cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Image Of Christ Ministry

በዚህ Channel✣ በክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለተሰራልን ስራና በእርሱም ምክንያት ወደ ብርሃን ስለወጣው ህይወትና አለመጥፋት የሚያወሱ፦ ✔️ ትምህርቶች (በፅሁፍና በድምፅ) ✔️ ግጥሞች ✔️ ዝማሬዎች ✔️ ምስሎች ወዘተ.... የሚቀርቡ ይሆናል። ማንኛውንም ጥያቄና አስተያየት https://t.me/glorious7gospel ይላኩልን። 💯ŜÃV€Đ B¥ ĠŘÃĆ€💯 ✟ማራናታ፦ ኢየሱስ ሆይ ናልን!✟

Show more
Advertising posts
1 932Subscribers
No data24 hours
-47 days
-330 days
Posts Archive
❤#የሰው_ሁለንተና ————————————— ✍️1 ተሰሎንቄ 5:23፤ የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ። 📌መጽሐፍ ቅዱስ ስለሰው ሁለንተና ምን ያስተምረናል? ✍️ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል መፈጠሩን፤ የመንፈስ፣የነፍስ፣የስጋ ጥምረትና ድምር ውጤት መሆኑን፤ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ አምላክ በሉዓላዊነቱ በሚያስተዳድረው ፍጥረት ውስጥ ምድርን የመጠበቅና የማበጀት አደራና ኃላፊነት የተቀበለ ክቡር ፍጥረት ነው። ✍️ሰው በፍጥረቱ ፣በዕውቀቱና በችሎታው ውሱን የሆነ፤ መለኮትነት የሌለው፤ መጽሐፍም እንደሚል “ ከእግዚአብሔር ሕይወትንና እስትንፋስ እየተቀበለ” የሚኖር በእግዚአብሔር ላይ ተደጋፊ ፍጡር እንደሆነ፤እናምናለን እናስተምራለን። ዘፍ 1፡26-27 , ዘፍ 2፡7, 1ተሰ5፥23, ዘካ12፡1 , ኢሳ57፡15-16, ዕብ4:11-12.... 📌የሰው ሁለንተና ሲል ምን ማለት ነው? ------------------------------- ✍️ 1ተሰ 5፡23 በመጀመሪያ ራሱን ቃሉን፥ ሁለንተና የሚለውን እንፍታው። ሁለንተና כָּלִיל ካሊይል፤ קָבַץ ቃባጽ፤ מָלֵא ማሌእ፤ ὅλος ሆሎስ፤ ὁλοτελής ሆሎቴሌስ፤ παντόθεν ፓንቶቴን፤ ሙሉ በሙሉ፤ ዙሪያ ሙሉ፤ ሙላት፤ ነገርን፥ ዕቃን፥ አካልን፥ በጠቅላላ ማለት ነው፤ የቁጥርን ሙላት፥ የማንነትን ተሰብስቦ አንድ ላይ መሆንን ወይም ያልጎደለ ማንነትንም ያመለክታል፤ ዘኁ. 4፥6፤ ሚክ. 2፥12፤ ናሆ. 3፥1፤ ዮሐ. 7፥23፤ 9፥34፤ 13፥10፤ 1ተሰ. 5፥23፤ ዕብ. 9፥4። በሉቃ. 19፥43 ያለው በየበኩሉ የሚለው ቃል ከዚህ አንድ ነው፤ በዙሪያ ሁሉ፥ በሁሉም አቅጣጫ ማለት ነው። (whole, complete, every whit, entire, all, all in all, wholly) ይህ የሁለንተና ትርጉም ነው። ወደ ሰው ሁለንተና ስንመጣ ደግሞ የሰው ሁለንተና ጠቅላላ ማንነቱ ነው። ያም አካላዊ ማንነቱ ወይም ሥጋው እና መንፈሳዊው ወይም በዓይን የማይታይ ማንነቱ፥ ማለትም፥ ነፍሱና መንፈሱ፥ በአንድ ላይ ጠቅላላ ማንነቱ ነው። ✍️ በ1ተሰ. 5፥23 ያለው ቃል ጳውሎስም ግልጽ አድርጎታል። ሁለንተናችሁን ሲል ሥጋን፥ ነፍስን፥ መንፈስን ብሎ አስቀምጦአል። ለምሳሌ የመኪና ሁለንተና ስንል ሞተሩ ብቻ ወይም ጎማው ብቻ አይደለም እነዚህ የመኪናው ክፍል ቢሆኑም ጎማ ወይም ሞተር ብቻውን መኪና ሊሆን አይችልም የመኪና ሁለንተና ስንል ሞተሩም ጎማውም Bodyውም ሁሉም አጠቃላይ መኪና ይባላል። እንደዚሁ የሰው ሁለንተና ስንል ስጋው ወይም መንፈሱ ብቻ ሳይሆን መንፈሱ ነብሱና ስጋው አንድ ላይ ሰው እንላለን። ✍️ሰው መንፈስ ቢሆን ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ከማለት ምንም የሚያግደው ነገር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ ግን በጠቅላላ ሰውን ሰው ይለዋል እንጂ መንፈስ አይለውም። ሰው መንፈስ ቢሆን ኖሮ ሰውን መንፈስ እያለ ለመጥራት ማንም የማይከለክለው ባለስልጣን ቃል ነው። ✍️በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሰረት ሰው ሲጀመርም ሲጨረስም ሰው እንጂ መንፈስ አይደለም። ዘፍ. 1:26-29,ዘፍ 2፥7, ዘፍ 5:1- ራዕይ 21፥3 📌መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚያስተምረው አይደለም አሁን ነውና ከትንሣኤ በኋላም እንኳን ሰው መሆናችን ይቀጥላል እንጂ መንፈስ ወይም ታናናሽ አማልክቶች አንሆንም። ራዕይ 21፥3 📌#ሰው_መንፈስ_ነው_ብለው_የሚያምኑ_ሊመልሷቸው_የሚገባ_ጥያቄዎች፦ =================================== 1. ሰው ሲፈጠር መጀመርያ የተፈጠረው መንፈሱ ነው ካልን በዘፍ 1፡27 ላይ “እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረው በእግዚአብሔርም መልክ ፈጠረው #ወንድና_ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” ይላል። ስለዚህ መንፈስ ጾታ አለውን? 2. በዘፍ 1፡29 ላይ “እግዚአብሔርም አለ እነሆ መብል ይሆናችው ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ ለምድርም አራዊት ሁሉ ለሰማይም ወፎች ሁሉ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው እንዲሁም ሆነ” በማለት ይናገራል። እንግዲህ በዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ ላይ የተፈጠረው መንፈስ ነው ካልን፤ መንፈስ ሐመልማል ይበላል ማለት ነውን? 📌ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሰው ሁለንተና የሚያስተምረውን እውነት ልብ ሳይሉና የቅዱስ ቃሉን ሀሳብ ሳይመረምሩ ሰው መንፈስ ነው የሚል የስህተት አስተምህሮ የሚያስተምሩ ሰዎች አሉ። ይህ አስተምህሮ አላማና ግብ የሌለው ሰዋዊና አጋንንታዊ አስተምህሮ ስለሆነ ቅዱሳን ሁላችን የመጽሐፍ ቅዱሱን አስተምህሮ ብቻ አጥብቀን ልንይዝ ይገባናል። 📌ይሁዳ 1:17፤ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤ ✍2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians) 14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። @የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን
Show all...
👍 1 1
👍 5
Show all...
👍 1 1
👉Verse of the day #Image_Of_Christ_Ministry #የክርስቶስ_መልክ_አገልግሎት share💯share💯share    ✅ @grace7alone ✅    ✅ @grace7alone ✅       🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Show all...
👍 2
👉Verse of the day #Image_Of_Christ_Ministry #የክርስቶስ_መልክ_አገልግሎት share💯share💯share    ✅ @grace7alone ✅    ✅ @grace7alone ✅       🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Show all...
2
Verse of the day
Show all...
4
Verse of the day
Show all...
1
Verse of the day
Show all...
5
Verse of the day
Show all...
2👍 1
Verse of the day
Show all...
6👍 1
3
Verse of the day
Show all...
2
Verse of the day
Show all...
1
   Verse of The Day 🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻 #Image_Of_Christ_Ministry #የክርስቶስ_መልክ_አገልግሎት
Show all...
3
ህያው አምላክ ነህ የተሰኘውን አዲሱን የዘማሪት አዜብ ሐይሉ  አልበም በዚህ የቴሌግራም ቦት አሁን መግዛት ይችላሉ። ➜ https://t.me/HiyawAmlakNehAlbumBot
Show all...
2
ህያው አምላክ ነህ የተሰኘውን አዲሱን የዘማሪት አዜብ ሐይሉ  አልበም በዚህ የቴሌግራም ቦት አሁን መግዛት ይችላሉ። ➜ https://t.me/HiyawAmlakNehAlbumBot
Show all...
