንደወረዱ ሁሉ "በኢትዮጵያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም ሰማያዊ ዜማ ከሰማይ መውረዱን ያሳያል። ✝️አባቱ በሞቱ ጊዜ እናቱ ታውክልያ በፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲያድግ አድርጋ ነበርና በሰባት ዓመቱ መንፈሳዊ ትምህርት እንዲማር የአክሱም ጉባዔ(ቤተ ቀጢን) ዘርግተው ያስተምሩ ወደ ነበሩት ወደ መምህር ጌዴዎን ወሰደችው። ✝️መምህር ጌዴዎን ለቅ/ያሬድ አጎቱ ናቸው። ቅ/ያሬድ ከአጎቱ ዘንድ ለመማር ፍላጎት ቢኖረውም አንድ አስቸጋሪ ነገር ገጠመው። እሱም የፈለገውን ማጣት፥አለማግኘት ነበር። ✝️ከዕለታት ባንድ ቀን ቅ /ያሬድ ትምህርቱን ለመቀበል ስለተሸገረ አጎቱ ጌዴዎን ክፉኛ ተናዶ እንደገረፈው ታሪክ ያስታውሰናል። በዚህ ሁኔታ የተሸገረ ቅ/ያሬድ በሁኔታው ተበሳጭቶና ተስፋ ቆርጦ ስለነበር የወሰደው አማራጭ ጉባዔ ቤቱን ጥሎ ወደ እናቱ ቤት መኮብለል ነበርና ከአክሱም ከተማ ወጥቶ ወደ ቤቱ እየተመለሰ ሳለ ደክሞት ከአንድ ዛፍ ቁጭ ብሎ ሲያለቅስና ሲያዝን እግዚአብሔር አንድ የሚያጽናና ምልክት አሳየው። ❤ይህም፦አንድ ትል የዛፏን ፍሬ ለመመገብ ፈልጎ ወደ ላይ እየወጣና እየወደቀ በተደጋጋሚ ማለትም ለስድስት ጊዜ ውድቀት ሲገጥመው ትሉ ተስፋ ሳይቆርጥ በሰባተኛው ጊዜ ወጥቶ ፍሬዋን ሲመገብ አይቶ ብልህ ሰው ከተለያዩ ነገሮች መማር ይችላልና ቅ/ያሬድ ይህን የትሉ ትጋትና አለመሰልቸት ተገንዝቦ እኔም እኮ እንደዚህ ትል ብተጋ ትምህርቱ ይገለጽልኝ ነበር ? ብሎ ወደ እናቱ ቤት ለመሄድ የጀመረውን ጉዞ አቋርጦ ወደ አጎቱ ወደ ጌዴዎን ጉባዔ ቤት አቀና። መምህሩ ጌዴዎንም በደስታ ተቀብሎ ማስተማሩን ቀጠለ። በዚህ ጊዜ ለብዙ ጊዜ አልገባ ያለውን ትምህርት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ተገለጸለት የታሪክ መዛግብት ያዘክራሉ። ✝️ትምህርቱንም በስፋት ስለቀጠለበት የመጻሕፍተ ብሉያትንና የመጻሕፍተ ሐዲሳትን ተርጓሚና ሊቅ ሆነ። ✝️እግዚአብሔር ትልቅ ሥራ ለመስራት ሲፈልግ ለሥራው መገለጫ በሆኑ ሰዎች ላይ መጠነኛ ፈተና ማሳየት ልማዱ ነው። ለምሳሌ ለኤልሳቤጥ፥ለሣራ፥ለቅድስት ሐና ያደረገውን ማየት ይቻላል። ✝️ለሣራ ይስሐቅን ያህል ልጅ ለኤልሳቤጥ ዮሐንስን ያህል ልጅ ለቅድስት ሐና እመቤታችንን ታህል ልጅ ለመስጠት በፈለገ ጊዜ በሰዎች እስከሚናቁ ድረስ በመካንነት እንዲቆዩ አድርጎ ነበር። በኋላ ግን ምንም እንኳን ሙቀትና ልምላሜ ቢለያቸውም እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላልና ልጅ ወልደው እንዲታቀፉ የተመኙትን ምኞች እነሆ ሰጣቸው። ✝️ እንደዚሁም ቅ/ያሬድ ትምህርት አልገባ ብሎት ለብዙ ዘመን ሲያዝንና ሲጉላላ የነበረ ቢሆንም የሚነሣ የሚሰጥ የሚያድን የሚገድል እግዚአብሔር መሆኑን ለመግለጽ እንደ ነበር እሙን ነው። ✝️ከዚህም ባሻገር ቅ/ያሬድ ከመጀመርያ ጀምሮ ትምህርት ተቀባይ ቢሆን ኑሮ ሰዎች የተገለጠለት ዜማ ካለው የቆየ ዕውቀት የተገኘ ነው ብለው ይናገሩ ነበር። ነገር ግን የፊደልን ቆጠራ ያስሸገረውና ብዙ ዓመታት የወሰደበት ሰው በአጭር ጊዜ ምጡቅና ሊቅ የዜማ ደራሲ መሆን የሚያስደንቅና በእግዚአብሔር ገላጪነት የተገኘ እንደሆነ ሰዎች ይረዳሉ። ✝️ቅ/ያሬድ በመምህሩ በጌዴዎን ተተክቶ የብሉይና የሐዲስ መምህር ሁኖ ያስተምር ነበር፣ብዙ ሊቃውንትንም አፍርቷል። ✝️በቅ/ያሬድ ዘመን ከተለያዩ የሮምና ታናሽ እስያ አገሮች የጉባዔ ኬልቄዶንን( ሁለት ባሕርይን) ውሳኔ አንቀበልም ብለው አገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ዘመን ነበር። ✝️ተስዓቱ ቅዱሳን በግዕዝ ቋንቋ በጣም ችሎታ ካለው ከቅ/ያሬድ በቀሰሙት የግዕዝ ዕውቀት ያልተተረጎሙ መጻሕፍትን እንደተረጎሙ የታሪክ ምንጭ ያሳያል። ✝️ይህ በእንዲህ እንዳለ ለቅ/ያሬድ ዜማ እንዴት ተገለጠ? እግዚአብሔር ሰማያዊውን ዜማ ሊገልጥለት ስለፈለገ ኅዳር 5 ቀን ከነገተ ኤዶም ሦሥት አዕዋፍን ቅ/ያሬድ ወዳለበት ላከ። ✝️እነዚያ ወፎች በአንድ ዛፍ ላይ ተቀምጠው በሰው አንደበት ያነጋግሩት ነበር።እንዲህም አሉት ያሬድ ሆይ ? አንተ ብፁዕ ነህ አንተን የተሸከመች ሆድም ብፅዕት ናት እያሉ ሲነግሩት እሱም እናንተ በሰው አንደበት የምትናገሩ አዕዋፍ ከየት መጣችሁ ? ሲል ወፎቹን ጠየቃቸው። ✝️ከሦሥቱ ወፎች አንዷ ከገነተ ኤዶም ወደ አንተ ተልከን የመጣን ነን፣ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሰማያዊን ዜማ ፥ማኅሌትን ትማር ዘንድ ልንነግርህ መጣን አለችው። ✝️ከዚህ በኋላ አዕዋፉ ሲሰወሩ ያሬድም በተመስጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተነጠቀ።በዚያም እግዚአብሔርን ያለ ማቋረጥ የሚያመሠግኑ መላእክት በመንበሩ ዙርያ ሁነው ልዩ ጣዕም ባለው ዜማ ሲያመሠግኑ ሲዘምሩ ተመለከተ። ✝️በዜማው ስለተመሰጠም እነርሱ ወዳሉበት ዘሎ ለመግባት አስቦ እንደነበር ታሪክ ይናገራል። በዚህ ጊዜ ሦሥቱ አዕዋፍ ወደ እርሱ መጥተው -ልክ "ፊልጶስ" ጃንደረባው ባኮስን የምታነበው ስለማን እንደ ሆነ ታውቀዋለህን ? እንዳለው ሁሉ "አንዷ ወፍ ያሬድ ሆይ? የሰማኸውን አስተውለኸዋልን ? ብላ ጠየቀችው። ✝️ጃንደረባው የሚነግረኝ ሳይኖር እንዴት አውቀዋለሁ?ብሎ ለፊልጶስ እንደ መለሰለት ሁሉ "እሱም አላስተዋልኩትም ብሎ መለሰላት። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለውን አዲሱን ስም ጥራ ስትለው ቅ/ያሬድም ኢየሱስ ክርስቶስ ብሎ በጠራ ጊዜ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዜማ ተገለጸለት ። ✝️ወድያውኑም በግዕዝ፥ በዕዝል፥ በአራራይ ዜማውን ማዜም ጀመረ። ከዚህ በኋላ ከኢየሩሳሌም ሰማያዊት ወደ አክሱም ከተማ ወደ ቤተ ቀጢን ተመለሰ። ከዚያም ሁኖ ታቦተ ጽዮን ወዳለችበት ፊቱን ወደ ምሥራቅ አዙሮ እጁን በመዘርጋት " ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ።/ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል ፣ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፣ የጽዮን መጀመርያዋ የሆነ እግዚአብሔር ሰማይን ፈጠረ ፣ዳግመኛም የ
Show all...
