cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ORTHODOX TEWAHIDO

ክርስቲያናዊ ትምህርቶችን ወደ ምናስተላልፍበት channel እንኳን በሰላም መጣችሁ ።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
178Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🙏 በድንግል ይሄን ቻናል ሳታዩ እንዳታልፉት Join የምትለውን ብቻ ይንኳት።🙏 @Tewahedo_Pictures @Tewahedo_Pictures
Show all...
#ሮሜ 8:34 እውነተኛ የቱ ነው። 👉ኦርቶዶክስ ወይስ ፕሮቴስታንት 👉እየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ወይስ ፈራጅ ❓ ❓ እርሶ ምን ይላሉ ❓
Show all...
በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩት እንዳታልፋ በቻናሉ ቀን በቀን አዳዲስ መንፈሳዊ ጥያቄዎች ይለቀቃል በማግስቱም የቻናሉ አባላት ድምፅ ከሰጡ በኋላ መልሱ ይለቀቃል። በጣም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ ቻናል ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ። https://t.me/+2LAPSS6mN_lmNTY0
Show all...

እሳት ቅኔ አማረው?! የተወለደበትን ቀዬ ትቶ ቃሉን ሊማር የወጣው ከርታታ ተማሪ! "በእንተ ስማ ለማርያም ስለ እመብርሃን" ከሚል ቃል በቀር ሌላ ስንቅ ያልያዘው ምስኪን ተማሪ! ከወላጆቹ እቅፍ ተነጥሎ ቤተክርስቲያንን ቤቴ ብሎ የወጣው የጽድቅ ስደተኛ ተማሪ! ምቾቱን ሳይፈልግ መሬት ላይ እየተኛ ስንቁን ለምኖ በጎስቋላ ጎጆ የሚያድረው ተማሪ! ሥጋውን አስርቦ ነፍሱን የሚያጠግበው በቃለ እግዚአብሔር ማዕበል ውስጥ እየዋኘ የሚያድረው ተማሪ! ጎጆውም ከቤት ተቆጥራ እሳት ነደደባት ሲባል መስማት ምንኛ ያቆስላል? የወላጆቹን ቤት ተሰናብቶ ወጥቶ ቤቱ ያደረጋት የሳር ጎጆ : ለምኖ የሚያመጣትን ስንቅና በስስት የሚያነባቸውን መጻሕፍቱን የሚያስቀምጥባት ምቾት አልባዋ ጎን ማሳረፊያው ተቃጥላ ስትጠብቀው ምን ተሰምቶት ይሆን? ምስኪኑ ተማሪ ዛሬ የት አድረህ ይሆን? አንተ ባለ ቅኔ ዛሬ ለጎጆህ ምን ተቀኝተህላት ይሆን? መቼም ቅኔ የማይጠራው የለም! እሳትም ቅኔ አምሮት ከቅኔ ቤት ገባ? የሚቻለንን ሁሉ አድርገን ስደተኛውን ቅኔ ወደ ቤቱ እንመልሰው:: ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ መጋቢት 2014 ዓ.ም. በእግዚአብሔር ስም #ሼር ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አደሩጉው ! @KeAbawandebet @KeAbawandebet
Show all...
ዲያቆን ሄኖክ 10 እገዛለሁ ባለኝ መስረት እግዚአብሔር ይስጥልኝ
Show all...
