cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Grace Tube

on June 15! “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤” — ኤፌሶን 2፥8 @gracecampaign

Show more
Advertising posts
365Subscribers
No data24 hours
-17 days
-130 days
Posts Archive
🌼🌼 366 ቀናቶችን, 12 ወራቶችን, 52 ሳምንታትን, 8764 ሰዓታትን, 527040 ደቂቃዎችን, 316224000 ሰከንዶችን, 18973440005 ማይክሮሰከንዶችን, እግዚአብሔር ጠብቆአችሁ በሰላም ለዚህች ዓመት አደረሳችሁ። ለዚህ ነው መዝሙረኛው ዳዊት በመዝሙሩ አንዲህ ያለው: “በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።” — መዝሙር 65፥11 🄷🄰🄿🄿🅈 🄽🄴🅆 🅈🄴🄰🅁
Show all...
ወንድሜ መኳንንት ሳሙኤልን በቅድሚያ ከዓመታት በፊት በሲሲሊያ ሃይስኩል የክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት አገልግሎቱ አውቀዋለሁ። ከልጅነቱ እድሜ ጀምሮ ወደ አገልግሎት ጎዳና ለመግባት የታደለ ነው። በይበልጥ ያስተዋወቀን ከአምስት ዓመት በፊት እግዚአብሔር እድል ሰጥቶን የሃዋሳ አጠቃላይ ክርስቲያን ተማሪዎችን ህብረት በጋራ እናስተባብር የነበረበት ግዜ ነው። በዚያን ግዜም ከዚያም በኋላ ስንጠያየቅ የመዝሙር ሥራውን እየሰራ እንደሆነ እንጨዋወት ነበር። እሄው እግዚአብሔር ረድቶት የመዝሙር አልበሙን ሊያስመርቅ ነሐሴ 13/2015 ከቀኑ 09:00 በሃዋሳ አቶቴ በሚገኘው የበሹ ሆቴል እንድናስመርቅ ጋብዞናል። መኳ እንኳን ጌታ ረዳህ! በርታ ወዳጄ! የሚያገለግልባት ታቦር ቃለ ሕይወት ቤ/ያንም እንኳን ደስ አለሽ!! ምንተስኖት መኩሪያ
Show all...
ከልቤ እንዳይወስዱህ … ሚሊየኖችን ለድጋፍ ሰልፍ የሚሹ ፣ ስለ አንድ ነፍስ መጥፋት የማይረበሹ ፣ እነርሱ ሲዘፍኑ ትክክል ተብለው ሌላው ሲዘምር የሚተቹ ፣ ከቤትህ ሊነቅሉኝ የሚታገሉኝ ፣ በአንተ ስም ምድርን ሊወርሱ የሚሹ ከልቤ እንዳይወስዱህ ጌታዬ እባክህ እርዳኝ ። ተናግሮ አናጋሪዎች ዝም የማለት መብትንም የሚገፍፉ ፣ አሳቃቂ ሁነው አንገት እያስደፉ ፣ ወገኔ የማይሉትን እያጠፉ መኖር የለመዱ ከልቤ እንዳይወስዱህ እባክህ ጌታዬ እርዳኝ ። ቤትህን የግላቸው ንብረት ያደረጉ ፣ በጉንጫቸው ስድብ የተሞሉ ፣ በኅብረ ቃል ታናሽነቴን ሲያብራሩ የሚውሉ ከልቤ እንዳይወስዱህ ጌታዬ ጠብቀኝ ። አንገታቸው የማይቀለስ ፣ ልባቸው የማይመለስ ፣ እኛ ከጠላን ማን ይወደዋል ? እኛ ካረከስን ማን ይቀበለዋል ? ብለው ሲያጥላሉ የሚውሉ ከልቤ እንዳይወስዱህ እባክህ ጌታዬ እርዳኝ ። ወንድማቸውን ሰቅለው ስለ ስቅለትህ በእንባ የሚያወሩ ፣ የሌላውን ክብር እየገፈፉ መራቆትህን የሚተርኩ ፣ ራሳቸውን ነዋሪ ሌላውን አኗኗሪ ያደረጉ ከልቤ እንዳይወስዱህ እፈራለሁ ጌታዬ ጠብቀኝ ። ጥላሸት የሚቀቡ ፣ የሰውን ስም ለማጉደፍ ለዘመናት ጭቃ ይዘው የቆሙ ፣ የራሳቸውን ከሀዲ ፈላስፋ የሚያደርጉ ፣ የሌላውን አማኝ መናፍቅ የሚሉ ፣ ብዙኃንና ሕግ አለሁ የሚላቸው ፣ ብቸኛን ማጥቃት ሥራ የሆነላቸው ከልቤ እንዳይወስዱህ እፈራለሁ ጌታዬ ጠብቀኝ ። ኢየሱስ ኢየሱስ እያሉ በአደባባይ ጥብቅና የሚቆሙልህ ፣ ሰይጣንን በዕድሜ አንሰው በተንኮል የሚበልጡ አዎ እነርሱ ከልቤ እንዳይወስዱህ ፣ መልካምነትህን እንዳይጋርዱብኝ እሰጋለሁ ። ጠላቶቼን እኔ እጠብቃለሁ ፣ አማኝ ነኝ ከሚሉ ጨካኞች አንተ እንድትጠብቀኝ እለምንሃለሁ ። ንጹሑ ምንጣፍ ላይ ከነጭቃቸው የቆሙ ፣ በጽዱ ልብስ አውሬነታቸውን የሸፈኑ ከልቤ እንዳይወስዱህ እለምናለሁ ። አንተ የሠራኸውን ሲያፈርሱ የሚውሉ ፣ በንስሐ የተመለሰን የሚከስሱ ፣ በይቅርታ የማያምኑ ፣ ለታሪካቸው ሲሉ ያንተን ሕማም መከራ ገደል የጣሉ ከልቤ እንዳይወስዱህ እሰጋለሁና ጌታዬ ጠብቀኝ ። ለምድርም ለሰማይም እኩል የሚታዘዙ ፣ መድኃኒትም መርዝም የጨበጡ ፣ ማሊያ እየለዋወጡ የሚጫወቱ ፣ ለበረታው የሚዘፍኑ ፣ ቃላቸውን በመለዋወጥ የትውልድን ልብ የሚያመረቅዙ ከልቤ እንዳይወስዱህ እሰጋለሁና ጌታዬ ጠብቀኝ ። ገድለው የሚያለቅሱ ፣ ዝናብ እየተቀበሉ ጠል ለመስጠት የማይፈቅዱ ፣ ሕይወቱን የሰጣቸውን እየናቁ ፈገግታቸውን ውለታ አድርገው የሚያስከፍሉ ፣ የሚሹትን እስኪያገኙ እንደ ድመት ለስላሳ የሆኑ ፣ ካገኙ በኋላ ጥፍራቸውን የሚሞርዱ እነርሱ ከልቤ እንዳይወስዱህ እፈራለሁ ጌታዬ ጠብቀኝ ። ወድቀው በወደቀ የሚስቁ ፣ ሰውዬው የሚያመሰግንበትን ጉድለት እየነቆሩ ለምሬት የሚያነሣሡ ፣ የእነርሱን ኃጢአት ጽድቅ የሌላውን እውነት ሐሰት የሚሉ ፣ ሌላው ሲናገረው እውነቱን እየነቀፉ እነርሱ ግን ሲሉት ትክክል ነው የሚሉ ፣ ሚዛን ጥለው ሚዛን የሆኑ ፣ ለአገር ለሃይማኖት እኛ ብቻ ነን የሚሉ እነርሱ ከልቤ እንዳይወስዱህ እሰጋለሁ ። ሳልናገር የሚናገሩኝ ፣ ሳልነካ ድንበሬን የሚጥሱብኝ ፣ ዝም ስል ዝም አትልም የሚሉኝ ፣ የመኖርና የመሞት መብቴን የነፈጉኝ ፣ የማዘን አዳምነቴን ረስተው ስሜት እንደሌለው ሰው በጭካኔ የሚወጉኝ አንተን ከልቤ እንዳይወስዱህ እፈራለሁ ። ለመዱ ሲባል አውሬ የሚሆኑ ፣ ሰው ሳይሆኑ ራሳቸውን መልአክ ነን ብለው የሚስሉ እነርሱ ከልቤ እንዳይወስዱህ እሰጋለሁ ። የሰውን ሥራ እያየሁ ያንተን ደግነት ስረሳ ፣ በምድር ሆኜ የገነትን ኑሮ ስሻ ፣ የማይታየውን መንግሥትህን ዘንግቼ በሚታየው ስታወክ ፣ ተስፋህን ረስቼ በእምነት ስወድቅ ፣ ያለውን የመጨረሻ አድርጌ የሚመጣውን ሕይወት እንደ ባዶ ተስፋ ስመለከት ፣ ያደረጉልኝን ሳይሆን ያደረጉብኝን ሳስብ ፣ ከክፉ ነገር ውስጥ ያወጣኽልኝን በጎ ነገር ስረሳ ያን ቀን ከልቤ እንዳላጣህ ፣ እንደ መግደላዊት ማርያም “ጌታዬን ወስደውታል” ብዬ የማትወሰድ መሆንህን እንዳልዘነጋ ፣ በትንሣኤ ቀን እንዳላለቅስ እባክህ ጌታዬ ድረስ ። “እነርሱ በክፋታቸው ምን ሆኑ ?” ብዬ በኃጢአት ቦምብ ኳስ እንዳልጫወት የተነሣኸው ኢየሱስ ክርስቶስ ልቤን መልስ ። በአሳቡ ተናውጦ ባንተ የረጋ እርሱ አሜን ይበል ! ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ተጻፈ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
አለሁ !!! ባሕረ ጥበባት በሆንከው ፣ ሁሉን እንደ መላህ በምታኖረው ባንተ አለሁ ። ደዌያትን በቃልህ ፣ አጋንንትን በሥልጣንህ በምትሸኘው ፤ ትላንትን ለመካስ ፣ ዛሬን ለማድረስ ፣ ነገን ለማውረስ አቅም ባለህ ባንተ አለሁ ። የሞትን አዋጅ በሕይወት ፣ የስቅላትን ደብዳቤ በሹመት በምትለውጠው ባንተ በመፍቀሬ ሰብእ/በሰው ወዳዱ ጌታ አለሁ ። የነበረው የነበረ እስከማይመስል ደብዛው ጠፍቷል ፣ ያለው የማያልፍ ይመስል ይሸልላል ። የሚታየው የማይታይ ሲሆን ፣ አፈር የላሰው እንጀራ ሲያገኝ ፣ ተስፋ ያጣው ቀን ሲወጣለት ባንተ ደስ ይለኛል ። እኔ ግን ባንተ አለሁ ! ይሻላሉ የሚባሉት ሲበላሹ ፣ አይረቡም የተባሉት ለተጠቃው ጠበቃ ሲሆኑ ፤ የጠሩኝ ሲመልሱኝ ፣ የመረጡኝ ሲከሱኝ ፣ አንተ ግን ንጋትህ ምሽት የሌለበት ብርሃን ነህና ባንተ አለሁ ። ራሴን በኃጢአት ጦር ወግቼ እንደማቆስለው እንደ እኔ አይደለህም ፣ ላይ ሳስቀምጣቸው ታች እንደሚወርዱት እንደ ሰዎች አይደለህም ። ዝናብ እንደሌላቸው ደመናዎች ከፍ እንዳሉት ሰዎች አይደለህም ። ኮከብ ክብር ተቀብለው የሲኦል ጨዋታ እንደሚጫወቱትም አይደለህም ። አንተ እንደ ራስህ ነህና እኔ ባንተ አለሁ ። ውስጡ በብቸኝነት ፣ ዙሪያው በሌጣነት ፣ ጀርባው በታሪክ የለሽነት ፣ ፊት ለፊቱ በጭጋግ ለተያዘበት አለኝታ አሳዳሪው በምትሆን ባንተ አለሁ ። ፍጹም ልጅህ ልታደርገኝ ፣ ፍጹም ሰው በሆንከው ፣ ሰማያዊ ልታሰኘኝ በምድራዊው እጅ በተጠመቅኸው ባንተ አለሁ ። መሰላሉ ቢሰበር ባንተ እወጣለሁ ፣ ደረጃው ቢረዝም ባንተ ራስ እሆናለሁ ። ቀኔ ላይ ምሽት ፣ ጀምበሬ ላይ ውድቅት ሌሊት ቢታወጅ እኔ ግን ባንተ አለሁ ። ምልክት ስሻ መኖሬ ከንቱ ነው ። ድንግል በድንግልና መፅነሷ ፣ ዘር ምክንያት ሳይሆናት አንተን መውለድዋ ትልቅ ምልክት ነው ። እንዴት ይሆናል ብዬ አልጨነቅም ፣ አንተ ደመና አዙረህ ማዝነብ ፣ በጠራራ ፀሐይ ጠል መስጠት ትችላለህ ። አንተን አይመጥንህም ፣ ይህን አልነግርህም ብዬ ዳር ዳሩን ስዞር ነበር ። ለምታውቀኝ ላንተ መሸፋፈን ፣ ልቤን ለምታነበው ላንተ ለመንፈስ ቅዱስ አለመናገር የፍጡርነቴ ድካም ነውና ሁሉን እነግርሃለሁ ። ቃል የገባውን በሚያጥፈው ዓለም ውስጥ ፣ የተመኘሁትን የምትፈጽም አንተ አለኸኝ ። እኔ ባንተ አለሁ ። ሞት የተፈረደበት የሚኖርብህ ሕይወት ፣ ኃይል የሌለው የሚሰለጥንብህ ድል አንተ ነህ ። እኔ ባንተ አለሁ ። አንተ ባትኖር አልኖርም ነበር ። ላንተም በማይቆጠር ምክንያት ክብር ምስጋና ይሁን አሜን ። ለቀዳማዊነትህ መነሻ የለህም ብሎ የሚያምን አሜን ይበል ! ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ተጻፈ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
ከፊቴ ገለል በል ! የጻድቃንን ጥበብ መታዘዝን ፣ ዓለሙን ከሠራው ጋር መስማማትን እንዳልመርጥ ፣ አላሳልፍ ያልከኝ እልኸኝነት ከፊቴ ገለል በል ። በሄደበት ሁሉ ጌታዬን እንዳልከተል ደስታዬን የምትዋጋ ፤ በቤተ ልሔም ልደቱ የድሀ ልጅነቴን ፣ በግብጽ ስደቱ በወገን መገፋቴን ፣ በናዝሬት ዕድገቱ የቀደመ ታሪኬን ፣ በዓርብ መከራው የተዛባ ፍርዴን እንዳልቀበል የምታደርገኝ አንተ እኔነት ከፊቴ ገለል በል ። የተጠሩትን በር ላይ ቆሜ እንድመልስ ፣ የተመረጡት ላይ ጭቃ እንድለጥፍ ፣ የተወደዱትን እንዳጠለሽ የምታደርገኝ አንተ ቅንዓት ከፊቴ ገለል በል ! የሞላውን ምስጋና እንዳጎድል ፣ የበዛውን ውዳሴ እንዳሳንስ ፣ የተደረገልኝን እንዳላይ ፣ የተሰቀለውን ጌታ እንዳላስተውል የምታደርገኝ አንተ ማጉረምረም ከፊቴ ገለል በል ። ለታመነልኝ አምላክ እንዳልታመን ፣ የወደዱኝን እንድጠላ ፣ ያከበሩኝን እንዳዋርድ ፣ የቀረቡኝን እንድርቅ ፣ ትላንተ የሰጡኝ ላይ እንድጨክን የምታደርገኝ አንተ ከዳተኝነት ከፊቴ ገለል በል ! በእግዚአብሔር መቻል እየተጠራጠርሁ ፣ በራሴ መቻል እንድታመን የምታደርገኝ ፣ የተዋረደውን ሰዋዊ ፍልስፍና ከመለኮት መገለጥ ጋር ቁመት የምታለካካኝ አለማመን ሆይ ከፊቴ ገለል በል ። ድንቅ ያደረገውን ኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን እንዳቃልል ፣ ደሙን እንዳላከብር ፣ ሞቱን እንዳልናገር ፣ ትንሣኤውን እንዳልመሰክር የምታደርገኝ አንተ ይሉኝታ ከፊቴ ገለል በል ። ስለ አቋም ትቼ ስለ አቋቋም ፣ ስለ ማወቅ ችላ ብዬ ብዬ ስለ መታወቅ ፣ ሥራን ጠልቼ ስፍራን እንድወድ የምታደርገኝ አንተ ከንቱነት ከፊቴ ገለል በል ። በቂም ቋጥረህ ዓይኔን ያጨለምህ ፣ በበቀል አሰማርተህ የአምላኬን ምሕረት ያስረሳህ ፣ የመላእክትን ወዳጅነት ሳይሆን የሰውን ሸርታታነት እንዳስብ የምታደርገኝ አንተ ዓለማዊነት ከፊቴ ገለል ! ጌታ ሆይ ! አንተ በሰማይ ታከብረኛለህና ፣ ሥራዬን ጨርሼ በምድር አከበርሁህ ለማለት አብቃኝ ። የሚሰማ ሁሉ አሜን ይበል ! ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ተጻፈ ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
አንተ ግን …. በደቂቃ ነገሮች በሚለዋወጡበት ዓለም አንተ ግን በስፍራህ ፣ አንተ ግን በህልውናህ ጽኑ ነህ ። ሰዎች ሥሩልኝ ሳይሆን ልሥራላችሁ ቢባሉ በቅን በማይመለከቱበት ዓለም ፣ አንተ ግን የበደሉህን በፍቅር ታያለህ ። መጠባበቅ በዝቶ ፣ ጣልና ልጣልልህ የሚል የዕቁብ ኑሮ ደርቶ ቢታይም ፣ አንተ ግን ሁሉን በጸጋ ትለቃለህ ። የጸናውን ለመንቀል ፣ ያመነውን ለማስካድ ትግል ባለበት ዘመን ፣ አንተ ግን ፈሪውን ታበረታለህ ። ጻድቁን በሚያረክሰው ዓለም ፣ አንተ ግን ደካማውን ብርቱ ነህ ትላለህ ። ጀርባን እያየ ፣ “ማን አለው?” ብሎ ዙሪያን እያጠና በሚያፈቅረው ዓለም ፣ አንተ ግን የብቸኛው ወዳጅ ነህ ። ጊዜ ከድቶት አንገት ሲደፋ ፣ በወደቀው ላይ ምሣር ሲበዛ አንተ ግን መፍረድ ስትችል ትምራለህ ። “አንቱ” ያለውን ሰው “አንተ” ለማለት በሚጣደፈው ዓለም ላይ ፣ አንተ ግን ከፍታህ ዝቅታ ፣ ክብርህ ማዋረድ የለበትም ። እጅግ የወደደ እጅግ በሚጠላበት ዓለም ፣ አንተ ግን እስከ መጨረሻው ትወዳለህ ። ያገለገለ ሰው “አህያ” በሚባልበት ዓለም ፣ አንተ ግን የተናቀውን ታከብራለህ ። ሥራን ትቶ ስፍራን በሚሻው ዓለም ላይ ፣ አንተ ግን ዝናን ታስንቃለህ ። ያልፈጠረው ላይ በሚጨክነው ዓለም ውስጥ ፣ አንተ ግን ፍጥረትህ ነውና ለሁሉ ትራራለህ ። የፈተናው ነፋስ የተሰበሰበውን ስንዴ በሚበትንበት ዓለም ፣ አንተ ግን “ትጉና ጸልዩ” ትላለህ ። በአንድ ጆሮ ሰምቶ በሌላው በሚያፈስሰው ዓለም መካከል ፣ አንተ ግን የነገሩህን ላትረሳ ትሰማለህ ። “እርሱ ነው ፣ እርሷ” የሚል ክስ በበዛበት ዓለም ፣ አንተ ግን ሁሉን ለንስሐ ትጠራለህ ። ቃላቸውን ለመፈጸም ዳተኛ ፣ ለመድረስ ዘገምተኛ የሆኑ በበዙበት ዓለም ፣ አንተ ግን ደመና ጠቅሰህ ፣ ባሕር ተራምደህ ትደርሳለህ ። ለማክበር ተሰባስቦ በሚያዋርድ ፣ ለድጋፍ ሰልፍ ወጥቶ በሚቃወም ዓለም ላይ ፣ አንተ ግን ላታሳንስ ከፍ ታደርጋለህ ። አንተ እንደ እኔ ፣ አንተ እንደ ሰዎች ፣ አንተ እንደ ጊዜው አይደለህም ። አንተ መግለጫ ፣ አንተ እኩያ ፣ አንተ አምሳያ ፣ አንተ ተቀራራቢ ፣ አንተ ተካካይ ፣ … የሌለህ ብቸኛ ነህ ። ያህዌ አንተ ግን ያው አንተ ነህ ። የሚወድህ ሁሉ አሜን ይበል ! ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ተጻፈ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