#ተስፋ_ቆርጠን_ነበር ተስፋ ቆርጠን ነበር ኤማሁስ የሄድነው በግፍ ስለሞተ ይቤዠናል ያልነው ስልሳውን ምእራፍ በሓዘን ተራመድን የሚያቃጥል ፍቅሩን/ሞቱን እያሰብን/(2) በመንገዳችን ላይ አንድ እንግዳ መጥቶ ጠየቀን በብርቱ መሃላችን ገብቶ አለም የሰማውን ባያውቀው ደነቀን እውነቱን ገለጽነው በእምነት ተናገርን #አዝ በስራና በቃል ብርቱ ነብይ ነበር በአይሁድ ተገድሎ አደረ መቃብር ይህ ሁሉ ከሆነ ሶስተኛ ቀን ሆነው በምኩራባችን ላይ መምህሩን ካጣነው #አዝ ዛሬ በማለዳ አዲስ ነገር ሰማን በመቃብር የለም ተነስታል ጌታችን ሴቶች አስገረሙን ስጋው የለም ሲሉ መላእክቱም ታዩ ህያው ነው እያሉ #አዝ መጻህፍትን ገልጾ በሚነግረን ነገር ልባችን በሚስጢር ይቀልጥብን ነበር አይናችን ተይዞ እኛ መች አወቅነው ቀኑ መሽታል እና በቤት እደር አልነው #አዝ እንጀራውን ቆርሶ በእጃችን ሲሰጠን ባይናችን ላይ ያለው አዚሙ ለቀቀን እንዳላዋቂ ሰው ከኛ ጋራ ያለው የትንሳኤው ጌታ ለካስ እየሱስ ነው(፫) ╔═★══════════📄══╗ ⛓ @ort_mezmur ⛓ ⛓ @ort_mezmur ⛓ ⛓ @ort_mezmur ⛓ ╚══📃══════════★═╝
Show all...
Watch "በእግዚአብሔር ፊት የምትቆም ገብርኤል ሆይ አንተ ስለእኛ ማልድልን #በቤንችኛ ቋንቋ እነሆ ዝማሬ በቤንችኛ tube" on YouTube https://youtu.be/xBYrx1ZmY78
Show all...
በእግዚአብሔር ፊት የምትቆም ገብርኤል ሆይ አንተ ስለእኛ ማልድልን #በቤንችኛ ቋንቋ እነሆ ዝማሬ በቤንችኛ tube

የር አፕ ይጣጉሾ ገብርኤሎ #subscribe#like#share

+ ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ - ርትዕት ኃልዮ - Thinking Orthodox + ዶ/ር ጂኒ ኮስንስታንቲኒውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅኋት ጌታችን በተቀበለው የሐሰት ፍርድ ዙሪያ ባደረገችው ተከታታይ የድምፅ ትምህርት /podcast/ ነበረ፡፡ በምሥራቃዊው የኦርቶዶክስ ዓለም ወገን ሆና እንዲህ ዓይነት ልበ ሙሉነት የተሞላች የነገረ መለኮት ልህቅት ምዕራባዊያኑን ስታንቀጠቅጥ ማየት በራሱ ልብን በኩራት የሚሞላ ነበር፡፡ በትምህርቶችዋ ላይ ምዕራባዊያኑ ምን ያህል የነገረ መለኮት አረዳድ ችግር ያለባቸው መሆኑን የምትገልጽበት መንገድ እና በጉዳዩ ላይ እንደ ግሪካዊነትዋ የምታሳየው የተጠያቂነት ሥልጣን አንጀት የሚያርስ ስለነበር በተለይ ከሀገር ውጪና በክፍለ ሀገራት ረዣዥም የአውቶቢስና የባቡር ጉዞዎችን በማደርግበት ጊዜ እርስዋን መስማት ልማዴ አድርጌ ነበር፡፡ ዶ/ር ጂኒን እንደ እኔ ኢትዮጵያዊና ኦርየንታል ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ ለሚሰማት ሰው ደግሞ መምህርትዋ ለኦርየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ያላትን አክብሮት የሚያሳዩ ንግግሮችን መስማቱ አይቀርም፡፡ በአንድ ትምህርትዋ ላይ ምሥራቃውያኑ /መለካዊያኑ/ ከካቶሊክ ስለተለዩበት ሁኔታ ስታነሣ ‘እኛ እና ኦሪየንታል ኦርቶዶክሶች የተለያየነው በአራተኛው ክፍለ ዘመን በኬልቄዶን ጉባኤ በተነሣ በአንድ ነገረ ክርስቶሳዊ ልዩነት ምክንያት ነው፡፡ ከካቶሊክ ጋር ደግሞ እስከ 1054 ድረስ አብረን ቆይተን ተለያይተናል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከካቶሊክ ጋር ያሉን የአስተምህሮ ልዩነቶች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሲሆኑ ከኦርየንታል ኦርቶዶክስ ጋር ያለን ልዩነት ግን በአራተኛው ክፍለ ዘመን የተለያየንበት አንድ ልዩነት ብቻ ነው፡፡ ይህም የሆነው ኦርየንታል ኦርቶዶክሶች እንዳሻቸው ትምህርት የማይለዋውጡና የጥንቱን ዶግማ ይዘው ጸንተው የሚኖሩ በመሆናቸው ነው’’ ብላለች፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ስታነሣ ኢትዮጵያዊያን ምንኛ ዳዊት ደጋሚዎች መሆናቸውን በማውሳት ለጥንታዊትዋ ቤተ ክርስቲያን እንደ ማሳያ አድርጋ ትጠቅሳለች፡፡ ዶ/ር ጂኒ ከነገረ መለኮት መምህርትነትዋ ባሻገር ምሁራዊ ሰብእና ያላት መሆንዋንም ተመልክቼአለሁ፡፡ በግል ለአንዳንድ ጥናቶች ምክር በጠየቅኋት ጊዜ ሃሳብዋን በመሥጠትና ጥያቄዎችን በመመለስ የምታሳየው ትብብር አስገራሚ ነበር፡፡ ከሁሉ በላይ የዶ/ርዋን ቀናነት ያየሁት ዲያቆን አቤል ካሣሁን አባቶችህን እወቅ የተሰኘውን ወሳኝ መጽሐፍ በሚያዘጋጅበት ወቅት የሠጠችው በይዘቱ ላይ የማማከር አገልግሎት ሳያንስ በመጽሐፉ ላይ የሚወጣ የመግቢያ ጽሑፍ ለማዘጋጀት ፈቃደኛ መሆንዋ ነው፡፡ ዲያቆን አቤል ‘መግቢያ እንድትጽፍልኝ ልጠይቃት ነው’ ነው ሲለኝ መቼም ምንም ሃሳቡን ብትጋራም ባላነበበችው የአማርኛ መጽሐፍ ላይ መግቢያ ለመጻፍ እንዴት ፈቃደኛ ትሆናለች?’ ብዬ ነበር፡፡ እርስዋ ግን ጥያቄ እንኳን ሳታነሣ ጽፋ በመላክ በአማርኛ ለሚታተም መጽሐፍ መግቢያ የጻፈች የመጀመሪያዪቱ የግሪክ ቴዎሎጂ መምህርት ሆናለች፡፡ ሰሞኑን ‘Thinking Orthodox’ የተሰኘውና አብዛኛውን ትምህርቶችዋን ለሰማ ሰው ለዓመታት ስትወተውትባቸው የከረሙ ብዙ ሃሳቦችን ያካተተችበት መጽሐፍዋ በገበያ ላይ ውሎአል፡፡ ለምሳሌ ከአፍዋ የማይጠፋው ፍሮኒማ /ሕሊና አበው/ በዚህ መጽሐፍ እጅግ ተተንትኖአል፡፡ በፖድካስትዋ ላይ ‘አባቶች ያሉትን ብቻ እንጂ የራስሽን ትንታኔ ለምን ትጨምሪያለሽ?’ በሚል የቀረበባትን ትችት ስትመልስ ‘ፍሮኒማ ማለት አባቶች ያሉትን እየደጋገሙ ማነብነብ ሳይሆን በእነርሱ ሕሊና ሆኖ ነገሮችን መረዳትና ማብራራት ነው’ ትላለች፡፡ አንዳንዴም ጠንከር ብላ /ጥቅሱን ላገኘው ያልቻልኩትን የቅዱስ ጎርጎርዮስን አባባል በመጥቀስ/ ‘If you don’t know theology , you have to shut up’ /ትምህርተ መለኮትን የማታውቁ ከሆነ ዝም በሉ/ ብላ ትገሥፃለች፡፡ የጂኒን መጽሐፍና የድምፅ ትምህርት የሚሰማ ሰው ያሉንን የነገረ ሃይማኖት ልዩነቶች ሳይዘነጋ በሚበዙት የጋራ ጉዳዮቻችን ላይ ብቻ አተኩሮ ማንበብ ይጠበቅበታል፡፡ አስቀድሞ የኦርየንታልና የምሥራቃውያንን ልዩነት ያልተረዳ ሰው ግን ብርድ ሊመታው ስለሚችል እንዲህ ያለውን የንባብ ነፋስ እንዲቀበል ጨርሶ አይመከርም፡፡ የጽሑፍዋ ምንጮች የሚበዙት የጋራ አባቶቻችን እንደመሆናቸው ምሥራቃዊት ስለሆነች ብቻ ‘የመለካዊት ጽሑፍ ጨርሶ አላነብም’ ማለት ደግሞ የቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ስፍሐ አእምሮና ስፍሐ ልቡና ያልወረሰ አስተያየት ያለው ሰው ይሆናል፡፡ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ‘የሚስዮናውያን ሕልም - በምዕራባዊያን ሚስዮኖች ላይ ኢትዮጵያዊ ዕይታ’ /The Missonary’s Dream : An Ethiopian Perspective on Western Missions in Ethiopia/ በተሰኘው ጽሑፋቸው ላይ የቤተ ክርስቲያናችንን ጥንቃቄ የተሞላበት አካታችነት እንዲህ ሲሉ ይገልጻሉ፡፡ ‘The Ethiopian Church is not unwilling to entertain new ideas from other religious communities as it is commonly depicted. .... Isaac of Nineveh, whose monastic writing is one of the three major works studied and read regularly in Ethiopian monasteries, was a Nestorian. Ibin al-Assal, the compiler of the Fitha Negest, the authoritative source of the Church’s canon Law, was a Malkite’ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በተለምዶ እንደምትሳለው ከሌላ ሃይማኖት ማኅበረሰቦች የሚመጡ አዳዲስ ሃሳቦችን ለማስተናገድ የማትፈቅድ አይደለችም፡፡ .... በገዳማት ዘወትር የሚነበበውና የሚጠናው ከሦስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት አንዱ የሆነውን መጽሐፍ የጻፈው ይስሐቅ ዘነነዌም ንስጥሮሳዊ ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያንዋ ሕገ ቀኖና ሥሉጥ ምንጭ የሆነው ፍትሐ ነገሥት አስተጋባኢ ኢቢን አል አሳል ደግሞ መለካዊ ነበር" (The Missionary factor in Ethiopia page 2 , Lund University, August 1996) የዶ/ር ጂኒንና መሰል የምሥራቃውያን መጻሕፍት አባቶቻችን በሔዱበት የስፉሐነ ልብ የንባብ አድማስ ማንበብ እጅግ ጠቃሚ ሲሆን "ጠርጥር ከገንፎ መሃል አይጠፋም ስንጥር" መንገድ (Skeptical reading method) በመከተል ማንበብ ያስፈልጋል:: መጽሐፉ በቶማስ አድማሱ ወደ አማርኛ ተተርጉሞአል:: እጃችን ሲገባ ደግሞ አንብበን በትርጉሙ ላይ እንወያይበታለን:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 4 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባ
Show all...