በተበቃይነት አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎች በፀባያቸው ማንኛውም በጐ ነገር ጥሩ ሆኖ አይታያቸውም፡፡ ሌላውን ሰው ደስ የሚያሰኝ ነገር እነርሱን ደስ አያሰኛቸውም፡፡ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ከመበቀል ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በእነርሱ ዘንድ ፈሪሃ እግዚአብሔር እና ሃይማኖት ቦታ የለውም፡፡ ሮሜ 12÷19 ከእንዲህ ዓይነቱ እጅግ አስቸጋሪ ሰው ጋር የሚኖር ወይም የሚሠራ ማንኛውም ሰው በቅድሚያ ማወቅ ያለበት፣ ከላይ የገለጽናቸውንና ሌሎችንም የአስቸጋሪነት ጠባይና እንዲሁም ከአስቸጋሪው ሰው ጋር አብሮ ሲኖር ሁልጊዜ ለጥቃት የተጋለጠ መሆኑን ነው፡፡ ይኸውም አስቸጋሪ ሰዎችን ለመምከር ወይም የአስቸጋሪ ሰዎችን ጠባይ ለመለወጥ ሳይሆን አስቸጋሪ ሰዎች ተለይተው የሚታወቁበትን ምልክቶች ለመጠቆምና እንዲሁም አብሮአቸው የሚኖረው ሰው፣ በአስቸጋሪ ሰዎች ጠባይና ድርጊት እንዳይጎዳ ራሱን መጠበቅ የሚችልባቸውን አንዳንድ መንገዶችን ለመጠቆም ነው፡፡ አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችንና ጎጂነት ያለውን ጠባያቸውን ለይተን እንድናውቅና እንዲሁም አብረን እንዴት መኖርና መሥራት እንደምንችል ጠቃሚ የሆነ ምክር ያስፈልገናል፡፡ ያለአግባብም ተስፋ እንዳንቆርጥ፣ በተረጋጋ መንፈስ መምራት እንድንችል፣ ዓላማችንን እንዳንሥት፣ እግዚአብሔር የሰጠንን የመምረጥና የመወሰን ነጻነቱን እንዳንለቅ፣ እንዲሁም በአስቸጋሪ ሰዎች እንዳንጎዳ አስፈላጊውን ድንበር ማበጀት እና ድንበሩን እንዴት ማስጠበቅ እንደምንችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ይህን ካደረግን ድንበር ምን እንደሆነ፣ እንዲሁም ድንበር የሌለው ሕይወት ምን ያህል ለጥቃት የተጋለጠ መሆኑን በቀላሉ መረዳት እንችላለን፡፡ ሰው ከሰው ሁሉ ጋር ሁልጊዜ በሰላም አብሮ መኖር የሚችል ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከልምዳችን እንደተረዳነው ከሰው ሁሉ ጋር ሁልጊዜ በሰላም መኖር አይቻልም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የሚቻላችሁ ቢሆን ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የሚያስፈልገውን ሁሉ አድርጉ” ሮሜ. 12÷18 ብሎ ባልጻፈም ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለብቻችን እንድንኖር ስላልፈጠረን፣ ከሰው ሁሉ ጋር ያለን ግንኙነት አስቸጋሪ ሲሆነብን፣ ከሰው ሁሉ ሸሽተን ለብቻችን ለመኖር ከማሰብ ይልቅ ተቻችለን መኖር የምንችልበትን መንገድ መፈለግ አለብን፡፡ ከምንጊዜውም የበለጠ በአሁኑ ጊዜ ሰዎች እርስ በእርስ ወዳጆች የነበሩ ጠላቶች ለምን ይሆናሉ? በሥልጣን፣ በገንዘብ ወዘተ ምክንያት ሰው የሰው ጠላት ለምን ይሆናል? ብለን መጠየቃችን አይቀርም፡፡ ችግሩን ብቻ ማውራት የማይጠቅም መሆኑን ነው የተረዳነው ነገር ግን መፍትሔው ምን ይሆን? ከሁሉም በላይ ሰላም፣ ፍቅር፣ ስምምነትና እንደዚሁም እውነተኛ የማኅበረሰብ እኩልነት መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ገላ. 5÷22 ሆኖም ሰላም፣ ሁለት ተቃራኒ ወገኖች የሚያገኙት