#መንፈስ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ! የእስትንፋሴ መሠረት ፣ የመኖሬ ምሥጢር ፣ የመንገዴ ቀያሽ ፣ የሃይማኖቴ አስረጂ ፣ የጥያቄዬ መልስ ፣ የራሴ ራስ ፣ የኑሮዬ ኑሮ ፣ የነፍሴ ነፍስ ፣ ያልተፈጠርህ ሕይወት ፣ የምስቅልቅሉ አስተካካይ ፣ የፀጥታው ወደብ ፣ የሰማይ መነጽር ፣ የመንፈሳዊ ዓለም ብርሃን ፣ መካኑን ባለፍሬ የምታደርግ ፣ የጸጋ ባለቤት ፣ የሀብታት ምንጭ ፣ የቤተ ክርስቲያን መሥራች ፣ የአገልጋዮች አንደበት ፣ የካህናት ሞገስ ፣ ሳልኖር የምታውቀኝ ፣ ኖሬ የምታበረታኝ ፣ ሞቴን በትንሣኤ የምትለውጥ ፣ በዘላለም ከተማ የምትቀበለኝ ፣ የምትሠራኝ ፣ የምትሠራብኝ ፣ የምታግዘኝ ወዳጄ ፣ ያለነቀፋ የምታስተምረኝ መምህር ፣ የምደገፍብህ ምርኩዝ ፣ የበረሃው ጥላ ፣ ሳላይህ ያየኸኝ ፣ የሕፃንነቴ አሳዳጊ ፣ በሚወዱኝ ውስጥ ሆነህ የወደድከኝ ፣ ዘመን ሲያባርር መጠጊያ ፣ ያከበረ ሲያዋርድ አንተ ንጹሕ ካባ ፣ ቀኑ ሲከፋ መጠጊያ ፣ የእናት ደጅ ሲዘጋ መጽናኛ ፣ መነሻ ሲጠፋ የአልፋው ፊደል ፣ መድረሻው ጭልም ሲል የዖሜጋው ማኅተም ፣ ጠባዬ ሲበላሽ አዳሽ ፣ ስቆሽሽ አጣቢዬ ፣ ሰይጣን ሲከሰኝ የስርየት ቃሌ ፣ ስሜ ሲጠፋ ስሜ ፣ ከጭቃ ስወድቅ ንጽሕናዬ ፣ ፍጥረት ሲያምፅብኝ ተዋጊዬ ፣ ከራሴ ስጣላ ሰላሜ አንተ ነህ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ! ላንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም ፣ ከልቤ እስከ አርያም ክብር ምስጋና ይሁን ! አሜን ! የሚሻህ ሁሉ አሜን ይበል ። @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
ምክር ለሰሚው /33 ወዳጄ ሆይ ! ጥበብ ስትጠራህ አትዘግይ ፤ ዕድል ከጊዜ ጋር በማይፈታ ቋጠሮ ታስሯል ። ያልያዝከውን ለመጨበጥ ፣ የጨበጥከውን መልቀቅ አስፈላጊ የሆንበት ጊዜ አለ ። የማያዩ የሚያዩትን ፣ አላዋቂዎች አዋቂዎችን ሲተቹ ያ ዘመን ግልብጥ ዘመን ነው ። ጥሩ ሥራን ለሕሊና ምግብነቱ እንጂ ለሰማይ ሽልማቱ ብቻ አትሥራው ። የመልካም ነገር ዋጋ ከፋይ እግዚአብሔር መኖሩንም እመን ። ሁለት ጊዜ ደውለህ ፣ ሦስት ጊዜ ፈልገህ ሊያገኝህ ያልፈለገውን ሰው ፍላጎቱን አክብርለት። ወዳጄ ሆይ ! ወንድምህ ሲጠቃ ቀጥሎ አንተም ተጠቂ ነህና በወንድምህ ክፉ ቀን ለራስህ ጩኽ ። ልጅህን በመንፈሳዊ ድፍረት ፣ በእውቀትና በእግዚአብሔር በመተማመን አንጸው ። መስበክ ማለት ወደ እሳት እየጨፈሩ የሚሄዱትን መመለስ ፣ ቀድሞ አይቶ ሰውን ማስጠንቀቅ ነው ፤ ስብከት እስትንፋስ ነው ። በመንፈሳዊ አንድነት ያለውን ክፍተት ቶሎ ካልዘጋኸው ፣ እንደ ሁለት የሸለቆ ግድግዳ እየተያዩ እንደማይገናኙ መሆን ነው ። ወደ ኋላ ያለውን ሰው ወደፊት አምጥተህ አለማምደው ። ጊዜና መድረክ የተሰወረ ጥበብን ይገልጻሉ ። ወዳጄ ሆይ ! የተቀበለችህ አገር ላይ የአደጋ ስጋት አትሁን ። በብዙ መገኘት ቢያቅትህ ለወዳጅህ በጥቂቱ እንኳ ድረስለት ። መስጠት ባትችል አብረኸው መቆም ትልቅ ዋጋ አለው ። ሞልቶ የተረፈውን ክብርህን በሆዳምነትህ አታጕድለው ። ያለፈውን ጊዜ ለትምህርት ብቻ አስታውሰው ። ባለፈው ሲጸጸቱ መኖር መመጻደቅ ፣ ባለፈው መልካም ነገር ብቻ መኩራት መኖርን ማቆም ነው ። ወዳጄ ሆይ ! አንተም አንድ ቀን በሌላው አገርና ቤት እንግዳ ትሆናለህና ለእንግዶች ቅድሚያ ስጥ ። ንግግርህ ካስናቀህ ዝምታን ገንዘብ አድርግ ። ብዙዎችን ከማሸነፍ ራስን ማሸነፍ ይበልጣል ። ላንተ ቦታ የሌላቸውን ሰዎች ስታሳድድ አክባሪዎችህን እንዳታጣ ተጠንቀቅ ። ዱር የሚያስፈራህ ሰዎች ስለሌሉበት ነው ። ሰው የሌለበት ከተማ ከሲዖል በላይ ያስጨንቃል ። ስለ ጎረቤቶችህና ስለ ከተማው ሰው እግዚአብሔርን አመስግን ። ይህ ሁሉ ወገን የማትከፍለው ጠባቂህ ነው ። ምክር ለሰሚው 33 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነዉ መዝሙር🎥 #StandardQuality Video 📟 አዲስ የመዝሙር ክሊፕ 📟 📇ርዕስ፦ #ይቅራ_ይቅር 👤ዘማሪት፦ ልዩነሽ ሙሴ 💾 ሙዚቃ፦ ይታገስ ብርሃኑ #Find_at 👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/watch?v=bVGpsVe_3Ik     🈁     @gracecampaign   🈁     🈁     @gracecampaign   🈁
Show all...
በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነዉ መዝሙር🎥 📟 አዲስ የመዝሙር ክሊፕ 📟 📇ርዕስ፦ #ይቅራ_ይቅር 👤ዘማሪት፦ ልዩነሽ ሙሴ 💾 ሙዚቃ፦ ይታገስ ብርሃኑ #Find_at 👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/watch?v=bVGpsVe_3Ik     🈁     @gracecampaign   🈁     🈁     @gracecampaign   🈁
Show all...
#ምክር_ለወዳጄ ምክር ለሰሚው /32 ወዳጄ ሆይ ! መቶውን ብር ሰጥቶ አሥሩን ብር ስጡኝ የሚል ፣ ሳምንቱን አድሎ ሰንበትን የሚጠይቅ ጌታ ፤ ተቀብሎ እንደገና አብዝቶ የሚሰጥ አምላክ ከእግዚአብሔር በቀር የለም ። የገንዘብ አሥራትህን ለእርሱ ፣ የዕድሜ አሥራትህን ለሕያውነትህ ምሥጢር አትከልክል ። ከአሥር አንድ ብታወጣ አሥራትህን መልሰህ የምትበላው ፣ የምትገለገልበት አንተው ነህ ። ሰንበትን ብታከብር ለሥጋህ ዕረፍት ፣ ለነፍስህ እፎይታ የምታገኘው አንተው ነህና ለራስህ ምቀኛ እንዳትሆን ተጠንቀቅ ። አሥራትም ላለፈው ተቀብያለሁ የምትልበት ምስጋና ፣ ለሚመጣው እንዳትራብ ዘር ነው ። አሥራትን አለመክፈል አልተቀበልኩም ብሎ እግዚአብሔርን መክሰስ ነው ። ሰንበትንም አለማክበር አልደረስኩም ብሎ ራስን መርገም ነው ። ያንተ ያንተ እንዲሆን ፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጥ ። አሊያ መንግሥታት አስጨንቀው ፣ ሌቦች ዘርፈው ፣ ጨካኝ ገዥዎች ወርሰው ባዶ ያደርጉሃል ። በሚያልፈው ገንዘብና ዕድሜ እግዚአብሔርን አክብርበት ። ወዳጄ ሆይ ! ለሰዎች መንገዱን ታሳያቸዋለህ እንጂ አንተ አትሄድላቸውም ። መድኃኒቱን ብትውጥላቸው ከበሽታቸው አይድኑም ። ስላላቸው ነገር አንተ ብትደሰት እነርሱ ፍሡሐን አይሆኑም ። ሰዎች ከእግዚአብሔርና ከራሳቸው ጋር እንዲገናኙ ምከራቸው ። ራሳቸውን ጠልፈው የሚጥሉ ሰዎችን በትዕግሥት እንጂ በጉልበት አታስተምራቸውም ። መጽሐፍን የሚጠሉ ሰዎች አብረው ምግብን ቢጠሉ መልካም ነበር ። ሰው ሥጋውን ብቻ ሲመግብ ሥጋዊ ፣ መንፈሱን ሲመግብ መንፈሳዊ ይሆናል ። በእንጀራ ብቻም አይኖርም ፣ በቃሉ ብቻም አይኖርምና በእንጀራና በቃሉ ኑር ። እንጀራ ብቻ ከሚሉ ሆድ አደሮች ፣ ቃሉ ብቻ ከሚሉ ሰነፎች ተጠበቅ ። ወዳጄ ሆይ ! ጸጋ ተሰጥቶአቸው ጸጋን የሚጠብቁ የዘነበው ዝናብ ካልዳመነ የሚሉ ናቸው ። ሥራ እያላቸው ሥራ የሚፈልጉ ሲናወጡ የሚኖሩ ናቸው ። ጊዜ ተሰጥቶአቸው ጊዜ የሚፈልጉ በራሳቸው የሚቀልዱ ናቸው ። ብዙ ወገን በዙሪያቸው እያለ ብቸኝነት የሚሰማቸው ራሳቸውን ብቻ የሚያዩ ናቸው ። ችሎታ እያላቸው በሰው ችሎታ የሚቀኑ የመለወጥ አሳብ የሌላቸው ናቸው ። የእኔ አገር እያሉ የሚያዳንቁ የሚያወሩለት እንጂ የሚሠሩለት አገር የላቸውም ። የእኔ አሳብ ብቻ የሚሉ አፍ እንጂ ጆሮን የከሰሩ ናቸው ። ጥረትን የማይፈልጉ ድኩማን ናቸው ። ማግኘትን ወደው መስጠትን የሚጠሉ ምንም የማያገኙ ናቸው ። አንተ ግን ያለህን ነገር ተመልከት ፣ የጎደልህን ታጣዋለህ ። ወዳጄ ሆይ ! መሰባሰብ ብዙዎች እንዲደመጡ ነውና በብዙሃን መካከል ብቻህን ተናጋሪ አትሁን ። እቅዶች ሳይኖሩህ የሰዎችን ዕቅድ አትተች ። ስታስጥል የምታስጨብጠውን ቀድመህ አስብ ። ማፍረስ ቀላል ነውና የመገንባት ሊቅ ሁን ። ማስተማር እንጂ መቅጣት ቀላል ነውና በመቅጣት አትመን ። አሻራህ በሰዎች ላይ እንዲኖር እያንዳንዱን ደቂቃ ለመልካም አጋጣሚ ተጠቀምበት ። ደግነትህ አጠገብ ስሌት ካለ ድካምህ ከንቱ ሁኖ ይቀራል ፤ የደከምህላቸውም ሰዎች ይጠሉሃል ። ድክመቶችህን የሚያውቁ ሰዎች በዚያ ሊያጠቁህ ይሻሉና ራስህን አበርታ ። በውበትህ የሚሳቡ ሰዎችን ፣ ውበት ያለው ቆዳ ላይ እንደሆነ ንገራቸው ። ቆዳ ሲላጥ ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት ነው ። ያላገባኸው ያገቡ ሰዎችን ስትመክር ሊሆን ይችላልና የሌሎችን ልምድ በራስህ ላይ እየተረጎምህ ከምትፈልገው ትዳር አትራቅ ። ወዳጄ ሆይ ! እምነትህን አንተ በምግባርህ ፣ ሰዎች በቀልድ እንዲንቁት አትፍቀድ ። እምነትህ ከሁሉም ነገርህ በላይ ነው ። ከሞት በኋላ የሚከተልህ ዜግነትህ ሳይሆን ሃይማኖትህ ነውና ሃይማኖትህን ነቍጥ እንደሌለበት ፀዓዳ ተመልከተው ። በማስተማር የሚደክሙትን አክብር ። መብራት ቢጠፋ እንደምትጨነቅ ፣ አስተማሪዎች ሲጠፉም ሕይወት ትጨልማለች ። ዘመኑ ያስጨነቀን ሁሉ ባልጎ ገላጋይ በመጥፋቱ ነውና መካሪ አታሳጣን ብለህ ጸልይ ። ምክር ለሰሚው 32 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ.ም. @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