3👍 1
#Verse_of_the_day
Show all...
#Verse_of_the_day
Show all...
ከመከራ ሁሉ የሚታደግ አምላክ መዝሙር 107 1 ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና።   2 እግዚአብሔር የተቤዣቸው፣ ከጠላት እጅ የታደጋቸው ይህን ይበሉ፤ 3 ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ፣ ከየአገሩ የሰበሰባቸው እንዲህ ይናገሩ። 4 አንዳንዶቹ ጭው ባለ በረሓ ተቅበዘበዙ፤ ወደሚኖሩባት ከተማ የሚያደርስ መንገድ አጡ። 5 ተራቡ፤ ተጠሙ፤ ነፍሳቸውም በውስጣቸው ዛለች። 6 በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው። 7 ወደሚኖሩባትም ከተማ፣ በቀና መንገድ መራቸው። 8 እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣ ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤ 9 እርሱ የተጠማችውን ነፍስ አርክቶአልና፤ የተራበችውንም ነፍስ በበጎ ነገር አጥግቦአል።  10 አንዳንዶቹ በብረት ሰንሰለት ታስረው የተጨነቁ፣በጨለማ፣ በጥልማሞት ውስጥ የተቀመጡ ነበሩ፤ 11 በእግዚአብሔር ቃል ላይ በማመፅ፣ የልዑልን ምክር አቃለዋልና። 12 ስለዚህ በጒልበት ሥራ ልባቸውን አዛለ፤ ተዝለፈለፉ፤ የሚደግፋቸውም አልነበረም። 13 በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው። 14 ከጨለማና ከጥልማሞት አወጣቸው፤ እስራታቸውንም በጠሰላቸው። 15 እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣ ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤ 16 እርሱ የናሱን በሮች ሰብሮአልና፤ የብረቱንም መወርወሪያ ቈርጦአል። 17 አንዳንዶቹ ከዐመፃቸው የተነሣ ቂሎች ሆኑ፤ ከበደላቸው የተነሣ ችግር ውስጥ ገቡ። 18 ሰውነታቸው የምግብ ዐይነት ሁሉ ተጸየፈች፤ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ። 19 በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው። 20 ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፤ ከመቃብርም አፋፍ መለሳቸው።
Show all...
👍 4
15 Do your best to present yourself to God as one approved, a worker who does not need to be ashamed and who correctly handles the word of truth. 2 ጢሞቴዎስ 2:15 https://kedusbible.com
Show all...
4
🥰 3
የአምልኮ ጥያቄ በጳውሎስ ፈቃዱ ጥቂት የማይባሉ አማኞች "አምልኮ" የሚለውን ፅንሰ ሐሳብ የሚረዱት በዝማሬ ውስጥ ነው። ይህ ጠባብ ትርጓሜ ደግሞ በአማኞች ሕይወት ላይ የራሱን አሉታዊ አሻራ ማሳደሩ አልቀረም። ለመሆኑ አምልኮና ግብር ያላቸው ዝምድና ምንድን ነው? ተጨማሪ ያንብቡ https://hintset.org/articles/view-point/the-question-of-worship
Show all...
Repost from Hintset
የአምልኮ ጥያቄ በጳውሎስ ፈቃዱ ጥቂት የማይባሉ አማኞች "አምልኮ" የሚለውን ፅንሰ ሐሳብ የሚረዱት በዝማሬ ውስጥ ነው። ይህ ጠባብ ትርጓሜ ደግሞ በአማኞች ሕይወት ላይ የራሱን አሉታዊ አሻራ ማሳደሩ አልቀረም። ለመሆኑ አምልኮና ግብር ያላቸው ዝምድና ምንድን ነው? ተጨማሪ ያንብቡ https://hintset.org/articles/view-point/the-question-of-worship
Show all...
Repost from Hintset
በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ፣ በወርኀዊው መጽሐፍ ግምገማ መርሓ ግብር የፊታችን እሑድ ለውይይት የሚቀርበው መጽሐፍ በአዱኛ ሂርጳ የተጻፈው፣ "የ'ለምን' አሻራ" የተሰኘው መጽሐፍ ይሆናል። በዕለቱ ተገኝተው የውይይቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን። መጽሐፉን በድምፅ ለማዳመጥ፣ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፦ https://semu.page.link/yttt4Sw5CcYRtV746 ምርጫዎ eBook ከሆነ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ ፦ https://www.tuba.et ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ -- በፌስቡክ ገጻችን ይከተሉን:- http://facebook.com/hintset ቴሌግራም ላይ ይከተሉን:- https://t.me/hintset ዩትዩብ ላይ ሰብስክራይብ ያድርጉ:- http://youtube.com/hintsetube ድረ ገጻችንን ይጎብኙ:- http://www.hintset.org
Show all...
“የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ካሉ ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ።”          1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥14 “And the grace (unmerited favor and blessing) of our Lord  flowed out superabundantly and beyond measure for me, accompanied by faith and love that are  in Christ Jesus.”        1Tim 1፥14           🔻ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻
Show all...
4
"እግዚአብሔር በጅምላ አልወደደንም። የእግዚአብሔር ፍቅር የጀማ ፍቅር አይደለምና በየግላችን ተወድደናል። ሲ ኤስ ሌዊስ እንደሚለው፣ እግዚአብሔር ለየግለ ሰቡ የሚሰጠው ጽንፍ የለሽ ትኵረት አለው። እያንዳንዱ ግለ ሰብ በእግዚአብሔር የተወደደው ከሌሎች ጋር ተደምሮ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር በምድር ላይ የፈጠረው ያንን አንዱን ግለ ሰብ ብቻ የሆነ ያህል ነው። ክርስቶስ የሞተልንም በዚያው መጠን ነው፤ በየግላችን!"
Show all...
4👍 3
“ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው።” (ሮሜ 10፥6-7)ጌታን ከሰማይ ማን ወደ እኛ ያወርድልናል? ከጥልቁስ ማን ወደ እኛ ያቀርብልናል? አይባልም። ጌታ ቅርብ ነው! በመሆኑም ጽድቅ የሚገኘው በእምነት ነው፤ ክርስቶስን ከሰማይ የማውረድን ወይም ከሙታን መካከል የማውጣትን ጀግንነት አይጠይቅም።[5] እግዚአብሔር ክርስቶስን ወደ ምድር ልኮታል፤ ከሙታንም አስነሥቶታል። ስለዚህ እግዚአብሔር ከሰዎች የሚጠብቀው ልዕለ ሰዋዊ ተግባርን ሳይሆን፣ በወንጌሉ ማመንን ነው።
Show all...
1
https://hintset.org/articles/most-misunderstood-verse/ የሐዋርያው ጳውሎስ መልእክት ወደ ሮሜ ሰዎች 8፥28ን በሚመለከት፣ ኤን.ቲ.ራይት በታይም መጽሔት ላይ ለንባብ ያቀረበውን ዐሳብ፣ እምነተአብ አየለ እንደሚከተለው ወደ አማርኛ መልሶታል።
Show all...
❤️#እርስ_በርሳችሁ ❤️ ----------------------- ✍️መጽሐፍ ቅዱስ በቅዱሳን መካከል ሊኖሩ የሚገቡ መልካም ግንኙነቶችና ሊኖሩ የማይገቡ መልካም ያልሆኑ ነገሮች ምን መምሰል እንዳለባቸው ያስተምረናል ያዘናል። ✍️ መልካም የሆኑ ግንኙነቶች፦ --------------------- 📌እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ። ቆላ 3:13 📌እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርህሩሆች ሁኑ። ቆላ 4:32 📌እርስ በርሳችሁ ምህረትን አድርጉ። ቆላ 3:16 📌እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ። ሮሜ 12:10 📌እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ። ሮሜ 15:7 📌እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ። ዕብ 10:25 📌እርስ በርሳችሁ ትህትናን ልበሱ። 1ጴጥ 5:5 📌እርስ በርሳችሁ ሰላምታን ተሰጣጡ። 1ጴጥ 5:14 📌እርስ በርሳችን ለፍቅርና ለመልካም ስራ እንተያይ። ዕብ 10:24 📌እርስ በርሳችሁ በትህትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም በፍቅርም ታገሱ። ኤፌ 4:2 ✍️መልካም ያልሆኑ ግኑኝነቶች፦ ------------------------ 👉እርስ በርሳችሁ ውሸትን አትነጋገሩ። ኤፌ 4:25 👉እርስ በርሳችሁ አትፈራረዱ። ሮሜ 14:13 👉እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ያዕቆ 4:11 👉እርስ በርሳችሁ አትበላሉ፣አትነካከሱ። ገላ 5:15 👉እርስ በርሳችሁ አትቀናኑ። ገላ 5:26 📌 የእግዚአብሔርን ምክሮች ሰምትን ማድረግ የምንችልበት ጸጋ ለእያንዳንዳችን ይጨመርልን። ✍️2 ቆሮንቶስ 13፡14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን
Show all...
4👍 2
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!