ታላቅ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ ሰላም በየትኛውም አቅጣጫ የሕይወት ሁለንተናዊ ፍጹምነትን የሚያመለክት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን እና የሀገርን ዕድገት ብልጽግና፣ ትምህርትና ጤናን፣ እንዲሁም ሕይወት በጠባይዓዊ ሞት ኅልፈት እስኪፈጸም ድረስ ያለውን ረዥም ሕይወት ይገልጣል፡፡ ግላዊና ማኅበራዊ ደኅንነትን ፀጥታና መረጋጋትንም ያሳያል፡፡ ዮሐ. 20÷19፡፡ ሰላም በምድር ለሰው ልጅ ከሚያስፈልጉ እጅግ የከበሩና የተወደዱ ከሁሉም ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ነገሮች ሁሉ በላይ ነው፡፡ ሮሜ 13÷10 ቅዱስ ጳውሎስ “ያለ ሰላም እግዚአብሔርን ማየት የሚችል የለም” እንዳለ ዕብ. 12÷14 ሰው ያለ ሰላም ማየት የማይችለው እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን ባልንጀራውንም ጭምር ማየት አይችልም፡፡ ሰላም የሌላቸው ወገኖች ሊተያዩ እና ሊነጋገሩ አይችሉም፡፡ መልካም ሥራ የሚገለጸው ለእግዚአብሔር ሕግ መታዘዝ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም እና የእግዚአብሔርን ሥራ በመሥራት ነው፡፡ ማቴ. 5÷16፣ ዮሐ. 4÷34፡፡ ሰው ያለእምነት እግዚአብሔርን ሊያስደስት አይችልም ዕብ.11÷6፡፡ ይልቁንም ሰው በክርስቶስ ሲያምን የተለወጠ ልብ ስለሚኖረው መልካም ሥራ ይሠራል፡፡ በዚህም በጐ ሥራው ይመሰገናል ዋጋውንም በመንግሥተ ሰማያት ይቀበላል፡፡ ማቴ. 25÷21፣ 2ኛ ቆሮ. 5÷10፡፡ “ዓለም በሦስት ነገሮች ማለትም በፍትሕ፣ በእውነትና በሰላም ትጸናለች” እንዲሉ ቤት ያለ ምሰሶ ሰላምም ያለ ፍትሕ አይጸናም፡፡ በኅብረተሰብ ውስጥ ፍትሕ ካለ አንዱ የሌላውን ሀብት አይመለከትም፡፡ የራሱን ትቶ በሌላው እጅ ያለውን በቅንዐት አያይም ደግሞም ፍትሕ እና ሰላም በሰፈነበት ኅብረተሰብ ውስጥ አስቸጋሪ ሰዎች ብዙም አይኖሩም፡፡ ቢኖሩም እንኳ በሚፈጥሯቸው እኩይ ተግባራት በእጅጉ ስለሚታወቁ የሌላውን ሰላምና መልካም ሥራ ሲያናጉ ይለያሉ ሁሉም ከተገነዘባቸው ደግሞ ብዙም ሕይወት አይኖራቸውም፤ ክፉ ሥራቸውንም ሥር ሳይሰድ መቁረጥ መለየት ይቻላል፡፡
Show all...
በርታ ሰውም ሁን!! ነቢየ እግዚአብሔር ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የሚሞትበት ቀን በቀረበ ጊዜ ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ ሲል አዘዘው፡- በርታ ሰውም ሁን የምታደርገውንና የምትሄድበትን ሁሉ ታከናውን ዘንድ በሙሴ ሕግ እንደተጻፈ ሥርዓቱንና ትእዛዛቱን ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ በመንገዴም ትሄድ ዘንድ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ ልጆችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ በፊቴም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በእውነት ቢሄዱ ከእስራኤል ዙፋን አይቋረጥም ብሎ የተናገረውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው፡፡ 1ኛ ነገሥት 2÷1-4 በነቢዩ ቃል መሠረትነት ላይ ተመርኩዘን ዓለም በተለያዩ ባሕርየት ባላቸው ሰዎች የተሞላች ናትና በመልካም ሥነ ምግባር አስተምሮ ዙሪያ ያለንን ግንዛቤ እንገልጻለን፡፡ በዓለም ላይ አንድ አይነት ባሕሪ ያሏቸው ሰዎች አሉ ለማለት በእጅጉ ያስቸግራል፡፡ ሰዎች በአንድ መሥሪያ ቤት አብረው የሚሠሩ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አብረውን የሚያገለግሉና የሚገለገሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ተለይተው የሚታወቁበት የራሳቸው የሆነ የተለየ ክፉ ጠባይ አላቸው፡፡ ይኸውም ከቁጥጥር ያለፈ ቁጣ፣ ጎጂ የሆነ ምላስ፣ በቀላሉ የመከፋት እና የማዘን ጠባይ የሚታይባቸው፣ አሁን ስቀው እና ተጫውተው እንደሆነ ከልቡናቸው በሚፈልቀው ክፋት ምክንያት ወዲያው የሚያኮርፉ፣ ዛሬ ያመሰገኑትንና ያደነቁትን ሰው በቅጽበት የሚነቅፉና የሚተቹ፣ አሁን በጣም የወደዱትን ትንሽ ቆይተው በእጅጉ የሚጠሉ፣ ስለ ራሳቸው እንጂ ስለ ሌላው ሰው ፍላጎት እና ፈቃድ ፍጹም ግድ የሌላቸው፣ ተጠራጣሪዎች፣ ስጉዎች፣ በየጥቃቅኑ ምክንያት የሚነጫነጩ፣ ስግብግቦች፣ በዚህች ምድር እኛ ብቻ እንኑር የሚሉ ሆዳሞች፣ የሌላው ሰው ጉዳይ የማይሰማቸው እና የማይቆረቁራቸው፣ የተማሩ የሚመስሉ ነገር ግን አንዳች የማያውቁ፣ በተተኪ ትውልድ ላይ ሬት የሚዘሩ ወዘተ ናቸው፡፡ አስቸጋሪ ከሆነባችሁ ሰው ጋር ያላችሁን ግንኙነት ሰላማዊ ለማድረግ፣ በየጊዜው በመካከላችሁ የሚፈጠሩትን ግጭቶች በተለያየ መንገድ ለመፍታት የተቻላችሁን ሁሉ ሞክራችሁ አቅቷችሁ ይሆን? የራሳችሁን ፍላጎት ትታችሁ አስቸጋሪው ወይም ነገረኛው ሰው የጠየቀውን ሁሉ “እሺ!” በማለት ሰላም ለመፍጠር ሳትሞክሩ እንዳልቀራችሁ እንገምታለን፤ “እሺ! አንተ እንዳልክ” በማለት የራሳችሁን ፈቃድ መሥዋዕት ብታደርጉም በመካከላችሁ ያለውን ግጭት ማቃለል እንዳልቻላችሁ ስትረዱ፤ “ሰላም ማምጣት የሚቻለው በደካማነት ሳይሆን በብርቱነት ነው” ብላችሁ በማመን ኮስተር ብላችሁ ጽኑ የሆነ አቋም ለመያዝ ሞክራችሁም፣ የምትፈልጉትን ዓይነት ውጤት ስላላስገኘላችሁ፣ አሁንም አልቻልኩም! አቃተኝ! ብላችሁ ተስፋ ቆርጣችሁ ይሆን? ሁኔታው የበለጠ እየከፋ ሲመጣባችሁ፣ ያ አስቸጋሪ የሆነባችሁ ሰው፣ የእናንተን ሕይወት መራራ በማድረግ እናንተን ለመቅጣት ታስቦ የተፈጠረ፣ እናንተ ደግሞ የእርሱን ሕይወት ለማመቻቸት ብቻ እግዚአብሔር “የመሥዋዕት በግ” አድርጎ የፈጠራችሁ መስሎ ተሰምቷችሁ ያውቅ ይሆን? በቀመሳችሁትስ መራራ ሕይወት ምክንያት ከላይ የጠቀስነውን ዓይነት ስሜት ቢሰማችሁ፣ ከአስቸጋሪው ሰው በስተቀር የሚፈርድባችሁ ሌላ አካል ይኖራል ብላችሁ አትገምቱ ይሆናል፡፡ “አእምሮው ከጡንቻ የተሳለ” እንደተባለ፡፡ አስቸጋሪ ሰዎች እንዴት ዓይነት ናቸው? ተለይተው የሚታወቁበትስ ምልክታቸው ምንድነው? አስቸጋሪ ሰዎች ተለዋዋጭ ባሕሪ ስላላቸው ምን እንደሚወዱ እና ምን እንደሚጠሉ፣ ምን እንደሚያስደስታቸውና እንደማያስደስታቸው ለይቶ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ አስቸጋሪ ሰዎች እውነተኛ ማንነታቸው እንዳይታወቅባቸው በቀልጣፋ ንግግራቸው ራሳቸውን የመደበቅ ልዩ ችሎታ ያላቸው በመሆናቸው ቀረብ ብለው ካላዩአቸው በስተቀር ሰላማዊ ሰው በመምሰል ብዙዎች “አስቸጋሪ” የምንላቸው ሰዎች በባሕሪያቸው እንዲሁም የአስቸጋሪነታቸው መጠን የተለያየ ይሁን እንጂ ሁሉም የሚመሳሰሉበት አንድ ነገር አለ፡፡ ይህም ከእነርሱ ጋር ተቀራርቦ መኖር፣ አብሮ መሥራትም ሆነ ቤተ ክርስቲያን አብሮ ማገልገል በጣም ከባድ መሆኑ ነው፡፡ አስቸጋሪ ሰዎች ምን ዓይነት አስተሳሰብ እና ጠባይ እንዳላቸው መሠረት ላይ ተመርኩዘን ተጨማሪዎችን ለማሳየት የሚከተሉትን ዘጠኝ ጠባዮች ከዚህ በታች እንመለከታለን፡፡ በማር. 7÷22 ተጠራጣሪነት ሀ. አስቸጋሪ አስቸጋሪ ሰዎችን አስቸጋሪ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች አንዱ በብዙ ነገር ተጠራጣሪ መሆናቸው ነው፡፡ በሃይማኖት፣ በሥልጣን፣ በሥራ፣ በማንኛውም መልካም ግንኙነት ይጠራጠራሉ፡፡ ያዕ. 3÷17 ለ. ቁጡነት ቁጡነት ብዙዎቻችን ቁጣ በአግባቡ ወይም በሥርዓቱ ሲገለጽ ነው የምናውቀው ነገር ግን እያየንና እየሰማን ያለው ቁጣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሲፈታ አላየንም፡፡ ታዲያ “በምንም ምክንያት እንዳትቆጡ” የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል መተላለፍ አይሆንምን? 2ኛ ጢሞ. 4÷2-3 ሐ. ነቃፊነት መንቀፍ ልማዳቸው የሆኑ ሰዎች ራሳቸውን ከሰው ሁሉ የበላይ አድርገው ሌላውን የበታች በማድረግ በየአደባባዩ በነቃፊ ቃል ንግግራቸውን ይከፍታሉ፡፡ እብሬት በተሞላበት ንግግራቸው አያውቁም እንዳይባሉ በማንኛውም ነገር ራሳቸውን ከፍ ከፍ በማድረግ የሚያሳዩትና የሚያቀርቡት ሁሉን እንደሚያውቁ አድርገው ነው፡፡ መጽ. ምሳሌ 20÷19 መ. ስለ ሌላ ሰው ስሜት ግድ የለሽነት አስቸጋሪ ሰዎች የሌላውን ሰው ስሜት ምን ያህል እንደሚጎዱ እያወቁ በግድ የለሽነት የመጣላቸውን ቃል ከአፋቸው አውጥተው ይወረውራሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የቤት ራስ ያለው እኮ ግድ የለሹን ሳይሆን ለዚች ቤት የሚያስበውን ነው፡፡ ዘሌ. 19÷17፣ ማቴ. 18÷19፣ ፊልጵስ. 3÷4 ሠ. አኩራፊነት ፊት ለፊት እንዲህ ዓይነት ቃላት ተናግረኸ ለምን ትጐዳኛለኸ በማለት ፈንታ ማኩረፍ የሚቀናቸው ሰዎች አሉ፡፡ ባኮረፈኝ ቁጥር ሁል ጊዜ እርሱን መለማመጡ አሁንስ ሰለቸኝ የምንል ስንቶች እንሆን? በዚሁ ምክንያት እናንተ በጸሎታችሁ ደግፉን የምንል ብዙዎች ነን፡፡ 2ኛ ቆሮ.1÷11 ረ. ለእኔ ብቻ ይደረግልኝ ባይነት ፊት ለፊት እንዲህ ዓይነት ቃላት ተናግረኸ ለምን ትጐዳኛለኸ በማለት ፈንታ ማኩረፍ የሚቀናቸው ሰዎች አሉ፡፡ ባኮረፈኝ ቁጥር ሁል ጊዜ እርሱን መለማመጡ አሁንስ ሰለቸኝ የምንል ስንቶች እንሆን? በዚሁ ምክንያት እናንተ በጸሎታችሁ ደግፉን የምንል ብዙዎች ነን፡፡ 2ኛ ቆሮ.1÷11 ስለ ሌላው ሰው ግድ የሌላቸው ለራሳቸው ብቻ የሚያስቡ የዚህ ዓይነቱ ፀባያቸው ምክንያቱ ምን ይሆን? “ ምክንያቱማ ፈረሱ የታሰረበት ቦታ መጋጥ ብቻ ነው፡፡” እንደተባለ፡፡ ማቴ. 23÷25 ሰ. ተለዋዋጭነት ተለዋዋጭ የሆነ ጠባይ ያላቸው አሁን ጥሩ ሰው መስለው እንደሆነ ጥቂት ቆይተው መጥፎ ይሆናሉ፡፡ ለአንድ ሳምንት ያህል ሰላማዊ ሰው መስለው እንደሆነ ድንገት ባልታወቀ ምክንያት ፍጹም ተለውጠው ሌላ ሰው ይሆናሉ፡፡ ሸ. አምባገነናዊነት ሁልጊዜ ሌላውን በቁጥጥራቸው ሥር ለማዋል ስለሚፈልጉ ከሰዎች ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት መፍጠር አይችሉም፡፡ ሁሉን በእጃቸው ጭብጥ በእግራቸው እርግጥ አድርገው መያዝ ስለሚፈልጉ የሌላውን ሐሳብ ምንም ያህል ጥሩና ትክክል ቢሆንም መቀበል አይፈልጉም፡፡ እያንዳንዳችሁ ሌሎችን የሚጠቅመውን እንጂ ራሳችሁን የሚጠቅመውን አትመልከቱ፡፡ ሮሜ 12÷3 ቀ. ተበቃይነት
Show all...