ሁሉ ካንተ ነው “ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ፥ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ችለን ልናቀርብልህ እኔ ማን ነኝ ? ሕዝቤስ ማን ነው ?” 1ዜና. 29 ፡ 14 ። ጌታ ሆይ ! ሁሉ በአንተ ፣ ሁሉ ከአንተ ፣ ሁሉ ለአንተ ነው ። ያላንተ ፈቃድ የሆነ ፣ ያላንተ ፈጣሪነት የተገኘ ፣ ካንተ በቀርም ክብሩን ሊወስድ የሚከጅል ማንም የለም ። ሁሉ ባንተ ነው ፣ የመሠረቶች መሠረት ነህ ፤ በውጥኖች ሁሉ ያንተ ውጥን ከሌለበት የአሳብ ቤት ሁኖ ይቀራል ። ባንተ አሳብና ባንተ ድርጊት መካከል ልዩነት የለም ። ያሰብከውን ታደርጋለህ ፣ ያደረከውንም አስበሃል ። ሁሉ ከአንተ ነው ፣ ነገርን ውብ አድርገህ ፣ አስማምተህ ፣ ለሥርዓት አስገዝተህ የምትሠራው አንተ ብቻ ነህ ። ሁሉ ላንተ ነው ፣ ሁሉን አድርገህልን ተመስገን ብቻ በሉኝ ያልከው አንተ ነህ ። ምስጋናችን የውለታህ ክፍያ ሳይሆን መታሰቢያ ነው ። ዘመናዊው ልባችን ሁሉ በእኔ ፣ ሁሉ ከእኔ ፣ ሁሉ ለእኔ እያለ ሸፍቶብናል ። ሁሉ በእኔ ብለን በጭንቀት አምጠናል ፣ ሁሉ ከእኔ ብለን የካብን መስሎን ንደናል ፣ ሁሉ ለእኔ ብለንም ራሳችንን ማስመለክ ዳድቶናል ። ሁሉ በእኔ ብለን አሳብ የማንቀበል ሆነናል ። ሁሉ ከእኔ ብለን እኔ ያልሠራሁት አይጣፍጥም ብለናል ። ሁሉ ለእኔ ብለን በቁማችን ሐውልታችንን ሠርተን አስመርቀናል ። ሁሉ በእኔ ብለን ፈቃድህን ጥሰን ሄደናል ። ሁሉ ከእኔ ብለን የፈጠርከውን ሳይሆን የፈጠርነውን ከጅለናል ። ሁሉ ለእኔ ብለን ለራሳችን መልክዕና ውዳሴ ደርሰናል ። አቤቱ ልዑል ሆይ ሁሉ ባንተ ነው ። ነፍሴን ሳልረዳት ያወቅኸኝ አንተ ነህ ። አቤቱ አዶናይ ሁሉ ከአንተ ነው ። እጄ የሠራልኝ ፣ ሰዎች የቆረሱልኝ የመሰለኝ ነገር ያንተ ጸጋ ነው ። ኤልሻዳይ ሆይ ሁሉ ለአንተ ነው ፣ ለምስጋና መስነፌ ከንቱነቴ ነው ። እረኛ ብሆን ንጉሥ ፣ በዱር ብኖር በቤተ መንግሥት እኔ እንጂ አንተ አትለወጥም ። እጄ ዘገነልኝ ፣ ክንዴ መከተልኝ ብዬ ራሴን አላታልልም ። ከብሬ የምበቀል ፣ አግኝቼ ሰውን የማዋርድ ብላሽ ነኝና አቤቱ ይቅር በለኝ ። ሁሉ ካንተ ነው ። ቤቴን ብሠራ ፣ ቤትህን ብሠራ የሠራኸው አንተ ነህ ። ለመወለድ አቅም ያልነበረኝ ለመኖር አቅም የለኝም ። ባንተ አሳብ ተፈጥሬ በራሴ አሳብ የምሳከር ነኝ ። ሁሉ ካንተ ነውና ዳኛ በደለኝ ፣ ባለጠጋ ነፈገኝ ፣ ንጉሥ ፈረደብኝ ብዬ አላዝንም ። ሁሉ ከአንተ ነው ። ዘመድ አላለቀሰልኝም ፣ ጓደኛ አልሳቀልኝም ብዬ በሸለቆና በተራራው አላጉረመርምም ። አጥቶም አግኝቶም መከፋት ከእኔ ይራቅ ። አጥቼ ዝም አሉኝ ብዬ ሰዎችን መኰነን ፣ አግኝቼ አልሳቁም ብዬ በሰው መደነቅ ከእኔ ይራቅ ። ሁሉ ካንተ ነውና ሁሉም ምስጋና ላንተ ይሁን ። የኀዘኔ ደራሽ አንተ ነህ ፣ የእልልታዬ አጋርም አንተ ነህ ። ሲከፋኝም ስደሰትም ያንተው ዕዳ ነኝ ። በምድር ላይ ላንተ እንደ መስጠት የሚያስደስት ምንም ነገር የለም ። አባት ለልጁ ሰጥቶ ስጠኝ ይለዋል ። ሰጥተኸኝ ስጥ ያልከኝ አንተ አባቴ ነህ ። ቤትህን ለመሥራት ልበ አምላክ ዳዊት እንኳ ፈቃድ አላገኘም ።  ያንተን ቤት መሥራት ፣ ሰብኮ ማሳመን ፣ አምልኮ ማስመለክ ዕድል ነው ። እኔ ባልሠራውም ለሚሠራው ድካሙን እንዳቀልለት እርዳኝ ። እኔ ካልሠራሁት ድርግም ይበል ማለትን ከእኔ አርቅ ። በማልኖርበት ዘመንም ያንተ ሥራ ይሠራ ። እነዚያ ባዶ እጆቼ ፣ ድቃቂ ሳንቲም የነጠፉ መዳፎቼ ዛሬ በረከት ካገኙ ያንተን ላንተ እሰጣለሁ ። ሁሉ ካንተ ነውና ለመስጠት ልቡን ፣ ለመቸር አቅሙን ለሰጠኸኝ ምስጋና እንዳቀርብ እመኛለሁ ። ሳትቆጥር ሰጥተኸኝ ሳለ ቆጥሬ እንዳልሰጥህ እርዳኝ ። ሊሰጥህ ከጅሎ እጁ ላጠረበት በረከት አፍስስለት ። ሰጥተኸው ሳለ ሰይጣን እጁን ለቆለፈበት አርነት አውጅለት ። በምስጋና የተፈራህ ፣ ተወደህ የምትከበር ፣ ተፈቅረህ የምትመለክ አንተ እግዚአብሔር ነህና ምስጋና ለታላቅነትህ ይሁን !!!! ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