ቅድስት ቤተክርስቲያን "ባለቤቱ ያለከበራት አሞሌ" ሆናለች ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ከመንፈስ እና ከውሃ በ40 እና 80 የተወለዱ ልጆቿ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ክብርን ማስከበር ሀገር ማፍረስ ይመስላቸዋል። ቤተክርስቲያን ስትገፋ መጮኸ እና "የፍትህ ያለ" ማለት የሀገርን ስር መሰረት መናድ ስለሚመስላቸው "ሀገር እንዳይፈርስ ቤተክርስቲያን ትፍረስ" የሚል መሪ ቃል የያዙ ይመስላሉ። የቅድስት ቤተክርስቲያኒቷ የበላይ ጠባቂ እና ስዩመ መንፈስ ቅዱስ የሆኑትን ቅዱሳን አባቶችን እንደ አቻ ጓደኛችን ጠብ እርግፍ አድርገን ገልቦ መስደብን የተለማመደ ትውልድ ፈርቷል። ቅዱስ ሲኖዶሱ አንድ ሆነ ተብሎ የጭብጨባው ግለት እና ሙቀት ገና ከእጃችን ላይ ሳይለቅ እዚህ እና እዛ ቆመው ቃል እና ዘለፋ የሚወራወሩ ጥባቆትንታቸው ከበጎች ይልቅ ለግል ዕሳቤያቸው ያደረጉ ብፁዓን አባቶችን ተመልክተናል። የመንግስት ታጣቂ በቶከሰው ጢስ ቦንብ ቤተክርስቲያንን እንደፈፀመችው በማድረግ አካላዊ ቅርጽ ሰርተው ይቅርታ እንደጠየቀች የሚገልጹ የመቅደሱን ቡክርና በፓለቲካ ምስር ሊሸጡ ያሰፈሰፉ የመቅደስ ውስጥ ነጋዴዎችን ታዝበናል። ከሃይማኖታዊ ቅኖና እና ህግጋቶች ይልቅ መቻቻል እና መከባበር የሚሉ ሽፍጦች በልጦብናል። እንደ ባቢሎን ሰራተኞች ቋንቋችን ተደባላልቋል። እርስ በእርሳችን መከባበር እና መደማመጥ ከተሳነን የምናከብረው አምላክ እና የምንሰማው ወንጌልም አይኖረንም። እኛ የናቅናት ቤተክርስቲያንን ማንም አያከብርልንም። እኛ የገፈተርነውን ዕምነት የትኛውም አካል በጥገኝነት ሸሸጎ አያስቀምጥም። መቅደሳችን ባለቤቱ ያላከበረው አሞሌ ሆናለች። https://t.me/tinshuabetekrestyan
Show all...
+ የሰጠኸኝ ሴት + እግዚአብሔር አዳምን "አትብላ ካልሁህ ዛፍ በላህን?" ብሎ ጠየቀው:: አዳምም :- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ አለ:: የሰጠኸኝ ሴት! በጣም ይገርማል:: ሚስቴ አላለም:: አዳምና ሔዋን የተገናኙ ቀን አዳም ያለውን አስታውሱ "ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ" ብሎአት ነበር:: ምንም እንክዋን አዳም ወላጆች ባይኖሩትም ሰው እናትና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ብሎም ነበር:: ራቁታቸውን ቢሆኑም አይተፋፈሩም ነበር:: አሁን በራቁቱ ብቻ ሳይሆን በሔዋንም አፈረባት:: እናትና አባቱን ይተዋል እንዳላለ ሔዋንን ራስዋን ተዋት:: ከሚስቱ ጋር መተባበር ቀርቶ ክስ ጀመረ:: አካሌ አጥንቴ ሥጋዬ ማለቱ ቀረና የሠጠኸኝ ሴት አለ:: የጫጉላው ጊዜ አለፈና ከሚስትነትዋ ሴትነትዋ ብቻ ታየው:: በጋብቻ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሠጠንን ነገር ሁሉ ቀድመን የራሳችን እናደርጋለን ነገሮች ሲበላሹ ግን ባለቤትነቱን ወደ እርሱ እንመልሰዋለን:: የሠጠኸኝ ሥራ የሠጠኸኝ ወላጆች የሠጠኸኝ ሰፈር የሠጠኸኝ ሀገር የሠጠኸኝ መሪ የሠጠኸኝ ጉዋደኞች የሠጠኸኝ ደካማ ሥጋ የሠጠኸኝ ዓይን ትናንት ሲሠጠን ዘምረን የተቀበልነውን ሥጦታ ዛሬ ለምሬት እንጠቅሰዋለን:: የሠጠኸኝ የሠጠኸኝ .... ሠጠኝና በላሁ ብለን ቀርጥፈን ለበላነው ዕፀ በለስ ፈጣሪን እንከስሰዋለን:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 17 2012 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Show all...