📖አቤቱ ቸሩ መድኃኔዓለም ሆይ ቀኑን ባርከህ እንዳዋልከን ምሽቱንም ያንተው ቸርነት ሳይርቅ በሰላም አሰድረን 📖 እንደ እኛ ክፋት ሳይሆን እንደ ቸርነትህ ተመልከተን 📖 እንደ እኛ ክፋትት ሳይሆን ቃል ኪዳን ስለገባህላቸው ስለ እናትህ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ ማረን 📖 ስለ ቅዱሳን ጻድቃንስማእታት ብለህ ማረን ይቅርም በለን 📖 ስለ ባለ ሟሉ ሥለ አብረሃም ስለ ይስሀቅ ዘሩን በ12 ነገድ ስለከፈልከው ስለ ያህቆብ ብለህ ማረን ይቅርም በለን በምህረት አይኖችህ ተመልከተን 📖በቸርነትህም ሃይማኖታችን በተዋህዶ እምነታችን እንድንጸና ጠብቀን 📖 የተራቡትን የተጠሙትን ጎብኝልን 📖 የአልጋ ቁራኛ የደዌ ዳኛ የሆኑትን በየ ሆስፒታሉ ያሊትንበየ ፀበል ቦታ የሚንከራተቱትን ጠዋሪ ቀባሪ ያጡትንም ወገኖቻችንን አንተ ጎብኝልን 📖 መንገድ ለጠፋባቸውም ብረሀናቸው ሁንላችው 📖 በፀሎት አስቡን አትርሱን ያሉን ወገኖቻችንም በምህረትህ አሥባቸው ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ሁሉ በእጅህ ነውና ቀኑን በሰላም እንዳዋልከን ምሽቱንም በሰላም አሳድረን አሜን አሜን...አሜን..አሜን..... ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አደሩጉው ! @KeAbawandebet @KeAbawandebet
Show all...
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላል አሜን ራሳችን የሺህ ሰው ያህል ያሳስበናል። እንኳን በሰባና በሰማኒያ ዕድሜ ሚሊዮን ዓመት ብንኖር ስለ ራሳችን አስበን የምንጠግብ አይመስልም። የተፈጠርነው ስለ ሌሎች እንድናስብ ነውና ስለ ራስ ማሰብ ያደክማል። ደግሞም ለራስ ዋስ መሆን አይቻልም። ስለዚህ ለራሳችን ራሳችን ዋስትና መስጠት አይቻለንም። በዚህ ዓለምና በሚመጣው ዓለም ዋሳችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዕብ.7፥22) በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደ ያዕቆብ ለራስ በማሰብ የደከመና ብዙ አቋራጭ መንገድን የተጠቀመ ሰው አናገኝም። ያዕቆብ ግን አቋራጩ ሩቅ ሆኖበት ፣ ቁሳዊ ትርፍ እርካታ ቢስ አድርጎት እንደ ነበር እናነባለን። ያዕቆብ ገና በእናቱ ማህፀን ሳለ ከወንድሙ ከኤሳው ጋር የሚገፋፋ ነበር ፣ በተወለደ ጊዜም ወንድሙ ስለ ቀደመው ተረከዙን ይዞ ወጣ። ይህ መገፋፋትና ተረከዝን መያዝ ገና በጠዋቱ የጀመረው ባሕርይ ነበር። ዓለማችን መገፋፋትና መጠላለፍ የበዛበት ዓለም ነው። ሕፃን ልጅ በእጁ ባለው ከመደሰት በሰው እጅ ባለው እንደሚያለቅስ እንዲሁም ሁሉን ለእኔ በሚል አመል ራሳቸውን የሚያውኩ ጥቂት አይደሉም። የሌላውን ነገር መመኘት ስንጀምር መገፋፋት ይከሰታል። ሁላችንም እኩል እንውደቅ ካላልን በቀር የሌላው የእኛ ሊሆን አይችልም። መስመር ጠብቀን ከመሮጥ የቀደመንን ጠልፈን መጣል ፣ በሐሜትና በነቀፋ ከአገር ማባረር አንዱ የመኖራችን እሴት ሥርዓት ሆኗል። ስለዚህ የምንጓዘው ጉዞ የመጠባበቅ ጉዞ ነው። ጅብ ፊትና ኋላ ሆኖ አይሄድም ይባላል። ምክንያቱም አንዱ ከፊት ሲሄድ ታፋው ያምረውና የኋላኛውን ሊገምጠው ይችላል። ስለዚህ ጅብ በመጠባበቅ ነው የሚሄደው። ዛሬም የሰው