ሁሉ ካንተ ነው “ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ፥ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ችለን ልናቀርብልህ እኔ ማን ነኝ ? ሕዝቤስ ማን ነው ?” 1ዜና. 29 ፡ 14 ። ጌታ ሆይ ! ሁሉ በአንተ ፣ ሁሉ ከአንተ ፣ ሁሉ ለአንተ ነው ። ያላንተ ፈቃድ የሆነ ፣ ያላንተ ፈጣሪነት የተገኘ ፣ ካንተ በቀርም ክብሩን ሊወስድ የሚከጅል ማንም የለም ። ሁሉ ባንተ ነው ፣ የመሠረቶች መሠረት ነህ ፤ በውጥኖች ሁሉ ያንተ ውጥን ከሌለበት የአሳብ ቤት ሁኖ ይቀራል ። ባንተ አሳብና ባንተ ድርጊት መካከል ልዩነት የለም ። ያሰብከውን ታደርጋለህ ፣ ያደረከውንም አስበሃል ። ሁሉ ከአንተ ነው ፣ ነገርን ውብ አድርገህ ፣ አስማምተህ ፣ ለሥርዓት አስገዝተህ የምትሠራው አንተ ብቻ ነህ ። ሁሉ ላንተ ነው ፣ ሁሉን አድርገህልን ተመስገን ብቻ በሉኝ ያልከው አንተ ነህ ። ምስጋናችን የውለታህ ክፍያ ሳይሆን መታሰቢያ ነው ። ዘመናዊው ልባችን ሁሉ በእኔ ፣ ሁሉ ከእኔ ፣ ሁሉ ለእኔ እያለ ሸፍቶብናል ። ሁሉ በእኔ ብለን በጭንቀት አምጠናል ፣ ሁሉ ከእኔ ብለን የካብን መስሎን ንደናል ፣ ሁሉ ለእኔ ብለንም ራሳችንን ማስመለክ ዳድቶናል ። ሁሉ በእኔ ብለን አሳብ የማንቀበል ሆነናል ። ሁሉ ከእኔ ብለን እኔ ያልሠራሁት አይጣፍጥም ብለናል ። ሁሉ ለእኔ ብለን በቁማችን ሐውልታችንን ሠርተን አስመርቀናል ። ሁሉ በእኔ ብለን ፈቃድህን ጥሰን ሄደናል ። ሁሉ ከእኔ ብለን የፈጠርከውን ሳይሆን የፈጠርነውን ከጅለናል ። ሁሉ ለእኔ ብለን ለራሳችን መልክዕና ውዳሴ ደርሰናል ። አቤቱ ልዑል ሆይ ሁሉ ባንተ ነው ። ነፍሴን ሳልረዳት ያወቅኸኝ አንተ ነህ ። አቤቱ አዶናይ ሁሉ ከአንተ ነው ። እጄ የሠራልኝ ፣ ሰዎች የቆረሱልኝ የመሰለኝ ነገር ያንተ ጸጋ ነው ። ኤልሻዳይ ሆይ ሁሉ ለአንተ ነው ፣ ለምስጋና መስነፌ ከንቱነቴ ነው ። እረኛ ብሆን ንጉሥ ፣ በዱር ብኖር በቤተ መንግሥት እኔ እንጂ አንተ አትለወጥም ። እጄ ዘገነልኝ ፣ ክንዴ መከተልኝ ብዬ ራሴን አላታልልም ። ከብሬ የምበቀል ፣ አግኝቼ ሰውን የማዋርድ ብላሽ ነኝና አቤቱ ይቅር በለኝ ። ሁሉ ካንተ ነው ። ቤቴን ብሠራ ፣ ቤትህን ብሠራ የሠራኸው አንተ ነህ ። ለመወለድ አቅም ያልነበረኝ ለመኖር አቅም የለኝም ። ባንተ አሳብ ተፈጥሬ በራሴ አሳብ የምሳከር ነኝ ። ሁሉ ካንተ ነውና ዳኛ በደለኝ ፣ ባለጠጋ ነፈገኝ ፣ ንጉሥ ፈረደብኝ ብዬ አላዝንም ። ሁሉ ከአንተ ነው ። ዘመድ አላለቀሰልኝም ፣ ጓደኛ አልሳቀልኝም ብዬ በሸለቆና በተራራው አላጉረመርምም ። አጥቶም አግኝቶም መከፋት ከእኔ ይራቅ ። አጥቼ ዝም አሉኝ ብዬ ሰዎችን መኰነን ፣ አግኝቼ አልሳቁም ብዬ በሰው መደነቅ ከእኔ ይራቅ ። ሁሉ ካንተ ነውና ሁሉም ምስጋና ላንተ ይሁን ። የኀዘኔ ደራሽ አንተ ነህ ፣ የእልልታዬ አጋርም አንተ ነህ ። ሲከፋኝም ስደሰትም ያንተው ዕዳ ነኝ ። በምድር ላይ ላንተ እንደ መስጠት የሚያስደስት ምንም ነገር የለም ። አባት ለልጁ ሰጥቶ ስጠኝ ይለዋል ። ሰጥተኸኝ ስጥ ያልከኝ አንተ አባቴ ነህ ። ቤትህን ለመሥራት ልበ አምላክ ዳዊት እንኳ ፈቃድ አላገኘም ። ያንተን ቤት መሥራት ፣ ሰብኮ ማሳመን ፣ አምልኮ ማስመለክ ዕድል ነው ። እኔ ባልሠራውም ለሚሠራው ድካሙን እንዳቀልለት እርዳኝ ። እኔ ካልሠራሁት ድርግም ይበል ማለትን ከእኔ አርቅ ። በማልኖርበት ዘመንም ያንተ ሥራ ይሠራ ። እነዚያ ባዶ እጆቼ ፣ ድቃቂ ሳንቲም የነጠፉ መዳፎቼ ዛሬ በረከት ካገኙ ያንተን ላንተ እሰጣለሁ ። ሁሉ ካንተ ነውና ለመስጠት ልቡን ፣ ለመቸር አቅሙን ለሰጠኸኝ ምስጋና እንዳቀርብ እመኛለሁ ። ሳትቆጥር ሰጥተኸኝ ሳለ ቆጥሬ እንዳልሰጥህ እርዳኝ ። ሊሰጥህ ከጅሎ እጁ ላጠረበት በረከት አፍስስለት ። ሰጥተኸው ሳለ ሰይጣን እጁን ለቆለፈበት አርነት አውጅለት ። በምስጋና የተፈራህ ፣ ተወደህ የምትከበር ፣ ተፈቅረህ የምትመለክ አንተ እግዚአብሔር ነህና ምስጋና ለታላቅነትህ ይሁን !!!! ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
Happy Mother's Day!🎂 መልካም የእናቶች ቀን🎆 ዛሬ የዓለም የእናቶች ቀን ነዉ፣ በዚህ የእናቶች ቀን ከአብራካቸዉ የተከፈልንባቸዉ እናቶች ያሉትን ያህል፣ ከአብራካቸዉ ሳንከፈል ነገር ግን በእናት ልክ ያሳደጉ ብዙ እናቶች ስላሉ በዓሉ የእነርሱም ነዉና፡ #መልካም_በዓል እንበላቸዉ!! መፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ያሉ ጀግና እናቶችን ከላይ በምስል ተያይዟል! @gracetube @gracetube
Show all...