ጉዞ ሳይሆን የጅብ ጉዞ የምንጓዝ መሆናችን ያሳዝናል። በማንኛውም የሕይወት አንጻር ወረፋ ቆመናል። ለመልካሙም ለክፉም ወረፋ ላይ ነን። ሕይወት በዙር የምትሄድ ጽዋ ናትና። በወረፋ አለም ከፊት ያለው ሲጠራ ተረኛ እኛ ነን። ስለዚህ ከፊታችን ያለው መልካም ዕድል ሲያገኝ አንድ ችግረኛ ከመቀነሱም በላይ ቀጥሎ እኛ ነንና ደስ ሊለን ይገባል። እንዲሁም ዓለም ወረፋ ነውና ከፊታችን ያለው በሞት ሲጠራ ቀጥሎ እኛ በመሆናችን መዘጋጀት ይገባናል። ኢየሱስ ክርስቶስ ካላላቀቀን በቀር ከወላጆቻችን እየተማርን ያደግነውን ነገር በትምህርትና በብዙ ጥረት እንኳ መላቀቅ አይቻለንም። አልቻልንምም። ወላጆቻችን በእቅፍ ሳለን ምግብ ሲያበሉን ምግብ ጣፋጭ ነው ፣ ምግብ ጠቃሚ ነው እያሉ አላሰደጉንም። "እገሌ ሊበላብህ ነው" እያሉ ነው ያሳደጉን። ስለዚህ ከማንኪያ ጋር የጠቀጠቁብንን አመለካከት ዲግሪ እያስያዝነው እንቀጥላለን እንጂ መተው አልቻልንም። የሁልጊዜ ኑሮአችን እገሌ እንዳይበላ ከጥጋብ በላይ መብላት ሆኗል። ያዕቆብ አድልኦና መከፋፈል በሚታይበት አስተዳደግ ስላደገ ለወንድሙ ፍቅር አልነበረውም። ልጆችን በልዩነት ማሳደግ የማይበርድ ጠብ በትውልድ ውስጥ መዝራት መሆኑን ከያዕቆብና ከኤሳው ዘሮች ማየት ይቻላል። ያዕቆብ የእግዚአብሔር በረከት የሆነውን በኩርና በምስር ወጥ ለመግዛት የሞከረ ሰው ነው። ወንድሙን እስከ አሁን ያሰናክለዋል። አባቱ ይስሐቅ ኤሳውን ሊመርቅ ጣፋጭ ምግብ አሰናዳልኝ ሲል ርብቃ ሰምታ ያዕቆብ በረከቱን እንዲወስድ የማታለል ጎዳናን ጠረገች። ያዕቆብ በማታለል የወንድሙን በረከት ቢወስድም ልቡ ግን ሰላም አላገኘም። በመጨረሻም ወንድሙን ፈርቶ ተሰደጀ( ዘፍ.27.)። በዘመናችን ያለው ትልቁ የሕዝባችን ውድቀት ምንድንነው? ስንል ውሸት ነው። ውሸት ዘመናዊነትና የኑሮ ስልት ሆኗል። በውሸት በረከት ሊሰበሰብ ይችላል። ነገር ግን ሰላም የለውም። የሰላምን እንጀራ ከመንፈሳዊ ሰው በቀር ማንም የማያገኛት ውድ ናት። ርብቃ ለልጇ ባሳየችው የማታለል ጎዳና የምትወደው ልጇን አጣችው። እስከ ሞት ድረስ ሳይተያዩ ቀሩ። ለሰዎች የምናሳየው የማታለል ጎዳና ለዘላለም አያገናኘንም። የሰው መንገድ አያገናኝምና። ለሰዎቹ አስበንና ተጨንቀን ሊሆን ይችላል። ሀጢያት ግን ይለያያል። ያዕቆብ በተሰደደበት በሶርያ ምድር በአጎቱ በላባ ቤት ከሃያ ዓመት በላይ አገለገለ። አጎቱ ብዙ ጊዜ አታለለው።እርሱ አባቱን አታሏልና የዘራውን አጨደ። በኋላም የገዛ ልጆቹ አታለውት ዘመኑን በሀዘን ፈጀ። ያዕቆብ በመረጠው አቋራጭ መንገድና የራስ ብልሃት ብዙ የደከመ ሰው ነው። ከአጎቱ ቤት ሁለት ሚስቶች ፣አሽከሮች ፣ ልጆችና ብዙ ከብቶች ይዞ ተመለሰ። ብቻውን ሄዶ ሠራዊት ሆኖ ተመለሰ። ባዶ እጁን ሄዶ ሀብቱ ምድርን ሞልቶ ተመለሰ። ያዕቆብ ግን በሕይወቱ እርካታ አልነበረውም። አንድ ቀንም ሚስቶቹንና ከብቶችን ልጆቹንም የያቦቅን ወንዝ ካሻገረ በኋላ ብቻውን ይተክዝ ጀመረ። እግዚአብሔርም ተገልጦለት ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር እስኪነጋ ታገለ። እግዚአብሔርም "ሊነጋ አቅላልቶአልና ልቀቀኝ" ቢለው ያዕቆብ ግን "ካልባረክኸኝ አልለቅህም" አለው (ዘፍ.32፥26)። እግዚአብሔርም ያዕቆብን ባረከው። ያዕቆብም እግዚአብሔርን አይቷልና ሰውነቱ ድና ቀረች። ያዕቆብ ሁለት ታማኝ ሚስቶች ነበሩት። ዛሬ አንድ ታማኝ ጠፍቷል። ኋላ የነገድ አባቶች የሆኑ አሥራ አንድ ልጆች ነበሩት። ቁጥር የሌላቸው ከብቶችና ንብረቶች ነበሩት። ታዲያ "ካልባረክኸኝ አልለቅህም" አለ። እነዚህ ሁሉ በረከቶች አይደሉም ወይ? አዎ በረከቶች ቢሆኑም እርካታዎች ግን አይደሉም። ያዕቆብ አንድ ከብት ይኖረኛል ብሎ እንኳ የሚያስብ አልነበረም። ብዙ ሺህ ከብቶች ቢኖሩትም በሕይወቱ ግን እርካታ አልነበረውም። ስለዚህ "ካልባረከኝ አልለቅህም" አለ። ያዕቆብ ከንብረት ሌላ መባረክ እንዳለ ተረድቷል። እርሱም ከፍታና ዝቅታ በሌለው በራሱ በእግዚአብሔር መርካት ነው። አንድ የቀዶ ጥገና ሐኪም የሆነ ወዳጄ "እንደ በሬ መኖር ሰለቸኝ" አለኝ። ንግግሩን ሲቀጥልም "በሬ ጠዋት ተነሥቶ ለመሥራት ይወጣል። ላቡን ጠብ አድርጎ ሲያርስ ይውላል። ማታ ሲመጣ ሣር ይቀርብለታል፣ ይበላል ፣ ላም አለችው አጠገቧ ይተኛል። ጥጆች አሉት ይረከቡታል። ጠዋት ሲነጋ ደግሞ ወደ ሥራ ይሄዳል። እኔም ጠዋት ሥራ ብዬ እወጣለሁ፣ ቀኑን በሙሉ ላቤን ጠብ አድርጌ እሠራለሁ። ማታ ወደ ቤት ስገባ እንደ ላሟ እኔም ሚስት አለችኝ፣ እንደ ጥጆች ልጆች አሉኝ። ከበውኝ እተኛለሁ። ሲነጋ ደግሞ ወደ ሥራ እሄዳለሁ። እኔና በሬው ልዩነታችን ምንድን ነው? በእውነት እንደ በሬ መኖር ሰለቸኝ" አለኝ። ለዚህ ወንድም የሚያስፈልገው ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቆ መኖር ነበር። ትልቁ መባረክ በእግዚአብሔር ማረፍ ነው። ትልቁ መባረክ ኑሮን መቀበል ነው። ትልቁ መባረክ አሁን በሆንነው መደሰት ነው። የኤፌሶን መልእክት ወንበራችን ላይ እንድንቀመጥ ያሳስበናል(ኤፌ.2፥6-7)። የእኛ ወንበራችን ከክርስቶስ ቀኝ በሰማያዊ ስፍራ መቀመጥ ነው። ስፍራችን እዚያ ነው። በምድር ስፍራና አገር የለንም። ሁሉም ነገር ከሰማይ ሲያዩት ትንሽ ነው። በምድር ትልቅ የሆነው እንኳ ከሰማይ ሲያዩት በጣም ትንሽ ነው። ከምንወርሳት አገር ሆነን ስንመለከተው ሀብትና ዝና ፣ ክብርና ውበት ትንሽ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተልን ለቁሳዊ ትርፍ ሳይሆን ለሰማያዊ በረከት ነው። እግዚአብሔር ለሰማያዊ በረከት ያብቃን ምስጋና ይሁን እንደ አምላክ ለሚሆን ለአብ ወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሜን #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አደሩጉው ! @KeAbawandebet @KeAbawandebet
Show all...
"ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ሆይ የመጻጉዕን ኃጢአት ይቅር እንዳልኸው፥ በሥልጣንህም ከሀሊነት በብዙ አሕዛብ ፊት ተግቶ አልጋውን ተሸክሞ እንዲነሣ እንደ አደርግኸው፤ እንደዚህም ሁሉ ኃጢአቴን ይቅር ብለህ ለእኔ ለባሪያህ የሥጋና የነፍስን ሕይወት ስጠኝ ። አባቴ ሆይ በክቡር ስም ስለተጠራሁ ደኅንነቴ ወራት ሁሉ በጎ አገዛዝ እገዛልህ ዘንድ አምልኮትህን አጽናልኝ።" (ውዳሴ አምላክ) ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አደሩጉው ! @KeAbawandebet @KeAbawandebet @KeAbawandebet
Show all...