Repost from AASTU-ECSF
ተቀብሎናል እርሱ ፃድቅ ቅዱስ ንፁህ አብዝቶ ቢሆንም ኃጢያተኛውን ወደደ እንጂ በፍፁም አልተወኝም ፅድቁንም አለበሰኝ ቅድስናውን ጨምሮ በራሴ እንደማልሰራው እንደማልበቃ አውቆ ኩነኔ በኔ ላይ የለም ሰርቶ ጨርሷል ሁሉንም መስቀል ላይ በሰራው ስራ ጨለማ ሕይወቴን አበራ ብቁ ልሆንም አልጥርም በራሴ ስራ አልጸደኩም ም'ረቱ ግን አድኖኛል ‘ማይጠፋ ህይወት ሰቶኛል ጽድቄ ነህ ክብሬ ማእረጌ ጌጤ ጽድቄ ነህ ክብሬ ማእረጌ ዉበቴ መድኅኒቴ እልሀለው በማዳንህ እደሰታለው ፍቅርህን እየታመንኩ በምህረትህ ‘ኖራለሁ ዘላለም አወራለሁ እዳዬን ከፍሏል እላለሁ በመስቀልህ ስራ ከሳሼን ዛሬም አሸንፌዋለው መሳቀቅ መሸማቀቄን ከላዬ ገፎ ጥሎታል በነጻነት እንዳመልከዉ የጥሉን ግድግዳ አፍርሷል አባት እና ልጅ ሆነናል በፍቅሩ ሕይወቴ በርቷል ያለነዉር ያለነቀፋ በፊቱ እንድሆን መርጦኛል ተቀብሎናል ተቀብሎናል ከነማንነታችን ተቀብሎናል ተቀብሎናል ተቀብሎናል ምንም ሳንሰራ እንዲሁ ወዶናል
Show all...
Repost from AASTU-ECSF
ተለቀቀ ተለቀቀ 🔥🔥 https://youtu.be/eb6IVQSbr9I
Show all...
መልካም የትንሣኤ በዓል! #Profile_Picture ሙሴ በምድረ በዳ እባብን እንደሰቀለ፣ የሰው ልጅም እንዲሁ ሊሰቀል ይገባዋል፤ይኸውም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው ነው።                              @Godly316 @kineforJesus,
Show all...
Melhik Podcast Season 2 Episode 14 ሀይማኖተኛ ሰው ነበርኩ ከእላሻ ፈቃዱ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን። አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው። በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፖድካስት ለማንኛውም አስተያየት በዚህ ቁጥር ይፃፉልን። @MelhikPodcast1 በተሻለ ጥራት ለመስማት ከታች ባሉት የፖድካስት አማራጮች #Subscribe ያድርጉ። Follow us On TikTok Find us on Social Medias Google Podcast | Apple Podcast | Spotify ለጓደኛዎ ያጋሩ @MelhikPodcast
Show all...
🛑 አንተን ባየ አይኔ |Anten Baye ayne Singer Bereket lemma
Show all...
🎸#Home_Made_Worship🎸🎸 With beautiful voice & guitar! #Audio_Version . ነብሴ ሆይ አስቢ 🎸 ዘማሪት #ሰሎሚት_ተስፋዬ ▷ @gracecampaign ◁ ▷ @alifetube ◁ ▷Join Us◁
Show all...
🎸🎸#Home_Made_Video🎸🎸 . ነብሴ ሆይ አስቢ ዳዊት ጌታቸዉ - Original Song 🎸 ዘማሪት #ሰሎሚት_ተስፋዬ ▷ @gracecampaign ◁ ▷ @gracecampaign ◁ ▷Join Us◁
Show all...
https://www.youtube.com/watch?v=6b9jSwBowMA #አንተን_ባየ_አይኔ #ግሩም_መንፈሳዊ_መዝሙር @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
#ግጥም #በዮናታን @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
#Today's_Message Grace is the atmosphere of salvation for humanity to dwell in. God the maker and giver of life and by life I mean any and all matter and substance, seen and unseen, what can and can't be touched, thoughts, image, emotions, love, atoms and oceans, All of it his handy work. One of which is Masterpiece. A masterpiece made with his imagery. God breathed into man and he became a living soul, formed with the intent of being infinitely fond. Creator and creation held in eternal bond. And it was placed in perfect paradise til something went wrong. Human deceived God and started lusting for his job which led to eternal separation from God. The seed of sin spread through our souls' genome, soaking us in Dept of sin. Sin separated we humans from a perfect and holy God. And the only way to get back is to get back to perfection. So how can this debt be paid? We can't fix ourselves! quite trying it's impossible! For sin brings death. But one way to fix this eternal separation is that someone must die in our place or the payment ain't permanent. The only one that can meet God's criteria is God ,therefore, God sent himself as Jesus to pay the cost for us! His righteousness, his death paid the dept! Pierced feet, pierced hand, blood stained son of God's fullness, forgiveness, Free passage into the promise land. That same breath God breathed into us, God gave up to redeem us! And anyone and everyone, and by everyone I mean everyone who puts their faith and trust in him and him alone can stand in full confidence of God's forgiveness! We are guaranteed full access to return to perfect unity. We have received life! Yes life, and we have been saved by God's amazing Grace! #Piniel @gracecampaign @gracecampaign
Show all...
#2021 Released 📟 #ካሰነበትከኝ_አልበም 📟 📇ርዕስ፦ #እየራራህልኝ 👤ዘማሪት፦ ሶሬቲ ሞገስ 🈁 @gracecampaign 🈁 🈁 @gracecampaign 🈁
Show all...